ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
የጥንቃቄ መልእክት:- 🔥በመኖሪያ ቤት አካባቢ መደረግ ያለበት የእሳት አደጋ ደህንነት ( ቅድመ ጥንቃቄ ተግባራት ):- 🔥 በመኖሪያ ቤት አካባቢ ከምግብ ዝግጅትና ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ክስተትም ሆነ አደጋን ለመቀነስ የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል ። 💥 ለኤሌክትሪክ ምድጃ መደረግ ያለበት ቅድመ ጥንቃቄ 💥 ➡️ ለረጅም ሰዓታት በምድጃው አለመጠቀም ፤ ብልሽት ሲያጋጥም በዘፈቀደ ከመነካካት ባለሙያ ማማከር ፤ በአጋጣሚ በምድጃው ላይ የእሳት ቃጠሎ ቢፈጠር ከዋናው መቆጣጠርያ ኤሌክትሪኩን ማቋረጥ ፤ 💥 ለቡታ ጋዝ ምድጃ መደረግ ያለበት ቅድመ ጥንቃቄ ➡️ ሕፃናትና የአዕምሮ ህመም ታማሚዎች ወደ ምድጃው እንዳይደርሱ አጥብቆ መከላከል ፤ ➡️ ምድጃው የሚቀመጥበት ሥፍራ ጋደል ያለ እንዳይሆን መጠንቀቅ ፤ ➡️ እሳት እየነደደ ነጭ ጋዝ ወይም ነዳጅ ከመጨመር መቆጠብ ፤ ➡️ የምድጃው ክሮች ተገቢ ውፍረት ሳይኖራቸው መገልገል እሳት ወደ ውስጥ በማስገባት የእሳት ቃጠሎ አደጋ የሚያስነሱ በመሆኑ በምድጃው የክር ማስገቢያ ቀዳዳ ስፋት መጠን ክሮችን በማስገባት መገልገል ፤ ➡️ በአጋጣሚ ጋዙ ቢደፋ እሳቱ ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት በሚል ምክንያት ምድጃውን አንስቶ ከመወርወር መቆጠብ ፤ ➡️ በተቻለ መጠን ድንጋጤን በማስወገድ እሳቱን ማፈን በሚችል ወይም ኦክስጅን በማሳጣት እሳቱን ለማጥፋት የሚያስችሉ መሣርያዎችን እንደ ጆንያ ፣ ብርድልብስ ወ.ዘ.ተ በመጠቀም ለማጥፋት መሞከር ፤ 💥 ለሲሊንደር ምድጃ መደረግ ያለበት ቅድመ ጥንቃቄ ➡️ በሲሊንደሩ ከመጠቀምዎ በፊት ጋዝ ማፈትለክ ያለማፈትለኩን ለማረጋገጥ በሬጉሌተሩ ዙርያ ማረጋገጥ ፤ በተጨማሪም የሲሊንደሩ ቫልቭ በትክክል ጠብቆ የያዘ መሆኑን ማረጋገጥ ፤ ➡️ ቱቦዎች በስለት ያልተቆረጡ ወይም በአይጥ ያልተበሉና ያልተቀደዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ፤ ➡️ ጥቅም ላይ ከማዋል በፊት የጋዝ ሽታ ካለ እሳት ከመለኮስ ወይም የብየዳና የቅጥቀጣ ሥራ ከመሥራት መቆጠብ ፤ ➡️ የሲሊንደሩን ቫልቭ ከፍቶ መለኮሻ ፍለጋ ያለመሄድ ፤ በቅድሚያ መለኮሻ ማዘጋጀት ፤ ➡️ በተለያየ ምክንያት በሲሊንደሩ ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ቢከሰት ድንጋጤን በማስወገድ ወፍራም በሆነ ልብስ በማፈን እሳቱን ማጥፋት ፣ እሳቱ በጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ከሆነ ቫልቩን በመዝጋት ሲሊንደሩን ከምድጃው በማላቀቅ ካለበት ክፍል ማውጣት 💥 በምግብ ማብሰያ/ ማዕድ ቤት / አካባቢ መደረግ ያለበት ቅድመ ጥንቃቄ 💥 ➡️ የምግብ ማብሰያ ምድጃውን ከመሬት ወለል ከፍ አድርጎ ተቀጣጣይ ካልሆኑ ነገሮች ማለትም ከድንጋይ ፣ ከሸክላ ወ.ዘ.ተ መገንባት ፤ ➡️ የቤቱ ግንባታ ከእንጨትና ከጭቃ ከሆነ ምድጃውን ወደ ግድግዳ አስጠግቶ አለመስራት ፤ ➡️ የቤት ግድግዳ እንጨቱ ለእሳት እንዳይጋለጥ ማድረግ ፤ ➡️ የምግብ ማብሰያ ማገዶ እና ፈሳሽ ተቀጣጣይ በማዕድ ቤት ውስጥ አለማከማቸት ፤ ➡️ ቅጠል ፣ ሰጋቱራና የመሳስሉትን በጥንቃቄ በመያዝና በአግባቡ በማከማቸት መገልገል ወይም መጠቀም ፤ ➡️ የምድጃ አካባቢን ከተቀጣጣይ ነገሮች እንዲፀዳ ማድረግ ፤ ➡️ እሳትን አዳፍኖ አለማሳደር ፤ ምድጃውን ከተገለገሉበት በሁዋላ እሳት መጥፋቱን ሳያረጋግጡ ትኩስ አመድ ወደ ውጭ አውጥቶ በተቀጣጣይ ነገሮች ላይ አለመድፋት ፤ ➡️ ምጣድና ሌሎችም ከፍተኛ ሙቀት ያላቸው ዕቃዎች ከምድጃው ላይ ከወጡ በሁዋላ በተቀጣጣይ ነገሮች ላይ አለማስቀመጥ ፤ በቀላሉ ልንከላከላቸዉ በምንችላቸዉ አደጋዎች ህይወትና ንብረታችንን እንዳናጣ ጥንቃቄ የዘወትር ተግባራችን ይሁን። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ወይም በ011-1-55-53-00 ፈጥነዉ ያሳዉቁ።

photo content
+4

በመዲናዋ የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል እየተከናወነ ያለውን ተግባር አስመልክቶ በዛሬው እለት በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቀረበ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ:: በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በመሩት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በከተማዋ የጎርፍ አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ 135 ቦታዎችን አስቀድሞ የልየታ ስራ መከናወኑ ተጠቁሟል፡፡ የጎርፍ ቅድመ አደጋን በመከላከል ረገድ በተለዩ የስጋት ቦታዎች ላይ የሚመለከታቸው 10 የከተማው ተቋማት ማለትም የመንገዶች ባለስልጣን ፣የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ ቢሮ፣የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ፣የሜጋ ፕሮጀክት፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፣ የደንብ ማስከበር:፣ የአካባቢ ጥበቃ ፣ የውሃና ፍሳሽ እና እንዲሁም የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣንን ያካተተ የጋራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ስራዎች እየተሰሩ እንዳለም በሰነዱ ተመላክቷል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በዚሁ ወቅት የጎርፍ ቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች ጋር ተያይዞ ተቋማት በየክ/ከተማው እያከናወኗቸው ያሉ የግንባታና መሰል ተያያዥ ስራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡ አክለውም ህብረተሰቡም የቅድመ አደጋ መከላከል ግንዛቤ ኖሮት ራሱን ከጎርፍ አደጋ ከመጠበቅ ባሻገር በተለያዩ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ባሉ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችሉ ተከታታይ የተቀናጀና የተናበበ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በአፋጣኝ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s

