1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
እኔ የከተማዬ የጽዳት ባለቤት ነኝ" በሚል መሪ ቃል የጽዳትና የመንገድ ዳር ማስዋብ መርሃ ግብር ተከናወነ።
የካቲት 16/2016:-በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የከተማ "እኔ የከተማዬ የጽዳት ባለቤት ነኝ" በሚል መሪ ቃል ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት እንዲሁም ጽዳት አስተዳደር በጋራ በመሆን የጽዳትና የመንገድ ዳር ማስዋብ መርሃ ግብር አካሄዷል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመገኘት ንቅናቄውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ይመኙሻል ታደሰ የጽዳት ስራ የግለሰቦች ብቻ ሳይሆን የሁሉም የማህበረሰብ ውጤት ነው ብለዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የከተማ የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ በእለቱ እንደገለጹት መንገድ ዳርን በማስዋብ የክፍለ ከተማችንን ብሎም የከተማችን ዜጎች የአኗኗር ሁኔታን በመቀየር ረገድ አስተዋጿቸው ከፍተኛ ነውና በስፋት እየተሠራ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል ።
የጽ/ቤት ኃላፊው አያይዘውም የአረንጓዴ ልማት ስራዎች በበዙ ቁጥር ዜጎች በንጹህና አረንጓዴ ስፍራ እንደፈለጉ ንጹህ አየር ለማግኘትና ለመዝናናት ይጠቀሙባቸዋል ብለው ፤ የተጀመረውን የማስዋብ ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለሀብቶችና በጎ ፍቃደኞች ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ጎን በመቆም የበኩላችሁን አሻራ እንድታስቀምጡ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
ህብረተሰቡ የተለያዩ በካይ ቆሻሻዎችን በማስወገድ ውብና ጽዱ አካባቢን መፍጠር እንዳለበት ተገለጸ።
ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ ፕሮግራም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ተካሄዷል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ በመገኘት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ጽዳት የሁልጊዜ ተግባራችን በመሆኑ የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ውብና ጽዱ ጉለሌን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ገልጸው ህብረተሰቡ አካባቢውን በማጽዳት የድርሻውን ማበርከት አለበት ብለዋል።
በጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማ እና ወረዳው አመራሮች ፣ የወረዳው ነዋሪዎች፣የፀጥታ አካላት እንዲሁም የጽዳት ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡፧
Gullele communication
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የከተማ አስተዳደሩ በግማሽ ዓመቱ ከተቋም ግንባታ አንፃር ያከናወናቸው ዋና ስራዎች፡-
---------------
👉 የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ከአሰራር ጋር በተያያዘ ህዝብን እያማረሩ ያሉ እና ተቋማዊ አደረጃጃት ሪፎርም የሚያስፈልጋቸውን በጥናት በመለየት በ16 ተቋማት በአሰራር የማዘመን፣ ግልፅ የሆነ የአሰራር ስታንዳርድና መስፈርቶችን ለመተግበር የሚችሉ የሪፎርም ስራ ተከናውኗል፣
👉 በነዚህ ተቋሞች የሚገኙ ከ19 ሺህ በላይ የሚሆኑ የመንግስት ሠራተኞችን ሙያዊ ብቃት ለመለየት የሚያስችል ባሕሪያዊና ቴክኒካዊ ፈተና በገለልተኛ ተቋማት የብቃት ምዘና መስጠት ተችሏል፣
👉 በግማሽ ዓመቱ ለ28,984 አመራሮችና ባለሙያዎች ክፍተትን መሠረት ያደረገ የክህሎትና የባሕሪ ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፣
👉 ለ371 አመራርና ባለሙያዎች ራሳቸውን እንዲያበቁ የረጅም ግዜ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ተደርጓል፣
👉 በተጨማሪም በማዕከል፣ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ላይ ያለውን የሰው ሀብት ለማመጣጠን የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና ሪፎርም ውስጥ ባሉ ተቋማት ላይ የሰው ሀብት ቁጥሩ ከ60 በመቶ ያነሰ እንዳይሆን ለማድረግ ሌላው በወረዳና ክ/ከተማ እንዲመደብ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ወደ ተግባር ተገብቷል፣
👉 በከተማችን ሌብነትና ብልሹ አሰራር ትግል ላይ ከፍተኛ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመገረጉ በማዕከል 520፣ በክ/ከተማ 110 እንዲሁም በወረዳ 736 በድምሩ 1ሺ 366 አመራርና ሰራተኛን ተጠያቂ ማድረግ ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በዛሬው እለት የካቲት 26/ 2016 አ.ም ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ በ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚያደርግና በልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው እለት 3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዛሬ ስብሰባው የከተማዋን አጠቃላይ ልማት እና ሁለንተናዊ እድገት እንዲሁም የነዋሪውን አዳጊ ፍላጎቶች ታሳቢ ያደረጉ ጉዳይ ላይ ተወያይቷል።
