cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

👪እዉነተኛ ፍቅር🌹🌹🌹

✍ለምን ወደድኩሽ? እንጃ❤ ✍ምንሽ ተመቸኝ? እንጃ❤ ✍እንዴት ማረከሽኝ? እንጃ❤ ✍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት፤ ✍ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ✍በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ ✍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት❣❣

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
635
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ሰማያዊዉ ሰማይ ወዳጅሽ ይሁን፤ ቡናማዉ አፈር አጋርሽ ይሁን፤ እስክመለስ ድረስ ሚስጥርሽን ለነሱ አጋሪያቸዉ፤ ንፋሱን ከሰማሽ እኔን ትሰሚኛለሽ፤ ዝናቡም ፍቅሬን ባንቺም ላይ ይጥላል፤ [ኤርቱሩል ለ ሀሊሜ❤ ] @Rizqislamiccalligraphy
Показать все...
​📝❤✔️️እውነተኛ ፍቅር) ✏️❤️✡🔯 📍1☂እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው፡፡ 📍2☂ለፍቅር ሁነኛ ማረጋገጫ እምነት ነው፡፡ 📍3☂ማንም ሰው አይናችን ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ነገር ግን ልባችን ውስጥ ዘልቆ የሚገባው አንድ ልዩ ሰው ነው፡፡ 📍4☂ራስህን እንድትሆን ለማይፈቅድልህ የፍቅር ወዳጅነት ራስን አሳልፈህ አትስጥ፡፡ 📍5☂በሌሎች የመፈቀርን ሀሰብ ከመውደድ በፊት፤ መጀመሪያ ራስን መውደድን ተማር፡፡ 📍6☂በማይረባ ድንጋይ ጊዚያቸውን እንዳባከኑ ሲገባቸው በእጃቸው የነበረው እንቁ እንደነበር ይገነዘባሉ፡፡ 📍7☂አንድን ሰው ለመልኩ ብቻ አናፈቅረውም፣ ለአለባበሱ ወይም ለምርጥ መኪናውም ልናፈቅረው አይገባም፤ የምናፈቅረው እኛ ብቻ ልንሰማው የምንችለውን ዜማ ስለሚያቀነቅኑ ነው፡፡ 📍8☂ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም ፣ ወይም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍም አይደለም ፣ ወይም ተቃቅፎ መታየም ሳይሆን ማንም ሊያስደስታችሁ በማይችልበት መንገድ ደስታን ሊፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው፡፡ 📍9☂ፍቅር እውር አይደለም ፣ ሌሎች በቀላሉ ሊያዩትን ያልቻሉትን ነገር እንዲያዩ የሚያስችል እንጂ! 👍10☂ላረጋግጥልሽ የምፈልገው ነገር ቢኖር፣ ምን ያህል እንደምናፍቅሽና አንቺ ካጠገቤ ርቀሽ አለም ምን ያህል ባዶ እንደሆነችብኝ ነው፡፡ ☂☂☂☂☂☂☂☂☂☂☂☂ Share ur friends !!!!!!!!♥ For any comment inbox '''''''👉@Entimia 💕 @rfhabesha 💕
Показать все...
አዲሱ ዓመት ከጎረቤት ረብሻ ከባለትዳር ጥቅሻ ከተናካሽ ውሻ ከገቢዎች ፈለጣ ከአለቃ ቁጣ ከመንግስት ለበጣ ከሞራል ስብራት ከገንዘብ ብድራት ከቀፋዮች ብልጠት ባዶ ቤት ከመግባት ከጅል ጋ ከመዋል ቪዛ ከመከልከል አጥር ከመዝለል ጨጏራ ከሚልጥ የመብራት መቆራረጥ ከሰራዊት ማስታወቂያ ከኢቲቪ ማስጠንቀቂያ ከሰይፉ ፉገራ ከፈሪ ፉከራ የፀዳ ይሁንላችሁ። ላላገባችሁ ትዳር ላገባችሁ ፍቅር ያድላችሁ። ባዲሱ ዓመት ከኪሳችሁ ፍራንክ ከጥርሳችሁ ሳቅ አይጥፋ። ቤታችሁ ቄጠማ ጎዝጉዙ ላንድ ልጅ አንድ ደብተር ግዙ በጎ ሰሪዎችን አግዙ። ወልዶ ለመሳም ዘርቶ ለመቃም ያብቃችሁ። መርቅኖ ከማቀድ አፍቅሮ ከማበድ በግፍ ከመሰደድ ካልተከደነ ጉድጏድ ውሃ ካቆረ መንገድ እጅ እጅ ከሚል ቀልድ ጦምሮ ከመታሰር ነግዶ ከመክሰር ከባለጌ ወንበር ከአሽሟጣጭ ከንፈር ከንፁህ ሰው ደም ከቆሸሸ ስም ከስኯር ወረፋ ከስልክ ጠለፋ ቀጥሮ ከሚቀር ከአካውንት ሀከር ከውሃ ሙላት ከወዳጅ ክህደት ከfacebook ጅንጀና ከውሸታም ዜና ብሎክ ከመደረግ like ከመነፈግ ይሰውራችሁ። አሜን! :¨·.·¨: ❀ ·. 🌹•°❀
Показать все...
