1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሳምንታዊ ከተማ አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ከወረዳ 8 አስተዳደር ጋር በመተባበር የ5 ወር የበጋ ፅዳት ንቅናቄና "አካባቢያችንን በማፅዳት ጽዱና ውብ የሆነች ከተማን እንፍጠር"በሚል መልእክት በወረዳው ጬፌ ኮንደሚኒየም አካባቢ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ መረሃ-ግብር አካሂዷል ።
በመረሃ-ግብሩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገቡ ይስማው፣የክ/ከተማው ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋኪሀ ሸሪፍ እና የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ 8 አስተዳደር አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች ፣የፀጥታ አሰከባሪ አካላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገቡ ይስማው እና የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማናዬ ጫኔ እንዲሁም የወረዳ 8 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይናለም ግርማ በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ጽዳት ለጤናማ ህይወትና አኗኗር መሰረትና የዘመናዊነት መገለጫ መሆኑን በመጠቆም ጽዱ፣ውብና ለኑሮ ምቹ የሆኑ አካባቢዎች መፍጠር የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የአካባቢያችንን ፅዳት መጠበቅ የዘወትር ባህልና ልምድ በማድረግ በንፅህና ጉድለት ምክንያት ከሚከሰቱ በሽታዎች እራሳችንንና ማህበረሰባችንን መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ሀላፊዎቹ አያይዘውም በቀጣይም የፅዳት ስራዎቻችን የከተማዋን ውበት ለመጠበቅ ከተጀመሩ የንቅናቄ ስራዎች ጋር በማስተሳሰር መስራትና የወንዞች ዳርቻና የፍሻሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በማጽዳት በጎርፍ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችና ስጋቶችን መከላከል ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተጠቁመዋል ።
በመጨረሻም በወረዳው በመልሶ መጠቀም የተዘጋጁ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ቀርበው በተሳታፊዎች የተጎበኙ ሲሆን ቆሻሻን በአግባቡ በመለየትና በማስተዳደር በመልሶ መጠቀም ዑደት ከተጠቀምንበት ትልቅ ሀብት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባልም ተብለዋል።
ግንቦት 3 ቀን 2016
በአራዳ ክ/ከተማ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ ተቋማትና ብሎኮች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዛሬው እለት ግንቦት 3 / 2016 አ.ም በተካሄደው የጽዳት ንቅናቄ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አማካሪ ወ/ሮ ሃዳስ ኪዱ፣ የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ፣ የወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ ሌሎች የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎችና ነዋሪዎች በፅዳት መርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።
እኔ የአካባቢዬ የጽዳት ባለቤት ነኝ" በሚል መሪ ቃል ሳምንታዊ ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 "እኔ የአካባቢዬ የፅዳት ባለቤት ነኝ" በሚል መሪ ቃል ሳምንታዊ ከተማ አቀፍ የጽዳት ንቅነቄ ዘመቻ ተካሂዷል፡፡
በጽዳት ንቅናቄው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኃላፊ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ እና ውብ እና ከሌሎች የአለም ከተሞች ተወዳዳሪ በማድረግ ነዋሪዎቿ አካባቢያቸውንና ጤንነታቸው የተጠበቀ በአስተሳሰብ የበለፀጉ በኢኮኖሚ ያደጉ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደተናገሩት ጽዳት የአንድ ወቅት ስራ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራችን በማድረግና አካባቢያችንን በንፅህና በመያዝ ጽዱ ውብ አካባቢን ለትውልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ በጎ ፈቃደኞችና ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት የመስመር ማዛወር ስራ ተጠናቀቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሪደር ልማት የኤሌትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በመስመር ማዛወር ስራው ወቅት የልማት ተናሺ ለነበሩ 2 ሺ 700 ደንበኞች በአዲስ መልክ በሰፈሩበት አካባቢ አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ ተከናውኗል፡፡
የኃይል መስመር ማዛወር ስራው አጠቃላይ 68 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪሜ የመካከለኛ እና 18 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ መደረጉን የከተማው ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ሳምንታዊው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሂደ።
በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚካሄደው ብሎክን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሃግብር በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች እስከ ብሎክ ድረስ የዘለቀ የፅዳት ንቅናቄ ከማለዳው 12:30 ጀምሮ በሁሉም ከ/ከተሞች የተካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ 24 ማዞሪያ አካባቢ በድምቀት ተካሂዷል።
በየሳምንቱ በሚካሄዱ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች ብቻ የአካባቢ ፅዳት አይጠበቅም ያሉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ፅዳትን ባህል አድርጎ የአካባቢን ፅዳት ማስጠበቅ እንደሚገባ አመልክተዋል።
አካባቢያችንን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን ዳግም የቆሻሻ መጣያ ቦታ እንዳይሆኑ ነዋሪው በባለቤትነት መጠበቅ ይኖርበታልም ብለዋል::
