1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎርፍ በመኖሪያ ቤታቸው በመግባት በንብረት ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።
በወረዳው ቀጠና 2 ልዩ ስሙ “ወይን አምባ” በተባለው አካባቢ ጎርፍ ወደ መኖሪያ ቤቶች በመግባት በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ቦሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ከ600,000 ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የፍራሽ፣አንሶላና ብርድ ልብስ ድጋፍ ማድረጉን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ዋኘው አስታውቀዋል፡፡
አካባቢውን የማጽዳትና ተያያዥ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት ሥራ አስኪያጁ፣ በቀጣይ መሰል ችግር እንዳይከሰት ነዋሪዎች ከወንዝ አካባቢ 50 ሜትር ርቀት ላይ መስፈር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቦሌ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብቴ አማረ በበኩላቸው በአካባቢው የሚገኘው ወንዝ በአፈር በመዘጋቱ ምክንያት ተፈጥሯዊ አቅጣጫውን በመሳት ወደመኖሪያ ቤቶች መግባቱን ገልጸው፣ በቤቶቹ ለሚኖሩ ነዋሪዎች በጊዜያዊነት የፍራሽና ብርድ ልብስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ለጎርፉ መከሰት ምክንያት የሆነውን አፈር የመጥረግና የማንሳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ሀብቴ ገልጸው፣ ነዋሪዎቹን ወደመኖሪያ ቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረግና በዘላቂነት አካባቢውን ከጎርፍ ሥጋት ነፃ ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፈጥኖ በመድረስ ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በቅርበት ድጋፍ እያደረጉላቸው እንደሆነ በመግለጽ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል አያይዘውም ወደ ቤታቸው ተመልሰው መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡
መጋቢት 14/2017
ለወረዳ አመራሮቻችን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቅቀናል።
ከተማችን ያለባትን ሃላፊነት ለመወጣት እና ለነዋሪዎቻችን ቀልጣፋ እና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቁ እና የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ አመራር በመገንባት ላይ እንገኛለን።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የጀመርነው መሠረታዊ ለውጥና የሪፎርም ስራ ይበልጥ ውጤት እንዲያስገኝ እና ብቃት ያለው የህዝብ አገልጋይ ለመፍጠር የአመራሩ ሚና ትልቅ በመሆኑ ይህን አቅም ለማሳደግ የተሰጠ ስልጠና ነዉ።
በቀጣይም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአመራር ምልመላና ስምሪት በብቃትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግና ለነዋሪዎቻችን ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኢፍጣር በአፋር
Iftar in Afar
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አካባቢ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
በተያያዘ በዚሁ ስፍራ በአካባቢው ባለዉ ወንዝ ዉስጥ ተከማችቶ የነበረዉን ከፍተኛ መጠን ያለዉን አፈር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በእስካቫተር እንዲከፈት በማድረግ በቀጣይ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የማቅለያ ስራ ተሰርቷል።
ኮሚሽኑ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 11 ቀጠና ሁለት እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ከሰሞኑ በጣለዉ የበልግ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
በጎርፍ አደጋዉ 105 ተጎጂዎች የዋጋ ግምቱ ከ600 ሺህ ብር በላይ የሆነ ፍራሽ ፣ ብርድልብስና አንሶላ ድጋፍ ተደርጓል።
ኮሚሽኑ በተለያዩ ምክንያቶች እሳትና መሰል አደጋዎች በሚያጋጥሙ ጊዜ አደጋ ቦታ ፈጥኖ በመድረስ የህዝብ ንብረትን የመታደግ ተግባርን ለመከወን በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና በማዕከል የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መ/ቤቱና ከሚመለከታቸዉ አካላት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግና ከዚህ ዓልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸዉም አደጋዎች ባጋጠሙ ጊዜ በነጻ የስልክ መስመር 939 ላይ በመደወል እንዲያሳዉቅም ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳውቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አፋር ክልል በመገኘት የክልሉን የግብርና እና የኢንደስትሪ አቅሞች የሚያሳዩ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ጉብኝታቸው ከስድስት ወራት በፊት ምርት የጀመረውንና 15 ቶን በሰዓት የሚያመርተውን የአዮዳይዝድ ጨው ማምረቻ ምልከታን ያካተተ ነበር። በተጨማሪም በአፋር ክልል የተሳካ የበጋ ስንዴ ምርት እየተካሄደበት ያለውን ልማት ሥራ እና የአይሮላፍ መኖ ባንክ ልማት ማዕከልንም ጎብኝተዋል። በክልሉ ስላለው የግብርና አቅም የነበረውን የተሳሳተ ምልከታ በማሸነፍ በመስኖ የለማ አስደናቂ የስንዴ ምርት መገኘት ችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባውን እና ከማሳ ወደ ገበታ ሙሉ የምግብ ምርት ሰንሰለት የሚያጎላውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካም መርቀዋል። ፋብሪካው በተገጠሙለት ዘመናዊ ማሽኖች በመጠቀም 420 ኩንታል ስንዴ በቀን መፍጨት የሚችል ሲሆን 300,000 ዳቦዎችንም በ24 ሰዓታት ማምረት ይችላል።
#PMOEthiopia
ፅዳት የስልጡን ማህበረሰብ መገለጫ ነው!!
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ወረዳ 2 አራት መንታ አካባቢ አካሒዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሳዲቅ ሽኩር በፅዳት ንቅናቄው ላይ ባስተላለፉት መልእክት አራዳ ክፍለ ከተማ ላይ እየለማ ያለውን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የከተማዋን ገፅታ እያሳመረ በመሆኑ የአካባቢውን ፅዳትም በማሻሻል ፅዱ ከተማን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃይለማርያም የአራዳ ማህበረሰብ አካባቢውን በአግባቡ በማፅዳት፣ በማስዋብና በማሳመር ጥሩ እይታ በመፍጠርና ጤንነትን በመጠበቅ በኩል ከፍተኛ ርብርብ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ በወረዳችን በፅዳት ሥራ ሞዴል መንደሮችን ለመፍጠር ትኩረት አድርገን እየሠራን ነው ብለዋል።
በፅዳት ፕሮግራሙ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የፅዳት ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአግባቡ የተያዘ ደረቅ ቆሻሻ #የጤና ጠንቅ ሳይሆን #ሀብት ነው
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር አደረሳችሁ።
በመዲናችን ከሚገኙ አቅመ ደካሞችንም እና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የአፍጢር መርሃ ግብር አከናውነናል።
ይህን የጾም እና የጸሎት ወቅት የእምነቱ አስተምሮ በሚያዘው መሰረት ድሆችን እና ጠያቂ የሌላቸዉን ወገኖች መርዳት፣ መደገፍ እና አቅመ ደካሞችንም በማሰብ መሆን አለበት።
እኛም ፆሙን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በሚገኙ 24ቱ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ዘወትር ማታ ማታ ለአቅመ ደካማ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ሰዎች የአፍጢር መርሃ ግብር በማዘጋጀት ነዋሪዎቻችንን እያስፈጠርን እንገኛለን::
በድጋሚ እንኳን ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር አደረሳችሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
