cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Gulele inspection Directorate

Gulele inspection directorate

Больше
Рекламные посты
1 372
Подписчики
Нет данных24 часа
+197 дней
+2530 дней
Архив постов
Repost from N/a
ቀን 21/08/2016 ዓ.ም ለሁሉም የመንግስት እና የግል የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ ግንቦት 1/2016 የሚሰጠው የመ/ራን እና የት/ት አመራር ሙያ ብቃት ምዘና የምትወስዱ ተመዛኞች ረቡዕ ሚያዚያ 23/2016 ከጠዋቱ 2፡30 የሚሰጥ በመሆኑ፤ 1ኛ. በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ /ግራውንድ/ ረቡዕ በ23/08/2016 ከቀኑ 2፡30 ጀምሮ 2ኛ. በአፋን ኦሮሞ /በኦሮሚኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች ጉለሌ ክፍለ ከተማ 11ኛ ፎቅ ረቡዕ በ23/08/2016 ከ2፡30 ጀምሮ 3ኛ. ለመዛኝ እና ለሱፐርቫይዘርነት የተመረጣችሁ መ/ራን፣ የት/ት ባለሙያዎች እና የጸጥታ አካላት ነገ ማለትም ማክሰኞ በ22/08/2016 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ ሰሜን ሆቴል አካባቢ ዳኪ ህንጻ 3ኛ ፎቅ እንድትገኙ N.B - መመዘኛ ቦታው መድኃኔአለም ሁለተኛ ደረጃ ሲሆን የመፈተኛ የክፍል ድልድል /Exam room/ በቴሌግራም ገጽ /Gulele Teachers and Edu.Leaders Professional Licencing or https://t.me/gtedu2016 በመግባት ድጋሜ የተስተካከለ /revised/ የክፍል ድልድል በማየት ድልድሉ ውስጥ ያልተካተተ ተመዛኝ እና የሚስተካከሉ መረጃ ካለ ለእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡/ ለበለጠ መረጃ 0111712358
Показать все...
ማስታወቂያ ለሁሉም የመንግስት እና የግል የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ ግንቦት 1/2016 የሚሰጠው የመ/ራን እና የት/ት አመራር ሙያ ብቃት ምዘና የምትወስዱ ተመዛኞች ሰኞ ይሰጣል ተብሎ የነበረው ኦረንቴሽን ወደ ረቡዕ ሚያዚያ 23/2016 ከጠዋቱ 2፡30 የሚሰጥ በመሆኑ 1ኛ. በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ /ግራውንድ/ ረቡዕ በ23/08/2016 ከቀኑ 2፡30 ጀምሮ 2ኛ. በአፋን ኦሮሞ /በኦሮሚኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች በድልበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረቡዕ በ23/08/2016 ከ2፡30 ጀምሮ N.B - መመዘኛ ቦታው መድኃኔአለም ሁለተኛ ደረጃ ሲሆን የመፈተኛ የክፍል ድልድል /Exam room/ በቴሌግራም ገጽ /Gulele Teachers and Edu.Leaders Professional Licencing or https://t.me/gtedu2016 በመግባት የክፍል ድልድል በማየት ድልድሉ ውስጥ ያልተካተተ ተመዛኝ ለእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ሪፖርት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
Показать все...
ይነበብ ለሁሉም የመንግስት እና የግል የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ ግንቦት 1/2016 የሚሰጠው የመ/ራን እና የት/ት አመራር ሙያ ብቃት ምዘና የምትወስዱ ተመዛኞች ሰኞ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ለሚሰጠው ኦረንቴሽን የመስጫ ቦታ በተመለከተ ፡- 1ኛ. በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ /ግራውንድ/ ሰኞ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ 2ኛ. በአፋን ኦሮሞ /በኦሮሚኛ ቋንቋ ምዘና ለመውሰድ ያመለከታችሁ ተመዛኞች በድልበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰኞ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ N.B - መመዘኛ ቦታው መድኃኔአለም ሁለተኛ ደረጃ ሲሆን የመፈተኛ የክፍል ድልድል /Exam room/ በቴሌግራም ገጽ /Gulele Teachers and Edu.Leaders Professional Licencing or https://t.me/gtedu2016 በመግባት የክፍል ድልድል ማየት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጊብሰን #GibsonSchool የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጊብሰን ትምህርት ቤት የሚማሩ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከተማ አቀፉን የሚኒስትሪ ፈተና ትምህርት ቤቱ ማስፈተን እንደማይችል እንዳሳወቀው ት/ቤቱ ገልጿል። ጊብሰን ትምህርት ቤት " ባጠፋቸው ጥፋቶች ምክንያት እግድ ስለተጣለበት ተማሪዎችን ማስፈተን አይችልም " የተባለ ሲሆን ትምህርት ቢሮው ተማሪዎችን ሌላ ትምህርት ቤት ወስዶ በማስፈተን የሚኒስትሪ ካርዱ ላይም " በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስር " የሚል እንደሚፃፍበት ተገልጿል። ይህን ውሳኔ ወላጆች እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ወላጆች ምን አሉ ? - ልጆቻችን በተማሩበት ት/ቤት ስር ነው መፈተን ያለባቸው - የተነገርን ነገር የለም - ባለቀ ሰዓት ነው ይህን የሰማነው - በተቀመጠው ካሪኩለም እንደሚማሩ ነው እኛ የምናውቀው - ልጆቻን ካሪኩለሙ የሚፈቅደውን ነው የሚማሩት - ቋንቋ ችግር አለ ወይ ? የለም - ሌሎች ት/ቤት የሚተገበረው ነው እዚህም ያለው - ከሌሎች የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚለየው ሳይንስ እና ሂሳብን በተጨማሪ እንግሊዘኛ ቋንቋ ያንኑ ካሪኩለም ጠብቆ ማስተማሩ ነው። እኛ ትምህርት ቤቱን የመረጥነው ተጨማሪ ቋንቋ ስለሚያስተምር ነው። - በተቀመጠው አማራጭ ሁለት ቋንቋ እያስተማረ ነው። አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ በትምህርት አይነት ደረጃ እየተማሩ ነው። የቀረ ነገር የለም። - በመደበኛው ፕሮግራም ምንም የተጣሰ ነገር የለም። የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ትምህርት ቤቱ ብዙ ጥሰት ፈጽሟል ብለዋል። አቶ አድማሱ ደቻሳ ምን አሉ ? ° የትምህርት አይነት ጨምሮ ማስተማር ° የክፍለ ጊዜ ጥሰት ° የትምህርት ቋንቋ አለማክበር ° የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሀገራችን " እንግሊዘኛ ነው " ብሎ ስታንዳርድ እስከመያዝ መድረስ፤ ° በእንግሊዝኛ አፋቸውን የፈቱ ካሉ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አለ እዛ መማር ይችላሉ ግን በከተማው ፍቃድ የወሰደ ት/ቤት " የአፍ መፍቻ ቋንቋው እንግሊዝኛ ነው " በሚል ማስተማር አይችልም። ° የሀገር በቀል ቋንቋ ጠል መሆን ተገቢ አይደለም። ° ተጨማሪ ቋንቋ በጥናት የተመለሰ ነው ይህንም እንዲታወቅ ብዙ ተሰርቷል ይህ ሆኖ እያለ ' አናውቅም፣ አልሰማንም ፣የሚመጣ ነገር የለም ' የማለት ነገር አለ። አንድ ወር ለቀረው የትምህርት ጊዜ ይህን ውሳኔ ለምን አሳለፋችሁ ? ለምን አልታገሳችሁም ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፦ " እኛ እልህ እየተጋባን አይደለም። የተወሰደው እርምጃ ከ4 ወር በፊት ነው። ነገር ግን ት/ቤቱ ተማሪና ወላጆችን መጠቀሚያ ለማድረግ ጥረት አድርጓል። እርምጃው ከተወሰደ ግን ቆይቷል። ከፈተና ጋር ተያይዞ ግልጽ ነው አንድ የትህምህርት ተቋም እውቅና ፍቃድ ኖሮት ወደ ፈተና ስርዓት ሲገባ ኮድ ይሰጠዋል ይህ የትምህርት ተቋም የእውቅና ፍቃዱ ቀድሞ የተነሳ ስለሆነ ኮድ ሊሰጠው አይችልም። ኮድ ባልተሰጠበት ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ይፈተኑ ቢባል ፈተናቸው ሊታረም አይችልም። ስለዚህ ኮድ ወዳለው ትምህርት ተቋም ወስደን ነው የምናስፈትናቸው።  " ሲሉ መልሰዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መሆኑን ይገልጻል። @tikvahethiopia
Показать все...
ለአዲስ ቅድመ አንደኛ ተቋማት የማመልከቻ ቅጽ 2016
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Photo from Fikiru Gebissa
Показать все...
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት የስታንዳርድ ኢንሰፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡ (መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በተካሄደው የቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ተቋማቱ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት በእያንዳንዱ ስታንዳርዶችና አመልካቾች ያሉበትን ደረጃ እና የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመላከትና ክትትል ቁጥጥር እና ድጋፍ በማድረግ ጥሩ የሰሩትን እውቅና በመስጠት ድክመት ያለባቸውን ደግሞ ክትትል ድጋፍ አላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ከዛ ካለፈ ደግሞ ተጠያቂ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ የቴ/ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋም እና የሰው ሀይል ልንፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡
Показать все...
