cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ መልስ አላት

ስንዱ እመቤቴ እርሱ ባለቤቱ በደሙ የመሰረታት ይህች ናት በዚህች ሀይማኖት እራሳችንን እናጽና ለሚጠይቆችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ 1ጼጥ 3፡15ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የተከፈተ ምን እንጠይቅሎ በታች በለው ይላኩልነን @ortodoxneg ኣርቶዶክሳዊ የሆኑ፦ 👉ስብከቶች 👉መዝሙሮች 👉መጸሀፍት በPDF 👉ግጥማች https://t.me/joinchat/AAAAAEh2IZg_nBDrO-n1FA

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
166
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ኢየሱስን ብታገኘው ምን ትለዋለህ) ልዩ የዳግማዊ ተንሳይ ቆይታ ከመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ https://t.me/deaconhenokhaile/3040
Показать все...
voice-changer-2021-05-14-23-21.mp325.31 MB
+ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ - ርትዕት ኃልዮ - Thinking Orthodox + ዶ/ር ጂኒ ኮስንስታንቲኒውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኋት ጌታችን በተቀበለው የሐሰት ፍርድ ዙሪያ ባደረገችው ተከታታይ የድምፅ ትምህርት /podcast/ ነበረ፡፡ በምሥራቃዊው የኦርቶዶክስ ዓለም ወገን ሆና እንዲህ ዓይነት ልበ ሙሉነት የተሞላች የነገረ መለኮት ልህቅት ምዕራባዊያኑን ስታንቀጠቅጥ ማየት በራሱ ልብን በኩራት የሚሞላ ነበር፡፡ በትምህርቶችዋ ላይ ምዕራባዊያኑ ምን ያህል የነገረ መለኮት አረዳድ ችግር ያለባቸው መሆኑን የምትገልጽበት መንገድ እና በጉዳዩ ላይ እንደ ግሪካዊነትዋ የምታሳየው የተጠያቂነት ሥልጣን አንጀት የሚያርስ ስለነበር በተለይ ከሀገር ውጪና በክፍለ ሀገራት ረዣዥም የአውቶቢስና የባቡር ጉዞዎችን በማደርግበት ጊዜ እርስዋን መስማት ልማዴ አድርጌ ነበር፡፡ ዶ/ር ጂኒን እንደ እኔ ኢትዮጵያዊና ኦርየንታል ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ለሚሰማት ሰው ደግሞ መምህርትዋ ለኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ያላትን አክብሮት የሚያሳዩ ንግግሮችን መስማቱ አይቀርም፡፡ በአንድ ትምህርትዋ ላይ ምሥራቃውያኑ /መለካዊያኑ/ ከካቶሊክ ስለተለዩበት ሁኔታ ስታነሣ ‘እኛ እና ኦሪየንታል ኦርቶዶክሶች የተለያየነው በአራተኛው ክፍለ ዘመን በኬልቄዶን ጉባኤ በተነሣ በአንድ ነገረ ክርስቶሳዊ ልዩነት ምክንያት ነው፡፡ ከካቶሊክ ጋር ደግሞ እስከ 1054 ድረስ አብረን ቆይተን ተለያይተናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከካቶሊክ ጋር ያሉን የአስተምህሮ ልዩነቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሲሆኑ ከኦርየንታል ኦርቶዶክስ ጋር ያለን ልዩነት ግን በአራተኛው ክፍለ ዘመን የተለያየንበት አንድ ልዩነት ብቻ ነው፡፡ ይህም የሆነው ኦርየንታል ኦርቶዶክሶች እንዳሻቸው ትምህርት የማይለዋውጡና የጥንቱን ዶግማ ይዘው ጸንተው የሚኖሩ በመሆናቸው ነው’’ ብላለች፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ስታነሣ ኢትዮጵያዊያን ምንኛ ዳዊት ደጋሚዎች መሆናቸውን በማውሳት ለጥንታዊትዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ ማሳያ አድርጋ ትጠቅሳለች፡፡ ዶ/ር ጂኒ ከነገረ መለኮት መምህርትነትዋ ባሻገር ምሁራዊ ሰብእና ያላት መሆንዋንም ተመልክቼአለሁ፡፡ በግል ለአንዳንድ ጥናቶች ምክር በጠየቅኋት ጊዜ ሃሳብዋን በመሥጠትና ጥያቄዎችን በመመለስ የምታሳየው ትብብር አስገራሚ ነበር፡፡ ከሁሉ በላይ የዶ/ርዋን ቀናነት ያየሁት ዲያቆን አቤል ካሣሁን አባቶችህን እወቅ የተሰኘውን ወሳኝ መጽሐፍ በሚያዘጋጅበት ወቅት የሠጠችው በይዘቱ ላይ የማማከር አገልግሎት ሳያንስ በመጽሐፉ ላይ የሚወጣ የመግቢያ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆንዋ ነው፡፡ ዲያቆን አቤል ‘መግቢያ እንድትጽፍልኝ ልጠይቃት ነው’ ነው ሲለኝ መቼም ምንም ሃሳቡን ብትጋራም ባላነበበችው የአማርኛ መጽሐፍ ላይ መግቢያ ለመጻፍ እንዴት ፈቃደኛ ትሆናለች?’ ብዬ ነበር፡፡ እርስዋ ግን ጥያቄ እንኳን ሳታነሣ ጽፋ በመላክ በአማርኛ ለሚታተም መጽሐፍ መግቢያ የጻፈች የመጀመሪያዪቱ የግሪክ ቴዎሎጂ መምህርት ሆናለች፡፡ ሰሞኑን ‘Thinking Orthodox’ የተሰኘውና አብዛኛውን ትምህርቶችዋን ለሰማ ሰው ለዓመታት ስትወተውትባቸው የከረሙ ብዙ ሃሳቦችን ያካተተችበት መጽሐፍዋ በገበያ ላይ ውሎአል፡፡ ለምሳሌ ከአፍዋ የማይጠፋው ፍሮኒማ /ሕሊና አበው/ በዚህ መጽሐፍ እጅግ ተተንትኖአል፡፡ በፖድካስትዋ ላይ ‘አባቶች ያሉትን ብቻ እንጂ የራስሽን ትንታኔ ለምን ትጨምሪያለሽ?’ በሚል የቀረበባትን ትችት ስትመልስ ‘ፍሮኒማ ማለት አባቶች ያሉትን እየደጋገሙ ማነብነብ ሳይሆን በእነርሱ ሕሊና ሆኖ ነገሮችን መረዳትና ማብራራት ነው’ ትላለች፡፡ አንዳንዴም ጠንከር ብላ /ጥቅሱን ላገኘው ያልቻልኩትን የቅዱስ ጎርጎርዮስን አባባል በመጥቀስ/ ‘If you don’t know theology , you have to shut up’ /ትምህርተ መለኮትን የማታውቁ ከሆነ ዝም በሉ/ ብላ ትገሥፃለች፡፡ የጂኒን መጽሐፍና የድምፅ ትምህርት የሚሰማ ሰው ያሉንን የነገረ ሃይማኖት ልዩነቶች ሳይዘነጋ በሚበዙት የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ብቻ አተኩሮ ማንበብ ይጠበቅበታል፡፡ አስቀድሞ የኦርየንታልና የምሥራቃውያንን ልዩነት ያልተረዳ ሰው ግን ብርድ ሊመታው ስለሚችል እንዲህ ያለውን የንባብ ነፋስ እንዲቀበል ጨርሶ አይመከርም፡፡ የጽሑፍዋ ምንጮች የሚበዙት የጋራ አባቶቻችን እንደመሆናቸው ምሥራቃዊት ስለሆነች ብቻ ‘የመለካዊት ጽሑፍ ጨርሶ አላነብም’ ማለት ደግሞ የቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ስፍሐ አእምሮና ስፍሐ ልቡና ያልወረሰ አስተያየት ያለው ሰው ይሆናል፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ‘የሚስዮናውያን ሕልም - በምዕራባዊያን ሚስዮኖች ላይ ኢትዮጵያዊ ዕይታ’ /The Missonary’s Dream : An Ethiopian Perspective on Western Missions in Ethiopia/ በተሰኘው ጽሑፋቸው ላይ የቤተ ክርስቲያናችንን ጥንቃቄ የተሞላበት አካታችነት እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ ‘The Ethiopian Church is not unwilling to entertain new ideas from other religious communities as it is commonly depicted. .... Isaac of Nineveh, whose monastic writing is one of the three major works studied and read regularly in Ethiopian monasteries, was a Nestorian. Ibin al-Assal, the compiler of the Fitha Negest, the authoritative source of the Church’s canon Law, was a Malkite’ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ እንደምትሳለው ከሌላ ሃይማኖት ማኅበረሰቦች የሚመጡ አዳዲስ ሃሳቦችን ለማስተናገድ የማትፈቅድ አይደለችም፡፡ .... በገዳማት ዘወትር የሚነበበውና የሚጠናው ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት አንዱ የሆነውን መጽሐፍ የጻፈው ይስሐቅ ዘነነዌም ንስጥሮሳዊ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያንዋ ሕገ ቀኖና ሥሉጥ ምንጭ የሆነው ፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ ኢቢን አል አሳል ደግሞ መለካዊ ነበር" (The Missionary factor in Ethiopia page 2 , Lund University, August 1996) የዶ/ር ጂኒንና መሰል የምሥራቃውያን መጻሕፍት አባቶቻችን በሔዱበት የስፉሐነ ልብ የንባብ አድማስ ማንበብ እጅግ ጠቃሚ ሲሆን "ጠርጥር ከገንፎ መሃል አይጠፋም ስንጥር" መንገድ (Skeptical reading method) በመከተል ማንበብ ያስፈልጋል:: መጽሐፉ በቶማስ አድማሱ ወደ አማርኛ ተተርጉሞአል:: እጃችን ሲገባ ደግሞ አንብበን በትርጉሙ ላይ እንወያይበታለን:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 4 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ
Показать все...
ህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡ የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡ ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡ ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints. It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡ ‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡ አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥር 10 2009 ዓ ም @Hamongog2 @Hamongog2
Показать все...

+++ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +++ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡ ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30) ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡ ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/) አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው:: ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) ሌላው አስገራሚ ነገር አቡነ ጎርጎርዮስ በታቦት ሥርዓት ከግሪኮች አንዲሚስዮን ጋር እንደምንመሳሰል ጠቅሰው ሲጽፉ ግሪኮቹ ደግሞ ስለ አንዲሚስዮን ሲያብራሩ ከኢትዮጵያ ታቦት ጋር የሚመሳሰል ብለው መጻፋቸው ነው። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚ
Показать все...
ቅዱሳን አባቶቻችን "ስለ ምጽዋት" እንዲህ አሉ :– ★ "አንተ ልትበላው ያልፈለግኸው እንጀራ የተራቡት ሰዎች እንጀራ ነው። በቁም ሳጥንህ ውስጥ ሰቅለህ የተውከው ልብስ ዕርቃኑን የሆነው ሰው ልብስ ነው። የማታደርጋቸው ጫማዎችህ ባዶ እግሩን የሚሔድ ሰው ጫማዎች ናቸው። የቆለፍክበት ገንዘብ የደሃው ገንዘብ ነው። የማትፈጽማቸው የቸርነት ሥራዎች ሁሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችህ ናቸው" (ቅዱስ ባስልዮስ) ★ "አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) (paraphrased) ★ "ወንድምህ ዕርቃኑን ወድቆ እያለቀሰ ነው ፣ አንተ ግን የሚያምር የወለል ንጣፍ ለመምረጥ ተቸግረህ ቆመሃል" ቅዱስ አምብሮስ ★ "ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም" ( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ★ "አባት ሆይ ወጪውን ሳናሰላ እንድንመጸውት አስተምረን" (ቅዱስ አግናጥዮስ) ግንቦት 3 2010 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ [email protected]
Показать все...
የእመቤታችንን ልደት እንዲህ በስልክ ጉባኤ አክብረነዋል፡፡ ((መሠረቶችዋ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው!)) (በመምህር ዳን ሄኖክ ኃይሌ) @deaconhenokhaile @deaconhenokhaile
Показать все...
_መሰረቶቿ_የተቀደሱ_ተራሮች_ናቸው_በመምህር_ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_128kbps_.m4a23.70 MB
+ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር+ የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል:: "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60) በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት:: በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም:: ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል:: የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል:: በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው:: ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው:: ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም:: እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ:: እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ:: በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር:: ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው:: ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ - በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ - በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን - በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሐምሌ 9 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4 Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Показать все...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

የእመቤታችን አነዋወር ከሐና ማኅጸን ጀምሮ እስከ ዕርገቷ እንዴት ነበር?✝ ግሩም ማብራሪያ ✅መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ✅መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ.ር) ✅መጋቤ ብሉይ ዮሴፍ ደሳለኝ http://t.me/abagebrekidan http://t.me/abagebrekidan
Показать все...
