1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በከተማ ውበት ጽዳት እና አረንጓዴ ልማት የተሠሩ ሞዴል ሥራዎች ተመረቁ።
በወረዳው በሞዴልነት በተለዩ ሶስት ብሎኮች የመንገድ አካፋዮችን የማስዋብ እንዲሁም የጽዳትና አካባቢ ልማት ሥራዎች የተመረቁ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶቹን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ ናቸው::
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በዚሁ.ወቅት ባደረጉት ንግግር አዲስ አበባ ውብ ጽዱና ምቹ ከተማ እንድትሆን የከተማ አስተዳደሩ ሰፊ ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል::
የቦሌ ክፍለ ከተማ በዘርፉ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እያከናወነ ያለው ተግባር ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
በወረዳ 1 የተከናወኑት የጽዳትና ከተማ ውበት ሥራዎች የሚደነቁ እንደሆኑ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዚህ ሥራ ላይ በመሳተፍ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሰይፉ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በ4ኛው ዙር የ90 ቀናት ዕቅድ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የጽዳትና ከተማ ውበት ሥራዎች እንደሚገኙበት አውስተዋል::
በወረዳው የተከናውኑት ሞዴል የጽዳትና ውበት ሥራዎች ውብና ጽዱ ክፍለ ከተማ ለመፍጠር እየተደረገ ባለው ርብርብ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ለመሆናቸው ማሳያ መሆናቸውን አመልክተዋል።
Bole Communication- ቦሌ
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት አዲስ ተቋማዊ የሰራተኛ ደንብ ልብስ አስተዋወቀ።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ እንደተናገሩት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ከልደት እስከ ሞት ድረስ ያለውን የሰዎች መረጃ በማደራጀት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ተቋሙን በማዘመንና በመደገፍ ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።
የክ/ከተማው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ በበኩላቸው ተቋሙ ያስተዋወቀው የደንብ ልብስ በመልበስና በቅንነት በማገልገል ለሌሎች ተቋማትም እንደ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለው ተቋሙን ለማዘመን እየሰሩ ያሉ አካላትን አመስግነዋል ።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ ጽ/ቤቱ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ ሰራተኞችን የደንብ ልብስ በመልበስ እና ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተናግረው በቀጣይም ከብልሹ አሰራር የጸዳ ዘመናዊ አገልግሎት እንሰጣለን ብለዋል።
በመጨረሻም የተሻለ የስራ አፈጻጸም ለነበራቸው የክ/ከተማ ፣የወረዳ ባለሙያዎች የምስጋናና የቦንድ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን እንዲሁም ከጽ/ቤቱ ጋር በቅንጅት ሲሰሩ ለነበሩ ተቋማት የዕውቀትና ሽልማት ተሰጥቷል።
ለፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎች እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አያለ በአሉ የሰላም ፣የጤና ፣የመተሳሰብና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል::
እንኳን ለ1445ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ!
በዓሉ የሰላም፣ በወንድማማችነትና በእህታማማችነት የደመቀ አንድነት የምናዳብርበት እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ ኢድ ሙባረክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኢድ አልፈጥር በአል የቅድመ ክፍያ የካርድ መሙላት አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት
ከዚህ በታች የተጠቀሱት ናቸው::
ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 9 (ሃያት)
ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 6 (ወሰን)
ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 7 (ካሳንቺስ)
ሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 2 (አራት ኪሎ)
ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 9 (አቃቂ)
ደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 10 (ለቡ)
ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 1 (ልደታ)
ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ቁጥር 2 (አየርጤና)
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇?Addis Ababa City Manager's OfficeGER1
Telgram:-
??👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
Boost this post to reach up to 11068 more people if you spend $14.
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኢድ አልፈጥር በአል ያለምንም አደጋ ክስተት በሰላም እንዲከበር አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን በመለየት በተለያዩ አማራጮች የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፈ እንደሚገኝ ገልፆ
በዓሉ ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ እንዲከበር ከኮሚሽን መ/ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉም አሳስቧል።
ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ፈጥነዉ እንዲያሳውቁም የሚከተሉትን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል::
የማዕከል መረጃ
939 ወይም 011-1-55-53-00
011-1-56-86-01
አራዳ ቅርንጫፍ
011-1-56-02-49
011-1-56-02-50
ቂርቆስ ቅርንጫፍ
011-4-66-34-20
011-4-66-34-21
አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ
011-2-76-91-45
011-2-76-91-46
ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ
011-4-42-55-63
011-4-42-55-64
አቃቂ ቅርንጫፍ
011-4-34-00-96
011-4-34-30-63
ቦሌ ቅርንጫፍ
011-6-63-03-73
011-6-63-03-74
ኮልፌ ቅርንጫፍ
011-3-69-60-85
011-8-69-68-69
ጉለሌ ቅርንጫፍ
011-2-73-07-31
011-2-73-06-53
ለሚኩራ ቅርንጫፍ
011-6-68-08-46
011-6-68-07-60
ልደታ ቅርንጫፍ
011-5-58-95-33
011-5-58-9043
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
1445 ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በኡመር መስጊድ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ::
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 1445ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ በኡመር መስጊድ በአንድ ማዕከል የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ፣ የወረዳ 13 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ኩመል እና የወረዳ 1 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ወልዴን ጨምሮ ከፍተኛ የሀይማኖት አባቶ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈውበታል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ!
የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04፣06 እና 07 አስተዳደሮች በጋራ በኢማም አህመድ አልጋዚ መስጅድ መድረሳ የ3ቱም ወረዳ ነዋሪዎች፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራስኪያጅ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ፣የክፍለ ከተማው ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተፈራ፣የ3ቱም ወረዳ አስተባባሪዎች እና አመራሮች፣የፅዳት ማህበራት፣የስጅዱ አስተባባሪዎች ፣በተገኙበት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ ለሙስሊም እምነት ተከታዮች እንኳን 1445ኛ ጊዜ ለሚከበረው ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳቹ በማለት በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የፅዳት ማህበራት፣ የ3ቱም ወረዳ አመራሮች እና ነዎሪዎች በአስተዳደሩ ስም አመስግነው ፅዳት ባህላችን በማድረግ አካባቢያችን ፅዱ እና ማራኪ ማድረግ አለብን ብለዋል።አክለውም እውነተኛ የሀይማኖት መቻቻል የታየበት የፅዳት ዘመቻ መሆኑ ገልፀው ሌሎችም በዓላት ላይ በጋራ ተባብረን ከተማችን ውብ እና ማራኪ ማድረግ አለብን ብለዋል።
በመጨረሻም የመስጅዱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብድልፈታ ግራኝ በዚህ ፅዳት ለተሳተፉ የክ/ከተማ አመራሮች የ3ቱም ወረዳ አስተባባሪዎች፣አመራሮች ፣የፅዳት ማህበራት እና ነዋሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ አያለ በአሉ የሰላም ፣የጤና ፣የመተሳሰብና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል::
የረመዳን ፆምና የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠውና የመረዳዳትና የአብሮነት ምሳሌ ነው" በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን
የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ በሚከበርበት ስቴዲየም ዙሪያ በዛሬው እለት መጋቢት 30/2016 የፅዳት ዘመቻ ተካሄዷል።
የፅዳት ተግባሩን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን የታላቁ ረመዳን ፆም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠውና የመረዳዳት ምሳሌ መሆኑን ጠቅሰው የእምነቱ ተከታዮች ይህንን በጎ ተግባር በመፈፀም ከፈጣሪ ዘንድ ታላቅ በረከትን እያገኙበት አሳልፈዋል ብለዋል።
አክለውም የታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ፣ በኢትዮጵያዊነት ገመድ የሚያስተሳስረን ታላቁ እሴታችን ነውም ብለዋል።
ወይዘሮ ሂክማ "እኛ ኢትዮጵያውያን አንድነታችን የጥንካሬያችን መሰረት፣ መተሳሰባችን ያቆራኘን ኢትዮጵያዊ ማሰርያችን፣ መከባበራችን የአብሮ መኖራችን ሚስጥርና መለያችን ሆኖ ዘመናትን ተሻግረናል ፤ ትውልዱም ይህንን ድንቅ ጥበብና ሚስጥር ይዞ እንዲቀጥልም እንሰራለን" ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍታለው ከፍያለው ታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል ከሀይማኖት መገለጫነቱ ባሻገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኩራት መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ በሰላም ሲከበር አንድነታችንን ያጠናክራልና በልዩ ትኩረት ልናከብረው ይገባል ምክንያቱም አንዳችን ያለአንዳችን ድምቀት የለንምና ብለዋል።
በፅዳቱ ላይ የተገኙት የተለያየ እምነት ተከታይ አባቶችና የፅዳት አምባሳደሮችም የእስልምና እምነት የአብሮነትና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉን በትብብርና በአንድነት በማክበርም የነበረውን ኢትዮጵያዊ ትስስራችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።
ዛሬ ማክበሪያ ቦታውን እንዳፀዳንም ክፋትንና የመለያየት ዘርንም ከውስጣችን ልናፀዳ ይገባል ያሉት የሀይማኖት አባቶቹ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህ የፅዳት ንቅናቄ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የከተማና የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::
