cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethiofica

Achachr leboldoch Aguag Azenagn ena Asferi Lboldochn be ethiofica Ena aznagn kelgoch Ena azeg

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
169
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስራ_ስድስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ..ልጄን አደራ እያለች ነበር ፍፁም እስር ቤት ዉስጥ የቤዛዊትን ልጃቸዉን አቅፋ መምጣት በጉጉት ይጠብቃል ነገር ግን ቤዛዊትን በላሁ የሚል ጅብ አልጮህ አለ። የቤዛዊት ቀብር ተፈፅሞ ልጇን ቤዛዊት ባወጣችላት ስም አየጠሩ ቤተሰቦቿ በከባድ ሀዘን ዉስጥ ሆነዉም ቢሆን በእሷ ምትክ ልጅ ሰጥታቸዉ አልፋለች እና የወለደቻትን ቆንጅዬ ሴት ልጅ እንደቤዛዊት አይተዉ እየተንከባከቧት ነበር። እስር ቤት ቀን ወራት ነዉ አመት ዘመን ነዉ ደቂቃ እየተንቀራፈፉ ነዉ የሚጓዙት ፍፁም ጥግ ላይ ተቀምጦ ወረቀት እና እስኪቢርቶዉን ይዞ የህይወቱን የመጨረሻ ክፍል በመፃፍ ላይ ነዉ ቤዛዊት ምን ገጥሟት ቀረች ለሚለዉ መልስ እንኳን መልስ ማግኘት አልቻለም በልቡ ቤተሰቦቿ አስገድደዋት ልጁን አስወርዳ ሌላ ባል አግብታ ይስላል እስር ቤቱ ዉስጥ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት ቤዛዊት "የምስራች ልጅ ልወልድልህ ነዉ" ብላዉ የጠፋችበት ወቅት ለእሱ ከባድ ነበር ስሙ የተጠራ እየመሰለዉ በለሊት "አቤት" ይል ነበር አንዳንዴ ቤዛዊት ያስጠራችዉ እየመሰለዉ በህልሙ ሁሌ ልጇን አቅፋ እየሳቀች ትቀርበዉና አጠገቡ ስትደርስ የዉሀ ሽታ ሆና እንደጉም ትበተናለች ይጨነቅ ይረበሽ ነበር። ሰከንዶች እያዘገሙ ደቂቃ ይሆናሉ ደቂቃወች ወደ ሰአት ለማደግ ይንቀራፈፋሉ ሰአታት ሰአት ሆነዉ ለመቆጠር አቅም ያንሳቸዋል ቀን እና ለሊት ለመለዋወጥ በጣም አሰልቺ ጊዜን የሚወስዱ እየመሰለው ቀን በመቁጠር ተጠምዶ ሲዉል ነበር። አመት አመትን እየተካ ፍፁምም የወጣትነት ፊቱ በጎልማሳ ፊት እየተቀየረ የጭንቀት ሀሳቦቹ ቀስ በቀስ እየቀለሉት ቀን መቁጠሩን ትቶ የተፈረደበትን ብዙ አመታትን ወደማገባደዱ ሲደርስ ጭንቀቱ ዳግም ማገርሸት ጀመረ። ፍፁም እድሜዉ ወደ ሀምሳወቹ እየተጠጋ ነዉ መፈቻዉ እየደረሰ ሲመጣ ወደ በፊቱ ሀሳብ ተመለሰ "ፍቅር አያረጅም ትዝታ አያረጅም እድሜ ቢጠወልግ ሰውነት ቢጃጅም" ቤዛዊት እሱን ለመጠየቅ መጥታ ልጅ አርግዤልሀለዉ ያለችዉን ቀን እያስታወሰ አሁን ቤዛዊት እና ልጁ ሊኖሩ የሚችሉበትን ሁኔታ እያሰበ ይቆዝም ገባ። የቤዛዊት ቤተሰቦች ለፍፁም ልጁን ለማሳየት ማረምያ ቤት ለመምጣት ያስቡና የተፈረደበት ፍርድ ብዙ አመታት መሆኑን ሲያዉቁ ልፋት እና ልጅቷን ማንከራተት እየመሰላቸዉ ጥቂት ጊዜያት በተግባር ባያረጉትም ያስቡት ነበር አመት እየተለወጠ በአመት ሲተካ እረሱት የቤዛዊት አባትም በህመም ተይዘዉ ብዙም ሳይቆዩ ስለሞቱ እህቷ ባል አግብታ የራሷን ሁለት ልጆች ወልዳ ከእናቷ ጋር የቤዛዊትን ልጅም ጭምር ፍቅር ሰጥተዉ እየተንከባከቧት አሳደጓት እድሜዋም ወደ ሀያወቹ እየተጠጋ ወጣት ሆናለች ፍፁም የመፈቻ ስሙ ተጠርቶ የነበረውን ሁሉ ታሪኩን ከፃፈበት ወረቀት ዉጪ ሁሉንም ለታሳሪወች አከፋፍሎ ሁሉንም አቅፎ ተሰናብቶ ከማረምያ ቤቱ ወጣ የብዙ አመት መኖርያ የነበረዉን እስርቤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ተመልክቶት ግቢዉን ለቆ ወደ ቤዛዊት እና ልጁ ገሰገሰ። የእነ ቤዛዊት በር ጋር ደርሶ ቆመ በር ማንኳኳት አልቻለም ቆሞ ልቡ ሲመታ እና ሲጨንቀዉ የግቢያቸዉን በር ተደግፎ ለመረጋጋት እየሞከረ በሩ ተከፍቶ ወጣት ሴት ወጥታ "ምን ሆነዉ ነዉ አሞት ነዉ ዉሀ ላምጣሎት?" ፍፁም አንገቱን ቀና አርጓ አያት የቤዛዊትን አይን የያዘች ደግነቷም እንደሷ የሆነ ቆንጆ ልጅ ልቡ ልጁ እንደሆነች እየነገረዉ የጥንቱ ፈገግታ ፊቱ ላይ ባይኖርም ለመሳቅ እየታገለ "ስምሽ ማነዉ?" ብሎ ጠየቃት ደንግጣ የፍፁምን የተዳከመ የከፋዉ የሚመስል ፊት ለአፍታ አይታ "ዳግማዊት" አለችዉ "የአባትሽን ስምም ንገሪኝ" ፍፁም መጀመርያ የቤዛዊትን ስም ሲጠይቃትም እንደዚህ ነበር ያላት ዳግማዊት ማን ነዉ ምን ፈልጎ ነዉ...በሚል የጥርጣሬ አይን እያየችዉ "ዳግማዊት ፍፁም" እያለችዉ አያቷ "ከማን ጋር ነዉ ደሞ የምታወሪዉ" እያሉ ወደ ደጅ ሲወጡ አብራዉ የቆመችዉን ሰዉዬ ተመለከቱት እርጅናዉ በርቀት አላሳይ እያለ ስለሚያስቸግራቸዉ በጣም ቀርበዉ ተጠግተዉ እያዩት "ማን ነህ አንተ" ፊቱ ዉስጥ የተደበቀ የበፊቱ ፍፁም እየታያቸዉ "ዉይ ዉይ አፈር በበላሁ ልጄ ልጄ ልጄ" ማልቀስ ጀመሩ ለፍፁም ሳይሆን ከሞተች አመታቶች ያለፋት ቤዛዊት ፍፁምን ሲያዩት ፊታቸዉ ላይ ድቅን ብላባቸዉ እንጂ። ፍፁም የቤዛዊት በህይወት አለመኖር ዉስጡ እየነገረዉ ነበር ወደ ቤት ዉስጥ እያለቀሰ ገብቶ ተቀመጠ ማዉራት አቅቶት በአይኑ ዳግማዊትን አያት አይኖቿ ላይ ለማታዉቃት ለወለደቻት እናቷ እንባወች ይታዩበታል ከተቀመጠበት ተነስቶ ተጠጋት "ዳግማዊት አባትሽ ነኝ" አቀፋት ወደ ደረቱ አስጠግቶ የብዙ አመት ናፍቆቱን ሀሳቡን በለቅሶ እየተንሰቀሰቀ ልጁን አቅፎ ማንባት ቀጠለ ቤዛዊት አለመኖሯን የሚያስረሳ ምትክ ስለሰጠችዉ ልጁን ደግሞ ደጋግሞ አቀፋት እስከ ህይወቱ ማብቅያ ለልጁ ለመኖር ቃል እየገባ። ♾ተፈፀመ♾ #ታሪኩ ይሄን ይመስላል...🕹ምስጋና :-ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ! 📬በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች 📮አስተያየት መስጫ📮 የሚለውን በመንካት አድርሱን!
