ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов

በቴክኖሎጂ የዘመነው የመዲናችን የአደጋ መከላከል የጥሪ ማእከልና ፈጣን ምላሽ ሰጪነት ተግባር በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉… See more

photo content
+4

በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር በ2017 በጀት አመት የካቢኔ አባል ካልሆኑ 25 ተቋማት መካከል ለሥራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ተጠሪ የሆኑት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የላቀ የስራ አፈፃፀም በማምጣት 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል። በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህ የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በጋራ አመራር የመስጠት ሚናን በማጎልበት፣ በፍፁም የስራ መሰጠት፣ ትጋት እና እንዲሁም የከተማችንን ነዋሪዎች በማገልገል ፅኑ ፍላጎት ለተጋችሁ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የመዲናችን ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ሁሉ እንኳን ደስ አለን/ ደስ አላችሁ ብለዋል። በዚህ በጀት አመት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሁለቱ ተቋማቶቻችን ያስመዘገቡት ይህ የላቀ ውጤት ለሚቀጥለው በጀት አመት ህዝባችንን ከዚህ በበለጠ ጠንካራ አላማ እና የስራ ትብብር፣ ለስራ መሠጠት፣ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ለማሳካት እንደ መስፈንጠሪያ የሚያነቃቃንና የበለጠ ውጤት እንድናስመዝግብ የሚያግዘን እንደሚሆን ፅኑ እምነት አለኝ በማለት የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+2