🎙 • ዳጊ ዲ 🔊 • በቃ @Birabiromusic @mussegirma
Показать все...
🎙 • Burik Omer 🔊 • ማማዬ @Birabiromusic @mussegirma
Показать все...
😍እጅግ ደጋግሜ አንብቤው ሁሌም የምወደው ፅሁፍ ነው! አንብቡትማ. …•••🌹 ሼር በአንድ ወቅት ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ በመሀላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው። ሁለት ልጆችም ወልደው ነበር ። ነገር ግን ችግር ላይ በመውደቃቸው ባል ሊሰራ ተሰማምተው ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ መስራት ጀመረ። በተከታታይ ለ16 ዓመታት ሰራ ከዚያ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ሰማ፤ደሞዙ በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው 3000 ብር ተሰጠው። የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋ ለመሄድ ተነሳ። በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት አገኘ... "ወዴት ትሄዳለህ ልጄ፧ ከየት ነውስ ምትመጣው?" አሉት። እሱም ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ።እሳቸውም እንዲህ አሉት:---"እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው ፤ እሱም እንዴት አባቴ?" ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም "በል አንድ ሺህ ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ" አሉት የቸገረው ነውና አንስቶ አንድ ሺህ ብሩን ይሰጣቸዋል። እኒህ አባትም "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል። ሁለተኛውን ሺህ አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ ይሉታል። እሱም በየዋህነት ሁለተኛውን ሺህ ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ፤ ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ። "በቃ ይሄ ነው?" ቢላቸው "አዎን ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን ልስጥህ" አሉት ሰጠ። እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለውት በባዶ ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ። በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ እሱም አብሮዋቸው ጉዞ እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ አለው። "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው። ሰለዚህ ተመልሶ በሚያወቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ። አንድ የዛ ከተማ ሰውም "የውልህ ወንድሜ እዛ ቤት ሂድ ያሳድርሀል፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም እድልህን ሞክር።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ። ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ ተረፍክ ፧ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው። ያቺ በአንድ ሺህ ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው። ሰለ መሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጓዳ ብቅ አለች " እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም የተወሰነ አካሉዋ ብቻ ነው ሰው የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ። "ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው "በማያገባህ አትግባ" የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ፤ ይህ የምታየው ሰው ሁሉ ሰለ ሚስቴ የማያገባቸውን አሰተያየት ሰለሰጡ የተገደሉ ናቸው፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድነት የመጡ ነበሩ። አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሀለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ። እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር። ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች። አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ አለው። "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ ብሎ አደረ። ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን ስታየው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት። ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነው። ሰውዬው ሶስቱ የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት። 1. አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ 2. በማያገባህ አትግባ 3. ክፉ ለማድረግ አትቸኩል _______ ሼር እና★አስትያየት @jolax7★ካደረጋችሁ "የምለቃቸው ምርጥ ምርጥ ፁሁፎች" ቶሎ ቶሎ ይደርሳቹሃል መልካም ጊዜ ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━ ............................%......................... ••●◉Join us share @rfhabesha ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉
Показать все...
