1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
ለሚሰጡት አገልግሎት ጉቦ የጠየቁ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የቄራዎች ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ ተገልጋዮችን ገንዘብ የጠየቁ ሁለት ተጠርጣሪ አመራሮች ፣ 1ኛ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ ከማል እና 2ኛ ምክትላቸው አቶ እድሪብሳ ማሞ ገንዘብ ካላመጣችሁ አገልግሎት አታገኙም በማለት ፤ እንግልት ሲፈጠሩ ቆይተው በደረሰ ጥቆማ በዛሬው ዕለት ከተገልጋይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተገልጋዬች ተከታትለዉ ለሰጡት ጥቆማ እያመሰገንን ፣ በቀጣይም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ትግል ከጎናችን በመሆን መተባበራችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርብለን።
በቀጣይም ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት የሙስና ተግባራትን ሲመለከት ለ ከንቲባ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ተቀባይ በመጠቆም ሙስናን የመከላከል ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ እናሳስባለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልእክት
የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤
የደም ጠብታ
የላብ ጠብታ
የዕንባ ጠብታ
የውኃ ጠብታ
ድምር ውጤት መሆኑን፣ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል።
Addis Ababa Delegation on Waste Management Knowledge Exchange in Accra
ACCRA, GHANA / ADDIS ABABA, ETHIOPIA – August 24, 2025 – A high-level delegation from the Addis Ababa City Administration, led by Engineer Wondimu Seta, City General Manager with the rank of Deputy Mayor, is on a knowledge exchange visit in Accra, Ghana. The mission focuses on modern solid waste management and liquid waste disposal and treatment.
The delegation includes officials from the Cleaning Management Agency and the Addis Ababa Water and Sewerage Authority, among them Mr. Gezahegn Desisa, Director General of the Cleaning Management Agency. The team is observing recycling and treatment facilities, many run through public-private partnerships, and holding discussions with Ghanaian counterparts.
Engineer Wondimu stressed that the lessons from Accra will be adapted to Addis Ababa’s needs, with strong involvement of private sector partners. He noted the visit supports the Addis Ababa’s effort to ensure sustainable cleanliness and make Addis Ababa a cleaner, more livable city.
For More Information
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የተመራ የልዑካን ቡድን በዘመናዊና ሳይንሳዊ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር እና በፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድና ማጣራት ላይ በጋና አክራ ከተማ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል፡፡
በኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልኡካን ቡድን ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና ከውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የተውጣጡ አመራሮች የተካቱቱበት ሲሆን የልኡካን ቡድኑ በተለይም በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም፣ በፍሻሽ ቆሻሻ አወጋገድ እና ማጣራት ላይ በዘርፉ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በጋና አክራ በመገኘት በመስክ ጉብኝት የተደገፈ የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ እያካሄደ ይገኛል።
የልኡካን ቡድኑ በዚሁ የልምድና የተሞክሮ ልውውጥ በጋና አክራ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የመስክ ጉብኝት ከማካሄድ ጎን ለጎን ከሚመለከታቸው የጋና መንግስት ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት በጉብኝቱና በውይይቱ የተገኙ ልምዶችና ተሞክሮዋችን ከአዲስ አበባ ከተማ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስተሮች በስራው ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የከተማችንን ጽዳት በዘላቂነት ለማስጠበቅና ለነዋሪዎቿ ጽዱ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ እየተከናወነ ላለው ተግባር ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ እና ዘርፉን የሚመሩ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ነሐሴ 18/ 2017 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ጉብኝት:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን ለአሸንዳ ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላት አደረሳችሁ!
አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በክረምት ወራት በልጃገረዶች ከሚከበሩ የአብሮነት ክብረ በዓላት መካከል ናቸው።
ልጃገረዶች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት አምረው፣ በባህላዊ የፀጉር አሰራር ደምቀው እና ተውበው በነፃነት አደባባይ ወጥተው ባህልና አብሮነታቸዉን ሲያሳዩ መመልከት እጅግ አስደሳች ነው።
እነዚህ በአላት በቀጣይም የበለጠ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል።
እንኳን አደረሰን ።
መልካም በዓል ይሁንልን !!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር የከተማ የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮችን፣ ነዋሪዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትን እንዲሁም የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ የፅዳት ንቅናቄ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ ባስተላለፋት መልዕክት በከተማ ደረጃ ‹‹ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ የብክለት መንስኤ ሊሆን አይገባም!›› በሚል ሀሳብ ከተማችንን ጽዱና ውብ ለማድረግ በተጀመረው የ5 ወራት ንቅናቄ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አመላክተው ለውጤቱ መሳካትም በየደረጃው የሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በጽዳት ንቅናቄ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘሁ እንዳሉት ክፍለ ከተማችን ውብ ለነዋሪዎቿ የምትመች ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ካሉ ተግባራት አንዱ የፅዳት ንቅናቄዎች መሆኑን ገልፀው ፅዳትን ባህል በማድረግና በፅዳት ንቅናቄዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዉ
ጽዳትን ህብረተሰቡ የየዕለት ተግባሩ በማድረግ አካባቢውን በማጽዳት ለመጪው ትውልድ ንፁህና ውብ ከተማ የማስረከብ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ጠቁመው፤ ጽዳት የስልጣኔ መገለጫ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የክ/ከተማው ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንየው ዘላለም በበኩላቸው በክረምት ወቅት የውሃ ፍሰት ከፍተኛ በመሆኑ የውሃ መውረጃ ቦዮች ፀድተው ለውሃ መውረጃ ክፍት መሆን ሲገባው በግዴለሽነት ቆሻሻ መጣል ተገቢ አለመሆኑን ጠቁመው፣ ቆሻሻ በዓይነት ተለይቶ በማስወገድ መልሶ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ ዐ7 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃዬ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ጽዱ ውብ እንድትሆን በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን ነዋሪው ጽዳትን ባህል እንዲያደርግ በስፋት ግንዛቤ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰዉ ቆሻሻ በአግባቡ ከተወገደ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ከተማዋን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ምቹና ፅዱ ለማድረግ የሚያስችል የጽዳት ንቅናቄ በኮልፌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ተካሄደ።
የዓለም አቀፍ፣የአፍሪካ እና የካሪቢያን-አፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ለሚካሄደውን ጉባኤ አዲስ አበባ ለእንግዶቿ ምቹና ፅዱ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ለማከናወን የጽዳት ንቅናቄ በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች እና በሁሉም ብሎኮች በዛሬው እለት ተከናውኗል።
በክፍለ ከተማዉ ወረዳ 01 በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄው ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ባስተላለፉት መልእክት የለውጡ ትሩፋት የሆነውን አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ ማድረግ በመቻላችን በርካታ የውጭ ቱሪስት መስህብ ሆናለች እንዲሁም ታላላቅ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶችን ማዘጋጀች መቻሏን አብራርተዉ አሁንም ከፊታችን የሚደረገው የአለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ በከተማችን አዲስ አበባ ስለሚካሄድ ይህንን ታሳቢ ያደረገ የፅዳት ንቅናቄ በሁሉም ወረዳዎች መካሄዱንም ጠቁመዋል።
ከተማችንን ፅዱና ውብ ከማድረግ ባሻገር የክፍለ ከተማችንን ፀጥታ የማስጠበቅ ስራም መጠናከር እንዳለበትም ዋና ስራ አስፈፃሚው መልእክት አስተላልፈዋል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ ጥበበ ሰለሞን በበኩላቸዉ ፅዳትን ባህል በማድረግ ያመጣነው ለውጥ ማስፋት ሁላችንም አከባቢያችን ጽዱ በማድረግ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የሚሰሩ ተግባራትን ማጠናከር እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።