photo content
+9

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ለሚገኙ የደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ ስራ ለተሰማሩ የህብረት ሽርክና ማህበራት እውቅና ምስጋና ሰጠ። የአዲስ ከተማ ክፍለ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ለሚገኙ 15 የደረቅ ቆሻሻ ህብረት ሽርክና ማህበራት 613 የማህበራቶቹ አባላት በተገኙበት እውቅና ምስጋና ሰጥቷል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ውብና ፅዱ አዲስ ከተማን ለመፍጥር የሽርክና ማህበራቱ እያደረጉ ያለውን ጥረት አድንቅው ይሄንን ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ሽርክና ማህበራቱ አቅማቸውን በማሳደግ በክፍለ ከተማ ደረጃ ዩኒየን ለመመስረት እያደረጉት ያለውን ጥረት አስተዳደሩ ከጎናቸው ሆኖ እንደሚደግፍ ገልጸው ሁልጊዜም ጽዱ እና ምቹ የሆነ የመኖሪያና የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ከነዋሪዎቻችን የነቃ ተሳትፎ ጋር በማቀናጀት መረባረብ ይገባል ብለዋል። በእውቅና መርሃ-ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረሰ ፈጠነ የደረቅ ቆሻሻ ህብረት ሽርክና ማህበራት በየዕለቱ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ ቤት ለቤት በማሰባሰብ የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸውን ገልፀው ቆሻሻ ሃብት በመሆኑ በዘርፋ ተደራጅተው የስራ እድል የተፈጠረላቸው በመሆኑ ራሳቸውን ከመለወጥ አልፈው ለበርካቶች አርአያ መሆን ችለዋል። በተጨማሪም ማህበራቱ ደረቅ ቆሻሻ ከመሰብሰብ አልፈው ማጓጓዝ እንዲችሉ በክፍለ ከተማችን ዩኒየን በመመስረት ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር ጥረት መደረጉ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ ጎንፋ የሽርክና ማህበራት በጽዳት ዘርፍ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት በጋራ እንደሚያሳኩ ገልጸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። Addis Ketema Communication ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s

128ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ተካሄደ። በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስ
+9
128ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ተካሄደ። በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደተናገሩት ጽዳት የአንድ ወቅት ስራ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን ማድረግና ይገባናል ያሉ ሲሆን አባቶቻችን በአድዋ በጦር ሜዳ ላይ ያሳዩትን ጀግንነት እኛም አካባቢያችንን ንጹህ እና ውብ በማድረግ የጽዳት ጀግኖች መሆን አለብን ብለዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ በበኩላቸው ፅዳትን ባህል በማድረግ አካባቢያችንን ከተማችን እና የትምህርት ተቋማትን ማራኪ፣ንፁህና ውብ እንዲሆኑ የማድረጉ ስራ በየእለቱ እየተጠናከረና እያደገ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቆሻሻ ሃብት በመሆኑ በመልሶ መጠቀም የተለያዩ ስራ እድል እንደሚፈጠርባቸው በመግለጽ አካባቢያችንን ፅዱ፣ ውብ ማራኪ እናደርጋለን በማለት ሃሳባቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በጽዳት ዘመቻው ላይ የከተማ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የጽዳት ማህበራት ፣ የጽዳት አምባሳደሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል ።

"128ኛው የዓድዋ ድል በዓልን በመከላከያ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ ደማቅ በሆነ ስነስርአት አክብረናል" በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን! ከንቲባ አዳነች አቤ
+6
"128ኛው የዓድዋ ድል በዓልን በመከላከያ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ ደማቅ በሆነ ስነስርአት አክብረናል" በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን! የዘንድሮውን የዓድዋ ድል በዓል የምናከብረው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን ድሉን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ገንብተን የዓድዋን ጀግኖች እየዘከርን በመሆኑ
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን! የዘንድሮውን የዓድዋ ድል በዓል የምናከብረው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን ድሉን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ገንብተን የዓድዋን ጀግኖች እየዘከርን በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል:: ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶችን ሁሉ ትተው በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው የተዋደቁበት እና የጋራ ድል የተጎናጸፉበት ይህ ታላቅ የድል ታሪክ የአንድነት፣ የመከባበር፣ የፍቅር፣ የጀግንነትና የፅናት ምልክት ሆኖ በወርቅማ ቀለም የተፃፈ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የጋራ ታሪካችን ነው፡፡ የዓድዋ ድል ታሪክ ለእኛ እና ለመጪው ትውልድ በአንድነት አገርን የመጠበቅ የመውደድናለአገርን ቅድሚያ የመስጠት አደራም ጭምር በመሆኑ፣ በአንድነት፣ በመከባበር፣ በፍቅር፣ በጀግንነትና በፅናት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ዳር በማድረስ የራሳችንን ዘመን የጀግንነት ታሪክ በጋራ እንድንፅፍ ያነሳሳናል፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! በድጋሚ እንኳን አደረሰን! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቴክኖሎጂን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ተቋማት የሶስኛ ደረጃ በማግኘት ተሸላሚ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በከተማው ቴክኖሎጂን ተግባራዊ
+2
ቴክኖሎጂን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ተቋማት የሶስኛ ደረጃ በማግኘት ተሸላሚ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በከተማው ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አድርጎ በመጠቀምና አገልግሎትን በማሻሻል ባለፉት ስድስት ወራት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል። በተደረገው የምዘና ስርዓትም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቴክኖሎጂን በተሻለ ሁኔታ በመግበሩ በአዲስ አበባ ካሉ ተቋማት የሶስተኛ ደረጃ በማግኘት እውቅና ተሰጥቶታል። … See more

photo content
+1

እንኳን ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡ እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡ የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አሳይቷል፡፡ የመጀመሪያው በጦርነቱ ዘመቻና ድል ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ በምናውቃት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች መካከል ወደ ዐድዋ ያልዘመተ ወገን የለም ብሎ መናገር እውነትን መናገር ነው፡፡ ሁለተኛው ክሥተት ደግሞ የዐድዋ ድል በተገኘ በሰባት ዓመቱ የዐድዋ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሲከበር ትርዒቱን ያቀረቡት ከተለያዩ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችች የመጡ የኢትዮጵያ ጦር አባላት ነበሩ፡፡ በዚህ ትርዒት ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት ሀገር መሆንዋን በዐደባባይ ሰልፈኛው አሳይቶ ነበር፡፡ ይሄንን በዐድዋ ዘመቻና በዓል የተንጸባረቀ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አጽንተን ልንይዘው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ኅብረ ብሔራዊ ማነነት ያላቸው ሕዝቦች በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ኅብረ ብሔራዊነታቸው ከፈጣሪ ሲያገኙት ነው፡፡ አንድነታቸውን ደግሞ እነርሱ ራሳቸው በዘመናት ትሥሥርና መሥዋዕትነት ገንብተውታል፡፡ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁለቱን፣ ነገር ግን አንዱ ከሌላው ጋር ሳይነጣጠል የሚኖሩትን መገለጫዎቿን ትታ ኢትዮጵያ አትሆንም፡፡ በእያንዳንዱ ጉዞዋ ይሄንን እያረጋገጠች መጓዝ አለባት፡፡ ሁለተኛው ዕሴት ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ሲባል ንኡስ ፍላጎቶችን መሠዋት ነው፡፡ ወደ ዐድዋ የዘመቱ ሁሉ በወቅቱ በነበረው ሥርዓተ መንግሥት የሚስማሙና የተደሰቱ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ግጭትም ቅራኔም ነበራቸው፡፡ አንዳንዶቹም በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ ቅር ተሰኝተው ከጠላት ጋር የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ነገሩ የሀገር ጉዳይ ሲሆንባቸው ግን ሁሉም ንኡስ ፍላጎቶቻቸውን ትተው፣ ለታላቁ ፍላጎት ለሀገር ህልውና መሥዋዕት ለመሆን መጡ፡፡ ማንኛውም ፍላጎት ከሀገር ፍላጎት በታች መሆኑንም አሳዩን፡፡ እንኳን ዛሬ ብዙ ዓይነት መረጃ፣ ዕውቀትና የሐሳብ መንገዶች ባሉበት ዘመን ቀርቶ ከመቶ ዓመት በፊትም ሰዎች ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ነበሯቸው፡፡ በፍላጎቶቻቸው የተነሣም ቅራኔዎችና ግጭቶች ነበሩ፡፡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ የምታስተሣሥር ዓላማ ሀገር የምትባለው ናት፡፡ ዛሬም ንኡስ ፍላጎቶቻችን ከኢትዮጵያ አይበልጡም፡፡ ኢትዮጵያን የሚያዳክም፣ የሚያሳንስና የሚያሳጣ መንገድ ከትልቁ ዓላማ የሚጋጭ መንገድ ነው፡፡ ጦርነት የትልቁ ዓላማ የኢትዮጵያ ህልውና ማስከበሪያ እንጂ የንኡስ አካባቢያዊና ግላዊ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ሊሆን አይገባም፡፡ ጦርነት ለትንሽ ነገር የሚወጣ ወጪ አይደለም፡፡ ዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉት ሁሉ ብዙ የመፍትሔ አማራጮችም አሉት፡፡ መከራከር፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ በሕግ መዳኘት፣ አንዱ ሌላው