ካቢኔው አዲስ አበባ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥን የመንገድ ልማት ኮሪደሮችን ለመገንባት የሚያስችል እቅድ ላይ የተወያየ ሲሆን የከተማዋን አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል የመንገድ ኮሪደር እና የአካባቢ ልማቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህ መሠረት የሚለሙት የመንገድ ኮሪደሮች የሚከተሉት ይሆናሉ:-
- ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ.ሜትር)
- ከቦሌ አየር መንገድ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ (4.9 ኪ.ሜትር)
- ከመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ በአራት ኪሎ በኩል የአድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ.ሜትር)
- ከፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙርያ፣ በለገ-ሃር ሜክሲኮ፣ በሳርቤት በኩል እስከ ወሎሰፈር (10 ኪ.ሜትር) ናቸው።
እነዚህ የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ሁለንተናዊ የመንገድ ዘመናዊነት ያሟሉ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማችንን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው።
የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ የሳይክልና ሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የከተማዋን ማስተር ፕላን እና አርባን ዲዛይን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሁም ለከተማዋ እጅግ ዘመናዊ የትራንስፖርት ፍሰት የሚያጎናፅፉ መሆኑ ታምኖበታል።
በተጨማሪም አስፈላጊ በሆኑ የኮሪደሩ ቦታዎች ላይ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ተሸጋጋሪ ድልድዮች፣ ማሳለጫዎች እና ሰፋፊ መጋቢ መንገዶችን ያቀፈ ሲሆን የከማ አረንጓዴ ልማትን ያካተተ እንደሚሆንም ታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔም የቀረበውን የመንገድ ኮሪደር ልማት እቅድ በጥልቀት መርምሮ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን ከነገው እለት ጀምሮ ወደ ስራ እንዲገባና ልዩ ክትትል እንዲደረግለት ወስኗል።
ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ነው"
አቶ ደረስ ፈጠነ:- የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የትምህርት ቤት የፅዳት ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ዘመቻ በደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አካሂዷል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲሳ አራርሳ በመሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፅዳት የሁል ጊዜ ስራ በመሆኑ ተማሪዎች የሚማሩበትን ትምህርት ቤት በማፅዳት እና የፅዳትን ጠቀሜታ ለወላጆቻቸው ማስገንዘብ አልባቸው። ስስሥ
ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረስ ፈጠነ ተማሪዎች የሚማሩበትን ት/ቤት እና የሚኖሩበትን አካባቢ ፅዳት ማስጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን በማጠናከር እና በተቀናጀ ተቋማዊ አሰራር የተጀመሩ ለውጦችን የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤
-------
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በቆየውና በትላንትናው እለት በተጠናቀቀው የከተማ አስተዳደሩ የሰባት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ከከተማ አስከ ወረዳ ያሉ የከተማው አመራር መዋቅር የተሳተፈበት ሲሆን፣ የበጀት ዓመቱ ዓመቱ የሰባት ወራት አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት ያለፉት ሰባት ወራት በርካታ ያሳካናቸው እና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች የሰራንባቸው የመሆናቸውን ያህል በዚህ ሳንረካ አሁንም በትኩረት ልንሰራለው የሚገቡ በርካታ ቁልፍ ስራዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
ባለፉት ሰባት ወራት በከተማዋ የተመዘገቡ ስኬቶች እና ተጨባጭ ውጤቶች ሊመጡ የቻሉት በየደረጃው ያለው የከተማዋ አመራር በአስተሳሰብ እና በተግባር አንድ ሆኖ እና ህዝቡን አስተባብሮ በመስራቱ ነውም ብለዋል።
በዚህም የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማረጋገጥ፣ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ፣ የሰው ተኮር ስራዎች በማሳካት፣ የከተማዋን ባለሀብት በማሳተፍ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ማስፋት፣ የኑሮ ውድነትን ከማቃላል እና ከከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት አንፃር ያስመዘገብነው አውንታዊ ውጤት ማሳያ ነውም ብለዋል።
ሆኖም አሁንም ርብርቦችን የሚጠይቁ የከተማዋ ቁልፍ ስራዎች በማለት ልዩ አፅኖት ከሰጧቸው ስራዎች መካከል የተጀመሩ የቋማት ሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለመረጠን ህዝብ የምንሰጠውን አገልግሎት ማሻሻል እና የተገልጋይ እርካታን በውጤት ማረጋገጥ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በልህቀት በመከወን፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ማጠናቀቅና የከተማዋን አጠቃላይ መሠረተ ልማት ማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ስራዎችን በትኩረት ማከናወን እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ አበክረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
