ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
ከክረምት መቃረብ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑና ስጋት ያለባቸው ተብለው በተለዩ ክፍለ ከተሞች ያለው የአደጋ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉 AMN-Addis Media Network ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

ከተማዋን የሚመጥን የስማርት ፖል ግንባታና በአንድ ማዕከል የማስተዳደር ውጥን ተጠናክሮ ቀጥሏል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በኮሪደር ልማት ሎት ሁለት የስማርት ፖል ዝርጋታና ተከላ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንዲሁም የተገነቡትን ስማርት ፖሎች በዋና መ/ቤት በአንድ ማዕከል ውስጥ ለመከታተል የሚረዳውን የስራ ስምምነት አካሂዷል፡ ከተማችን አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ በማድረግ ነዋሪዋን የሚመጥን፣ ለኑሮ ምቹ የሆነና የጊዜውን ቴክኖሎጂ የዋጀ የማድረግ ስራውን ለማጠናከር የሚረዳውን ስምምነት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፤ ግንባታውን እያከናወነ ካለው የስራ ተቋራጭ የቻይና ጃንግዙ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚ እና ቴክኒካ ኮርፖሬሽን ግሩፕ ጋር በትናንትናው እለት ግንቦት 20/2017 አ.ም ስምምነት አድርገዋል፡፡ በስምምነቱ ውስጥ በኮሪደር ሎት ሁለት ላይ የሚከናነውን የስማርት ፖል ዝርጋታና ተከላን አስመልክቶ ያሉ ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ፤ በተጨማሪም የተገነቡ የስማርት ፖሎችን አሁናዊ መረጃዎችን በአንድ ማዕከል ለመቆጣጠርና ለመመከታተል የሚያስችል ግንባታን በዋና መ/ቤት ማከናወን እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ ከማዕከሉ ግንባታ ጋር ተያይዞ የስራ ተቋራጩ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ስራውን አጠናቆ እንደሚያስረክብ የገለፁ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ የከተማውን የመብራት ፖሎች አሁናዊ መረጃን መሰረት በማድረግ የመንገድ መብራቶችን የሀይል አጠቃቀም ለመቆጣጠር፣ የሚያጋጥሙ ብልሽቶችን ለመለየትና በወቅቱ ለመፍታት፣ የመሰረተ ልማቱን በአንድ ማዕከል ለማስተዳደር እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡ የስራ ተቋራጩ በመጀመሪያው የኮሪደር ግንባታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ሲሳተፍ የነበረ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+1

“የላቀ የጤና አገልግሎት ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ሲካሄድ የነበረው የጤና ባለሙያዎች ውይይት የማጠቃለያ መድረክ አድርገናል:: መድረኩ የጤና ባለሙያዎች ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ሚና በመረዳት በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ፣ ለሀገረ ግንባታ በጋራ መቆምን ፣ የተሻለ አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመምከር እና ከባለሙያዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን በማዳመጥ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው:: የጤና ባለሙያዎቹ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች እና የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጤናማነቱ የተጠበቀ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እንዲሁም በሽታዎችን ለመከላከል አጋዥ መሆናቸዉን ያነሱ ሲሆን ፤ በጤና ሴክተር ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ እና የሁሉን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን በሚገባዉ ላይም ተግባብተናል። በቀጣይ የጤና ሴክተሩን ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ፤ ነባር የጤና ተቋማት ለማሻሻል፣ ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ አዳዲስና ዘመናዊ የጤና ተቋማትን ግንባታ ማጠናቀቅ፣ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት፣ ወቅቱ የደረሰበት ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች ማሟላት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰረታዊ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል:: የጤና ባለሙያዎቹ በርከት ያሉ የጥቅማጥቅም እና የደሞዝ ማሻሻያ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን አገልግሎትን የሚመጥን ጥቅማጥቅም አለመኖሩን በመገንዘብ እየተሰራ ባለዉ በጤና ሪፎርም ጥናት ላይ በመመስረት በአጭር ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን አምነንበታል። በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚፈቱትን የትርንስፖርት አገልግሎታ ፣በማህበር ተደራጅቶ የመኖሪያ ቤት መገንባትን ፣ ነፃ የህክምና አገልግሎት፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያን መመሪያ በተሟላ ሁኔታ መተግበርን ጨምሮ አስተዳደሩ በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ምላሽ ለመስጠት ተግባብተናል:: በመጨረሻም ያሏቸዉን ጥያቄዎች ቢሆን እያገለገሉ የሚጠይቁት እንጂ ከሙያዊ ስነምግባር ዉጪ ስራ አቁመዉ የሚጠይቁት አለመሆኑን አረጋግጠዋል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+9

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። ኢንስትትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው። የምርምር ስራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመትንበያና የትንበያ ስራዎችን በመስራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል። የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ ሲሆን ዛሬ በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ስራዎች ምልከታ ተደርጓል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+5

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጋና የመጡ የጆስፖንግ ግሩፕ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ተቀብሎ ቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን ፣ ኢኬቲ ሴራሚክስ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ድርጅትን እና በመሰራት ላይ የሚገኘውን የቦሌ አራብሳ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ማዕከል ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን አስጎብኝቷል። ይሄው ልዑክ ቡድን በትናንትናው ዕለት በረጲ ላንድፊል ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ /Waste to energy/ ጣቢያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን መጎብኘታቸው የሚታወስነው ። በጉብኝቱ ላይም በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ//ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰን ጨምሮ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ፣ በጋና የጆስፖንግ ግሩፕ ልዑካን ቡድን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በመዲናችን አዲስ አበባ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ተብለዉ በተለዩ ቦታዎች ላይ አደጋዉን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተከናወኑ ስራዎች ላይ የተካሄደውን የመስክ ምልከታ አስመልክቶ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ዘገባን በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

FB_IMG_1748458768568.jpg0.47 KB

FB_IMG_1748458765012.jpg0.50 KB

FB_IMG_1748458761485.jpg0.38 KB

FB_IMG_1748458757846.jpg0.36 KB

FB_IMG_1748458753346.jpg0.66 KB

FB_IMG_1748458748153.jpg0.39 KB

FB_IMG_1748458744501.jpg0.38 KB

FB_IMG_1748458768568.jpg0.47 KB

FB_IMG_1748458765012.jpg0.50 KB

FB_IMG_1748458761485.jpg0.38 KB