ዋና ዳይሬክተሩ አከለውም ባለፉት አመታት የከተማዋን ፅዳት ለማስጠበቅ በተደረጉ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ተጨባጭ ለውጥ መምጣት መቻሉን ገልፀዋል።
የን/ስልክ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ በበኩላቸው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ!" በሚል መሪ ቃል ከብክለት የፀዳች ከተማን ለመፍጠር የተጀመረውን ከተማ አቀፍ ንቅናቄ ለማሳካት ሁሉም ህብረተሰብ እና ባለድርሻ አካል በቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በፅዳት ስራው ላይ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች : የፀጥታ አካላት : የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት : አጠቃላይ የመዋቅሩ ሰራተኞች : ባለድርሻ አካላት እና የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ተሳትፈዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+8
አዲስ አበባ ከተማ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲካሄድ የነበረው የትራንስፎርሜሽናል እቅድ ዝግጅት ወርክሾፕ ተጠናቅቋል::
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማችን ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲያስችል በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በቤቶች አቅርቦት ፣ በመሬት ልማትና አስተዳደር፣ በገቢ አሰባሰብ እና በትራንስፖርት ለውጥ አምጪ የሆኑ ግቦች ላይ በተደረገው ውይይት መሰረት በቀጣይ ልዩ ትኩረት አድርገን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል::
ከንቲባ አዳነች አክለውም ከወርክሾፑ ባገኘነው ግብዓት ፣ በደረስንበት ተግባቦት ልክ እና ለመረጠን ህዝብ በገባነው ቃል መሰረት ጥያቄዎችን ለመመለስ በቀጣይ ድጋፍ እያደረጉ ካሉ ባለድርሻ አካላት ፣ ከከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም ከሌሎች ተባባሪ አካላት ሁሉ ጋር በመቀናጀት ለውጤታማነታቸው 24/7 እንተጋለን ብለዋል::
በቅድመ አደጋ ጥንቃቄ ዙሪያ (ከእሳት አደጋ: ከኤሌክትሪክ እና ከጎርፍ አደጋ) ጋር በተያያዘ የህይወት ተሞክሮ የጥንቃቄ መልእክት የተላለፈበት" ህልም ነጣቂው" በሚል ርእስ ተዘጋጅቶ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የተላለፈ ትምህርታዊ ዶክዩመንታሪ ዝግጅት እንድትከታተሉት በአክብሮት ተጋብዛችሁዋል::
ዋርካ | የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሠራር ላይ ያተኮረ ዝግጅት - ክፍል አንድ
+7
ዛሬ የከተማ አስተዳደራችን ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክሾፕ ማካሄድ ጀምረናል።
በወርክሾፑ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በሚያስችሉ በተመረጡ ስድስት አጀንዳዎች ላይ ስልጠና የሚሰጥ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት የሚከናወን ሲሆን በስልጠናው ዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ለአመራራችን ስልጠናዎችን ይሰጣሉ።
ሃገራችንን ለማበልጸግ በሁሉም ዘርፍ ያለ እረፍት መስራታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
+9
አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ እየሰራናቸው ካሉ ስራዎቻችን መካከል አንዱ በሆነው የኮሪደር ልማት ስራ ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም አመራሮች ጋር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተገኝተን አበረታተናቸዋል።
በዚህ የኮሪደር ልማት በተለወጠው አዲሱ የስራ ባሕላችን መሠረት፣ በዓላትን ጨምሮ 24/7 በሚመሩ፣ በሚያስተባብሩ እንዲሁም በሚሰሩ ትጉህ ሰራተኞች በሀገራችን አይተነው የማናውቀውን የስራ ቅልጥፍና፣ ጥራትና ውጤት ተመልክተናል።
መንገዶቻችን ለእግረኛ፣ ለሞተር አልባ ተሽከርካሪ እና ለብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት የተመቹ እንዲሆኑ፤ የህዝብ የጋራ መገልገያ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት፤ ጽዱ፣ ለመኖር ምቹ፣ አረንጓዴ እና ውብ አዲስ አበባን ለመገንባት በፕላናችን መሠረት ዲዛይን ከማዘጋጀት እስከ ግንባታ ድረስ ያለውን ስራ በላቀ የኃላፊነት ስሜት፣ የሙያ ብቃትና ትጋት እየመራችሁና እያስተባበራችሁ ያላችሁ አመራሮች፣ መሀንዲሶች፣ ባለሙያዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም ለስራ የተመቻቸ ዓውድ ለመፍጠር በንቃት የተሳተፋችሁ የጸጥታ አካላት እኛ ብቻ ሳንሆን የከተማችሁ ነዋሪዎችም ያመሰግኗቹኋል።
ተባብረን የማይገፋ የመሰለውን ተግዳሮት እየተሻገርን ከተማችንን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በመዲናችን የትንሳኤ በአል ማግስት ፅዳት ምን ይመስላል?ቀጣዩን ቪዲዮ ይከታተሉ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በመዲናዋ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት የጎላ አደጋ ሳይከሰት ተከብሯል
በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ሕብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።
ኮማሽኑ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በበአሉ ዋዜማ በተከሰተ የእሳት አደጋ ሕይወቱ ካለፈ አንድ ግለሰብ ውጪ ሌላ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አልደረሰም።
ቅዳሜ ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጄነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሰራተኛ በጄነሬተሩ ላይ በተነሳ እሳት ወዲያው ሕይወቱ ማለፉሞ ተመልክቷል።
ይሁን እንጅ በበዓል ወቅት ሊኖር ከሚችለው የአደጋ ተጋላጭነትና ስፋት አኳያ አደጋዎች አለመከሰታቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል።
ኮሚሽኑ ከበዓሉ አስቀድሞ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት መከናወኑም መግለጫው አስታውሷል።
ኮሚሽኑ ማህበረሰቡ የቅድመ አደጋ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ መተግበሩ በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሶ ለዚህም በመግለጫው ምስጋና አቅርቧል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
