ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በእርግጥም የተሻለው ሁሉ ይገባችኋል ! ዛሬ ማለዳ በ11 ክፍለ ከተሞች ከ5 ቢለዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዉ የተገነቡ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ እና 1,155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላትን በጥቅሉ 1277 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል። በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት ከከተማችን ሀብት መሬት እና በጀት፤ ከእኛ ከአመራሮች እና ከሰራተኛው ደግሞ ጉልበት እና ጊዜ እፍታውን ወስደን እንዲሁም ማህበረሰቡን በማስተባበር ለትውልዱ ቅድሚያ ስጥተን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ገንብተናል ። ባለፋት 3 ዓመታት ለስራ ቦታዎች እና ለመኖሪያ አካባቢዎች ጭምር ትኩረት በመስጠት በድምሩ 3,789 የህፃናት የመጫወቻ ማዕከላትን እና 1,530 የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ እነዚህ ደረጃዉን ጠብቀን የገነባናቸዉ መሰረተ ልማቶች 50 % ወጪያቸው የተሸፈነዉ በማህበረሰቡ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል። በመጨረሻም፣ ለወጣቶችና ህጻናት የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከላትን ለመገንባት ስናደርገው በነበረው ጥረት ሁሉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ላስተባበሩ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

