ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
"የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፍያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻያ መጣያ አይደሉም!" በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት "የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፍያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻያ መጣያ አይደሉም!" በሚል መሪ ሀሳብ የክረምት የፅዳት የንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል። የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ፣ ክ/ከተማው አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የተለያዩ የህብረተሰብብ ክፍሎችና የፅዳት አምባሳደሮች ተሳትፈዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በንቅናቄው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፅዳት የክብር፣ የማንነትና የኩሩ ህዝብ መገለጫ ኤንደሆነ፣ ንፁህ ምቹ የመኖርያ አካባቢ መፈጠር የእያንዳንዱ ነዋሪ ጥረት ስለሚጠይቅ ሁሉም የራሱን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ጠቁመው፣ ከተማችን አዲስ አበባ ከለውጡ ማግስት በተሰሩ ስራዎች ገፅታዋ በመለወጡ ለውጡን በቅብብሎሽ ማስቀጠል እንደሚገባ፣ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መጠበቅ፣ የውሃ መውረጃ መስመሮችን ከቆሻሻ አፅድተን የውሃ መውረጃ ማድረግ ከጎርፍ ተጋላጭነት በመቀነስ የከተማችንን ንፅህና በመጠበቅ ሞዴል ብሎክና መንደር ፈጥሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው ከተማችን አዲስ አበባ በቆሻሻ አሰባሰብ፣ አወጋገድና ማስተዳደር መሻሻል እንዳለበትና ቆሻሻ ሀብት የሚሆነዉ በአግባቡ ማስተዳደር ከተቻለ መሆኑን፣ ጎን ለጎን የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው፣ ከተማችን አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ ፅዱና ለዓይን ማራኪ ሆና እንድትቀጥል ሰፊ ንቅናቄ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዉ፣ የዓለም የዲፕሎማት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በመሆኗን በፅዳት ማረጋገጥ ይገባል በማለት የክረምት የፅዳት ንቅናቄ በይፋ አስጀምረዋል።

photo content
+5

የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ከተቋቋመ በአጭር ጊዜያት ውስጥ መዲናችን ውብ፣ ማራኪ እና ብርሐናማ ከተማ እንድትሆን ያስቻለ አበረታች ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስታወቁት በመዲናዋ የመሠረተ ልማት እና የማዘጋጃ ቤታዊ ተቋማት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነትን በቅንጅት ለማጠናከር በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው። በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን ባለስልጣኑ ከተቋቋመበት ካለፉት 10 ወራት ወዲህ ያከናወናቸውን ዋና ዋና የስራ አፈፃፀሞች በሪፖርት አቅርበዋል። አቶ ሰብስብ በዚሁ ሪፖርታቸው ባለስልጣኑ በተለይም ከኮሪደር፣ከወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክቶች እና ነባር መንገዶች ጋር ተያይዞ ያከናወናቸውን የመብራት ዝርጋታ ስራዎች አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ እና በከፊል የተጠናቀቁትን በሪፖርታቸው አመላክተው ያልተጠናቀቁ ስራዎች ደግሞ በተያዘው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ተግዳሮት የሆኑ ችግሮችን አንስተዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መካከል ከኡራኤል ቤተክርስትያን- በከሳንቺስ ቶታል- ሴቶች አደባባይ- አዋሬ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝበት ሲሆን ከዮርዳኖስ ሆቴል-ሴቶች አደባባይ አዋሬ እንዲሁም ከሃይሌ አለም ህንፃ - ካሳንቺስ ትራፊክ - አንበሳ ጋራዥ - ጎሮ እንደሚገኙበትም አመልክተዋል። አቶ ሰብስብ በሪፖርታቸው በከተማዋ የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት በሁለት አካላት ይቀርብ እንደነበር ጠቅሰው ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በኩል ይቀርብ የነበረው የዋና ዋና መንገዶች መብራት ከተቋማቸው ጋር ርክክብ እንደተካሄደበት አስረድተዋል።ይሁን እንጅ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ርክክብ ባለመካሄዱ ተገቢውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት ረገድ ተግዳሮት ስለፈጠረ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎትአስተዳደር ባለስልጣን ከተቋቋመ በአጭር ጊዜያት ውስጥ እያከናወናቸው ላሉ አስደማሚ ስራዎች ያላቸውን አድናቆት ገልፀው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የመብራት ዝርጋታም በአዲሱ ተቋም በኩል ቢተላለፍ ለስራው ውጤታማነት የተሻለ እንደሆነና ይህም በአፋጣኝ ተግባራዊ እንደሚሆን አስረድተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+4

1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች የተደረገው የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ *** 1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በድምቀት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ያደረጉት የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀትና በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ከኢድ ሶላቱ ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡ የኢድ ሶላቱ በታቀደው መሰረት በሠላም እንዲከናወን ላደረጉ ታዳሚዎች፣ የኃይማኖቱ መሪዎች፣ ከፀጥታ አካሉ ጎን በመቆም የማስተባበር ስራ ሲሰሩ ለነበሩ ወጣቶችና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቦ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅርና የሠላም እንዲሆንላቸው በድጋሚ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አልአድሃ ዓረፋ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም ፡የመጠያየቅ ፡የመደጋገፍ እና የዓብሮነት በአል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+9

