1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
ከሁሉም በፊት የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!
ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ማጠናቀቅን ባህል ያደረገችው አዲስ አበባ ዛሬም ተጨማሪ ብስራት ለነዋሪዎቿ እነሆ ብላለች!!
ከአራት ኪሎ ፣ ቀበና እስከ ኬኒያ ኤምባሲ ያለው መንገድ በኮሪደር ልማት ስራችን አልምተን እና አስውበን ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት እንዲውል ክፍት ያደረግን ሲሆን ይህም ሶስተኛው ያጠናቀቅነው ስራችን ነው::
አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ በማድረግ ዓለም-አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር መንዝረን ምቹ የእግረኛ መንገዶችን ፣ የሞተር አልባ(ብስክሌት) መንገዶች ፣ ምቹ የታክሲ/ባስ ማውረጃና መጫኛ ስፍራዎችን ፣ የመኪና ፓርኪንጎችን ፣ አረንጏዴ ስፍራዎችን ፣ የመንገድ ዳርቻ ማረፊያ መቀመጫዎችን ፣ የህዝብ መናፈሻዎችን ፣ የከተማዋን ስታንዳርድ የሚመጥኑ መብራቶችንና ፉዋፉዋቴዎችን ባጠረ ጊዜ ገንብተን አዲስ አበባ ከተማን 24 ሰዓት የደራችና ከቆሻሻ በእጅጉ እየጸዳች ያለች ከተማ አድርገናል::
የኮሪደር ልማት ስራን የሰራንባቸው አካባቢዎች የተሳለጠ ትራንስፖርትና ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር በተጨማሪ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠሩ እና 24/7 በመስራት አዲስ የስራ ባህል በማስተዋወቅ ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን አለምአቀፍ ተወዳዳሪ የሆነች ዘመናዊ ከተማ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::
ይህ የኮሪደር ስራ እውን እንዲሆን ፕሮጀክቶቹን በመከታተል የደገፋችሁ፣ በትጋት ያስተባበራችሁ፣ ከሁሉ በላይ በእልህ አስጨራሽ ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ በትዕግስት ከጎናችን በመቆም የደገፋችሁን በተለይም መሬታችሁን ለልማት የለቀቃችሁ ፣ ከመኖሪያ አካባቢያችሁ ያዘዋወርናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በቀና ትብብራችሁ እና ከራስ በላይ ለትውልድ ዘላቂ ልማት በማሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድናሳካው አቅም ስለሆናችሁን እጅግ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: አዲስ አበባ ታመሰግናችኃለች::
በኮሪደር ልማት ያጌጠች በዲጂታል አገልግሎት የዘመነች ለመኖር ምቹ ከተማ -አዲስ አበባ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በጋራ የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅት መርሐ ግብር አካሄዱ
**************************
የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ በሚል መሪ ቃል በዘንድሮው ዓመት የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለየት የሚያደርገው ችግኞቹን በራሳችን አቅም አዘጋጅተን መትከላችን ነው ብለዋል የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሰምሃል ገብረመድህን የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ዝግጅቱን ባስጀመሩበት ወቅት
ወይዘሮ ሰምሃል አክለውም የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶክተር) ሀሳብ የሆነውን 6ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከአገልግሎታችሁ ጎን ለጎን ለመደገፍ የወጣችሁ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል ።
የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ መርሐ ግብሩ 6ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ብለዋል የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሃዲ ረሺድ
በዚህ በሁለተኛው የአርበኝነት መርሐ ግብር ላይ መሳተፍ ትልቅ እድለኝነት ነው ያሉት አቶ አብድልሃዲ ይህንን ተነሳሽነት በአገልግሎት ዘርፉም መድገም ያስፈልጋል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ተድባባ ማርያም አየናቸው፣ የወረዳ 04 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ናሆም መንግስቱን ጨምሮ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የእሳት አደጋ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተገኝተዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
'የምትተክል ሃገር የሚያፀና ትውልድ!"
🌴 የ50ሺ ችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ ጉድጓድ ቁፋሮ ተካሄደ🌱
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት በአቃቂ / ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩንቨርስቲ የ2ኛ ምእራፍ 6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ለማኖር የሚያስችለውን የጉድጎድ ቁፋሮ አካሄደ::
በፕሮግራሙ ላይ የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በም/ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ እንደተናገሩት እንደ ፅ/ቤት በያዝነው ክረምት ከ50 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል እየተረባረብን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም አረንጓዴ አሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያግዝ እና የአካባቢ መራቆትን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ ጽ/ቤቱ ከተልእኮው ጋር የሚጣጣመውን ይህን ግዙፍ ተግባር በተጠናከረ ሁኔታ በስኬታማነት እንደሚያጠናቅቀው አመልክተዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
"የምትተክል ሃገር፣ የሚያጸና ትውልድ!"
