cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media

በሀገራችን ኢትዮጵያ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እንድሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ምርጥ የቴሌግራም ቻናል። Offical Group @BeteamhramediaGroup Telegram፦ https://t.me/Bete_amharamedia Facebook፦ https://www.facebook.com/beteamharamediaa/

Больше
Рекламные посты
4 237
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-1830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የላሊበላ ወጣቶች ተላላኪውን በዓዴን አሳፍረው መለሱት። የላሊበላ ከተማ ካድሬ ዛሬ በ06/09/2015 ዓ.ም ፋኖ ይመታ የሚል የድጋፍ ሰልፍ ጠራ። በሰልፉ ላይ ብአዴን ያደኸያቸው የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ነበር የተገኙት። ነገር ግን እሳት የላሰው የከተማው ወጣት በጎን የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ነገሮች በተፈለገው መልኩ መሄድ ሳይችሉ ቀሩ። ካድሬ ትናንት ከኦነግ ተዘጋጅቶ የተላከለትን መልዕክት በሚዲያ አስተላለፈ። መሬት ላይ የሆነው ግን ሌላ ነበር። በመጨረሻም ሁለቱም ሰልፍ በፖሊስና ሚኒሻዎች ተበተነ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዛሬ የታላቅ አማራ ሰማእት የአባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሰማእትነት እለት ነው ..‼️‼️           የአማራ ሕዝብ አባታችን ለትግል ከተነሱበት ጊዜ ይልቅ ዛሬ በከፋ የኅልውና ስጋት ውስጥ ይገኛል። በአንፃሩ ከዚያ ዘመን ይልቅ ዛሬ ለአማራነቱ ሰማእትነትን ለመቀበል በጽናት የቆመው እጅግ ብዙ ነው። ፈተናው ምንም ቢበረታ የአባታችንን የሰማእትነት አደራ ተቀብለን የሕዝባችንን የፍትኅ፣ እኩልነት እና ነፃነት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተን የሁሉም፥ በሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን እውን እንደምናደርግ ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የለኝም። ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለታላቁ የአማራ ሰማእት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ! ክብር የአባታችን ቃልኪዳን ወራሽ ሆነው በጽናት በትግል ላይ ላሉ ሁሉ!
Показать все...
አማራ ባንክ አ.ማ ለ29 የሚሆኑ የራያ ገበሬዎች በረጅም ጊዜ ብድር ትራክተሮችን ገዝቶ አስረክቧል።
Показать все...
“በዓይነቱም በግዝፈቱም ወደር የማይገኝለት የዓለምን ክብረወሰንን ይሰብራልም ተብሎ የሚጠበቅ መፈናቀል በቅርቡ በኢትዮጵያ ይኖራል!” -ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጠ/ሚሩ ከአራት የማይበልጡ ቤቶችን ለማደስ ዶማ ይዘው ወጥተዋል። ምሽቱን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ ተጥለዋል። የአሁኑ የሚከፋው ደግሞ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች በአከባቢው ፈጽሞ መገኘት የለባቸውም በሚል የተጀመረው እስከግድያ የሚደረስ እርምጃ ነው። ዓርብ ሌሊት በሰበታ በመንግስት ሃይሎች በተውሰደ እርምጃ የተገደሉ ሰዎች 4 ደርሷል። አራት ነፍሶች በአንድ ሌሊት። እንደሰማሁት አሁን የተጀመረው ቤት የሚፈርስባቸው ሰዎች በአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ ቤት መከራየት አይችሉም። የሚያከራያቸው ካለ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ይከፍላል። ወደ ሀገራችሁ ሂዱ! ነው እየተባሉ ያሉት። መሄጃ የለንም ብለው ወዳጅ ዘመድ ጋ የተጠጋ እግር በእግር ክትትል ተደርጎበት ይደበደባል፡ ይታሰራል፡ እንደነ አቶ መሀመድና ባለቤታቸው ከሆነ ደግሞ በጥይት ተደብድቦ ይገደላል። አይናችሁን ማየት አንፈልግም ዓይነት ፍጹም አረመኔያዊ ተግባር ነው መሀል ኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ያለው። ሰውዬው ደግሞ አብራር አብዶን ያስናቁ ቲያትረኛ ወጥቷቸዋል። 