ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
“በመትከል ማንሰራራት!” አዲስ አበባ መትከል ጀምራለች። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content

photo content
+9

ፅዱ፥ ውብ እና ደህንነቷ የተጠበቀች አዲስ አበባ!” በሚል መሪ ቃል የ90 ቀናት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተግበሪያ እና የ"ፅዱ ኢትዮጵያን" በመዲናችን ይፋዊ የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ:- በመዲናችን ፅዳት እና በአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ተፅእኖ ፈጣሪዎች የእውቅናና ሽልማት መርሐግብር በምስል:- ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+7

መዲናችን አዲስ አበባ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችውን አስደማሚ ስኬት እና የከተማችን ስማርት ሲቲ ኢኒሼቲቭ ለማሳካት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ ። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ይህን ያስገነዘቡት በዛሬው ኦለት በአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር አዳራሽ ከአራት ሺህ በላይ የከተማዋ ነዎሪዎች በታደሙበት "ፅዱ፣ ውብ እና ደህንነቷ የተጠበቀች አዲስ አበባ!” በሚል መሪ ቃል የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተግበሪያ እና የ"ፅዱ ኢትዮጵያን" በመዲናችን ይፋዊ የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ የመክፈቻ ስነስርአት በተካሄደበት ወቅት ነው። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረኩ እንደተናገሩት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እና በጎ ፈቃድ የ90 ቀናት የንቅናቄ ግብ ንፁህ እና ውብ አዲስ አበባ መፍጠር፣ቆሻሻን ተረማምደን የማናልፍበት አዲስ አበባን፣ ልጆቻችን በሰላም የሚጫወቱባት፣ጽዳት፣ ውበትና ምቹ እና ተስማሚ መኖሪያ የህዝባችን ወሳኝ እና የሚገባ አጀንዳ የሚሆንባት ከተማ መፍጠር ነው ብለዋል። አዲስ አበባ በፍጥነት እያደገች፣አዳዲስ ሕንፃዎች እየተገነቡ ያለባት፣መንገዶችም እየተስፋፉ ያለባት ከተማ እንደሆነች ገልፀዉ በመንገዶቻችን ላይ ዛፎች የተደረደሩባት፣ ወንዞቻችን ያለ ቆሻሻ የሚፈሱባት፣ ህዝባችን ደህንነቱ ተጠብቆ በሰላም የሚኖሩባት፣ቀንና ሌሊት ደህንነቷ የተጠበቀች ከተማ እንድትሆን በትኩረት መስራት ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል። አክለዉም መንገዶቻችንን፣ የወንዞች ዳርቻዎች፣ የተዘጉ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በዚህ በ90 ቀንናት ሁሉንም በማጽዳት፣ ህገ-ወጥ የቆሻሻ መጣያ ቦታዎችን በማፅዳት እንዲሁም በካይ ቆሻሻዎችን በማስወገድ በምትካቸው ዛፎችን በመትከል አረንጓዴ ቦታዎችን ማልማትና ማብዛት ይገባናል ብለዋል። አኢንጅነር ወንድሙ አያይዘውም የጀመርነዉን ይህንን የለዉጥ ጉዞ በቀጣይም አብረን በምንሰራቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ከተማችንን የበለጠ የምናስዉብበትና አካባቢያችንን በብርሃን የምንቀይርበት፣ ምቹ ያልነበሩ መንገዶችን የምናስተካክልበት እንዲሁም የከተማችንን መሰረታዊ አገልግሎቶችን የምናሻሽልበት ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የከተማችንን ስማርት ሲቲ ኢኒሼቲቭ ከማሳካት እያንዳንዱን የከተማችን ነዋሪ በፋይዳ መመዝገብ አንዱ መለኪያ መሆኑን ጠቅሰዉ የዚህ የ90 ቀን የንቅናቄ አጀንዳዎች ከቃል የዘለለ የከተማችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ ሲሉ አመልክቸው ሁሉም እዚህ መድረክ የተገኘ አካል በጋራ በመስራት የተለወጠች እና ምቹ አዲስ አበባን ለትዉልድ በመፍጠር ለቀጣዩ ትዉልድ ምቹ አዲስ አበባን ልናወርስ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በበጀት አመቱ በፅዳትና በአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና ተፅእኖ ፈጣሪዎች የእውቅናና ሽልማት የመስጠት ስነ ስርዓት ተካሂዷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