photo content
+3

photo content
+9

የኤጀንሲውን ሲስተም በአዲስ የመተካት ሂደት ዝግጅት ተገመገመ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎት እየሰጠበት የሚገኘውን ሲስተም የሚተካ አዲስ ሲስተም አልምቶ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ተገምግሟል። ከአቅም ፣ ፍጥነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በነዋሪው ቅሬታ እየቀረበበት ያለውን በስራ ላይ ያለውን ሲስተም በመተካት የተቋሙን አገልግሎት ወደ ኦንላይን የሚያሻግርው ይኸው ሲስተም ባጠረ ግዜ ወደ ስራ ለማስገባት የልማት ሂደቱን በበላይነት እንዲመራ ሃላፊነት ከተሰጠው የኢትዮጵያን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኤንስቲትዩት ጋር ግምገማ ተደርጓል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እና የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታዬ ግርማ አጠቃላይ የዝግጅት ምዕራፍ ሂደቱን ገምግመዋል። ሲስተሙ ለምቶ ተጠናቆ በ2018ዓ.ም የኦንላይን አገልግሎትን በማስጀመር ወደ አገልግሎት ይገባል ተብሎ ይጥበቃል። ለበለጠ መረጃ በ7533 ይደውሉ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎች በአድዋ መታሰቢያ ሙዝየም ውስጥ እየሰጡ ባለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ስለ #ሀገር_ፍቅር ካነሷቸው ሀሳቦች :- 🇪🇹 በሀገር ግንባታ እና በብሔረ መንግስት ግንባታ ሂደት የሀገር ፍቅር ቁልፍ ሚና አለው 🇪🇹 ለሀገር ህልውና እና ማበብ ፍቅር አስፈላጊው ነገር ነው 🇪🇹 የሀገር ፍቅር ከአድናቆት የተሻገረ ራስን እና አንድያ ህይወትን ለሀገር ጥቅም እስከ መስጠት የሚዘልቅ ነው 🇪🇹 ለሀገር ጥቅም ሲባል የግል ምቾትን ሀብትን ስልጣንን እና ደህነትን መተው የሀገር ፍቅር ማሳያ ነው 🇪🇹 የሀገራችንን አርበኞች ጨምሮ እነ መሀተመ ጋንዲ ኔልሰን ማንዴላ አብርሀም ሊንከን በሀገራቸው ጥልቅ ፍቅር ወድቀው በብሔራዊ ፍቅር ተመርተው ሀገራቸውን ነፃ አውጥተዋል 🇪🇹 ሀገራችን በነብሳቸው ተወራርደው ደማቸውን ያፈሰሱ አጥንታቸውን የከሰከሱ አርበኞች ሀገር ናት 🇪🇹 የሰው ልጅ ከራሱ በላይ ለሆነ ነገር መኖርን እና አሻራውን ትቶ ማለፍ ካሻው የሀገር ፍቅር ያስፈልገዋል 🇪🇹 የሀገር ፍቅር ያላቸው ሰዎች ሀገራቸውን ሲወዱ በመውደዳቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ስቃይ ተቋቁመው ላፈቀሩት ነገር ቅድሚያ ይሰጣሉ 🇪🇹 ሀገራት እንደ ሀገር ሳይፈርሱ የሚቆዩት ዜጎቻቸው ለጋራ ዓላማ ባላቸው ፍቅር እና ራሳቸውን ባስገዙበት የፍቅር ልክ ነው 🇪🇹 የሀገር ፍቅር የስሜት ማዕበል የሚንጠው ሳይሆን የህይወት ዘመን ፍቅር ነው 🇪🇹 ለሀገር የሚኖር ፍቅር ደካማና ልፍስፍስ አይደለም:: ለረጅም ጊዜ የሚቆይና አንድነትን የማምጣት ሀይሉ ከፍተኛ ነው 🇪🇹 የሀገር ፍቅር ካለ የማይተዋወቁ ሰዎች በዓላማ ተሳስረው ለጋራ ግብ ስኬት ይሰለፋሉ:: ለቆሙለት ዓላማም ይሰዋሉ 🇪🇹 የሀገር ፍቅር ተራሮችን ያንቀጠቅጣል መጪውን ጊዜ ይገነባል:: ያለፈውን መጥፎ ጊዜ እንድንረሳ ያደርጋል 🇪🇹 ለሀገር መስዋእት ስንሆን ከመረሳት ይልቅ ለዘለዓለም እንታወሳለን 🇪🇹 በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ መስመር የለቀቀ ነገር ካለ እንዲስተካከል መጠየቅ የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው 🇪🇹 ራሳቸውን ለሀገራቸው ሲሉ መስዋዕት ያደረጉ ሰዎች ደም ዘር ነው ይዘራል ፍሬም አለው ያፈራል:: 🇪🇹 የሀገር መሰረታዊ እመርታ መስዋዕት ለመክፈል በተዘጋጁ ትውልዶች የሚረጋገጥ ነው 🇪🇹 ፍቅር ፅናት እና አይበገሬነት አንዱ የሌለውን ሌላው እያሟላ እና እየተጋገዙ የሀገር ፍቅርን ከፍታ ያሰምራሉ 🇪🇹 የሀገር ፍቅር የወለደው ፅናት ሲኖር ዜጎች በአንድ እጃቸው መሳሪያ በሌላ እጃቸው ሞፈር ይጨብጣሉ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+7

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ የሰላም፣ የፀጥታ እና አለምአቀፍ አመራር መድረክ መክፈቻ ወቅት ባደረጉት ንግግር ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አፀፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ አለምአቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል። አለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም አፅንኦት ሰጥተው አንስተዋል። ኢትዮጵያ በይፋ ወደ ብሪክስ የተቀላቀለችው በ2015 ዓ.ም ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ፍትኃዊ የሆነ፣ እኩልነት የሚሰፍንበት ብዝኃ ዋልታዊ አለምን ለመፍጠር ከሚተጉ ሀገራት ጋር በእኩል ደረጃ የተሰለፈችበት ስብስብ ነው። እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ ታደርጋለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የብሪክስን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ ሲገልጹም የሚከተለውን ብለዋል። ”ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለአለምአቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል። አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል። የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል።”

photo content
+8

አሳታፊ ጉዞ፤ የተደራጀ አመራር፤ የትጋት አመት ፤ 24/7 የመስራት ውጤት!!