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስር : ...ቤዛዊት ግን አልነበረችም ምግቡን መሶብ ዉስጥ አስቀምጠዉ ጉዋሮ ለጎዋሮ ቤዛዊትን አሰሷት ወደ ዉጪም ወጥተዉ አላፊ አግዳሚዉን ቤዛዊትን ያየ በማለት ጠየቁ ነገር ግን ቤዛዊት የዉሀ ሽታ ስለሆነች ወደ ቤታቸዉ በረንዳ ተመልሰዉ ተቀምጠዉ በነጠላቸዉ እያበሱት ነገር ግን የሚፈስ ድምፅ የሌለዉ የእዉነት እንባ ማንባት ጀመሩ። ማልቀሱ ብቻዉን ግን ትርጉም እንደሌለዉ ሲገባቸዉ ቤዛዊትን ፍለጋ አስበዉ ሲቆሙ ቤዛዊት ከዉጪ እየገባች አጠገባቸዉ ቆመች ፊቷ ላይ ደስታ ይነበባል ደረቷ እንደማበጥ ብሏል እማማ ስንቅነሽን በፍቅር አይን እያየቻቸዉ ደረቷ ዉስጥ የደበቀችዉን ብዛት ያለዉ ብር አዉጥታ ደንግጠዉ የቋሙት እማማ ስንቅነሽ እጅ ላይ አስቀመጠችዉ። (ከደቂቃወች በፊት) ቤዛዊት ከፀበል ስትወጣ ቅልል የሚል ስሜት እየተሰማት ነበር አይምሮዋም ሙሉ ለሙሉ ባይባልም እየስተካከለ ማሰብ ማገናዘብ እየጀመረች ነበር ቤት ገብተዉ እማማ ስንቅነሽ በሀሳብ እርቀዉ ሲሄዱ አስተዋለቻቸዉ ባዶዉን መሶብ ሲከፍቱ እንደቸገራቸዉ ገባት ለዛም ነዉ አይን ላይን የተያዩት ገዥቼ መጣሁ ሲሏት ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸዉ አሰበች እሳቸዉ እንደወጡ እስዋ ቦርሳዋን መፈለግ ጀመረች ዉስጡ ብር እንደሌለዉ ስታይ ተናደደች ነገር ግን የባንክ ደብተሯን ስላየችዉ እና ማዉጣት እንደምትችል ሲገባት እየተቻኮለች ወጣች" አሁን እማማ እጃቸዉ ላይ ያለዉን ብር እያዩ ደንግጠዉ እና ከየት አምጥታዉ ሊሆን እንደሚችል እያሰቡ "ከየት አመጣሽዉ ልጄ" አሏት "የኔ ነዉ ከባንክ አዉጥቼዉ ነዉ" አለቻቸው ደስታ ባዘለ ንግግር አላመኗትም ተጠራጠሯት ከሰዉ ነጥቃ ቀምታ ያመጣች መስሏቸዉ ነበር እየተሻላት እንደመጣ ግን በንግግሯ በሁኔታዋ እያረጋገጡ ሲመጡ አምነዋት ተያይዘዉ ወደ ዉስጥ ገቡ። እማማ ስንቅነሽ በቤዛዊት የጤና ለዉጥ ደስተኛ ሆነዋል ማስታመማቸዉን ፍቅራቸዉንም ሳይቀንሱ ከጎኗ ናቸዉ ቤዛዊትም ከቀን ወደ ቀን ፍፁም ጤነኛ እየሆነች ነዉ አስተሳሰቧም ወደ ጤነኝነት ተመልሷል እማማ ቤዛዊትን ያገኟትን ቀን አስታወሱ እርቃኗን ብርድ ላይ መንገድ ጥግ ተቀምጣ ነበር ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ ያዩዋት በሩቁ ልብስ መስጠት ምግብም ማቀበል ይችሉ ነበር ነገር ግን ከመልካምነታቸዉ ባሻገር የሆነ ሀይልም አብሯቸዉ ነበር። ለቤዛዊት መዳን ምክንያት ለመሆን ነበር የዛን ቀን ያገናኛቸዉ አንዳንድ አጋጣሚዎች አጋጣሚ የሚታለፉ ነገሮች ብቻ አደሉም ምክንያትም ዉጤትም ሊሆኑ ይችላለ። ቤዛዊት ጤናዋ እንደተመለሰ ወደ ፍፁም ጋር ሄዳ ብታስጠራዉም እሱ ማግኘት ስላልፈለገ ሳታየዉ ሳታገኘዉ ተመለሰች እንደበፊቷ ለምን አላገኘኝም ስትልግን አይምሮዋን አላጨናነቀችም አንዳንድ ነገሮች በጭንቀት እና በትግል አይፈቱም ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ስትመለስ ከባንክ ብር አዉጥታ ለቤት የሚያስፈልጉ በርካታ እቃወች ገዝታ ተመለሰች እሳቸዉም ጣፋጭ ምግብ እየሰሩ እየጠበቋት ነበር። ምግቡ እስኪደርስ ለቤተሰቦቿ ስልክ ደወለች ድምፆን እንደሰሙ ድጋሜ ከሞት እንደተነሳች ቆጥረዋት በስልክ መሰማማት እስኪያቅታቸዉ ተጯጯሁ እናቷ እና እህቷ አሁን ካልመጣን ያለሽበትን ነገሪን ስላሏት ቤዛዊት የእማማ ስንቅነሽን ቤት አቅጣጫ ነግራቸዉ በደስታ ስልኩን ዘጋችዉ። ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ምግቡ ቀርቦ እየበሉ እማማ ማጉረስ ሲያበዙባት "ጠገብኩ በአንድ ጉርሻ" እያለቻቸዉ የማጥወልወል ስሜት ስለተሰማት ከገበታዉ ተነስታ እየተንደረደረች ማስታጠብያ ፈልጋ የጎረሰችዉን እንዳለ እየተፋች። "ሆዴን ሳያመኝ አይቀርም" አለች ትንሽ እንደ ቦርጭ ገፋ ያለዉን ሆዷን ዳበስ እያረገች እማማ ስንቅነሽ ግን ልብ ብለዉ ሁኔታዋን ሲያስተዉሉት ነበር የሰዉነቷ ቅርፅ ለዉጥ ማስመለሷ ሁሉ ነገር ለቤዛዊት ባይገባትም እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊት ማርገዝ ታዉቋቸዉ ነበረ። ፍፁም ካለችዉ ሰዉ ይሁን ከተረገመዉ ልጃቸዉ ያወቁት ነገር ባይኖርም። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ...እየተጣደፈች ወጣች መንገድ ላይ በደስታ ብዛት ፊቷ ላይ ጤነኛ የሆነ ፈገግታ እየታየባት ወደ ማረምያ ቤቱ ከመግባቷ በፊት ከለመደችዉ ምግብ ቤት ምግብ አስቋጥራ አዲስ ህይወት አዲስ ጅማሬ እንዳገኘ ሰዉ መንፈሷ ብሩህ ሆኖ ስትከንፍ ደርሳ ፍፁምን አስጠርታዉ በሽቦ በታጠረዉ ክልል አሻግራ የፍፁምንን መምጣት መጠባበቅ ጀመረች። ፍፁም የጀመረዉን የህይወቱን መፅሀፍ እየፃፈ የእሱ መታሰር ከቤዛዊት በአካል እርቋ ተስፋዉ ጨልሞ ፍቅራቸዉ ያሰበዉ ሳይሆን በጅምር ቀርቶ እሱም እሷም በየራሳቸዉ መንገድ ላይ ተራርቀዉ መቅረታቸዉን ፅፎ እስከዛሬ ቀን ያለዉን የህይወቱን ምስቅልቅል ወረቀቱ ላይ ካሰፈረ በኋላ ወደ ፊት የሚፈጠረዉ ስለማይታወቅ የታሪኩን ፍፃሜ ገና እያየ የሚቀጥለዉ ስለሆነ በተቀመጠበት እየተከዘ የስሙን መጠራት ገና እንደሰማ ተስፈንጥሮ ቆሞ በደስታ ልቡ ጮቤ እየረገጠ እየጨፈረ መራመድ ጀመረ። ከቤዛዊት ዉጪ ማንም ሊጠይቀዉ እንደማይመጣ ልቡ ስለዋቀዉ ነዉ መደሰቱ ካስከፋት ቀን ጀምሮ የእሷን መምጣል በጉጉት በልመና ሲጠብቅ ስለነበር አይኖቿ እየናፈቁት አየተደሰተ ወደ ዘመድ መጠየቅያዉ ስፍራ ደረሰ። አይን ለአይን በርቀት ሲተያዩ ሁለቱም ፊት ላይ ብልጭ ብሎ የጠፋ ፈገግታ ታየ አይናቸዉ ሳይነቀል ተጠጋጉ በተወሰነ እርቀት ተጠጋግተዉ አቅራቢያቸዉ ያለች የማረምያ ቤቱ ፖሊስ ቤዛዊት የያዘችዉን ምግብ ለፍፁም ጎርሳ እንድታቀብለዉ በማንክያ ውስጡን ነካ ነካ ካረገች በኋላ ነገረቻት ቤዛዊት መጠነኛ ጉርሻ በአፍዋ እያኘከች "እንዴት ነህ ፍፄ" እያለች ምግቡን አቀበለችዉ አፏ ላይ የያዘችዉ ምግብ አላስወራ ስላላት ተረጋግታ አኝካ እዋጠችዉ ፍፁም በደስታና በፍቅር እያያት ነበር ፊቷ ላይ የማይነበብ ፍፁም ሰላም ይነበብባታል ጤናዋ እንደተስተካከለ ገምቶ በልቡ ተመስጌን እያለ የአፍ አመል ስለሆነ "ደህና ነኝ አንቺስ እንዴት ነሽ?" ተነፋፍቀዋል መሀላቸዉ ላይ ግን የሚያስተያይ ነገር ግን የማያገኛኝ አጥር አለ እስርም እንደዚህ ነዉ "ልጅ ልወልድልህ ነዉ" እያለች እጆቿን ወደ ሆዷ ሰዳቸዉ ሆዷን በቀስታ መዳበስ ጀመረች ፍፁም መልስ ሳይሰጣት አብረዉ ያደሩበትን ቀን አስታወሰ ተሽሎት ከሆስፒታል የወጣቀን አሰላዉ አንድ ወር ከሳምንት አካባቢ "እርግጠኛ ነሽ ሀኪም ቤት ሄደሽ ነበር? " ጠየቃት በማመን እና ባለ ማመን መሀል ባለ ግር የማለት ስሜት ዉስጥ ሆኖ ቤዛዊት ፊቷን ከላይ ወደ ታች እየነቀነቀች "አዎ የአንድ ወር ከሰባት ቀን ልጅ ሆዴ ዉስጥ አለ" ፍፁም ጥርጣሬዉ እነደጉም በኖ ጠፋ በቤዛዊት እና በእሱ አንድ አምሳል እንዳለ ልቡ አሰየነገረዉ ፊቱ በደስታ እየፈካ ጣቶቹን በአጥሩ ላይ እደገፈ ባይነካኩም እሷም በሱ ትይዩ እጆቿን ዘረጋች "እወድሻለሁ " ሲል በቀስታ አወራ "እኔም እወድሃለሁ " የእሷ ድምፅ ከሱ በጣም ቀንሶ በዉስጡ አብረሀኝ ከጎኔ ብትሆን ልጃችንን አብረን እናሳድግ የሚል አስተያየት አብሮት ነበረ። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስራ_አራት ...አብረን እናሳድግ በሚል አስተያየት ቤዛዊት እና ፍፁም ለደቂቃዎች ቃላት ሳያወጡ ማሃላቸዉ ባለዉ ሽቦ በአይኖቻቸው እየተያዩ ነገር ግን ሁለቱም ልቦቻቸዉ ተጨንቀዉ ሀዘን የተበረዘበት ፍንጣቂ ደስታን ተሸክመዉ በአይኖቻቸዉ ፍቅርን አብሮ መሆንን ተርበዉ ጥቂት ከተያዩ በኋላ "ልጃችንን ወልጄ በፍቅር አሳድገዋለሁ" ቤዛዊት ይሄን ስታወራ የእንባ ሳግ አፍዋ ዉስጥ እንቅ እያረጋት ለማልቀስ እያኮበኮበች ነበር ፍፁም ከእስር የመፈቻ ጊዜዉ በጣም እሩቅ ስለሆነ ያለእሱ የምታሳለፍቻዉ አመታት እየታያት በተለይ ያ ጠይም መጀመርያ የትምህርት ቤቱ በር ላይ አይታዉ ደስ ብሏት ሰአት የጠየቀችዉ ነገሮችን ያስተማራት የመከራት ህመሟን ችሎ እያስታመማት ስታጠፋ ስትበድለዉ ከጎኗ ያልራቃት ሁሉ ነገሯ የሆነዉ ፍፁም በእሷ ህይወት በተያያዘ ጉዳይ በድንገተኛ ፀብ የሰዉ ነብስ አጥፍቶ ለእስር ተዳርጎ ፊት ለፊቷ ቆሞ ስታየዉ ልጅ ከእሱ ማርገዟን የደስታ ዜና ይዛ እንኳን