የሁሉም ሥራ መለኪያ ውጤት እንጂ ሂደት አይደለም ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ በቀሩን የበጀት ዓመቱ ወራት ውስጥ በግምገማ መድረኩ መሠረት መላው የከተማ አስተዳደሩ አመራር በትጋትና በቅንጅት በመስራት የሚለካ እና ለውጥ የሚያመጣ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳት አደጋ ፎረም ኮሚቴ ለጎርፍ ተጋላጭ ተብለው በአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ከተለዩ 29 ቦታዎች መካከል በከፍተኛ ሁኔታ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ 6 ቦታዎች ለቅድመ መከላከያ ስራ ያመች ዘንድ ያሉበትን ሁኔታ ተዟዙሮ ምልከታ አካሂዷል።
በምልከታው ወቅት ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገለፁት በተደጋጋሚ ጊዜ በጎርፍ አደጋ ቤት ንብረታቸው ለውድመትና ለብልሽት መጋለጡን ገልፀው የሚመለከተው አካል ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ እና የእሳትና አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አቃ/ቃ/ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር ተስፋዬ ሞናሴ ኮሚቴው በምልከታው የቦታዎቹን በጎርፍ ተጋላጭነት መመልከት መቻላቸውን ገልፀው ክ/ከተማው በቀጣይ የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀርና ቦታዎቹን በማስጠናት አደጋውን ቀድሞ መከላከል በሚቻልበትና ዘላቂ መፍትሔ በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶበት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳት አደጋ ፎረም ኮሚቴ ለጎርፍ ተጋላጭ ተብለው በአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ከተለዩ 29 ቦታዎች መካከል በከፍተኛ ሁኔታ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ 6 ቦታዎች ለቅድመ መከላከያ ስራ ያመች ዘንድ ያሉበትን ሁኔታ ተዟዙሮ ምልከታ አካሂዷል።
በምልከታው ወቅት ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገለፁት በተደጋጋሚ ጊዜ በጎርፍ አደጋ ቤት ንብረታቸው ለውድመትና ለብልሽት መጋለጡን ገልፀው የሚመለከተው አካል ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ እና የእሳትና አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አቃ/ቃ/ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር ተስፋዬ ሞናሴ ኮሚቴው በምልከታው የቦታዎቹን በጎርፍ ተጋላጭነት መመልከት መቻላቸውን ገልፀው ክ/ከተማው በቀጣይ የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀርና ቦታዎቹን በማስጠናት አደጋውን ቀድሞ መከላከል በሚቻልበትና ዘላቂ መፍትሔ በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶበት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
ከከተማ እስከ ወረዳ ካሉ አመራሮቻችን ጋር ስናደርግ የነበረው የስራ አፈጻጸም ግምገማችንን ትላንት ምሽት አጠናቅቀናል::
በግምገማችን ለስራ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት የጀመርናቸው ስራዎቻችን ያሉበትን ደረጃ የለየን ሲሆን ውጤት ካገኘንባቸውና ካሳካናቸው ስራዎቻችን ውስጥ የአመራር የሃሳብ እና የተግባር አንድነት በመገንባት አመራሩ ስራ ላይ እንዲያተኩር መደረጉ ፣የከተማችንን ገጽታ ያሻሻሉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርጉ ትልልቅ እና ታሪካዊ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ፣ በርካታ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የሰው ተኮር ስራዎቻችን የከተማችንን ነዋሪዎች ችግር ያቃለለ መሆኑን ማረጋገጥ ፣ የከተማችንን ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማሳተፍ የሰራናቸው የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን ዝቅ ብለን ከመረጠን ህዝብ ጋር እየመከርን እያዳመጥን ምላሽ የሰጠናቸው የህዝብ ጥያቄዎች እንዲሁም የገቢ አሰባሰባችን አበረታች ሲሆኑ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተግባብተናል::
አመራራችን ተቀናጅቶ ያሳካቸው ስራዎች መልካም ቢሆንም በቀሪ ወራት ከህዝብ ችግር እና ጥያቄ አንፃር ለመረጠን ህዝብ የምንሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል በሰው ሃይል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በልህቀት መከወን፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ሁሉ ማጠናቀቅና የከተማዋን አጠቃላይ መሠረተ ልማት ማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ስራዎች ላይ መስራት፣ ለወጣቶቻችን ሰፊ የስራ እድል መፍጠር እንዲሁም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስወገድ ረገድ በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንዳለብን ተስማምተናል::
የአመራራችንን አቅም እየገነባን ተቋማት በአሰራርና በአደረጃጀት በማጠናከር ለኑሮ እና እንደ ስሟ አበባ የሆነች ከተማ መገንባታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ !!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ9ኛው የከተሞች ፎረም ልዩ ተሸላሚ ሆነ!!