የትውልዱ ተጠቃሚነት ይቀጥላል ! ለህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እና ቅሬታዎችተጨባጭ ምላሽ ፤ የወሰነውም ፣ የተገበርነው ም ለህዝብ ነው !

photo content
+4

ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል። Har'a ganama Ministira Muummee Li Qiang waliin walittidhufeenya Itiyoo-Chaayinaa waggoota 55 lakkofsise irratti marii'anneerra. Akka michuuwwan walittidhufeenyisaanii haalarratti hundaa'ee hin jijjiiramneetti waggoota torban darbanitti walta'insi keenya firiiwwan gurguddoo godhateera. Utubaawwan dinagdee ijoo ta'an kan akka indaastirii, albuudaafi ICT dabalatee xiyyeeffannoon keenya akkuma jirutti ta'ee, dameewwan walta'insaa kanbiroo cimsuuf kanneen akka Artifiishaal Intelejensii, loojistiksiifi humna anniisaa qulqulluu irratti waltaanee hojjechuuf humni guddaan akka jiru ilaalleerra. Thank you, Premier Li Qiang, for our engaging exchange this morning on Ethio-China relations, now in its 55th year. As all-weather partners, our cooperation has borne significant fruit over the past seven years. By maintaining our focus on key economic pillars, including industry, mining, and ICT, we see even greater potential to deepen collaboration and build capabilities in these areas, as well as in artificial intelligence, logistics, and the clean energy sector.

photo content
+5

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እንኳን ለመደበኛ ጉባኤያችሁ አደረሳችሁ ፡፡ መደራጀት ሃይል ነው። የመደራጀት ዋና ግቡ በተናጠልና በተበታተነ መንገድ ማሳካት የማንችለውን በህብረት በቀላሉ ከግብ ማድረስ ማስቻሉ ነው። ወጣቶች ተደራጅታችሁ መንቀሳቀሳችሁ ለተጠቃሚነታችሁ እና በሁሉም ዘርፍ ያላችሁን ተሳትፎ ለማጐልበት ወሳኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት! የምንሰራው ከምንም በላይ ለወጣቶች እና ለነገ ትዉልድ ተጠቃሚነት ነው። የከተማችን አመራሮች 70 በመቶ ያህሉ ወጣቶች ናቸው። የወጣቶችን ስብዕና መገንቢያ እና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በስፋት እየሰራን ያለነዉም በአካል እና ስነልቦና የጎለበታችሁ ብቁ ዜጋ ትሆኑ ዘንድ ነዉ። የከተማችን ወጣቶች በልማት ላይ ያላችሁ ተሳትፎ በተለይ በበጎ አድራጎት ስራ ያከናወናችሁት ስራ እጅግ ያስመሰግናችኋልና በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ጉባኤያችሁ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+7

ተግተዉ የሰሩትን ሁሉ እናመሰግናለን ! የከተማ አስተዳደራችን 15,960 ፕሮጀክቶችን ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አድርጓል። በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ አጭር እና አቋራጭ መንገዶች ፤ የትራፊክ ማሳለጫ ተሻጋጋሪ ድልድዮች የትራፊክ ፍሰትን በማቀላጠፍ እና ፕሮጀክቶቻችን በማያያዝ ለነዋሪው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ያለቸው ናቸው ። ፕሮጀክቶቹ ከ50 እስከ 60 ስፋት ያላቸዉ ድልድዮቹ እስከ 300 ሜትር ርዝመት ያላቸዉ ግዙፍ መንገዶች ያካተቱ ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ከዉጪ በሚገኝ ብድር ይገነባል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም ብድሩ ሳይገኝ ቀርቶ በከተማ አስተዳደሩ አቅም መገንባት የተቻለ ነዉ። የከተማችን ነዋሪዎችም የተገነቡ መንገዶችን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት አደራ እያልኩኝ ፤ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን ድርሻ ላበረከታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ባለስልጣን ፤ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪ ድርጅቶች እና የአቃቂ ቃሊቲ እና የቦሌ ክለከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች እና ድርሻ ለነበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+3

photo content