የቅ/ፅ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ አለሙ ግኝት ሪፖርቱን ያቀረቡ ሲሆን የትንተናው ዋና አላማ፣ የቴ/ሙ ትምህርትና ስልጠና ኢንስፔክሽን አላማዎች፣ የኢንስፔክሽን ስነድ ትንተና አስፈላጊነት፣ የኢንስፔክሽን ትኩረት መስኮች መለኪያ ክብደትና አመልካች ብዛት የሚያሳይ መረጃ፣ የቴ/ሙ ትምህርት ስልጠና ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ደረጃዎች ፣ ተቋማት ኢንስፔክሽን ከትምህርት ፖሊሲ፣የ2016ዓ.ም በኢንስፔክሽን ትግበራ ሂደት የታዩ ጥንካሬዎች ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎች እና ዋና ዋና ግኝቶች ላይ ዝርዝር መረጃ አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በጉለሌ፣ አራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ ህጋዊ እውቅና ፍቃድ ባላቸው 56 አጫጭር ቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመጨረሻም በኢንስፔክሽ ግኝት የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ የቴ/ሙያ ተቋማት የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት የስታንዳርድ ኢንሰፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡ (መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በተካሄደው የቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ተቋማቱ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት በእያንዳንዱ ስታንዳርዶችና አመልካቾች ያሉበትን ደረጃ እና የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመላከትና ክትትል ቁጥጥር እና ድጋፍ በማድረግ ጥሩ የሰሩትን እውቅና በመስጠት ድክመት ያለባቸውን ደግሞ ክትትል ድጋፍ አላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ከዛ ካለፈ ደግሞ ተጠያቂ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ የቴ/ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋም እና የሰው ሀይል ልንፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡
Показать все...
የስብሰባ ጥሪ በጉለሌ ፣ አራዳ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ ለምትገኙ ህጋዊ የዕውቅና ፍቃድ ያላችሁ የአጫጭር ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት በሙሉ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ትም/ስ/ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም የተካሄደውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሐሙስ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ስለሚካሄድ የተቋሙ ባለቤት እና ሀላፊ(ዲን) የጉለሌ ፣ አራዳ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ቅ/ጽቤት ስራ አስኪያጅ ፣ የዕውቅና ፍቃድ ዳይሬክተርና ቡድን መሪ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሠዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ፡፡ ሰዓት ይከበር!! የስብሰባው ቦታ አድራሻ ፡ - አራት ኪሎ ከብርሀንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት ድንቅ ስራ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ፡፡
Показать все...
ማስታወቂያ በ2015 ለ2016 እውቅና ፈቃድና እድሳት ምዘና የተካሄደላችሁ የት/ት ተቋማት በሙሉ፡- ነገ ማለትም በ17/07/2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በድልበር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የድህረ እውቅና ክትትልና ቁጥጥር ግኝት ስለሚቀርብ የት/ቤቱ ባለቤት እና ር/መ/ራን፣የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ፣አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች፣የክ/ከተማ መ/ራን ማህበር፣ የ10ም ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የቅ/አንደኛ ደረጃ እና የመጀመሪያ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮች፣የወረዳ ቡድን መሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት በድልበር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንድትገኙልን እናሳስባለን፡፡ ሰዓት ይከበር!!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Photo from Fikiru Gebissa
Показать все...
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለግል ትምህርት ተቋማት በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በድንገተኛ ኢንስፔክሽን የሥርዓተ ትምህርት ጥሰት ሲፈጽሙ ተገኝተው ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ አስተካክለናል ብለው በደብዳቤ ባሳወቁት የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ በድጋሜ በተደረገው የቁጥጥር ስራ አብዛኛው ትምህርት ተቋማት የነበረባቸውን ችግር ያላስተካከሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ፡፡ በዚህም መሰረት በእነዚህ ትምህርት ተቋማት ላይ በመመሪያው መሰረት ቅ/ጽ/ቤቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድና በዚህም ከጥፋታቸው የማይታረሙ ከሆነ የዕውቅና ፍቃዳቸውም የማያድስ መሆኑን በጥብቅ እያሳሰብን ፡፡ ሌሎች በድብቅ የስርዓተ የትምህርት ጥሰት የምትፈጽሙ ትምህርት ተቋማት ካላችሁ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ የመንግስትን ስርዓተ ትምህርት ብቻ ተግባራዊ እንድታደርጉ በጥብቅ እያስጠነቀቅን በቀጣይ በማንኛውም የስራ ቀን በማንኛውም ተቋም በድንገት የቁጥጥር ስራ በመስራት ችግሩ በተገኘባቸው ትምህርት ተቋማት ላይ በመመሪያው መሰረት እስከ ዕውቅና ፍቃድ ዕገዳ የሚያደርስ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን ፡፡ በየደረጃው የምትገኙ የጉድኝት ማዕከል ሱ/ቫይዘሮችና የትምህርት ባለሙያዎችም አፈፃፀሙን በቅርብ በመከታተል እንድታሳውቁን እናሳስባለን ፡፡ በቅንጅታዊ አሰራር የመንግስትን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እናደርጋለን !! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት
Показать все...