ደስታዋ ሙሉ ሊሆን አልቻለላትም የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ልቦናዋ ያዉቀዋል የጎደለዉ ፊት ለፊቷ የቆመዉ የቀድሞዉ አስተማሪ ፍፁም ደምሴ ነበር። "የምታለቅሺ ከሆነ እቀየምሻለሁ" ፍፁም ቆጣ ሲልባት ማልቀሷን ተወችዉ ከቤዛዊት ጋር እንደተለያየ ፍፁም ልጁን መዉለዷ መልካም ነዉ ወይ ሲል እራሱን ጠየቀ ባትወልደዉ እና ወደ ፊት ሌላ ጥሩ አሳቢ መልካም ባል አግብታ ከእሱ ብትወልድ እያለ አስቦ ነበር ቤዛዊት ወልጄ በፍቅር አሳድገዋለሁ ያለችውን ሲያስታዉስ ሀሳቡን በምንም ተአምር እንደማትቀበለዉ ሲገባዉ ያሻዋን ታርግ ሲል ማሰቡን እርግፍ አርጎ ተወዉ። መታሰር ከማሰብ ባያግድም ከተግባር ግን ስለሚያግድ ከጎኗ ሆኖ ምንም ሊያረግላት ስለማይችል ለመምከር ይሞክራል እንጂ እሷ የፈቀደችዉን ሁሉ እንድታረግ ከልቡ ፈቅዶላት ነበር ቤዛዊት ፍፁምን ጠይቃዉ እየተመለሰች መንገድ ላይ ለፍፁም የነገረችዉን የምስራች ለቤተሰቦቿም መናገር እንዳለባት ገምታ የሚሰጡዋትን መልስ ለመስማት ጉዋጉታ ወደ ቤቷ አመረች ። ቤት ዉስጥ ሁሉም ተሰብስበዉ ምግብ ቀርቦ ከተመገቡ በኋላ ማእዱ ተነስቶ ቡና ለመጠጣት አየጠበቁ ቤዛዊት "የምነግራችሁ ትልቅ ጉዳይ አለ" የሁሉም ሰዉ ጆሮ እና ቀልብ እሷ ላይ አረፈ። ቤዛዊት በሽታዋ የተነሳባት አሁን ደሞ ምን ልትለን ይሆን እያሉ ነበር ቤተሰቦቿ ቤዛዊት ወሬዉን ከመጀመሯ በፊት ኮስታራዉን አባቷን በቀስታ አይታቸዉ "ይሄን የምነግራችሁ እናንተ የኔ የምወዳችሁ ቤተሰቦቼ ስለሆናችሁ ስለማከብራችሁም ነዉ ነገር ግን የራሴን ዉሳኔ እንድትጋፉኝ አልፈልግም.." ትንፋሽ ለመሳብ ንግግሯን ገታ አረገች እናት እና አባቷ እየተያዩ ነበር ቀጥላ የምትለዉ ለመስማት ወደ ዋና ሀሳቧ እንድትገባ አስበዉ ምን ልትላቸዉ እንደ ሆነ ለመገመት እንኳን ስላልቻሉ ታላቅ እህቷ ከተቀመጠችበት ተነስታ ከቤዛዊት አጠገብ ቆማ እህቷን እያቀፈቻት "ምን ለመናገር ፈልገሽ ነዉ ምንም ይሁን ግን እኔ ሁሌም ከጎንሽ አለሁ" ድጋፏን አቅፋ ገለፀችላት ቤዛዊት ካቆመችበት አንገቷን ወደ መሬት አቀርቅራ "እኔና ፍፁም ልጅ ልንወልድ ነዉ" ይህንን እንዳለች አባቷ ከተቀመጡበት ተነስተዉ ቆመዉ "እየቀለድሽ መሆን አለበት ከነብሰ ገዳይ አርግዣለሁ እያልሽን ባልሆነ" የፌዝ ሳቅ እየሳቁ ቤዛዊት ካቀረቀረችበት አንገቷን ቀና እያረገች አባቷን እያየቻቸዉ "አባ አብጄ ታምሜ እኔን ማየት ካልወደድክ የኔን ተስፋ የኔን ፍላጓትን ለማሙዋላት ምን የሚይዝህ ነገር አለ ነዉ የኔ ሀዘን እንጂ ደስታዬ ትርጉም አይሰጥህም" ቤዛዊት አባቷን እንዴት ታስረዳቸዉ በምንም ሊረዷት አይችሉም በቆመችበት ልብሶቿን እያወላለቀች "ይሄ ከሆነ የሚያስደስትህ ኡ ኡ እያልኩ ከዚህ ቤት አወጣለሁ" ቤዛዊት ሆን ብላ የአባቷን ልብ ለማየት ነበር ይሄንን ማረግ የጀመረችዉ ያሰበችዉም ተሳካላት አባቷ ልብስ እያወላለቀች ሲያይዋት ተጠግተዉ ያወለቀችዉን ልብስ እንድትለብስ እየረዷት "ያንቺን ደስታ እነጂ ሀዘንሽን መቼም አስቤ አላዉቅም" ሲሏት ቤዛዊት የጀመሩትን ወሬ ሳታስጨርስ አቀፈቻቸዉ። ሊጠናቀቅ ሁለት ክፍል ይቀረዋል። ይቀጥላል... SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ...አቀፈቻቸዉ እናቷ መቼም ቢሆን የእሷን ፍላጎት ተጋፍተዉ ባያዉቁም ትምህርትን ሳትመረቅ ልጅ ለመዉለድ በመቸኮሏ ቅር ቢሰኙም አጣሁዋት አይምሮዋ ተቃዉሶ ተቀጨችብኝ ብለዉ ካዘኑበት በርካታ አመታት ጤናዋ ተመልሶ ከፊታቸዉ ቆማ የልጅ ልጅ ላሳያችሁ ነው ማለቷ ለእሳቸዉ አለም ነበር የሚያስጨንቃቸዉ ሁሌ የልጃቸዉ ጤንነት ብቻ ስለነበር። ትምህርት ስራ ገንዘብ ሀብት ....የህይወት መስመሮች ዉስጥ ያሉ መንገዶች ሊሆኑ ይችላሉ ዋናዉ የህይወት ዋስትናችን ግን ጤንነታችን ላይ የተመረኮዘ ነዉ። የቤዛዊት ሆድ ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ፍፁም ጋር በየሳምንቱ ሳትቀር የሚያስፈልገዉን ይዛ እየጠየቀችዉ የመዉለጃዋ ስዓት ሲቃረብ የህመም ስሜትም ጀመራት። በበፊቱ የአይምሮ ህመሟ ወቅት እሷ ሳይታወቃት ስትወድቅ ስትነሳ ሰዉነቷ ልጁን ለመቋቋም አልቻለም ነበር ሆድዋ አካባቢ ቀላል የህመም ስሜትን እየተሰማት መራመድም እያቃታት ፍፁምን መጠየቅ እየፈለገች ነገር ግን ከአቅሟ በላይ ስለሆነ ቤት ዉስጥ እራሱ ጉድ ጉድ ማለቱ ሲያቅታት ቤተሰቧቿ ወደ ሆስፒታል ወሰዷት። የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ሆና ቤዛዊት እህቷን "ወረቀት እና እስኪርቢቶ አቀብይኝ" አለቻት "ምን ልትፅፊ ነው ደሞ" እያለች እስኪርቢቶ ከቦርሳዋ አዉጥታ ወረቀት ስላጣች "ወረቀት ግን የለኝም ቤዚ" ቤዛዊት ፊት ላይ እርግዝናዉ ይሆን ባልታወቀ ሁኔታ ተለዋዉጣለች ጉንጮቿ ቀልተዋል የአይኖቿ ቆቦች ወፍረዉ አይኗን መግለጥ ያቃታት ነዉ የምትመስለዉ "ለፍፁም የምፅፍለት ነገር ነበር ተይዉ በቃ ልጄን ወልጄ አንድ ላይ ከልጄ ጋር ስንሄድ እነግረዋለሁ" አለችና በትግል ለመሳቅ እየሞከረች "የልጄን ስም ዳግማዊት ፍፁም ብላትስ" እህቷን እየጠየቀቻት የእንሽርት ዉሀዋ ፈሰሰ። የማዋለጃ ክፍል ዉስጥ ሀኪሞቹ ቤዛዊትን ለማዋለድ ጥረት እያረጉ ነዉ ቤተሰቦቿ በረንዳ ላይ ሆነዉ በጭንቀት የልጃቸውን ሁኔታ ለማወቅ ከወድያ ወዲህ ይንጓማለላሉ ቤዛዊት የምጥ ጩሀት ተጮሀለች "ኡ ኡፍ ኡ ኡ " ጩሀቷን ዉጪ የሚሰሙት እናቷ መቆም ስላልቻሉ አንጀታቸዉን እስር አርገዉ ተቀመጡ አባቷ በሀሳብ ጭልጥ ብለዉ ሄደዋል እህቷ በፍርሀት እርዳለች የቤዛዊት ሁኔታ አወራሯ አልጣማትም ነበር። ፍፁም በየሳምንቱ መምጣት አስለምዳዉ ስትቀር ቅር ያለዉ ቢሆንም የሆዷን መግፋት የመዉለጃዋ ቀይ እየደረሰ ስለመጣ እየተጨነቀም ቢሆን ልጁን አቅፋ መጥታ እንደምታሳየዉ ተስፋ እያደረገ ነበር። ዶክተሮቹ እንድትበረታ እየነገሯት ነው ኦፕራሲዮን ማረግ የፈሩ ይመስላሉ ቤዛዊት ለመጨረሻ ጊዜ ስትጮህ ከሆዷ አዲስ ሰዉ አዲስ ፍጥረት ወደ አለም ቀላቅላ በዛችዉ ቅፅበት የእሷ ህይወት ግን ከዚህ አለም ሾልኮ ሄዶ በድን ሆና ነበር (ከደቂቃዎች በፊት) ቤዛዊት በአልጋ እየተገፋች ወደ ማዋለጃ ክፍል ከመግባቷ በፊት በተኛችበት ሆና ቀና ማለት እየከበዳት ከርታታ አይኗን ለመግለጥ እየታገለች ቤተሰቦቿን ተሰብስበዉ ለአፍታ አየቻቸዉ እናቷ እየሮጡ የሚገፋዉ አልጋ ላይ ደርሰዉ እጇን ለመሳም ሲሞክሩ ቤዛዊት ቃል ከአፏ አወጣች "ልጄን አደራ ልጄን አ ደ ራ" ሁሉ ነገር የታያት ይመስል ነበር። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር : #ምዕራፍ_ሀለት ፡ #ክፍል_ስምንት ፡ ...ብርድ ልብሱን መሬት ላይ ጣለዉ ጌታቸዉ የለበሰዉን ሱሪ እያወለቀ ከእንቅልፏ ያልነቃችዉን አይምሮዋ በትክክል እያሰበ ያልሆነዉ ምስኪኗ በሽተኛዋ ቤዛዊት ላይ ተከመረባት የቤዛዊት አይኖች በድንጋጤ አብርተዉ መቁለጭለጭ ጀመረች የት እንዳለች ለማስታወስ አልቻለችም እላይዋ ላይ የተከመረ ነገር እንዳለ ለማዉረድ እየታገለች ነበር አቅም ግን እያነሳት ሲመጣ ዝልፍልፍ ብላ ተሸንፋ የጌታቸዉ መጫወቻ ሆነች። ቀሚሷን አዉልቆ የዉስጥ ሱሪዋን እያወለቀዉ መታገሏን ስላቆመች "ምን አስባ ነዉ" ብሎ ለአፍታ ተመለከታት አንገቷ ወደ ቀኝ ዘመም ብሎ በትራስ ተደግፎ ከአፏ ምራቅ ይወርዳል አይኗቿ እንደቀሉ ናቸዉ ህመሟ ብሶባታል እሷ አደለችም ስትታይ አንጀት ትበላለች እላይዋ ላይ የተከመረዉ ሰዉ ግን ስሜቱ አሸንፎት ህመሟ አይታየዉም ቢታየዉም ምንም አልመሰለዉም የእሱንም የዉስጥ ሱሪ ቀስ ብሎ አዉልቆት ተገናኛት እላይዋ ላይ መጨፈር ጀመረ የቤዛዊት አይኖች ግን ካረጀዉ ኮርኒስ ዉስጥ የሚፈሩት አይጥ መኖር አለመኖሩን ፈዘዉ እያዩ ይመራመራሉ። ፍፁም በጠዋት ቤዛዊት ያመጣችለትን ምግብ ሊበላ ሲከፍተዉ እስረኞች አብረዉት ሊበሉ ከበቡት ከእነሱም መሀል ፎጣ አናቱ ላይ የማይለየዉ ማስረሻ ሁሉ ነገር አብቅቷል የትላንቱ ፀብ ተረስቷል ብሎ ለመጉረስ እጁን ዘረጋ ነገር ግን በዘረጋዉ እጁ እንጀራ ጠቅልሎ ወደ አፉ እያስጠጋ የፍፁም ቡጢ አርፎበት እጁ ላይ የነበረዉ ምግብ ተበታተነ ማስረሻ ግን ለመማታት እጁን አልዘረጋም የተቀጡት ቅጣት አስተምሮት ነበር ፍፁም አንድ ቡጢ ሰንዝሮ አልበቃዉም ማስረሻ ሆድ ላይ ተቀመጠ በተመሳሳይ ስዓት ቤዛዊት ገላ ላይ ጌታቸዉ ተቀምጧባት ነበር ፍፁም እየደጋገመ ቦክስ መሰንዘር ማስረሻን ማድማት ጀመረ በዛዉ ሰዐት የታመመችዋ ቤዛዊት