photo content
+7

photo content
+4

photo content
+4

photo content
+3

photo content
+5

ከተማችን አዲስ አበባን የሚመጥን ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በላቀ ብቃት አንደ ምንገነባ አንጠራጠርም ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት እና ክፍለ ከተሞች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል። ቢሮአችን የከተማዋን ሁሉን አቀፍ አንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ መረጃ በፍጥነት እንዲደርስ በማድረግ በኩል ላሳየው ላቅ ያለ አፈጻጸም የተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት ህዝባችን ብቁ በከተማው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን ጥራት ያለው መረጃ በመስጠት ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት አሁንም በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን። "አምና በስኬት ላይ ነበርን፤ዘንድሮም በስኬት ላይ ሆነናል፤ወደፊትም በስኬት ላይ ስኬት እየተጎናፀፍን ለከተማችን ሁለተናዊ ፈጣን እድገት በመረጃው ዘርፍ መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ እንዲሳካ ላደረጋችሁ በየደረጃው የምትገኙ የኮሙኒኬሽን አመራሮች ፣ስራተኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በሙሉ ድሉ የእናንተም ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ከሁሉም በላይ ማከናወንን የሰጠን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን በ2017 በጀት ዓመት የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እውቅናና ሽልማት አበርክተናል። በዚሁም መሰረት፦ የካቢኔ አባል ከሆኑ ቢሮዎች፦ 1ኛ. የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ 2ኛ. ሠላምና ፀጥታ ቢሮ 3ኛ ፋይናንስ ቢሮ 4ኛ. ትምህርት ቢሮ 5ኛ. ኮሚኒዩኬሽን ቢሮ ከክፍለ ከተሞች፦ 1ኛ. ቦሌ 2ኛ. አቃቂ ቃሊቲ 2ኛ. ለሚ ኩራ 3ኛ. ኮልፌ ቀራኒዮ የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት፦ 1ኛ. የደንብ ማስከበር ባለስልጣን 2ኛ. የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን 3ኛ. የመንገዶች ባለስልጣን 4ኛ. የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት ኤጀንሲ 5ኛ. የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆኑ፤ እንዲሁም 33 ወረዳዎች ተሸላሚ ሆነዋል። እውቅናና ሽልማቱ የሁሉም አመራር፣ በየደረጃው ያሉ ባለሞያዎች፣ የባለድርሻ አካላት እና አብሮን ለሰራዉ ህዝባችን የተሰጠ ሲሆን ይህም ይበልጥ ሰርተን የህዝባችንን የመልማት ፍላጎት የምናሳካበት እንጂ የሚያዘናጋን አይደለም። በመሆኑም፤ እውቅናው በቀጣይ በጀት ዓመት አልቀን በመስራት የህዝባችንን ተጠቃሚነት እንድናረጋግጥ ትልቅ አደራም ጭምር ነው። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አብረን አቀድን ፣ አብረን ሰርተን፣ አብረን ውጤት አምጥተናል ! ባለፉት ቀናት ስናካሂድ የነበረው የከተማችን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት አጠናቅቀናል። በግምገማችንም የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን በማላቅ እና የተለዩ ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተግባብተናል ። ከተማችን በሁሉም ዘርፍ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሀገራዊና አህጉራዊ ብሎም አለምአ ቀፋዊ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ፤ ስሟና ግብሯ የተናበበ ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንደምንቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ጤናዉ የተጠበቀ ፣ አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመዉ ብልፅግና ወሳኝ ነዉ። ዛሬ ማለዳ መላዉ አመራራችን ከ2017 አመታዊ የስራ ግምገማችን እና እቅድ ዉይይት ጎን ለጎን የማስ ስፓርት አከናዉነናል ። በትጋት ወደ ስኬት! ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን አመራር ያሳተፈ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መካሄዱን ቀጥሏል። የግምገማ መድረኩ መሰረታዊ ጭብጦች፦ 👉የአመራር ውህደት እና ቅንጅት በከተማዋ ለተመዘገቡ እመርታዎች መሰረት መሆኑ፤ 👉ከማዕከል እስከ ወረዳ እና ቀጠና ያለው የፓርቲ እና መንግሥት አመራር በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራታቸዉ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤ 👉በተለይም በአመራሩ መካከል ያለው ጤናማ የውድድር መንፈስና የላቀ የስራ ተነሳሽነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤ 👉በማህበራዊ ጉዳዮች በተለይም በትምህርት እና ጤና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤቶች መኖራቸውን፤ 👉ከኢኮኖሚ አኳያም በርካታ ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የሴቶች እና ወጣቶች ተጠቃሚነትን በስፋት ማሳደግ መቻሉን 👉አምራቾችና ሸማቾችን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችሉ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት አገልግሎት ውስጥ ማስገባት በመቻሉ የገበያ ትስስርን በማሳለጥ የህዝባችንን የኑሮ ጫና ማቅለል መቻሉ፤ 👉ከፍተኛ የገቢ አሰባሰብ አቅም በመፍጠርና ከተሰበሰበዉ አጠቃላይ ገቢ 71 በመቶ ያህሉን ለዘላቂ ልማቶችና የድህነት ቅነሳ ተግባራት በማዋል የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉ፤ 👉የኮሪደር ልማቱ የፈጠረው የከተማ ውበት ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍሰት ፣ የማኑፋክቸሪግ ዘርፉ መነቃቃት ፣ 👉የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በመንግሥትና በህዝብ የተባበረ ክንድ እውን በማድረግ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሰላማዊ እና ለጎብኚዎቿ ጭምር ምርጥ መዳረሻ መሆን መቻሏ፤ የከተማዉ ነዋሪ ከመቼውም ጊዜ በላቀ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአካባቢ የልማት ስራዎችን በመስራት ይበልጥ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱ ወዘተ... በግምገማ መድረኩ የተነሱ ዋነኛ የትኩረት ማዕከላት ሆነዉ ቀጥለዋል ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን! ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምረናል። የ2017 በጀት ዓመት ከመቼውም የበለጠ ስኬት ያስመዘገብንበት ነው ፤ የእቅድ አፈፃፀማችን 95 በመቶ ተሳክቷል። መዲናችንን ለሀገር ክብር የምትመጥን፣ እንደ ስሟ “ውብ አበባ" ለማድረግ በኮሪደር ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻ ልማት ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ እና የገቢ እቅድን በማሳካትና ያገኘነውን ገቢ በቁጠባና ብክነትን በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ በማዋል ዙሪያ በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል። በሁሉም ስራዎቻችን ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ቀጣይነትን ያረጋገጥንበት፣ የበጀት ጉድለትን በህብረተሰብ ተሳትፎና በጐ አገልግሎት እየሞላን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በመስራት ውጤታማ የሆንበት በጀት ዓመት ነው። ለነዚህ ሁሉ ስኬቶች አብራችሁን የለፋችሁ፣ ከራሳችሁ በላይ ህዝባችንን ያስቀደማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች እና የደከማችሁና ውጤት ያስመዘገባችሁ አመራሮቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ከልብ እናመሰግናችኋለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ዛሬ ትዉልድ ላይ የምናደርገው ኢንቨስትመንት እና የምንዘራው መልካም ዘር ነገ በብዙ እጥፍ ይከፍለናል።… See more

photo content
+6

የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በፅኑ መሰረት ላይ የሚጥል ነው።" ኢ/ር ወንድሙ ሴታ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ ፣ የክ/ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ መምህራን እንዲሁም የክ/ከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶችን መገንባት መቻሉንና የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት በበጀት ዓመቱ በርካታ በጀት በመመደብ ትምህርት ቤቶችና የአይሲቲና ሌሎች የትምህርት መሰረተ ልማት መገንባት መቻሉንና በዚህም የተማሪ ጥምርታን በመቀነስ ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን አንስተው የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በፅኑ መሰረት ላይ የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በክፍለ ከተማው ልማትን ባህል በማድረግ በርካታ ትልልቅ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በማህበረሰቡና በባለሀብቱ ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ጥራት ፣ ፍትሀዊ ተደራሽነትና ለማረጋገጥ በ2017 በጀት ዓመቱ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስመረቅ መቻሉንና አንስተው ህብረተሰብም ሆነ ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቶቹ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ሊንከባከባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል ። በመጨረሻም ከምርቃት መርሃ-ግብሩ ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል ፕሮግራም ተካሂዷል። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager