cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተስፋችን የበጎ አድራጎት ማህበር

የማህበራችን ሳምንታዊ ፕሮግራም ሰኞናማከረሰኞ በፅሁፍ የተለያዮ ቀልዶች ይቀርባሉ። ዕሮብናሀሙስ በ "Audio" ትረካ ይቀርባል። አርብና ቅዳሜ አዝናኝ የ "tik tok" ቪድዮ ይቀርባል። ቅዳሜ እና እሁድ በፅሁፍ አስተማሪ እና የማህበረሰባችንን ችግር የሚፈቱ ሀሳቦች ይቀርባሉ። ማሳሰቢያ ሁሉም የማህበሩ አባል ችግሩን በማንኛውም ቀን፣እና ሰዓት ግሩፑመናገር ይችላል።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
151
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#ጠቃሚ_መልእክት አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ ውሾች (Wild dogs) ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገልጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃዬትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው፡፡ ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት› ፡፡ ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡ የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና «በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው?» ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡ ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዬ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡ #ይህ_መልእክት ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡ መልካም ቀን🙏 @eth_tibeb
Показать все...
✨ደስታህ በራስህ እጅ ነው ያለው ። ብቻህን ሁነህ ደስታን መፍጠር ከቻልክ አንተ ሙሉ ሰው ነህ ። ብቻውን ደስታ መፍጠር ያልቻለ ከሰዎች ጋር ቢሆን ደስታ መፍጠር ደስተኛ መሆን ይቸገራል ብቸኝነት ስለሚሰማው ጥገኝነትን ይፈልጋል ። ✨ስለዚህ በራሳችን ደስታ ፈጣሪዎ እንድንሆን ዘወትር ማመስገን ፣ ሳቅን መፍጠር ፣ የሚስደስታችሁን ስእል ፣ ግጥም መፃፍ ፣ ማዜም ፣ መደነስ ፣ ልባችሁን ያሻችሁን ማድረግ እና ደስታ መፍጠር እንችላለን ። ከራሳችን ጋር በመሆን የራሳችን ውበት ማየት እንዴት ደስ ይላል ። ✨ደስታ በእኛ ውስጥ ያለ የአስተሳሰባችን ውጤን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል እኛ ደስተኞች እንድንሆን ምክንያቶች እንዲከሰቱ መጠበቅ የለብንም ጥገኞች መሆን የለብንም ። መልካም ቀን ቤተሠቦች @eth_tibeb
Показать все...
🔮ውድቀትህን ለሚመኙ ስትል ጠንካራ ሁን ሰው ታሞ እንጅ ታምቶ. አይሞትም ገንዘብ ከድህነት እንጅ ከሞት አያስቀርም ለምቀኞችህና ውድቀትክን ለሚሹ ሰዋች ረጅም እድሜ ተመኝላቸው ምክንያቱም ወደ ፊት ገና ከዚ በላይ ስኬታማ ስትሆንና ከፍ ስትል የማየት እድል ያገኛሉ። መልካም ቀን 🙏 @eth_tibeb
Показать все...
ስብዕና የሠው እውነተኛ መልክ ነው። ፨፨፨፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "...ከህመሞች ሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን ከስብዕና መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሠው የገጽ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሠው እውነተኛ መልክ ነው። በየዕለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር፣ እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ሰብዕናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ሰብዕናችን ነው። የሰብዕና ስንኩልነት፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉአገር ይንዳሉ፣ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከም ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው። ሰብዕና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብዙ ሠው ሰብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካለገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። ዕድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና።" ሰናይ ቀን ይሁንልን !!!!🌗🌓 ኢዞፕ ለተሻለ ነገ !!! @ezobe
Показать все...
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ እይታን በጥቂቱም ቢሆን መለወጥ ሕይወትን ቀላል ያደርጋል፡፡ ♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️ "....ምድር ትንሽ ነች በግዙፍ ፍጥረተ-ዓለም ውስጥ በሚገኝ ትንሽ ፕላኔት ላይ ነው የምንኖረው፡፡ ታወቂው የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሐውኪንግ እንዳለው ከአንድ መቶ ቢሊየን ጋላክሲዎች መካከል በአንደኛው ኮከብ ውጭ በሚገኝ በጣም አነስተኛ በሆነ ፕላኔት ላይ ነን፡፡ እኔና አንተ ከዚህ ካለነው ቢሊየኖች ውስጥ አንዱ ነን፡፡ በየእለቱ የሚገጥሙን ችግሮች ያን ያህል በጣም ግዙፍ ናቸውን? እይታን በጥቂቱም ቢሆን መለወጥ ሕይወትን ቀላል ያደርጋል፡፡ ፈተና ሲገጥመኝ ለራሴ ይህን ጥያቄ አቀርባለሁ፡- «ይህ ነገር ከዛሬ አንድ ዓመት በኋላም ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ይገኛልን? የማይገኝ ካልሆነ በፍጥነት አልፌው እጓዛለሁ። ከባልደረቦችህ ወይም ለቤተሰቦችህ እንድታነሳ የምመክርህ ሌላኛው ጥያቄ ደግሞ ይህ ነው፡- «በዚህ ምክንያት ሕይወት ትቆማለችን?›› ካልቆመች ነገሮች በቀላሉ ይሰክናሉ፤ የሰከነ አእምሮ ሁሌም ያሸንፋል። ከባድ አደጋ አድርገን የምንቆጥራቸው ችግሮች ብዙውን ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከታቸው በረከት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በሕይወቴ የምድር ፍፃሜ መቃረቡን እንዳስብ ያደረጉኝ ከባድ ችግሮች ገጥመውኛል። ነገር ግን ጊዜ ሲያልፍ እነዚያ ችግሮች ሕይወቴን የተሻለ በደስታ የተሞላ ያደረጉልኝ ሆነዋል፡፡ ለአንተም ይኸው እውነት እንደሚሆን እምነቴ ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ በመልካም ነገር ላይ እተኩር፡፡ ከበፊቱ ይበልጥ ሳቅፈገግታ ከፊትህ አይለይህ፡፡ ሕይወት አጭር ነች ዓለም ትንሽ ነች ነገር ግን በጣም ሰፊም ነች፡፡" ኢዞፕ_ለተሻለ ነገ !!!! 💚💛❤️@ezobe💚💛❤️
Показать все...
