1 474
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-2130 дней
Архив постов
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቅንጅታዊ ፎረም የስራ አፈጻጸም አበረታች ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤቱ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት የቅንጅታዊ ፎረም የእቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው እለት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ በቅንጅታዊ ፎረሙ የተከናወኑ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በከተማው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ የተቋማት አመራሮች፣ከክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ እና እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አካላት ጋር በጋራ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቅድመ አደጋ መከላከልና ፣በከተማ ፅዳት በተለይም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣ ሞዴል ፅዱ ወረዳና ብሎክ ከመፍጠር እንዲሁም በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሳለጥ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት፣ቅድመ አደጋ ከመከላከል አንፃር የተሰሩ ስራዎች በሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል፡፡
በዚሁ መድረክ በቢሮ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተቋማትና በየደረጃው ያለው መዋቅር የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች የተሻሉ እንደነበር ጠቅሰው ይሁን እንጅ እነዚህ ተግባራት አሁንም ህብረተሰቡን ያሳተፈ በሆነ መልኩ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አክለዉም በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ረገድ የከተማው ተቋማት ቅንጅታቸውን አጠናክረው በመስኩ የቅድመ አደጋ መከላከል ላይ የጎርፍ እና ሌሎች አደጋዎችን ከመከላከል፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ከማቀላጠፍ፣የቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታን ከማፋጠን፣ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ፣ቆሻሻን በወቅቱ ከማንሳት እና የግንዛቤ ስራን ከማጠናከር አንፃር ሰፊ ስራ መከናወኑን አመልክተዋል።
በተጨማሪም ስራዎችን ስንሰራ የህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ መሆን እንዳለበት ጠቅሰዉ በከተማዋ የሚሰጡ አጠቃላይ አገልግሎት የተሟላ ለማድረግ የሁሉም ተቋም ሀላፊነት እንደሚያስፈልግና ተቋማትም በጋራ ተቀራርቦ መስራት እንደሚያስፈል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የትንሳኤ በዓልን በኮሪደር ልማት ከካዛንችስ ወደ ገላን ጉራ ከተዘዋወሩት ነዋሪዎቻችን ጋር ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Ayyaana du'aa ka'uu, jiraattota keenya misooma koriidariif Kaazaanchis irraa gara Galaan Gurraatti naanneffaman waliin
Waaqni Itoophiyaa Fi Uummata Ishee Haa Eebbisu
See less
የትንሳኤ በዓል ከእሳትና መሰል አደጋዎች ተጠብቆ በሰላም ተከብሮ አልፏል።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የተከበረዉ የትንሳዔ በዓል ሰላማዊና ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ በሰላም ተከብሮ አልፏል ።
ሆኖም በበዓሉ ዋዜማ በየካ ክፍለ-ከተማ ፈረንሳይ ጉራራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በአንድ የምግብ ማብሰያ ክፍል ዉስጥ ቀላል የእሳት አደጋ አጋጥሞ እንደነበር ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የትንሳዔ በዓል ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከኮሚሽን መ/ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች ባሻገር ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የከተማ አስተዳደሩ መዋቅር አመራሮች በግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዉ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ ያደረጉት አስተዋጾኦ ከፍተኛ ነበር።
በከተማ አስተዳደሩ በቅንጅት በተከናወነው የቅድመ ጥንቃቄ ስራና ለህብረተሰቡ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ በአከባበር ሂደቱ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።
የከተማ አስተዳደሩ ለህብረተሰቡና ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም የጥንቃቄ መልዕክቶችን ለህብረተሰቡ በማድረስ ሚዲያዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጾ ምስጋናዉን ያቀርባል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም ህብረተሰቡ በበዓላት ሰሞን ሲያደርጋቸዉ የነበሩትን የጥንቃቄ ተግባራት በመደበኛ እንቅስቃሴ ወቅትም እንዲተገብር ያሳስባል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ፣ኮንትራክተሮች እንዲሁም አማካሪዎች ጋር በዓልን በስራ ቦታ አክብረናል።
አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ ቀን ከሌት ለምታደርጉት ትጋት እያመሰገንኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት ካዛንችስ ይኖሩ የነበሩ ጎረቤቶቻቸውን በገላን ጉራ በመገኘት ጎብኝተው እንኳን ለትንሳኤ በአል አደረሳችሁ ብለዉ ማእድ አጋርተዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ላደረጉት ጉብኝት እና ማእድ በማጋራታ ለነዋሪዎቻችን ላስተላለፉት የበዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በራሴና በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!
በበአላት ወቅት ጥንቃቄ አይለየን!
በመዲናችን አዲስ አበባ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ከትንሳኤ በአል አከባበር ጋር ተያይዞ አደጋን ለመከላከል የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎቻችን ሙሉ ዝግጁነትን ተላብሰው በየቅርንጫፍ ጣቢያዎቻችን 24/ 7 የአገልጋይነት ዲስፕሊን ተላብሰው በበአል ዋዜማውም ሆነ የበአሉ ቀን በተጠንቀቅ(Standby) የሚያገለግሉ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በመዲናችን ለእሳት አደጋን ለመከላከል የተደረገውን ዝግጁነት በስፍራው ተገኝቶ ያዘጋጀውን ዘገባ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ
የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ፣ኮንትራክተሮች እንዲሁም አማካሪዎች ጋር በዓልን በስራ ቦታ አክብረናል።
አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ ቀን ከሌት ለምታደርጉት ትጋት እያመሰገንኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
