1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
ለመረጃ ግልፅነት:-
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እንኳን ለደመራና ለብርሐነ መስቀሉ በአል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ እያለ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሪጅን ኦፕሬሽን ኮርዴኔሽን ፅ/ቤት በስሩ የሚገኙ ሪጅንና አገልግሎት መስጫ ማእከላት አድራሻ እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ሪጅን ማስተባበሪያ ቢሮ ለመዲናችን ነዋሪዎች ለማንኛውም ከኤሌክትሪክ ጋር ለተያያዙ አገልግሎቶች በነፃ መስመራችን 905 ይደውሉ ሲልም አስታውቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
የከተማችን ልዩ ድምቀት ለሆነው እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነዉ።
ለመላዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
መልካም በዓል !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ በሁሉም ክፍለከተማዎች እና ወረዳዎች ዘውትር በዓል በመጣ ቁጥር እንደምናደርገው የመሰቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተናል ።
በዚህ ተግባር የቆየዉን የመደጋገፍ እና ተካፍሎ የመኖር ባህል ከሰዉ ተኮር እሳቤዎቻችን ጋር አቆራኝተን የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነዉ።
ይህንን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጎናችን ሆናችሁ የምትደግፉ ልበ ቀናዎች በሙሉ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በመዲናችን 1ሺህ 547 ደመራ የሚደመርባቸው ቦታዎች ፅዱ ተደርገዋል
የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ ጽዱና ውብ በሆነ ስፍራ እንዲከበር ለማድረግ "በእምርታና ማንሰራራት የታጀበ በዓላትን እናክብር!" በሚል መሪ-ቃል በመዲናዋ የሚገኙ #1547 ደመራ የሚደመርባቸውን ቦታዎች ፅዱ እንዲሆኑ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ መረጃ አመልክቷል።
ደመራ የሚደመርባቸውን ቦታዎች በጋራ ማፅዳት ለበዓሉ አጋርነትን ለማሳየት እህትማማችነትን፣ ወንድማማችነትን፣ አብሮነትን ለማጠናከር እና በዓሉም ፅዱና ውብ በሆነ ቦታ እንዲከበር ለማስቻል እንደሆነ በፅዳቱ ላይ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ከበዓሉ ቀደም ብሎ የተሰሩ የቅድመ ፅዳት ስራዎች ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ለማድረግ እና በዓሉ የተከበረባቸው ቦታዎች ፅዳታቸውን ጠብቀው ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ ከ2ሺህ በላይ ባሉ የግንዛቤ ባለሙያዎች የቤት ለቤት ግንዛቤ፣ በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ፣ በህትመት እና በማህበራዊ ሚዲያ እንዲሁም በቡና ጠጡ ፕሮግራም እና በተንቀሳቃሽ የጎዳና ላይ ሞንታርቦ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ሲፈጠር እንደቆየ ተገልፅዋል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የምናመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመያዝና በአካባቢያችን ለተመደቡ ፅዳት ማህበራት በመስጠት የከተማችንን ፅዳት በጋራ እንጠብቅ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሀገር ባለውለታዎች እና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ያስተላለፏቸው 253 ቤቶች (በምስል):
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከጳጉሜ ቀናት እስከ መስከረም አጋማሽ ወር የተካሄዱ አበይት የስራ ክንውኖች በፎቶ ስላይድ ሲቃኝ:- …
See more
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
**************************
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ
የመስቀል በዓል ሲታሰብ እውነት ተቀብራ እንደማትቀር እናስባለን። መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ተራራ ሠርቶ ነበር። የቀበሩት ሰዎች ከዚህ በኋላ እንደማይወጣ ደምድመው ነበር። አንዳንድ አማኞችም ተስፋ ቆርጠው ነበር።
ጊዜው በረዘመ ቁጥር ቀባሪዎቹ ያሸነፉ መስሏቸው ተደሰቱ። የተቀበረው መስቀልም ታሪክ የሆነ መሰለ።
ብርቱ ሰዎች፣ እውነት ፈላጊ ሰዎች፣ አቧራውን የሚገልጡ፣ ቆሻሻውን የሚያነሡ ሰዎች፣ ሲመጡ ግን መስቀሉ ከተቀበረበት ወጣ።
እውነት አይቀበርም። ጊዜው ሲደርስ አቧራውን አንሥቶ ዐሻራውን ያሳያል። ሐሰቱን እንደ ጉም አትንኖ፣ ሐቁን እንደ ዐለት አግንኖ ያሳያል።
የኢትዮጵያም እውነት እንደዚሁ ነው። የአውራ ዶሮዎች ጩኸት የፀሐይን መውጣት አያስቀረውም። የሌሊት ወፎች ክንፍ የፀሐይን ንጋት አያግደውም። በዚህም ተባለ በዚያ ፀሐይ ትወጣለች።
የኢትዮጵያ እውነት እንደ መስቀሉ ሁሉ አቧራውን ጥሶ፣ አፈሩን አፍልሶ፣ ቆሻሻውን ደርምሶ ይገለጣል። የወጓት ያዩዋታል። ከላይ ሆነው እንዳዩዋት ሁሉ፣ ከታች ሆነው ይገረሙባታል።
በመደመር ደመራ እየተመራን፣ በትጋት እየቆፈርን፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናወጣዋለን። ይህ ዓመት የኢትዮጵያ ብርሃን ሲወጣ የምናይበት ይሆናል።
በድጋሚ መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም
በደመራ ስነ-ስርዓት ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች!
👉ደመራ የሚደመርበት ቦታ ከኤሌክትሪክ መስመር ፣ ከመኖሪያ ቤቶች ፣ ከነዳጅ ማከማቻና መሸጫ ጣቢያዎች ፣ ከጋራዦችና ከመሠል ተቀጣጣይ ቦታዎች መራቅ ይኖርበታል ።
👉ለደመራው የምንጠቀምበት የችቦ መጠን እጅግ በበዛ ቁጥር እሳቱ ከቁ ጥርጥር ወጪ ሆኖ ለአደጋ መነሻ ምክንያት ስለሚሆን የችቦውን መጠን ውስን ማድረግ ያስፈልጋል።
👉ችቦ እየነደደ እሳቱን ለመዝለልና ደመራው ላይ ለመውጣት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አደገኛና ህይወትን የሚያሳጡ ናቸው ።
👉ችቦ በተለኮሰ ሰዓት ህጻናትና ታደጊዎች ወደ ዳመራው እንዳይቀርቡ አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል ።
👉ከመኖሪያ ቤት ችቦ ተለኩሶ በሚወጣበት ጊዜ እሳቱ መጋረጃና ሶፋ እንዲሁም ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ላይ አርፎ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ።
👉 በመለኮስ ሂደት ነዳጅ መጠቀም አይመከርም ።
👉የደመራው ስነ -ስርዓት እንደተጠናቀቀ እሳቱን ሙሉ በሙሉ በውሃ ማጥፋት ያስፈልጋል ።
የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንተግብር !
ከዚህ ዓልፎ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ እጅግ የተጎሳቆሉ ቤቶችን በማፍረስ የገነባናቸውን 253 ቤቶች የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ የሀገር ባለውለታዎች፣ ሀገር ሲያገለግሉ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የአልጋ ቁራኛዎች፣ ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላልፈናል ።
ባለፈዉ እሁድ ያስተላለፍናቸው ላይ የዛሬው 253 ቤቶች ሲጨመሩ እሰከአሁን በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ 3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከገነባናቸው 3 ሺህ በላይ ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 924 ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው ወገኖቻችን ማስተላለፍ ችለናል።
ቤቶቹ የጸዱ፣ መሰረታዊ ግብአቶች የተሟሉላቸዉ፣ ዘመናዊ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥሩ፣ የራሳቸው ቅጥር ጊቢና የጋራ መገልገያዎች ያላቸው፣ የህፃናት መዝናኛና መጫወቻ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን ያካተቱ ናቸው።
ይህንን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጎናችን ሆናችሁ ለምትደግፉ ልበ ቀናዎች እና ያስተባበራችሁ የከተማችን አመራሮች በሙሉ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል
ከንቲባ አዳነች አቤ
