ru
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Открыть в Telegram
1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
ዛሬ "ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና ባህል ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና" በሚል መርህ ሀሳብ ከአዲስ አበባ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያይተናል። ከለውጡ ወዲህ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አዲስ አበባ ከተማ በገዢው ፓርቲና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው የፖለቲካ እሳቤ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሀገራዊ እና በከተማ አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተግባቦት እየፈጠርን ተቀራርበን የመስራት ባህል እየገነባን ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥት ስልጣንን ለመጨበጥ በህዝብ ይሁንታ ምርጫን ማሸነፍ እንዳለባቸው የሚታወቅ ቢሆንም፣ ፓርቲያችን ብልጽግና ስልጣን ከያዘ በኋላ አዲስ እና የላቀ የፖለቲካ ባህል መለማመድ አለብን ከሚል ቁርጠኛ አቋማችን የተነሳ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግሥት ካቢኔ ውስጥ ጭምር እንዲካተቱ ተደርገው አብረን በመስራት አዲስ የፓለቲካ ባህልን በተጨባጭ እየገነባን ነዉ። በከተማችን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል ላከናወናቸው በርካታ የልማት ስራዎች አበረታተዉ፣ ይበልጥ ልናተኮርባቸው በሚገቡን ጉዳዮች ዙሪያም ገንቢ አስተያየቶች ሰንዝረዉ የተለያዩ የህዝቡን ፍላጐቶች መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። እኛም እንደ ከተማ አስተዳደር የጀመርነውን አዎንታዊ መስተጋብር ማሳለጥ እንዲሁም የህዝቡን ፍላጐቶች መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በፍጥነት እና በጥራት መስራትን አጠናክረን እንደምቀጥል አረጋግጠንላቸዋል። በመጨረሻም የፖለቲካ ምህዳርን ይበልጥ እያሰፋን ለሀገር ሰላም እና ልማት የሚጠቅሙ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በትብብር እና በጋራ መስራተችንን አጠናክረን ለመቀጠል መግባባት ላይ ደርሰናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+2

photo content
+9

"የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው የገጠር ኮሪደር በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው። በዛሬው እለትም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንቢጣ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን አስጀምረናል። ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ሲሆኑ አርሶ አደሩም ጤናማና ክብር ያለው ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው። በአካባቢው ከ2 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጎርፍና ድርቅ አደጋ ይታወቅ የነበረውን አካባቢ የልማት ተምሳሌት ያደርገዋል"። ጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ምሽት በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት የኢትዮጵያን ታላቁን የክብር ኒሻን ለቢል ጌትስ ሸልመዋል። ይኽ የከበረ ሽልማት የጌትስ ፋውንዴሽን ባለፉት 25 አመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸ… See more

ከስጋት ነጻ እንሆናለን የሚል ተስፋ ሰንቀናል" ለአመታት የጎርፍ ስጋት ጥያቄ ሆኖባቸው የቆየው የውሀ መውረጃ ቱቦ ግንባታ በመጀመሩ ተስፋ የሰነቁት ነዋሪዎች

"እፎይታ አግኝተናል" ክረምት በመጣ ቁጥር በርካታ ጉዳት ሲያደርሱባቸው የነበሩ ወንዞች ላይ ድልድይ በመሰራቱ እፎይታ ያገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ነዋሪዎች… See more

የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት የመዲናዋን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት ስጋት ለመቅረፍ እየተሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነ…