መሸከም፣ የትየለሌ አትራፊ መንገዶች አሉት፡፡ ትልቋ ዓላማ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ስንል ንኡስ ዓላማዎቻችንን እያመሙን እንኳን ቢሆን መሠዋት አለብን፡፡ ሦስተኛው ዕሴት የጦርነትን ምርቅና ፍትፍት ማወቅ ነው፡፡ ጦርነት ምንም ያህል በአሸናፊነት ቢጠናቀቅ የሚያስከፍለው ዋጋ አለው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ሀገር ሆኖባቸው፤ ሉዓላዊነት ሆኖባቸው፤ የታላቅ ዓላማ ጉዳይ ሆኖባቸው እንጂ ጦርነት የመጀመሪያ አማራጫቸው አልነበረም፡፡ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ነገሩ በሰላም እንዲቋጭ ደጋግመው ጽፈዋል፤ ለምነዋል፡፡ አልሆነም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዘማቾች ግን ከድል የተመለሱት በደስታ ብቻ አይደለም፡፡ ከፊታውራሪ ገበየሁ ጀምሮ አያሌ ጀግኖች ለትልቁ ዓላማ ለኢትዮጵያ ህልውና ሲሉ ተሠዉተዋል፡፡ የሄዱት ሁሉ አልተመለሱም፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በድልና በኀዘን ነው የተመለሰው፡፡ ብዙዎችም በየአካባቢያቸው በፌሽታ አልነበረም ድሉን ያከበሩት፡፡ እንኳን በራሳቸው ወገኖች፣ በጣልያኖች መሞት ኢትዮጵያውያን አዝነዋል፡፡ ጦርነት ተገድደን ብቻ ለትልቁ ዓላማ ስንል የምንገባበት የመጨረሻ አማራጭ እንጂ ከደረት ኪሳችን ቶሎ የምንመዘው አይደለም፡፡ እዚህም እዚያም የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በጠመንጃ ለመፍታት መነሣት የዐድዋ ዘማቾችን ኀዘን አለመጋራት ነው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ድልን ብቻ ሳይሆን ጦርነት የሚያስከትለውን መከራም ጭምር አስተምረውን አልፈዋል፡፡ አራተኛው ትዕግሥት፣ ዝግጅት እንጂ ፍርሐት አለመሆኑን ነው፡፡ ጣልያኖች ከሦስት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ሲገፏት ነበር፡፡ በሀገሪቱ የደረሰውን የእንስሳትና የሰዎች ማለቅ ምክንያት አድርገው ትንኮሳውን አባብሰው ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እየተገፋች እንኳን ቢሆን ታግሣለች፡፡ ትዕግሥቷ ግን ከዐቅመ ደካማነቷ የመጣ አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር እየተዘጋጀች ስለነበር እንጂ፡፡ እህል እስኪደርስ፣ ሰው እስኪያገገም፤ የተገዛው መሣሪያ እስኪደርስ፣ የደረሰው መሣሪያ ከጦሩ ጋር እስኪላመድ ታግሣለች፡፡ በመጨረሻ ግን የትዕግሥቷን ውጤት በዐድዋ ተራሮች ላይ አሳይታለች፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬም ትታገሣለች፡፡ እየተገፋችም እንኳን ቢሆን ትታገሣለች፡፡ የምትታገሠው ስለሚያቅታት አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር ስለምትዘጋጅ ነው፡፡ ያ የባሰው ነገር ሲመጣ የዐደዋውን ድል በብዙ እጥፍ ትደግመዋለች፡፡ እነዚህን ዕሴቶች ዘወትር ማሰብ፣ አስበን መተግበር እንድንችል የሚያስታውሰን ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ ዐድዋን የሚመጥን ታሪኩንም ዕሴቱንም የምናስብበት መታሰቢያ ዘመቻው በተጀመረበት ሥፍራ ባስገነባን ማግሥት ነው በዓሉን የምናከብረው፡፡ ይሄም ለዘንድሮው በዓል ሞገስና ክብር ጨምሮለታል፡፡ ዛሬ መታሰቢያውን በከበረ ሁኔታ አከናውነናል፡፡ ነገ ግን የአድዋን ዕሴቶች በሚገባ በመጠቀም እንደ ዐድዋ ተራሮች የጸናች ኢትዮጵያን መገንባት ይቀረናል፡፡ ያ ደግሞ የሁላችንንም ስክነት፣ ብስለትና ጥምረት ይፈልጋል፡፡ በድጋሚ መልካም የዐድዋ ድል በዓል ይሁን፡፡ ኢትዮጵያ‍ በልጆቿ‍ ጥረት‍ ታፍራና‍ ተከብራ‍ ለዘላለም‍ ትኑር!! ፈጣሪ‍ ኢትዮጵያና‍ ሕዝቦቿን‍ ይባርክ! የካቲት 22/2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

