ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
photo content
+7

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋን እንደሚከላከል ተገለጸ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራአመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፈረንሳይ አቦ ፀበል ጀርባ በተዘጋጀዉ ስፍራ ላይ ዛሬ ሀምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ችግኝ በመትከል አሻራቸዉን አኑረዋል። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ -ግብር ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጾ ያለዉ በመሆኑ ኮሚሽን መ/ቤቱ ከተሰጠዉ ተልዕኮ አኳያ የችግኝ መትከልና መንከባከብ መርሀ -ግብር ስራን በልዩ ትኩረት እንደሚተገብር አስታዉቀዋል። በዚሁ መርሀ -ግብር ላይ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ ተራማጅ ተረፈ በበኩላቸዉ ባደረጉት ንግግር የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች የሰዉን ህይወትና ንብረት ከማዳን ተልዕኮአቸዉ ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርም የኩላቸውን የላቀ ሚና እየተወጡ በመሆኑ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል። በመርሃግብሩ ላይ የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ተወካዮች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች ተሳትፈዋል፡፡ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ አስመልክቶ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ!

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት " ይህ የሁላችንም ጉዳይ ነው" በሚል ርእስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኤፍኤም 98. 1 ጋር በመተባበር የሚያቀርብላችሁ ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም 2ኛውን ክፍል እነሆ ብለናል ። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የፖሊሲ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የፖሊሲ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

photo content

በኤሌክትሪክ አጠቃቀም ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች:- ማንኛውም ደንበኛ ከቆጣሪ በኋላ በቤት ውስጥ የሚከናወኑ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዎችን በቂ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎችና ደረጃቸውን በጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች መከናወናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ በቤት ውስጥ ሆነ ከቤት ውጪ የምንጠቀምባቸው ማንኛውም የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ከህፃናት ዕይታ ማራቅ እንደሚገባ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ለጊዜው የማንጠቀምባቸውን የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከሶኬት አላቆ ማስቀመጥ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለኤሌክትሪክ አደጋ ስጋት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማስወገድ፤ እርጥበት እና እርጥበት አዘል ሁኔታዎችን ከኤሌክትሪክ አካባቢ ማስወገድ ይጠበቃል፡፡ ትክክለኛ እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ የቤት ውስጥ የመስመር ዝርጋታ በሚከናወንበት ወቅት ቅድሚያ ኤሌክትሪክ ከቆጣሪ ማቋረጥ እንዲሁም ሁሌም በጥንቃቄ እና ሀሳብን ሰብስቦ ስራውን በትኩረት ማከናወን ይገባል፡፡ ጥንቃቄ ሁሌም ለራስ ነውና፤ በኤሌክትሪክ አጠቃቀም ወቅት ሁሌም ተገቢውን ጥንቃቄ ተግባራዊ እንድናደርግ መልዕክታችን እናቀርባለን፡፡ Addis Ababa Region Electric Utility የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በሴን ወንዝ ************ በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በሴን ወንዝ ላይ በጀልባ በመንቀሳቀስ ትዕይንት ሲያቀርብ
+6
የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በሴን ወንዝ ************ በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ቡድን በሴን ወንዝ ላይ በጀልባ በመንቀሳቀስ ትዕይንት ሲያቀርብ Ethiopian Broadcasting Corporation

በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታወጀ ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች
+1
በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታወጀ ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።

photo content

photo content
+9

photo content
+9

በ2016 የበጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የክፍለ ከተማና የወረዳ የስራ አስኪያጅ ፅ /ቤቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው። ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ስኬት የበኩላቸውን ድጋፍ እና አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትም ዋንጫና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል። በዛሬው እለት ሐምሌ 18 ቀን በተካሄደው የ2016አ.ም የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ / ቤት የማጠቃለያ የሴክተር ጉባኤ ላይ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ የዋንጫ፣የሰርቲፊኬት እና የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በዚሁ መድረክ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 11 የወረዳ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤቶች ለእያንዳንዳቸው የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና የዴስክቶፕ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። ከክ/ ከተሞች ከ1- 3 ደረጃ ከወጡት በተጨማሪ ቀሪዎቹ እጅግ በተቀራረበ ደረጃ ውጤታማ አፈጻጸም ያስመዘገቡ በመሆናቸው ዋንጫና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል። በዚሁ መድረክ በከተማዋ ጽዳት፣ በአደጋ መከላከል እና በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ዘርፎች ስኬታማነት ድጋፍና እገዛ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ለሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችም በስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት እውቅናና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል። የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ባዘጋጀው በዚህ የእውቅና መድረክ ላይ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የዋና ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ እስማኤል፣ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ ር እሸቱ ለማ እና የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ሽልማቱን በመስጠት መልእክትም አስተላልፈዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬቶ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ለተጎዱት ወገኖቻችን የእርዳታ ድጋፍ በማድረግ እንተባበር። በጥሬ ገንዘብ ለመርዳት የምትፈልጉ የክልሉ መስተዳድር የከፈተዉን የባንክ ሂሳብ ቁጥር የምናሳዉቃችሁ ይሆናል። በአይነት ድጋፍ መስጠት ለምትፈልጉ በየክፍለከተማው ለዚሁ ዓላማ በሚዘጋጁ ስፍራዎች በመገኘት መርዳት ትችላችሁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+3

በ2016 በጀት ዓመት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አመርቂ ውጤት ተገኝቷል፡- የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን የበጀት ዓመቱን አፈፃፀም እየገመገመ ነው። በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አመርቂ ውጤት የተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል። የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪነት መታወቂያን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በከተማዋ የሚከሰቱ አደጋዎችን አስቀድም መከላከል እንዲቻል በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት መገኘቱንም ገልጸዋል። ከተማዋ ውብ ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ በየጊዜው የጽዳት ተግባራትን በማከናወን ነዋሪው ጽዳትን ባህሉ እንዲያደርገው አበረታች ስራዎች መከናወኑን ገልፀዋል። በኤሌክትሪክም አገልግሎት አንጻርም በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ጥረት የተደረገበት መሆኑን ምክትል ስራ አስኪያጇ አብራርተዋል። በቴከኖሎጂ ተደግፈው የሚሰጡ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በመጨመራቸው እና ቅንጅታዊ አሰራሮች በመሳለጣቸው ምክንያት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን እርካታን ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

photo content
+6

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2016 በጀት አመት የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤውን በዛሬው እለት እያካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወጎኖቻችን የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በዚሁ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የየዘርፍ ሃላፊዎች፣ የክፍለከተማ እና የወረዳ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየታደሙ ይገኛሉ። በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ መድረኩን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረዋል። በጉባኤው የ2016 በጀት አመት አጠቃላይ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የእቅድ አፈፈፃፀም እና የ2017 በጀት አመት እቅድና ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።