ዛሬ ማለዳ የ5ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በከተማችን ከሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አትሌቶች፣ የተለያዩ ስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን አስጀምረናል።
አረንጓዴና ውብ አካባቢን ለመፍጠር፣ በተፈጥሮ የበለጸገችና ከአየር ብክለት የፀዳች አዲስ አበባን ለትውልዱ ለማዉረስ ቃላችንን በተግባር መንዝረን ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባደረግነው ርብርብ የከተማችንን አረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለናል።
በኮሪደር ልማታችንም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ስንተክል ከርመናል።
ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎቻችን የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ እድሜ፣ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዲሁም ሃይማኖት ሳይገድባቸው የከተማዋን ተፈጥሯዊ ሚዛን መጠበቅ የሚችሉ ሀገር በቀል ዛፎችን፣ ለገፅታ ድምቀት የሚሆኑ የውበት እፅዋቶችን እንዲሁም የአትክልትና የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
ዘንድሮም በከተማችን 20 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ለመስራት የተዘጋጀን ሲሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ላይ በመሳተፍ ለትውልድ የሚሆን አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የዲጂታል አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ 800 ዘመናዊ ኮምፒውተሮችን ለወረዳ ጽ/ቤቶቹ አሰራጨ
ኤጀንሲው በተቋም ግንባታ ፕሮግራሙ የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ ዋነኛው የትኩረት መስክ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
በዚህ ዕቅድ ውስጥ አንዱ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻልን ታሳቢ ያደረጉ በሁሉም ክ/ከተሞች የሚገኙ ወረዳዎችን ሙሉ ለሙሉ በልዩ ኔትዎርክ የማስተሳሰር፣ በዋና መስርያ ቤት ቁጥጥር ስር የሚሆን የካሜራ ስርዓት ዝርጋታ መተግበር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በፕሮጀክት ተይዘው መቋጫ ላይ ደርሰዋል።
የዲጂታላይዜሽን ደረጃን ለማሳደግ በወረዳ ጽ/ቤቶቻችን ያሉ የኮምፒውተር ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሰረተ ልየታ እጅግ ዘመናዊ ኮምፒውተሮች ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ግዢ በማከናወን ከተቋሙ ሲስተም ውጭ ሌላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተቆልፎ 800 ኮምፒውተሮች ለ119 ወረዳዎች ስርጭት ተደርጓል።
በዕለቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የከተማ ምክትል ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች ዶክተር ቱሉ ጥላሁን /ስማርት ሲቲ ዘርፍ/ እና አቶ የማነ ደሳለኝ /ልማት ዘርፍ/ በተገኙበት የርክክብ መርሃ ግብር ለክ/ከተሞች ተከውኗል።
ተቋሙ በ119 ወረዳዎች ሲያክናውን የነበረው የመሰረት ልማት ስራ ማጠናቀቂያ የሆነው በሁሉም ወረዳ የተገጠሙ ካሜራዎች የሙከራ ስርጭት እና ተያያዥ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ዋና ዳይሬክተሩ በቀሪ ሁለት ሳምንታት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ፕሮጀክቱ እንደሚመረቅ ገልፀዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የማሽነሪ ኦኘሬተሮችን አስመረቀ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአሽከርካሪዎች ማስልጠኛ ማዕከል ለአደጋ ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የተዘጋጀዉን የቲዮሪና የተግባር ስልጠናቸዉን ያጠናቀቁ የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ሰልጣኞችን ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም አስመርቋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በምረቃው ላይ እንደተናገሩት የዛሬ ተመራቂዎች የሰዉን ህይወትና ንብረት ከአደጋ ለመታደግ በሚደረገዉ ጥረት ትልቁን ኃላፊነት የተሸከማችሁ በመሆኑ በስልጠና ቆይታችሁ ያገኛችሁትን ዕዉቀት ክህሎት በጥብቅ ስነ-ምግባር እንድትፈጽሙ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ ብለዋል።
የማሰልጠኛ ማዕከሉ ኃላፊ ኮማንደር አለማየሁ ጦፉ በኩላቸዉ እንደተናገሩት በዛሬዉ ዕለት የተመረቁት ማሽን ኦፕሬተሮች በማሰልጠኛ ማዕከሉ የተሰጣቸዉን የቲዮሪና የተግባር ስልጠና በተገቢዉ ያጠናቀቁና በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የተዘጋጀዉን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና አልፈዉ የመንጃ ፈቃድ እንደተሰጣቸዉ አብራርተዋል።
በዛሬዉ ዕለት ለምረቃ የበቁት ማሽን ኦፕሬተሮች
ቁጥራቸዉ 21 ሲሆን ተመራቂዎቹ ከኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽ ዘርፍ የተመረጡ እንደሆነ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኮሚሽን መ/ቤቱ አመራሮችና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የተገኙ ሲሆን ተመራቂዎችም ለታዳሚዎች ትርዒት አቅርበዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ኤጀንሲው ሁለት የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኞቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ገለጸ።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምርያ ጋር በመቀናጀት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆኑ ሁለት ተጠርጣሪዎች በ2015ዓ.ም ኢትዮጵያዊ ላልሆነ ግለሰብ የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ መስጠታቸው ከተቋሙ የዲጂታል ምዝገባ ሲስተም ላይ በወጣ መረጃ በመረጋገጡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ኤጀንሲው በተያዘው ሳምንት የቀሪ ወረዳዎችን መሰረተ ልማት በማሟላት የተቋሙን አገልግሎት በሁሉም ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የትኛውም የዲጂታል ምዝገባ የተመዝጋቢው እና መዝጋቢ መረጃዎች በቋት ላይ የሚቀመጥ መሆኑ ሌብነትን ለማጋለጥ ምቹ ሁኔታን መፈጠሩንም አመልክቷል።
ኤጀንሲው ነዋሪዎች ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ እራሳችሁን ጠብቁ ሲል መልእክቱን አስተላልፎ መሰል ሁኔታዎች በአገልግሎት ላይ ሲያጋጥም በ7533 የነፃ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ እንደሚቻል አመልክቷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