photo content
+9

photo content

ፈጣንና ተለዋዋጭ በሆነው የዲጂታል የመረጃ ዘመን የአጀንዳ የበላይነትን በመያዝ ቀጣይነት ላለው የልማት ስራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የድህረ እውነታ ዘመንን በእውቀት ተረድቶ መስራት ይጠይቃል- አቶ ተፈራ ሞላ በስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት እና ተጠሪ ተቋማት ላሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የሚዲያ እና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን ለማጠናከር የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋና ስራ እና የስራ አስኪያጅ የልዩ ወረዳው ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ሞላ የድህረ እውነታ ዘመን የሚጠይቀውን የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አውድ በሚገባ በመረዳት፣ ነጣጣይ ትርክቶችን በመመከት፣ የዘርፉ ተዋንያን ሀገረ መንግስት ከማፅናትና የጋራ አሳበሳቢ ትርክት የበላይነት እንዲይዝ ከማድረግ አኳያ ገንቢ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል። አክለውም ለዚህም ዘርፉ በተጠናከረ እውቀትና እውነት እየተመራ ያለበትን የአሰራር ስርአት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡ የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት በም/ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ ከሀሰተኛ መረጃ ሊጠበቅ የሚችልበትን በእውነትና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ትክክለኛ እና ምክንያታዊነትን የሚያጎለብቱ መረጃዎችን በስፋት የሚዳረሱበትን አማራጮችን እና አውታሮችን በይበልጥ በማጠናከር ረገድ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ዘመኑ የድህረ እውነት ዘመን መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ይሄን የሚመጥን ሙያዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ ፅኑ ትግልና ዝግጁነትን መላበስ እንደሚገባም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሚዲያ አማራጮች የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚገባ በመመከት እና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከትክክለኛው ምንጭ እንዲያገኝ በማድረግ በመዋቅራችን የተቀናጀ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ በእውቀትና በእውነት ላይ ተመስርተን በተናበበ አጀንዳና መልእክት ላይ መስራት ይገባል ሲሉም ገልፀዋል። በመድረኩ ላይ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የቀውስ ጊዜ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ማንዋል ለውይይት የቀረበ ሲሆን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትች እና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ላይም ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+8

መቀመጫውን ጋና ያደረገው እና በዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ የካበተ ልምድ ያለው የጆስፖንግ ግሩፕ ኩባንያ ልኡካን ቡድን አባላት በመዲናችን ባደረጉት ቆይታ ግዙፉን እና ታሪካዊውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል። የልኡካን ቡድኑ በጉብኝታቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ገለፃ ተደርጎላቸዋል። የልኡካን ቡድኑ አባላትም የአፍሪካ ህብረት መዲና፣ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት መቀመጫ እና የዲፕሎማሲ ማእከልና መናኸሪያ በሆነችው አዲስ አበባ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ አስደናቂ የሆነው የአድዋ ድል ክስተት መታሰቢያነት ይህን የመሰለ ግዙፍ እና ማራኪ ሙዚየም መገንባቱ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካውያን እና በዓለም ዙሪያ ሁሉ ያሉ የመላዉ የጥቁር ሕዝቦች አርማ በመሆኑ ሁሌም በትዉልድ መካከል ሲዘከር እንዲኖር የድሉ መታሰቢያ የሆነውን የአድዋ ድል ሙዚየምን በስፍራው ተገኝተው በመጎብኘታቸውም የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+7

"ቱቦዎች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ቃል የፅዳት ንቅናቄ ተካሔደ :፡ የክፍለ ከተማው ፅዳት አስተዳደር በወረዳ 01 ከቻይና ካንፕ እስከ አየር ጤና ድረስ "ቱቦዎች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል፡፡ በንቅናቄው የተገኙት የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ ህብረተሰቡ የአካባቢ ፅዳትን ባህሉ እንዲያደርግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው መጪው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የፍሳሽ ማስገጃ ቱቦዎችና የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት መጠበቅ እንደሚገባና ከህግ ተጠያቂነት እራስንም ማዳን እንደሚገባም አሳስበዋል። የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥበበ ሰለሞን ፅዳትን የዘውትር ተግባር በማድረግ አካባቢያችንን ከብክለት መታደግ አለብን ያሉ ሲሆን የፍሳሽ ቱቦዎችን በቆሻሻ ተሞልተው አካባቢያችን እንዳይበክሉ በፅዳት መጠበቅና ክረምቱን ተከትሎ የሚመጣውን የጎርፍ አደጋ መቀነስ እንደሚገባ ገልፀዋል። "ቱቦዎች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም"በሚል የተዘጋጀው የጽዳት ንቅናቄ በቀጣይ ለ5 ወራት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል። Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+9