አስገራሚ ታሪክ አንዱ ሚስቱን ይመታታል።በአጋጣሚ ሊገድላት ሳያስብ በእጁ ትሞትበታለች።ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ እዳ እንዳይሆንበት ምን ማድረግ እንዳለበት ያስባል።አስቦ አሰላስሎ በስተመጨረሻም አንድ ሀሳብ መጣለት።እሱም ወደስፈራቸው አዋቂ ነኝ ባይ ሰው ጋር መሄድ ነበር።ታዲያ ይሄ አዋቂ ተብዬ ሰውም መፍትሄ የሚለውን ሀሳብ እንዲህ ሲል ይመክረዋል።ደጅህ ላይ ተቀመጥና ቆንጆ ወጣት ሲያልፍ ካየህ "አንዳች የምታግዘኝ ነገር አለ"በለውና ወደ ቤትህ አስገባው።ከዚያም ግደለውና ከባለቤትህ እሬሳ ጋር አጠገብ ለአጠገብ አጋድመው።የእሷን ቤተሰቦች ጥራና"ከዚህ ወጣት ጋር ሲያመነዝሩ ስመለከት እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እርምጃ ስወስድባቸው በእጄ ሞቱ" ብለህ ንገራቸው አለ። አባወራውም መላ ነው ተብሎ የተነገረውን ተቀብሎ ደጃፍ ላይ ሄዶ ቁጭ ብሎ መጠባበቅ ይጀምራል።ብዙም ሳይቆይ አንድ ወጣት በአጠገቡ ሲያልፍ ተመለከተና"ወንድሜ አንዴ ላስቸግርህ?የሆነች ነገር እንድታግዘኝ ፈልጌህ ነበር"ብሎ አስማምቶ ወደ ቤት ያስገባዋል።እንደተመከረው ይገድለውና ከሚስቱ ጀናዛ አጠገብ ያጋድመዋል።የሚስቱ ቤተዘመዶች ሲመጡም በዝሙት ላይ አግኝቷቸው ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እርምጃ እንደወስደባቸው ይነግራቸዋል።እነርሱም ጥፋተኛ ሳያደርጉት ምክንያቱን ይረዱትና ይተውታል።ይሄንን የማምለጫ ዘዴ ነግሮት የነበረው ሰውዬ ጉዳዬ ከምን እንደደረሰ ሊጠይቀው ቤቱ ይከስታል።ጉዳዩ ሰውዬም የመከረውን እንዳደረገ እና እንደተስካለት በኩራትና በምስጋና ይነግረዋል።እስኪ የገደልከውን ልጅ አሳየኝ ብሎ አዋቂ ተብዬው ይጠይቀዋል።ገዳዩ ወስዶ ሲያሳየው ለካስ የተገደለው የራሱ የአዋቂ ነኝ ባዩ ልጅ ኖሯል!! በሳሉን ቢላዋ መቆረጥ ይሉሀል እንዱህ ነው!! አሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ(ረ.ዐ)እንዲህ ይላሉ፦የተንኮል ሰይፉን የሳለ እራሱ ይቄረጥበታል።የሌሎችን ነውር አደባባይ የሚበትን የራሱ ነውር አደባባይ ይታይበታል። ከተመቻችሁ ሼር አድርጉት!!! ||•••••••••••🔴🔴🔴••••••••••••••|| @rfhabesha ||•••••••••••🔴🔴🔴••••••••••••••||
Показать все...
ከፊታችን እየመጣ ያለ ታላቅ የፆም ሳምንት እንዳያልፋችሁ ..!! የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ ከረመዳን ወር በመቀጠል ፆም በላጭ የሚሆንበት ወር የሙሀረም ወር ነው። 📒📔📕 ሶሒሁ ሙስሊም (1163) _ ✋ እናም እንደምታውቁት ይህ አሁን ያለንበት ወር የሙሀረም ወር ከመሆኑ ጋር ከፊትለፊታችን ታላላቅ የፆም ቀናቶች አሉ ስለነዚያ በዝርዝር እንተዋወስ፡ ● ሀሙስ (ስራችን ከአላህ ዘንድ የሚቀረብበት ቀን ስለሆነ ፁሙት)፣ ● ጁምዓ (ከአሹራ በፊት ያለው ዘጠነኛው ቀን ነውና ይሄን ቀን መፆም ይወደዳል ፁሙት)፣ ● ቅዳሜ (አሹራ ነውና ፁሙት የአንድ አመት ወንጀል ያስምርላችኋል)፣ ● እሁድ (አሹራን አስከትለህ እሱንም መፆም ይወደዳልና ፁሙት)፣ ● ሰኞ (አሁንም ይህ ቀን ስራችን ከአላህ ዘንድ የሚቀረብበት ቀን ስለሆነ ፁሙት)፣ ● ማክሰኞ (የአያመል ቢይድ አንደኛው ቀን ነውና ፁሙት)፣ ● እሮብ (የአያመል ቢይድ ሁለተኛው ቀን ነው)፣ ● ሀሙስ (የአያመል ቢይድ ሶስተኛው ቀን ነው)። ✋ አደራ በተቻለን አቅም ለመፆም እንሞክር ምንዳቸው በጣም ትልቅ ነው፣ ከረመዳን ፆም በመቀጠል ትልቅ ምንዳን የሚያስገኙ የፆም ቀናቶች ናቸው። ሌሎች ይደርሳቸው ዘንድ ሼር አድርግ ምናልባትም አንተ ሼር አድርገህ የማያውቁ ሰወች አንብበውት ቢፆሙ የነሱን እኩል ምንዳ ታገኛለህ። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ ሌሎች ሰዎችን ወደ መልካም ስራ ያመላከተ ልክ እርሱም ያን ስራ እንደሰራው ተደርጎ ይያዝለታል።
Показать все...