📌 #አቅምህን_ተረዳ_የሞተ_ሰው_እንኳን_መዎኘት_ይችላል። ▫️ በህይወት ያሉ ሰዎች ግን መዋኘት እንደማይችሉ ያምናሉ። ህይወት ያለው የሚያስበው የሚያገናዝበው ሰውነቱን ማዘዝ የሚችለው ሰው ያልተረዳውን ነፍሱ ከስጋው የተነጠለችው ሰው ግን መንሳፈፍ ይችላል አይሰምጥም ዋናን አውቆታል። 📌አየህ ማወቅ ማለት ለችግሮችህ ተጨንቀህ እንቅልፍ አተህ ማደር ማልቀስ መወራጨት ሳይሆን የችግሮችህን መንስኤ ተረድተህ ምላሽ መስጠት ነው። ስለተወራጨህ ስለተጨነክ የሚፈጠር ለውጥ የለም በዝምታ እና በመረጋጋት ውስጥ ሁነህ ችግርህን ስትረዳው ነው ለውጥ የሚጀምረው። መቼም አካሉ ከነፍሱ የተለየች ሰው የሰራውን ስራ አንተ መተግበር አይከብድህም እሱን አቅምህን ፈልገህ ተጠቀምበት። #ይህን_መልዕክት_በቅንነት_ቢያንስ_ለ_5_ጓዋደኛዎ_Share_ያድርጉ። @FACTS_FOR_KNOWLEDGE
Показать все...
ሁለቱ ጆሮዎቻችን ጎን ለጎን ሲቀመጡ እውነተኛ የልብ ቅርፅን ይሠራሉ። በእንግሊዝኛው ቃል ላይም HEART በመሀል EAR የሚል ቃል እንዳለ አስተውላችኋል? ፈላስፉዎችም እንደሚሉት ጆሮ ወደ ልብ የሚወስድ መንገድ ነው ምን ለማለት ይመስላችኋል?? #SHARE_ያድርጉ #SHARE_ያድርጉ Join us for more👇 @FACTS_FOR_KNOWLEDGE ሀሳብና አስተያየት👇 @FACTSFORKNOWLEDGEBOT
Показать все...
የሠው ልጅ አይን 10ሚሊየን የተለያየ ቀለም መለየት ይችላል። #SHARE_ያድርጉ join us👇 @FACTS_FOR_KNOWLEDGE
Показать все...
👉ምን አልባት አፍቃሪ ነኝ😍 ግን ሰውን አልጎዳም 👉ምን አልባት ሰውን መርዳት ደስ ይለኛል ግን ከሰው ምንም አልጠብቅም🙉 👉ምን አልባት ተናዳጅ ነኝ👈😳 ግን ቂም አልይዝም 👉ምን አልባት ሰው አክባሪ ነኝ ግን አጎብዳጅ አይደለሁም😛 👉ምን አልባት ምንም ችግር ፣ቸነፈር ያላየው እመስላለው😥 ግን በውስጤ ብዙ ጉዳቶች አሉ 👉ምን አልባት አመስጋኝ ባልመስልም 🙏 ግን ፈጣሪዬን አማራሪ÷ ኮናኝ አይደለውም 👉ምን አልባት ፈጣሪዬን ብዙ ነገር ጠይቄው ባማርረውም ግን እሱ እንደፈጠረኝ የምረሳ ልጅ አይደለውም🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Показать все...
ምን አልባትም የዋህ እሆናለው😊 ግን ሞኝ አይደለሁም ምን አልባትም አላኮርፍም 😔 ግን ተቀይሚያለው ምን አልባትም አላስታውስም😒 ግን አልረሣም ምን አልባትም ትዝታ የለኝም 👈 ግን ተስፋ አለኝ ምን አልባትም ስድብ አወቃለው ግን አልሣደብም🤐 ምን አልባትም እበላለው ግን አልጠግብም🍔 ምን አልባትም እስቃለው😄 ግን ደስተኛ አይደለውም 🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.