እንኳን ለ128ኛ የአድዋ ድል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

በትምህርት ቤቶች ዘወትር አርብ የጽዳት ንቅናቄ በማድረግ የትምህርት ማህበረሰቡን ጤና መጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ:: ኮልፌ ኮሙኒኬሽን የካቲት 22/2016 ዓ.ም በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው በሚገኙ
+7
በትምህርት ቤቶች ዘወትር አርብ የጽዳት ንቅናቄ በማድረግ የትምህርት ማህበረሰቡን ጤና መጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ:: ኮልፌ ኮሙኒኬሽን የካቲት 22/2016 ዓ.ም በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው በሚገኙ 137 ትምህርት ቤቶች ላይ የጽዳት ንቅናቄ የተካሄደ ሲሆን በክፍለ ከተማ ደረጃ በአንድ ማእከል በጀነራል ዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህር ቤት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴን ጨምሮ የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ ተፈራ፤የክፍለ ከተማ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ መምህራን ፤ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ በጽዳት ንቅናቄውን ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ ት/ቤቶቻችን ዘውተር ጽዱና ውብ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን የተሳለጠ ማድረግ አለብን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ ተፈራ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በሁሉም ትምህርት ቤቶች የ5 ወራት የጽዳት ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን ያስታወቁ ሲሆኑ ዘወትር አርብ በጊቢውና ከግቢው ውጪ ባለው 10 ሜትር ራዲዮስ የጽዳት ንቅናቄ በማድረግ የትምህርት ማህበረሰቡን ጤና መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡ Manneen barnootaa keessatti hojii qulqullinaa gaggeessuun fayyaa hawaasa barnootaa akka eegamu akka taasisu ibsame.

የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ጽዳትን ባህል በማድረግ ጽዱና ውብ አካባቢን መፍጠር እንዳለባቸው ተገለፀ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በእንጦጦ ወንጌላውያን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤቶ
+8
የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ጽዳትን ባህል በማድረግ ጽዱና ውብ አካባቢን መፍጠር እንዳለባቸው ተገለፀ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በእንጦጦ ወንጌላውያን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤቶች ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። በጽዳት ንቅናቄው ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሽቱ ሃይሉ እንደገለጹት በክፍለ ከተማው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የጽዳት ዘመቻዎች በማድረግ ሀገር ተረካቢው ትውልድ ጽዱና ውብ አካባቢን የሚፈጥርና ቆሻሻን ሀብት መሆኑን ተረድቶ አወጋገዱን ዘመናዊ እንዲያደርጉ ነው ብለዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ በመልሶ መጠቀም የተሰሩ የተለያዩ ዕቃዎች በአውደ ርዕይ ቀርበዋል ፡፡ በጽዳት ዘመቻው ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣መምህራንና ተማሪዎች ፣ የጽዳት ማህበራት ተሳትፈውበታል ። Gullele communication