1መቶ 24 ከተሞች የተሳተፉበት የከተሞች ፎረም ከየካቲት 9 -14 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ሲካሄድ እንደ ነበር ይታወሳል።
ፎረሙ በዛሬው እለት ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ልዩ ተሸላሚ በማደረግ ሲሆን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ለከተማ አስተዳደሩ አበርክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተሞች ፎረም ላይ የነበረው ተሳትፎ እጅግ ውጤት ተኮርና ለሌሎች ከተሞች ተሞክሮን ያቋደሰ ስለ መሆኑ አቶ መኮንን ያኢ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ም/ቢ/ኃላፊ ገልፀዋል። በተጨማሪም የከተሞች እርስ በእርስ ግኑኝነቶችን ያጠናከረና ልምድ የመለዋወጥ እድል ያመቻቸ ፎረም እንደነበረም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን የብልፅግና ተምሳሌት ከተማን የመፍጠር ራዕይን አንግባ በርካታ አመርቂ ስኬቶችን እያስመዘገበች የምትገኝ ከተማ መሆኗን የገለፁት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ ሲሆኑ፣ በፎረሙ ላይ በተለያዩ መንገድ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ ለጎብኚዎችና ለተሳታፊ ከተሞች በማስተዋወቅ ማካፈላቸውን ገልፀዋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የኮልፌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በርካታ ነዋሪ አገልግሎት የሚያገኝበት ተቋም በመሆኑ ለተገልጋይ ምቹ የማድረግ ስራ መሰራቱን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው አስታወቁ፡፡
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀምን ከተጠሪ ተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ እንደተገለፀው ፅ/ቤቱ ባለፉት 6 ወራት በድግግሞሽ ከ1 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎችን በፅዳት ዘመቻ ማሳተፍ፤በንቅናቄዎች የተወገደ ቆሻሻ 28.494 ሜኪ፤33 ብሎኮችን 21 ት/ቤቶችን 6 ተቋማትን ሞዴል እንዲሆኑ ማድረጉን እና በሲቪል ምዝገባና በነዋሪዎች አገልግሎት ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ በ8 ወረዳዎች በማካሄድ 3820 ህፃናትን መመዘገቡን፤53948 መታወቂያ ማሰራጨቱንና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመፍጠር የስራ ቦታን ምቹ የማድረግ ስራ መሰራቱን በሪፖርቱ ተገልጾዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት የስራ መመሪያ እንደገለፁት ተቋማቱ በርካታ ህብረተሰብ አገልግሎት የሚያገኝባቸው እንደሆኑ አመልክተው በአገልግሎቶቹን በማዘመን የህዝብን እርካታ የምናሳድግበት መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጨምረው እንደገለፁት ከፅዳት ስራችን አንፃር ክፍለ ከተማውን ጽዱ ውብ ማራኪ የማድረግ ስራዎቻችንን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ እንዳሉት በፅዳት ስራ የግንዛቤ፤የአወጋገድና ቆሻሻን ወደ ሀብት መቀየር ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባን ከሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ተግባራት ውጤታማ በሆነ መልኩ መፈፀም ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በግማሽ ዓመቱ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የ3 ቱም ተቋማት የወረዳ ፅ/ቤቶች፤እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማትና በክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ከሌሎች አመራሮች ተበርክቶላቸዋል፡፡
Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ኮሙኒኬሽን
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