10ሺዎችን በጎን ያፈናቅሉና ዶማ ይዘው ቅዳሜን ጠብቀው ሶስት ቤቶችን ሲያሳድሱ በካሜራ እይታ ውስጥ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ረጅም ሀተታ ለቀው ይሄዳሉ። እሳቸው ጋ አመራር እንዲህ ነው። ነገም ይቀጥላል። ሌላ ቅዳሜ ይመጣል። 10 ሺዎች ይፈናቀላሉ። 10 ቤትች ይታደሳሉ። ይኸው ነው። ይልቅስ የከፋው ግዙፉ መፈናቀል ከፊት እየመጣ ነው። ምናልባትም ይኸኛውም መፈናቀል በዓይነቱም በግዝፈቱም ወደር የማይገኝለት ይሆናል። የዓለምን ክብረወሰንን ይሰብራልም ተብሎ የሚጠበቅ ነው። አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ ብር ይፈጃል የተባለውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቅልፍ ያጡለት የቤተመንግስት ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን የአዲስ አበባና ዙሪያዋን ነዋሪዎች እንደሚያፈናቅል እየተነገረ ነው። 500ሺህ ዜጎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ቤታቸው ይፈርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከወዲሁ መጀመሩንም እየሰማሁ ነው። እናቶች ተጨንቀዋል። አባቶች መላ ቅጡ ጠፍቷቸዋል። ሰዉ የት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት እንደእብድ መንገድ ላይ እያወራ ወዲህ ወዲያ ይንከላወሳል። የአቶ አቢይ አህመድ መንግስት ይዞ የመጣው ዱብ እዳ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው አይተውት ሰምተውት የሚያውቁት አይደለም። ይሄ መቼም ቁጣ ነው። ፈጣሪ የተቀየመው ነገር ቢኖር እንጂ እንዲህ ዓይነት ህዝብ የሚያስለቅስ፡ ሀገር ማቅ የሚያስለብስ አገዛዝ ምን ቢፈርድበት ነው የሰጠው? የጫካ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለሟቸው ቅንጡ ፕሮጀክቶች ትልቁ ነው። የኢትዮጵያን ዓመታዊ በጀት ሁለት እጥፍ ይስተካከላል። ገንዘቡ ከየት ይመጣል የሚለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ሰጪዎች በቀር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። ለምክር ቤቱ አያገባችሁም ብለዋል። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር ዮናስ ብሩ እንዲህ ዓይነት በህዝብ የተመረጠንና ሰይሞት ስልጣን የሰጠውን ምክር ቤት አያገባችሁም የሚል መሪ የትም ሀገር ኖሮም ተፈጥሮ አያውቅም ብለዋኛል ሰሞኑን። አቶ አያልቅበት እንደልቡ ናቸው። የህዝብ ንቀት እስከአፍንጫቸው ደርሶ በአፍጢማቸው ሊደፋቸው ደርሷል። ምንም ነገር አይቀበሉም። ማንንም አይሰሙም። ከእነመንግስቱ ብሃይለማርያምና መለስ ዜናዊም ብሰው ሁሉን ነገር ፈላጭ ቆራጭ ሆነው አርፈዋል። ሀገሪቱን የግል ንብረታቸው አድርገዋታል። ሚኒስትሮቻቸውን የግል አሸከሮቻቸው እንጂ በራሳቸው የቆሙ መንግስትን የሚወክሉ አድርገው አይመለከቷቸዋም። በዙሪያቸው ሰጋጅ፡ ምንጣፍ ጎታች ሰብስበዋል። በአጭሩ ሰው ጤፉ ናቸው። ሚሊዮኖች ቢፈናቀሉ፡ ሚሊዮኖች ቢገደሉ ስሜት አይሰጣቸውም። ይህን ሁሉ መዓት ሀገሪቱን ላይ ከምረውና ቆልለው፡ ፈካ ፈታ ብለው ሲታዩ እውን ይሄ የጤና ነውን የሚል ጥያቄን ያጭራል። እንግዲህ ይህ የጫካ ፕሮጀክት አሁን ባለው ዋጋ 850ቢሊየን ብር ወይም 15ቢሊየን ዶላር የምሚፈጅ ነው። ስራው ተጀምሮ እስኪያልቅ ከአንድ ትሪሊየን ብር ሊሻገር እንደሚችል ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ይህን ብር ይዘን ሂሳቡን በተለያዩ ለኢትዮጵያውያን የህይወይትና ሞት ሽረት በሆኑ ጉዳዮች እንመንዝረው። በዶላር ያለውን ሂሳብ ወስደን ማለት ነው። 15 ቢሊየን ዶላር፥ ሶስት የህዳሴ ግድብን ይገነባል። 1ቢሊየን ዶላሩ 20 ሆስፒታሎችን በየክልሉ ማቆም ያስችላል። ሌላ 1 ቢሊየን ዶላሩ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ዩኒቨርስቲዎችን ያቋቁማል። 1 ቢሊየን ዶላር በትግራይ፡ በአማራና በአፋር ክልሎች የወደሙ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች መልሶ በተሻለ መልኩ ለመገንባት ያስችላል። 1 ቢሊየን ዶላር የኮይሻ ሀይድሮ ኤሊክትሪክ ፕሮጀክት ግንባታን እንዲጠናቀቅ ያደርጋል። በ1 ቢሊየን ዶላር 3ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ይገዛል። ለ20 ሚሊየን የተራቡ ዜጎቻችን ከአምስት ወራት በላይ ቀለብ እንዲኖራቸው ያደርጋል። 1 ቢሊየን ዶላር 4ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስኳር ለመግዛት ያስችለናል። 1 ቢሊየን ዶላር 2ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ይገዛልናል። አርስ አደሮቻችን ተንበሸበሹ ማለት ነው። እንግዲህ እስከአሁን የተጠቀምነው 6 ቢሊየን ዶላሩን ብቻ ነው። 9 ቢሊየን ዶላር ይቀረናል። እንቀጥል ይሆን? የአብይ አስተዳደር 2ቢሊየን ዶላር ገንዘብ እንዲሰጠው የገንዘብ ሚኒስትሩንና የብሄራዊ ባንክ ገዢውን አሜሪካን ድረስ ለአንድ ሳምንት አቆይቶአቸው ደጅ ሲጠኑ ከርመዋል። ባዶ እጃቸውን ቢመለሱም ያቺን ዶላር ለማግኘት ያደረጉት ተጋድሎ መቼም የሚዘነጋ አይደለም። የዶላር ጠኔ ውስጥ ሆኖ የሚሰቃየው መንግስት ነው እንግዲህ ከየት እንደሚሸመጠጥ ግልጽ ባልሆነ 15ቢሊየን ዶላር እነኋይት ሀውስንና በኪንግሃም ቤተመንግስቶችን የሚያስንቅ ግዙፍ ቤተመንግስት ለማስገንባት እየተዘጋጀ ያለው። 98 በመቶ ከመካከለኛ ገቢ በታች የሚኖር ህዝብ ባለባት፡ 30 ሚሊዮን የምግብ እርዳታ ጠባቂ የሆኑ ዜጎች በሚኖሩባት፡ 38 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሚያሰቃያት፡ በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት ምጥ የሆነበት ሲሶ ያህል ህዝብ በሚርመሰመስባት ሀገረ ኢትዮጵያ ነው እንግዲህ አቶ አብይ አህመድ የሀገሪቱን የሁለት አመት በጀት በአንድ ቅንጡ ቤተመንግስት ላይ ለማባከን ቀበቶአአቸውን ታጥቀው የተነሱት። ከገንዘቡ በላይ አፈር ከድሜ ያስጋጡት የሀገሪቱ ስርዓተ መንግስትና የህግ የበላይነት እጅግ የሚያሳስብ ነው። አያገባህም የተባለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፉን ሎጉሞ የሰውዬውን የእብደት አካሄድ ቆሞ እያየ ነው። እንደውም አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባላት ''አበጀህ የእኛ ልጅ'' ዓይነት ውዳሴና ሙገሳ እያዥጎደጎዱ ናቸው። በኢትዮጵያ መሬት አንዲት ስንዝር መሬትና አንዲት ስባሪ ሳንቲም ያለምክር ቤቱ ፍቃድና እውቅና መነካት እንደሌለበት ቢታመንም ከህግ በላይ፡ ከሀገሪቱ በላይ ለመሆን በሚታትሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መዳፍ ውስጥ ተጨብጦ የቀለጠው ምክር ቤቱ ታላቅ ታሪካዊ ስህተት እየሰራ መሆኑን አለመረዳቱ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን ፕሮጀክት ማስቆም ይገባዋል። ምንምአይጠቅምም። ራስ ሳይጠና ጉተና እንዲሉ የኑሮ ሰማይ እንደእንቅብ ለተደፋበት 98በመቶ ለሚሆን ህዝብ የጫካ ፕሮጀክት ሸክም ሆኖ ወገቡን የሚቀነጥስ እንጂ ቀና የሚያደርገው ፈጽሞ አይሆንም።
Показать все...