የክፍለ ከተማው የፅዳት አምባሳደር ሻምበል አርቲስት ስዩም ዘለቀ በበኩላቸው አዲስ አበባን ውብና ጽዱ በማድረግ የዓለም አቀፍ፣የአፍሪካ እና የካሪቢያን-አፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ለሚካሄደውን ጉባኤ ተሳታፊዎችን ለመቀበል ኀብረተሰቡን ያሳተፉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው በተካሔደዉ የጽዳት ንቅናቄ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳዉ አመራሮች፣ የጽዳት መዋቅር ባለሞያዎች ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበር፣ ወጣቶችና የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ
ነሐሴ 17/ 2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት ተካሂዷል::
ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ :-በኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ውስጥ የመንግስትና የግል አጋርነት ጽ /ቤት የተፈረመውን ስምምነት ለሚለሙ 30 ፕሮጀክቶች ከ733 ቢሊዬን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ እና 37 አልሚዎችን የሚያካትት በመሆኑ ፤ ልማቱን ዉጤታማ ለማድረግ ካቢኔዉ መርምሮ እንዲያፀድቅ የቀረበለት አጀንዳ በመወያየት ፣ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ፣ የሚፈጥሩት ሰፊ የስራ እድል እና ከተማን ትብብር የማልማት ትልቅ ፋይዳ እና አዲስ አሰራር በመሆኑ ከቢኔው በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አፆድቋል፡፡
2ኛ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ አፈፃፀም ደንብ በተመለከተ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ጥራት ያለው ሥልጠና ለመስጠት፣ ኮሌጆችን ውጤታማ ከማድረግ እና በተደራጀ አግባብ ለመምራት በሚያስችል መልኩ የደንቡ መውጣት እገዛው የጎላ በመሆኑ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ በከተማችን ያስገነባናቸውን የገበያ ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎች ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
አዲስ አበባ እንደ ስሟ እያበበች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጐብኚዎቿ ሳቢ ሆናለች።
በቀድምዋ አዲስ አበባ ይከናወኑ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ኩነቶች በመጡ ቁጥር የከተማዋን የተጎሳቆሉ ገፅታዎች ፣ የተበከሉ አካባቢዎች ፣ አንገት አስደፊ ገፅታዎች በጥቅሉ ገመናችንን ሌሎች እንዳያዩት በረጃጅም ባነር የመሸፈን ታሪክ በልጆቿ የሌት ተቀን ትጋትና በነዋሪዎቿ ትብብር ታሪክ ሆኗል ።
ዛሬ ከማለዳዉ አንስቶ ከአራዳ ጀምረን፣ በሜክሲኮ ፣ በለገሀር እና ሳር ቤት የአፍሪካ ህብረት አካባቢ የከተማችንን ገፅታ ይበልጥ የሚያሻሽሉ ፣ ለወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያሳለጡ ፣ የሚያዘምኑ የአካባቢዎቹን ዉበት የሚጨምሩ ፕሮጀክቶችን ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
ለአብነትም አራዳ( ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ) እና ፓርኪንግን እንዲሁም አፍሪካ ህብረት ጋር ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ፣ ፓርኪንግና የህፃናት መዝናኛ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።
የአፍሪካ ህብረት የገበያ ማዕከልና ፓርኪንግ የተሰራዉ ለዲፕሎማሲዉ ማህበረሰብ የተለያዩ የስጦታና የባህል መሸጫዎችን በአቅራቢያዉ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን በ28,500 m2 ላይ የተገነባ ዘመናዊ ማዕከል ነዉ፣ሁለት ቤዝመንትና ፕላዛ ፣ 250 ሱቆች እና 250 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይችላል ፣ በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻ እና ማረፍያዎች 45 መጋዘንና የመጸዳጃ ክፍሎች ፣ ፋውንቴይን ፣ አምፊ ቴአትር እና ፕላዛ አሉት።
ሌላኛዉ ባሻ ወልዴ ችሎት ጋ የተሰራዉ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያና ገበያ ማዕከል ሲሆን፣ በተመሳሳይ ካፍቴሪያዎች ፣ሱፐርማርኬት ፣ሱቆች ፣ሬስቶራንቶች ፣ ፕላዛ እና 200 የመኪና ማቆሚያ በውስጡ የያዘ ነዉ።
ሁለቱም ማእከላት ዘመናዊ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያና፤ የደህንነት ካሜራ ተገጥመውለታል ፣ ለህፃናት ፣ለአቅመ ደካምችና አረጋዉያን ምቹ እና አካታች መሰረተ ልማት ነዉ።
በጥቅሉ ከሜክሲኮ እስከ ለገሃር እና አፍሪካ ህብረት ዙሪያ ባሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ 13 የመኪና ማቆሚና 10 ተርሚናሎች እስከ 3769 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ የፓርኪንግ እና ተርሚናል መሰረተ ልማቶች ጭምር ይገኙበታል ።
እነኚህ ለከተማችን እድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች በታለመላቸዉ ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ ሌት ተቀን ለደገፋችሁ አመራሮች ፣ ባለሙያዎችና የየአካባቢዉ ማህበረሰብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