''የእመቤታችን አኗኗርዋ''.mp37.14 MB
+ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ + ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅስ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል ብለህ እንዳትጠቅስ ገና ወንጌላት አልተጻፉም:: ቢጻፉም ማቴዎስ በሕይወት እያለ በቃሉ መመስከር ሲችል ጽሑፉን ማስረጃ ማድረግ አያስፈልግህም:: ስለዚህ ለመነሣቱ ማስረጃዎች ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች ነበሩ:: በሕይወት ያሉትን የዓይን ምስክሮችን መጥቀስ ይቻላል:: የዓይን እማኞች ምስክርነት ከጽሑፍ በላይ የታሪክ ማስረጃ ነው:: ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ጌታ ትንሣኤ "እነ እገሌ አይተውታል" እያለ መዘርዘርን መረጠ:: ጌታ ከተነሣ በኋላ እንደ ቀድሞው ለሁሉ አልታየም:: እርሱን ለማየት የተገባቸው ጥቂት ወደ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ:: በማኅበር ያዩት አሉ:: በግል ያዩት አሉ:: ያዩት ነገር ወንጌል የሆነላቸው ብፁዓን ዓይኖች ያሏቸው እንዴት የታደሉ ናቸው? የተሰቀለውን ተነሥቶ ያዩት! ዳግም በሚመጣበት አካል የተገለጠላቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? ከመድኃኔ ዓለም አፍ ተቀብለው ኪዳን ያደረሱ! የጌታን ቅዳሴ ተቀብለው ያስቀደሱ! የትንሣኤው ማግስት ምስክሮች እንዴት ዕድለኞች ናቸው? ቢሞቱም እንኳን መነሣታቸውን በጌታ ትንሣኤ አይተው ደስ ብሎአቸው ያንቀላፉ እነርሱ ምንኛ የታደሉ ናቸው? ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ከተጠቀሱት ከነ ኬፋ በተጨማሪ ለይቶ ጌታ ለማን ለማን እንደታየ ገለጸ:: ለያዕቆብ ታየ ብሎ የእልፍዮስን ልጅ ለይቶ ጠቀሰው:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት እንደሚሉት ይህ ሐዋርያ ከሌሎች በተለየ የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል አልቀምስም ብሎ የተሳለና አክፍሎትን የጀመረ ነበርና ጌታ ለይቶ ክብሩን አሳይቶታል:: ከዚያም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ ብሎ የጌታን ድኅረ ትንሣኤ አስተርእዮ ዘረዘረ:: እኔ ማለትን የማይወደው ትሑት ቅዱስ ጳውሎስ "ከሁሉ በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ አለ:: ጭንጋፍ ምንድር ነው? ጭንጋፍ (ጸዕጻዕ/ ተውራድ) ለፅንስ የሚነገር ቃል ነው:: መወለድ ያለበትን ጊዜ ያልጠበቀ ያለ ጊዜው የተወለደ ፅንስ ነው:: በመጠኑ ከሌላው ጊዜውን ከጠበቀ ፅንስ የሚያንስ ሲሆን ዕድገቱን በተገቢው ጊዜ ከሚወለድ ልጅ ጋር ለማስተካከል ሲባል በሙቀት ማቆያ ክፍል እንዲቆይ ይደረጋል:: ይህ ፅንስ ሲወለድ በሕመም ውስጥ ሆኖ ተሰቃይቶ ተጨንቆ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ የተጠቀመበት ይህ አንድ ቃል የሕይወት ታሪኩን ጠቅልሎ የያዘ ድንቅ ቃል ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያን ብርሃን የሆነ ሐዋርያ ቢሆንም እንደ ዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በጊዜው የተጠራ አልነበረም:: እርሱ ከሐዋርያት ጋር አብሮ በዳግም ልደት የተወለደ ሳይሆን ያለ ጊዜው ክርስቶስ ባረገ በስምንተኛው ዓመት የተጠራ ነበረና ራሱን ካለ ጊዜው ከተወለደው ፅንስ ጋር አመሳስሎ እንደ ጭንጋፍ የምሆን ብሎ ጠራ:: ጭንጋፍ ሲወለድ በመጠኑ ከሌላው ፅንስ ያነሰ ይሆናል:: ቅዱስ ጳውሎስም ራሱን ጭንጋፍ ካለ በኋላ "እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ብሎ አብራርቶታል:: (1ቆሮ 15:9) ልጅ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ በሥቃይ ነው:: ጤና ያጣል ይታመማል:: እናቲቱም ትታወካለች በድብታ በጭንቀት ትቸገራለች:: ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እናት ያለ ጊዜው ከተወለደ ልጅዋ ጋር እናታዊ ትስስር ለመፍጠርና የእናትነት ፍቅርዋን ለመሥጠት ባልጠበቀችው ጊዜ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ትቸገራለች:: በአጭሩ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ እሱም ይሰቃያል እናቱንም ያስጨንቃል:: ወዲያው እንደሌላ ሕፃን በሰው እጅ አይታቀፍም:: ከተፈጥሮአዊ እስከ ሰው ሠራሽ እንደየጊዜው እየዘመነ በሔደው የልጅ ሙቀት መስጫ መንገድ እየታገዘ የሰውነት አካሎቹ በአግባቡ መሥራት እስከሚችሉና በሽታ መቋቋም እስከሚችል ይቆያል:: ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጭንጋፍ ነበርኩ ያለው ለዚህ ነው:: በዳግም ልደት የተወለደው በደማስቆ መንገድ ወድቆ ሊቋቋመው ባልቻለው ብርሃን ተመትቶ ነበር:: "ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ?" የሚል ድምፅ ሲሰማ ፅንስ ነውና ዓይኑን እንኳን መግለጥ አልቻለም ነበር:: ከተወለደ በኋላም ወዲያው ወደ ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ወደ ሐዋርያት ማኅበር አልገባም:: እንደ ጭንጋፍ የምሆን እንዳለ ሙቀት ያስፈልገው ነበርና የሰው እጅ ሳያቅፈው ሦስት ዓመት በሱባኤ ቆይቶ በመንፈስ ቅዱስ ተማወቀ:: "ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። ከሦስት ዓመት በኁዋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ" ብሎ ስለ መንፈሳዊ ኃይል መልበሱ ይናገራል:: (ገላ 1:15-18) ጭንጋፍ ሆኖ የተወለደ ልጅ የሚገጥመው ችግር ከወላጆቹ ጋር በሥነ ልቡና ለመተሳሰር መቸገሩ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስን ለማመንና እንደ ልጅ ለመቀበል የቤተ ክርስቲያን ማኅበርም ተቸግራ ነበር:: "ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት" ሐዋ 9:26 ስለዚህ ሐዋርያው እንደ ጭንጋፍ ነኝ አለ:: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጌታ መነሣት ምስክሮች ብሎ ሌሎችን ከዘረዘረ በኋላ "ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ" ብሎ ተናገረ:: ክርስቶስ ተነሥቶአል ወይ ብለው ሲጠይቁህ አዎ ተነሥቶአል እነ እገሌ አይተውታል ብለህ ዘርዝረህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለህ መናገር መቻል እንዴት መታደል ነው!? ወዳጄ ክርስቶስ መነሣቱን ታምናለህ:: ልክ ነህ ለብዙዎች ታይቶአል:: አንተስ ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ ማለት ትችል ይሆን? ጌታ ከተነሣ በኁዋላ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ለብዙዎች ታይቶአል:: ብዙዎቹ ቅዱሳን አይተውታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ አይቶታል : ቅድስት አርሴማ አይታዋለች : አቡነ ተክለ ሃይማኖት አይተውታል : አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተመልክተውታል:: አባ ጳኩሚስ በዕንባ ተመልክቶታል : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አይታዋለች:: ሁሉም ቅዱሳን ብዕር ቢሠጣቸው ከዕንባ ጋር "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለው የትንሣኤውን ማስረጃ ዝርዝር ይቀጥላሉ:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በበረሃ ሲጸልይ አይቶት ነበርና ሰው ባገኘ ቁጥር ወቅቱ የፋሲካ ሰሞን ባይሆንም እንኳን በፈገግታ ተሞልቶ "ክርስቶስ ተነሥቶአል!" ብሎ ያበሥርና ሰላምታ ይሠጥ ነበር:: ጌታ ሆይ ለእኔ ለኃጢአተኛው የምትታየኝ መቼ ይሆን? ቸርነትህን አይቻለሁ! ፍቅርህን አይቻለሁ! ብሩሕ ገጽህን የማየው መቼ ይሆን? መች እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አየዋለሁ? እኔም እንደ ቅዱሳንህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔ ታየኝ" ብዬ የተቀመጠውን ብዕር አንሥቼ የምጽፈው መቼ ይሆን? አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! አቤቱ ፊትህን ከእኔ አትመልስ! አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! "ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ዘቀራንዮ ለላሕይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ" "የቀራንዮው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ውበትህን ልናየው እንመኛለን" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ማዕዶት 2012 ዓ ም አዲስ አበባ
Показать все...
ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ፡፡ እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን እንዲህም እንላለን፦ እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል (ማቴ1:23) ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2 ንፅህት )በስጋሽም ድንግል ነሽ (ማቴ1:23) (ህዝ44:2) ያሸናፊ የልኡል እግዚአብሔር እናት ሆይ (ሉቃ1:35)ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32) የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ ልኡል እግዚአብሄር ካንች ጋር ነውና(ሉቃ1:28-30) ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመዳህኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን በ1ቆሮ5:20 በፅድቅ ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልናሃጢአታችንም ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን። እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡ ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡ ኦርቶዶክስ መልሥ አላት ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመሥቀሉ ክቡር ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ @And_Haymanot @And_Haymanot @And_Haymanot @And_Haymanot
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.