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከከተማው ተቋማት ቴክኖሎጂን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም በአንደኝነት ተሸላሚ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በስድ
+1
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከከተማው ተቋማት ቴክኖሎጂን በተሻለ ሁኔታ በመጠቀም በአንደኝነት ተሸላሚ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በስድስት ወራት የከተማ የቴክኖሎጂ ተግባራት አፈፃፀም በከተማው ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አድርጎ በመጠቀምና አገልግሎትን በማሻሻል የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል። በዚህ መሰረት በተደረገው ምዘና የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎትን በተሻለ ሁኔታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በመስጠት እና በተመግበር የአንደኝነት እውቅና ተሰጥቶታል። በመርሃ-ግብሩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተገኝተው እውቅናውን የተቀበሉ ሲሆን ለውጤቱ መገኘት ቢሮው ያደረገው ድጋፍ ትልቅ መሆኑን አንስተዋል። ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ሃላፊው ያነሱ ሲሆን እውቅናው ይበልጥ ተቋሙ የአገል ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቅም የሚሆን መሆኑን አክለዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የስነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት እየተዘጋጀ ያለውን የተቋሙን የብራንዲንግ ዲዛይን ፓኬጅ የመጨረሻ ረቂቅ በዛሬው እለት ለስትራቴጂ
+3
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የስነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት እየተዘጋጀ ያለውን የተቋሙን የብራንዲንግ ዲዛይን ፓኬጅ የመጨረሻ ረቂቅ በዛሬው እለት ለስትራቴጂክ ካውንስል ቀርቦ ውይይት ተካሂደ:: የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ራእይ፥ተልእኮና ኃላፊነት ጋር የተሳሰረ ቀላልና ግልፅ፥ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሁም የቀለም ስብጥሩና ምልክቶች ከእነ ትርጉማቸው በርካታ አማራጮችን የያዘ የብራንዲንግ ዲዛይን ፓኬጅ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የስነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ቀርቦ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ የመጨረሻ ረቂቅ የሎጎ ዲዛይን ተመርጧል:: በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በውይይቱ ወቅት 'አለ' የስነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ከዚህ ቀደም በነበሩ ውይይቶች የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት የመጨረሻ ረቂቅ በማቅረባቸው አመስግነው በዛሬው የውይይት መድረክ የተመረጠውን ዲዛይን በፍጥነት ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:-

photo content
+5

"የመዘጋጃ ቤታዊ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከር የህብረተሰቡን የአገልግሎት ፍላጎት ያሳካል።"አቶ ሰዒድ ዓሊ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመዘጋጃ ቤታዊ ቅንጅታዊ አሰራር ፎረም ምስረታ አካሄደ። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ እንደተናገሩት የመዘጋጃ ቤታዊ ቅንጅታዊ አሰራር ፎረም መመስረቱ በመዘጋጃ ቤታዊ የሚሰጡ አገልግሎቶች የመብራት ፥መንገድና ውሀ በቅንጅት ለመስራትና የሚፈጠሩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው የተመሰረተውን ተቋማዊ ፎረም በማጠናከር የህብረተሰቡን የአገልግሎት ፍላጎት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳምጠው አበበ በበኩላቸው የመብራት፣ የውሃና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎቶችን ለነዋሪዎች ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎትን ለመስጠት የፎረሙ መሙስረት ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልጸው ሁሉም በፎረሙ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎች ግባቸውን እንዲመቱ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ይገባል። የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደተናገሩት በስራ አስኪያጅ ተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማከናወን እንዲቻል በፎረሙ ምስረታ ስራን ቆጥሮ መስጠት እንዳለ ሆኖ በአፈጻጸማችን ወቅት ስራዎችን ቆጥሮ በመቀበል ሁሉም ለስራዎች ስኬታማነት ልንሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በአንድ ፎረም አማካኝነት መከናወናቸው ሁሉም ስራዎችን በኃላፊነት መስራት እንዲችል የሚያደርግ መሆኑንና በቀጣይም የሚነሱ ጥያቄዎችን በማስተካከል አፈጻጸሙን ማሳደግ ይገባል ብለዋል። በፕሮግራሙ ስራን ቆጥሮ ለመስጠትና ቆጥሮ ለመቀበል እንዲቻል ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማት ጋር ሰነድ ተፈራርመዋል። Lideta sub-city communication office ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና በአሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያሰለጠናቸውን 1,658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ አስመርቀና
+9
ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና በአሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያሰለጠናቸውን 1,658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ አስመርቀናል። ለሁለት ዓመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ተመራቂዎቹ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ ሲሆን፣ አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ለማሳካት ትልቅ ሚና ያለው የትውልድ ግንባታችን አካል ነው። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+2