አሁን ይሄ ግፍ እንደት አይነት ሰው መሸከም ይችላል😭😭😭 ኦሮሞ በልጅ ልጆችህ ተከፍሎ የማያልቅ ግፍ አለብህ። ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና ሚስት ትላንት ማታ ተገደሉ። በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንት በስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት አካባቢ ሆኖታል። ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በሆላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽንጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራውንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ "ቤት እስክታገኙ "እዛ ግቡ" ብሎዋቸዉ ገቡ። ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ። ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል። በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል። ተስፋ ነዳ - ከጳውሎስ ሆስፒታል። Emat Gurage Media
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአበበ በለው ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ! ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል። ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል። አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት። የአማራ ህዝብ ህግ ያለ እንዳይመስለው። ህግ የለም። እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት። የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል። ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። የሚያስከብረው ሀይል ብቻ ነው። የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው። አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም። አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል። የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል። የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው። አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሄር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ሀይል ነው። ሌላው ጠላት ይበቃናል። ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም። የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው። መገደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው። እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው። ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቀጣፊ የአንዱን ቤት በዘሩ እያፈረሱ የአንዱን ቤት መጠገን ከማስመሰል ያለፈ ምንም አይባልም።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የህወሃት እና የኦነግ አክቲቪስቶች በመቀሌ እየመከሩ ነው! ትግሬዎች ብቻቸውን መቆማቸው ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው በደንብ የተረዱት ይመስላል። ቂማቸውን በሆዳቸው ይዘው ጥላትን የመቀነስ ወዳጅን የማባዛት ስትራቴጂ እየተከተሉ ነው። “የጥላቴ ጥላት ወዳጄ ነው” በሚል ፖለቲካዊ ስሌት ከኦሮሞ ጋር ጥምረት ፈጥረዋል። መቸም በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ወጣት ያለቀው በኦሮሞ ፖለቲከኞች አመራር ሰጪነት እንደሆነ የሚጠፋው ትግራዋይ ይኖራል ብዬ አላስብም። ታሪክም እንደዛ ብሎ ነው የሚመዘግበው። በቀደም የሀይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ወደ መቀሌ አቅንቶ ከነ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያይቶ ተመልሷል። ትላንት ደግሞ ተፅዕኖ ፈጣሪ የኦሮሞ የማህበራዊ አንቂዎች ወደ መቀሌ ጉዞ አድርገዋል። መቸም የሁለቱ ጥምረት ለአማራ ህዝብ ምን ይዞ እንደሚመጣ የሚጠፋው አማራ ያለ አይመስለኝም። የእኛ ልጆች እርስበርሳቸው ገመድ ጉተታ ላይ ናቸው። አንዱ አንዱን ሲዘረጥጥ ይውላል። ፍፁም መግባባት አቅቶናል።
Показать все...
ስለምንድን ነው የምታወሩት ኧረ አማሮች በሳል ሁኑ አንድ ተላላኪ ባንዳ በሚጥለው ውዳቂ ወሬ አትነዱ‼️ ምሬ ዛሬም ምሬ ወዳጆ ፋኖ ነው‼️ ሰላም ነው‼️
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.