photo content

በሁሉም መስኮች በፍጥነት እያደገች ያለችውን መዲናችን አዲስ አበባን የሚመጥን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦትን ለማጠናከር የመሠረተ ልማት ተቋማት ቅንጅታቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ማጠናከር እንደሚገባቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው እለት ከመዲናዋ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የቅንጅታዊ አሰራርን በተቋማት መካከል ለማጠናከር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከከተማ አስተዳደሩ 6 የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ተቋማት ጋር በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በተዘጋጀው እና በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመሩት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በመዲናችን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ይስተዋላሉ በሚል ከከተማዋ የመሠረተ ልማት እና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ተቋማት የተነሱ አንዳንድ ችግሮችን በመለዬት በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛና በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት መዲናችን አዲስ አበባ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ ፓለቲካ እና የዲፕሎማሲ ማዕከል ብሎም የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ከተማዋን የሚመጥን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በጋራ እንደ አንድ ሆነው በመፍታት የህዝቡን የአገልግሎት ፍላጎት ማርካት እንደሚገባቸው አመልክተዋል። ከከተማችን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና አቅርቦት ጋር ተያይዞ በመኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት እንዲሁም በአደባባዮች አና የኮሪደር ልማቱ በተገነባባቸው የከተማዋ ክፍሎች በርካታ ስራዎች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ መከናወናቸው በእጅጉ አበረታች እንደሆነ የገለፁት ኢንጅነር ወንድሙ ይህ መልካም አፈፃፀም ከሃይል መቆራረጥ ጋር የሚነሱ ችግሮችን ተቀናጅቶ በመፍታት ረገድ ሊጠናከር እንደሚገባም በአፅንኦት ገልፀዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው መጪው ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይም ባረጁ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የሚነሳ የእሳት አደጋዎችን ከመከላከል፣ ከመንገድ ዳር እና የውስጥ ለውስጥ መብራት ዝርጋታ፣ ለውሃ አቅርቦት መቆራረጥ መንስኤ የሚሆን የሃይል አቅርቦት እና ሌሎች ችግሮችን በተቻለ መጠን በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች ከከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ከቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ ከእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከፅዳት አስተዳደር እና ከመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+6

ዛሬ ማምሻውን ከስሎቬኒያ ፕሬዚዳንት ከክብርት ዶ/ር ናታሻ ፒርስ ሙሳር ጋር በመሆን ፒኮክ የከተማችን ግዙፉ ፓርክ ውስጥ ዘመናዊ የንብ ማነቢያ ሰርቶ ማሳያ (Urban Beeking Observatory) ስራ በይፋ አስጀምረናል። ከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት ማሻሻል ላይ ያተኮረ ሰፊ ለውጥ እያስመዘገበች ይገኛል ፤የከተማ ግብርና የዚህ አጀንዳ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ይህም የምግብ ዋስትናን ማዕከል ያደረገ የአረንጓዴ ልማት ማስፋፋትን ይጨምራል። ፕሮጀክቶችን በተሳካ መልኩ በማከናወን የህዝባችንን ኑሮ ለመለወጥ ያስችለን ዘንድ ከአለም አቀፍ አጋሮች፣ ኤምባሲዎች እና ሀገሮች ጋር በንቃት አብረን እንሰራለን። ለአብነትም ዛሬ ከክብርት ፕሬዚዳንቷ ጋር በመሆን በይፋ ስራ ያስጀመርነው ፒኮክ የከተማ የንብ ማነቢያ ሰርቶ ማሳያ አንዱ ሲሆን ስሎቬንያ በከተማ ንብ እርባታ የላቀ ልምድ ያላት በመሆኗ ይበልጥ ትብብራችንን ለማጠናከር እንሰራለን። ልምዳቸዉን በማጋራትና ሀገር በቀል እሳቤያችን ለመደገፍ ወስነው ተጨባጭ ስራ በመጀመራቸው ፕሬዚዳንት ናታሻ እና በኢትዮጵያ የስሎቬኒያ አምባሳደር የሆኑትን ክርስቲና ራዴጅ ከልብ አመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content

አዲስ አበባ በቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከተማ ሆነች ++++++++++++++++++++ የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስልጠና ማዕከል ጋር በመተባበር "ውብ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን ለመፍጠር የሚዲያዎች ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ለሚዲያ ባለሙያዎች ያዘጋጁት የአቅም ግንባታ ስልጠና መርሐግብር ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ለማ (ዶ/ር) በሰልጠና መርሐግብሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት ለመቀየር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። ከአራት ዓመት በፊት በከተማዋ ከሚመረተው ደረቅ ቆሻሻ 2 ነጥብ 5 በመቶው ብቻ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ 12 ነጥብ 5 በመቶውን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል መቻሉን አስታውቀዋል። በከተማዋ ከሚመረተው ቆሻሻ 94 በመቶን በመሰብሰብ በተገቢው ቦታ የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም አዲስ አበባ በቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከተማ መሆን ችላለች ብለዋል። ህብረተሰቡን የጽዳት ባለቤት ለማድረግ በየሳምንቱ በሚካሄደው የጽዳት ንቅናቄ በአማካኝ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል። አጠቃላይ ቆሻሻን ከመሰብሰብ፣ ከማጓጓዝ፣ መልሶ ጥቅም ላይ ከማዋል እና ህብረተሰቡን በጽዳት ንቅናቄው ከማሳተፍ አንጻር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+9

photo content
+3

photo content

photo content

photo content
+6

photo content
+4