"ፅዱ፥ ውብ እና ደህንነቷ የተጠበቀች አዲስ አበባ!” በሚል መሪ ቃል የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተግበሪያ እና የ"ፅዱ ኢትዮጵያን" ንቅናቄ መርሀ ግብር ከደቂቃዋች በኋላ ይጀመራል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

በሚሊኒየም አዳራሽ ተከስቶ የነበረው የዕሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል ትናንት ምሽት 4:00 ሰዓት ገደማ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከስቶ የነበረው የዕሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ ኮሚሽን ገልጿል። በአደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት አደጋ አልደረሰም። ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናደርሳችኋለን። ሰኔ 21/ 2017 AMN-Addis Media Network ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+7

የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትርፋቶችን ያስገኘ ስራ ነው። በዚህ ዓመት ከሚተከለው ችግኝ ጋር ከ47.5 ቢሊየን ገደማ እንደርሳለን። ይህም በሚቀጥለው ዓመት ከምንተክለው ጋር ሲደመር 54 ቢሊየን ልንደርስ ያስችለናል። በዚህ መርሃ ግብር ያመናችሁ፣የተሳተፋችሁ እጆቻችሁ ጭቃ የነካ፥ የተከላችሁ፥ የተንከባከባችሁ ኢትዮጵያውያን፣በኢትዮጵያ የምትገኙ ዲፕሎማቶች፣ይህንን ህልም የደገፋችሁ የየትኛው ሃገር ዜጎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፥ እንኳን ደስ ያለን ልላችሁ እወዳለሁ። ከነገ ጀምሮ በየዕለቱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

በዛሬው ዕለት ከተማ አቀፍ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በይፋ አስጀምረናል። ከለውጡ ወዲህ የበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት የአንድ ወቅት የንቅናቄ ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሌ ተግባር እና ባህል ማድረግን ታሳቢ በማድረግ ተቋም መስርተን፣ ተቋማዊ አሰራርን በመዘርጋት ባከናወንነው ስራ የሚሊዮኖች እንባ ታብሷል። በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትም የበርካቶች እምባ የሚታበስበት፣ ለአቅመ ደካሞች 2,500 ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች በመገንባት የዘመሙ ጎጆዎች የሚቃኑበት፣ ለ500,000 ሰዎች ማዕድ በማጋራት የክረምት የኑሮ ጫናን ማለፍ የምናስችልበት፣ ወላጅ የሌላቸዉ 440 ህፃናት አሳዳጊና ተንከባካቢ ቤተሰቦች የሚያገኙበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ከተማችንን አረንጓዴ የምናለብስበት እና ሌሎች በርካታ ስራዎችን የምንሰራበት አያሌ ዝርዝር ተግባራትን ያቀፈ ነው። በምሳሌነት የምንገልጻችሁ የከተማችን ባለሀብቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተቋማት በሙሉ በተለመደው መልኩ በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ እና በእውቀታችሁ አብራችሁን እንድትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ እስካሁን ላበረከታችሁት ታሪካዊ አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

#ዜና_ሹመት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የጥናትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታከለ ደሲሳ በአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ የፕሮጀክትና ላንድፊል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለአቶ ታከለ ደሲሳ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

#ዜና_ሹመት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የጥናትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታከለ ደሲሳ በአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አሰተዳደር ኤጀንሲ የፕሮጀክትና ላንድፊል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ለአቶ ታከለ ደሲሳ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት

photo content
+7

ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:50 ገደማ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7 ሱሉልታ ፍተሻ ጣቢያ ከመድረሱ በፊት ባለዉ ቁልቁለት መንገድ ላይ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ እንደ ኮሚሽኑ ገለፃ አደጋው የደረሰው ከባድ ጭነት ጭኖ ይጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ የጫነዉ ጭነት ተሳፋሪ ጭኖ ወደ ሱሉልታ ይጓዝ በነበረዉ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በመወደቁ ነዉ። በአደጋዉ በሚኒባስ ታክሲ ዉስጥ የነበሩ አራት ተሳፋሪዎች ህይወታቸዉ ማለፉን የገለፀው ኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወታቸዉ ያለፈዉን ሰዎች ከሰባት ሰዓታት ጥረት በኋላ የሟቾቹን አስከሬን ከተጫናቸዉ ጭነትና ከተሽከርካሪ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። የሟቾችን አስከሬን ለማዉጣት የኮሚሽኑ እና የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ክሬኖች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን በሂደቱም የአዲስ አበባ ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አመራርና አባላት ድጋፍ አድርገዋል ብሏል።

photo content
+5