ምስኪን ልብ እየደማ ነበር ፍፁምን እስረኞች ተረባርበዉ ከማስረሻ ሰዉነት ላይ አነሱት ማስረሻ በደም ተላዉሶ እያቃሰተ ነዉ ፖሊሶች እየተሯሯጡ መጡ በአሁኑ ለፍፁም አላዘኑለትም እያዳፉ እየገፈታተሩ ከግቢዉ ይዘዉት ወጥተዉ ለብቻ ሰዉ የሚታሰርበት ጨለማ እና አስፈሪ ጠባብ ክፍል ዉስጥ ወርዉረዉ ቆለፉበት ፍፁም እራስህን አጥፋ አጥፋ የሚል ጥሪ ጭንቅላቱ ዉስጥ ሲያቃጭልበት እራሱን እንዴት ማጥፋት እንዳለበት እያሰበ "መሞት አለብኝ" ሲል ደመደመ በሀሳብ ዉስጥ ሆኖ እጆቹን ወደ ኪሱ ሲከት የእሱን እና የቤዛዊትን ከመጀመርያው ጀምሮ የያዘዉን ወረቀት ነካዉ አዉጥቶ በደበዘዘ ብርሀን ለማንበብ ሞከረ ወደ ቤቴ እያነከስኩ ስገባ አልገዬ ላይ ተኝታ ጠበቀችኝ ሳያት ደስ አለኝ አጠገቧ እንዳልቀሰቅሳት ተጠንቅቄ ተኛሁ ነገር ግን ነቅታ በአይኖቿ እያየችኝ የዛን ለት ክብሯን ሴትነቷንም ሰጠችኝ..... ይሄንን አያነበበ የመሞት ሀሳቡ ከልቦናዉ ተገፎ እላዩ ላይ ለዉጦት የነበረዉ የተለየ ፀባይ ጠፍቷ የድሮዉ ፍፁም እየሆነ "ፈጣሪ እስኪወስደኝ አልተዋትም " ሲል በልቡ ቃል ገባ ጌታቸዉ በጀብደኝነት የቤዛዊትን እርቃን ገላ እየዳሰሰ ከላይዋ ላይ ተነስቶ ወደ መሬት ወርዷ በድጋሜ ተመለከታት ልብሷን እንኳን ለመልበስ አልሞከረችም አይኖቿ ኮርኒሱ ላይ ተተክለዉ ደርቃ ቀርታለች እየተገላመጠ ሱሪዉን ለባብሶ ወደ ዉጪ ወጣ ከደቂቃወች በኋላ ሲመለስ ቤዛዊት ሲወጣ እንዳያት አሁንም ደርቃለች ደስ አለዉ የሰራዉ ክፉ ስራ እነደማይጋለጥበት እረግጠኛ ሆነ በመታመሟ ሊያዝንላት ሲገባ ተደሰተ በታመመች ልክና እራሷን ባልቻለች ወቅት ሁሉ የእሱ ሀጥያት ተደብቆ የሚቆይ የማይታወቅበት ስለመሰለዉ ተደሰተ እርቃን ገላዋ አሁንም የተረገመ አይኑ ዉስጥ ስለገቡ እየተቻኮለ ሀጥያቱን ደገመዉ ሲጨርስ ቤዛዊትን ልብሷን አለባብሶ ከላይ ብርድ ልብስ ደርቦላት ምንም እንዳልተፈጠረ ወጥቶ ሊሄድ ሲል እማማ ስንቅነሽ ደረሱ። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስር : ...ቤዛዊት ግን አልነበረችም ምግቡን መሶብ ዉስጥ አስቀምጠዉ ጉዋሮ ለጎዋሮ ቤዛዊትን አሰሷት ወደ ዉጪም ወጥተዉ አላፊ አግዳሚዉን ቤዛዊትን ያየ በማለት ጠየቁ ነገር ግን ቤዛዊት የዉሀ ሽታ ስለሆነች ወደ ቤታቸዉ በረንዳ ተመልሰዉ ተቀምጠዉ በነጠላቸዉ እያበሱት ነገር ግን የሚፈስ ድምፅ የሌለዉ የእዉነት እንባ ማንባት ጀመሩ። ማልቀሱ ብቻዉን ግን ትርጉም እንደሌለዉ ሲገባቸዉ ቤዛዊትን ፍለጋ አስበዉ ሲቆሙ ቤዛዊት ከዉጪ እየገባች አጠገባቸዉ ቆመች ፊቷ ላይ ደስታ ይነበባል ደረቷ እንደማበጥ ብሏል እማማ ስንቅነሽን በፍቅር አይን እያየቻቸዉ ደረቷ ዉስጥ የደበቀችዉን ብዛት ያለዉ ብር አዉጥታ ደንግጠዉ የቋሙት እማማ ስንቅነሽ እጅ ላይ አስቀመጠችዉ። (ከደቂቃወች በፊት) ቤዛዊት ከፀበል ስትወጣ ቅልል የሚል ስሜት እየተሰማት ነበር አይምሮዋም ሙሉ ለሙሉ ባይባልም እየስተካከለ ማሰብ ማገናዘብ እየጀመረች ነበር ቤት ገብተዉ እማማ ስንቅነሽ በሀሳብ እርቀዉ ሲሄዱ አስተዋለቻቸዉ ባዶዉን መሶብ ሲከፍቱ እንደቸገራቸዉ ገባት ለዛም ነዉ አይን ላይን የተያዩት ገዥቼ መጣሁ ሲሏት ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸዉ አሰበች እሳቸዉ እንደወጡ እስዋ ቦርሳዋን መፈለግ ጀመረች ዉስጡ ብር እንደሌለዉ ስታይ ተናደደች ነገር ግን የባንክ ደብተሯን ስላየችዉ እና ማዉጣት እንደምትችል ሲገባት እየተቻኮለች ወጣች" አሁን እማማ እጃቸዉ ላይ ያለዉን ብር እያዩ ደንግጠዉ እና ከየት አምጥታዉ ሊሆን እንደሚችል እያሰቡ "ከየት አመጣሽዉ ልጄ" አሏት "የኔ ነዉ ከባንክ አዉጥቼዉ ነዉ" አለቻቸው ደስታ ባዘለ ንግግር አላመኗትም ተጠራጠሯት ከሰዉ ነጥቃ ቀምታ ያመጣች መስሏቸዉ ነበር እየተሻላት እንደመጣ ግን በንግግሯ በሁኔታዋ እያረጋገጡ ሲመጡ አምነዋት ተያይዘዉ ወደ ዉስጥ ገቡ። እማማ ስንቅነሽ በቤዛዊት የጤና ለዉጥ ደስተኛ ሆነዋል ማስታመማቸዉን ፍቅራቸዉንም ሳይቀንሱ ከጎኗ ናቸዉ ቤዛዊትም ከቀን ወደ ቀን ፍፁም ጤነኛ እየሆነች ነዉ አስተሳሰቧም ወደ ጤነኝነት ተመልሷል እማማ ቤዛዊትን ያገኟትን ቀን አስታወሱ እርቃኗን ብርድ ላይ መንገድ ጥግ ተቀምጣ ነበር ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ ያዩዋት በሩቁ ልብስ መስጠት ምግብም ማቀበል ይችሉ ነበር ነገር ግን ከመልካምነታቸዉ ባሻገር የሆነ ሀይልም አብሯቸዉ ነበር። ለቤዛዊት መዳን ምክንያት ለመሆን ነበር የዛን ቀን ያገናኛቸዉ አንዳንድ አጋጣሚዎች አጋጣሚ የሚታለፉ ነገሮች ብቻ አደሉም ምክንያትም ዉጤትም ሊሆኑ ይችላለ። ቤዛዊት ጤናዋ እንደተመለሰ ወደ ፍፁም ጋር ሄዳ ብታስጠራዉም እሱ ማግኘት ስላልፈለገ ሳታየዉ ሳታገኘዉ ተመለሰች እንደበፊቷ ለምን አላገኘኝም ስትልግን አይምሮዋን አላጨናነቀችም አንዳንድ ነገሮች በጭንቀት እና በትግል አይፈቱም ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ስትመለስ ከባንክ ብር አዉጥታ ለቤት የሚያስፈልጉ በርካታ እቃወች ገዝታ ተመለሰች እሳቸዉም ጣፋጭ ምግብ እየሰሩ እየጠበቋት ነበር። ምግቡ እስኪደርስ ለቤተሰቦቿ ስልክ ደወለች ድምፆን እንደሰሙ ድጋሜ ከሞት እንደተነሳች ቆጥረዋት በስልክ መሰማማት እስኪያቅታቸዉ ተጯጯሁ እናቷ እና እህቷ አሁን ካልመጣን ያለሽበትን ነገሪን ስላሏት ቤዛዊት የእማማ ስንቅነሽን ቤት አቅጣጫ ነግራቸዉ በደስታ ስልኩን ዘጋችዉ። ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ምግቡ ቀርቦ እየበሉ እማማ ማጉረስ ሲያበዙባት "ጠገብኩ በአንድ ጉርሻ" እያለቻቸዉ የማጥወልወል ስሜት ስለተሰማት ከገበታዉ ተነስታ እየተንደረደረች ማስታጠብያ ፈልጋ የጎረሰችዉን እንዳለ እየተፋች። "ሆዴን ሳያመኝ አይቀርም" አለች ትንሽ እንደ ቦርጭ ገፋ ያለዉን ሆዷን ዳበስ እያረገች እማማ ስንቅነሽ ግን ልብ ብለዉ ሁኔታዋን ሲያስተዉሉት ነበር የሰዉነቷ ቅርፅ ለዉጥ ማስመለሷ ሁሉ ነገር ለቤዛዊት ባይገባትም እማማ ስንቅነሽ የቤዛዊት ማርገዝ ታዉቋቸዉ ነበረ። ፍፁም ካለችዉ ሰዉ ይሁን ከተረገመዉ ልጃቸዉ ያወቁት ነገር ባይኖርም። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ....እማማ ስንቅነሽ ደረሱበት ቤዛዊት እዉነተኛዉ አለም ላይ አልነበረችም ህመሟ በሰራላት አለም ዉስጥ ሰምጣ ጠፍታለች አካሏ አልጋዉ ላይ ይጋደም እንጂ አይምሮዋ በትክክል እየሰራ አይደለም አይኖቿ ኮሮኒሱ ላይ ተተክለዉ የምታስበው ባይታወቅም ተክዛ እሩቅ ሄዳለች የደፈረሱት አይኖቿ ግን መደፈሯን ያወቁ የጠረጠሩ ይመስል ያልፈሰሱ እንባወች አቅርረዋል የተንጨባረረዉ ፀጉሯ ትራሱ ያስጠላዉ ይመስል ተመነቃቅሮ ይታያል። እማማ ስንቅነሽ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ የጠረጠሩት የልጃቸዉ ፊት ላይ የመደናገጥ የመቻኮል የመቅበዝበዝ ምልክት እንዳዩ ነው። "ምን አረካት አንተ አዉሬ" ሲሉ ልጃቸዉ ላይ ጮሁበት "ምንም ምንም" እያለ እናቱን ገፍቷቸዉ ሊወጣ ሲል ቤዛዊት ከተኛችበት አልጋ ተነስታ ስትቆም ሁለቱም ዞረዉ አዩዋት ቤዛዊት በቆመችበት አይኖቿን ወደ መሬት ልካ የምትፈልገዉ ነገር ያለ ይመስል ዙርያዋን ስታስስ ቆይታ ጥግ ላይ ከድስት አናት ላይ የተቀመጠ ማማሰያ አንስታ ወደ ጌታቸዉ በፍጥነት ተጠግታ ጌታቸዉን መምታት ጀመረች። ጌታቸዉ "ምን መሆኗ ነዉ ይቺ እብድ" እያለ እራሱን ለመከላከል ፊቱን በእጆቹ ሲከላከል ቆይቶ ቤዛዊትን በሀይለኛ ጥፊ መሬት ላይ ጣላት እማማ ስንቅነሽ የድረሱልኝ ጩሀት መጮህ ጀመሩ "ልጄን ገደላት ድረሱልኝ ልጄን ገደላት" ጌታቸዉ እየተንጎማለለ በፍጥነት ቤቱን ለቆ ወጣ የእማማ ስንቅነሽንም ጩሀት ሰምቶ የመጣ ማንም ሰዉ አልነበረም። እንደ እማማ አይነት መልካም ልብ ሲኖርህ ለልጄ ለዘመዴ እያልክ አትወግንም ለእዉነት ብቻ ነዉ የምትቆመዉ። ጌታቸዉ ከዛን ቀን በኋላ ወደ ቤቱ አልተመለሰም ምን አልባት አደጋ ደርሶበት ሊሆን ይችላል አልያ ስራ አጊንቶ ቀንቶት ሌላ ቦታ እየኖረ ከሆነ እንኳን ጤነኛ አይምሮ ኖሮት ይኖራል ብሎ ማመን ይከብዳል። እማማ ስንቅነሽ እንግዳ የሆነች በህይወት የሌለች የልጃቸውን አምሳል የምትመስል ምስኪን ልጅ ይዘዉ ተሰቃዩ በየፀበሉ ፈጣሪን እየለመኑ መንከራተት ቤዛዊትን ከጉያቸዉ ሳይነጥሉ የጎረሱትን እያጎረሷት የጠጡትን እያጠጧት አብረዋት ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ። እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በጠዋት ፀበል ይዘዋት ሄደዉ ወደ ቤት ሲመለሱ ቤዛዊት አልጋ ላይ ተቀምጣ በራሷ አለም እየዋኘች እማማ ስንቅነሽም ከጎኗ ተቀምጠዉ በሀሳብ ጭልጥ አሉ። የቤዛዊት ነገር እያሳሰባቸዉ ነዉ ትንሽ ለዉጥ ስላላዩባት ፈጣሪን ማማረር እየጀመሩ ነዉ በዛላይ የሚላስ የሚቀመስ ነገር ቤት ዉስጥ የለም እጃቸዉ ደርቋል የሚረዳቸዉ ሰዉም ጠፍቷል ከሀሳባቸዉ ሲባንኑ ወደ መሶቡ አምርተዉ ሲከፍቱት ባዶ መሆኑን አረጋገጡ "ምን አረኩህ ፈጣሪ" እያሉ ሲዞሩ ከታመመችዋ ከቤዛዊት አይን ጋር ተገጣጠሙ እንደድሮ ጤነኛ በነበረች ሰአት እንደምታያቸዉ አይነት አስተያየት ስታያቸዉ ፀበሉ ለዉጥ እንዳለዉ ጠርጥረዉ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታ እየተነበበ "ጨርሰህ ማርልኝ አይ እኔ ማማረር ብቻ ሆነ ኑሮዬ ተመስገን" እያሉ ወደ ቤዛዊት ቀርበዉ በእጃቸዉ ፊቷን ደበስበስ እያረጓት "እራበሽ አደል ሆዴ ገዝቼ መጣሁ" አሉና እያዘገሙ ወጡ ነገር ግን መግዣ ብር እንደሌላቸዉ ልባቸዉ ያዉቃል ጎረቤት ሁሌ መለመን ማስቸገር ታክቷቸዋል የማያዉቁትን ሰዉ ለመለመን ድፍረቱ ባይኖራቸዉም ቤዛዊትን በረሀብ አልገላት ነገር እኔስ ብሞትም እድሜዬን ጨርሻለሁ እያሉ ለልመና ወደ ጎዳና መጡ። "የሰዉ ፊት ለካ ዱላ ነዉ " ጥቂት እጃቸዉን ዘርግተዉ እንደቆሙ ነገር ግን በአይኑ ገርመም አርጎ እያየ የሚያልፋቸዉ እንጂ ሳንቲም የሚሰጣቸዉ ጠፍቶ ሲተክዙ አንዲት ሴት የታሰረ ምግብ በፌስታል እያደለች እሳቸዉ ጋር ደረሳ እጇን ስትዘረጋላቸዉ እያመሰገኑ ተቀብለዋት ቤት ዉስጥ ብቻዋን ጥለዋት ወደ ወጡት ወደ ቤዛዊት አመሩ። የቤቱን በር ገፋ አርገዉት እንደገቡ የቤዛዊት ቦርሳ ተከፍቶ ዉስጡ ያሉት እቃወች መሬት ላይ ተበታትነዉ አዩ ቤዛዊት ግን አልነበረችም። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ #ምዕራፍ_ሁለት : #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ...እየተጣደፈች ወጣች መንገድ ላይ በደስታ ብዛት ፊቷ ላይ ጤነኛ የሆነ ፈገግታ እየታየባት ወደ ማረምያ ቤቱ ከመግባቷ በፊት ከለመደችዉ ምግብ ቤት ምግብ አስቋጥራ አዲስ ህይወት አዲስ ጅማሬ እንዳገኘ ሰዉ መንፈሷ ብሩህ ሆኖ ስትከንፍ ደርሳ ፍፁምን አስጠርታዉ በሽቦ በታጠረዉ ክልል አሻግራ የፍፁምንን መምጣት መጠባበቅ ጀመረች። ፍፁም የጀመረዉን የህይወቱን መፅሀፍ እየፃፈ የእሱ መታሰር ከቤዛዊት በአካል እርቋ ተስፋዉ ጨልሞ ፍቅራቸዉ ያሰበዉ ሳይሆን በጅምር ቀርቶ እሱም እሷም በየራሳቸዉ መንገድ ላይ ተራርቀዉ መቅረታቸዉን ፅፎ እስከዛሬ ቀን ያለዉን የህይወቱን ምስቅልቅል ወረቀቱ ላይ ካሰፈረ በኋላ ወደ ፊት የሚፈጠረዉ ስለማይታወቅ የታሪኩን ፍፃሜ ገና እያየ የሚቀጥለዉ ስለሆነ በተቀመጠበት እየተከዘ የስሙን መጠራት ገና እንደሰማ ተስፈንጥሮ ቆሞ በደስታ ልቡ ጮቤ እየረገጠ እየጨፈረ መራመድ ጀመረ። ከቤዛዊት ዉጪ ማንም ሊጠይቀዉ እንደማይመጣ ልቡ ስለዋቀዉ ነዉ መደሰቱ ካስከፋት ቀን ጀምሮ የእሷን መምጣል በጉጉት በልመና ሲጠብቅ ስለነበር አይኖቿ እየናፈቁት አየተደሰተ ወደ ዘመድ መጠየቅያዉ ስፍራ ደረሰ። አይን ለአይን በርቀት ሲተያዩ ሁለቱም ፊት ላይ ብልጭ ብሎ የጠፋ ፈገግታ ታየ አይናቸዉ ሳይነቀል ተጠጋጉ በተወሰነ እርቀት ተጠጋግተዉ አቅራቢያቸዉ ያለች የማረምያ ቤቱ ፖሊስ ቤዛዊት የያዘችዉን ምግብ ለፍፁም ጎርሳ እንድታቀብለዉ በማንክያ ውስጡን ነካ ነካ ካረገች በኋላ ነገረቻት ቤዛዊት መጠነኛ ጉርሻ በአፍዋ እያኘከች "እንዴት ነህ ፍፄ" እያለች ምግቡን አቀበለችዉ አፏ ላይ የያዘችዉ ምግብ አላስወራ ስላላት ተረጋግታ አኝካ እዋጠችዉ ፍፁም በደስታና በፍቅር እያያት ነበር ፊቷ ላይ የማይነበብ ፍፁም ሰላም ይነበብባታል ጤናዋ እንደተስተካከለ ገምቶ በልቡ ተመስጌን እያለ የአፍ አመል ስለሆነ "ደህና ነኝ አንቺስ እንዴት ነሽ?" ተነፋፍቀዋል መሀላቸዉ ላይ ግን የሚያስተያይ ነገር ግን የማያገኛኝ አጥር አለ እስርም እንደዚህ ነዉ "ልጅ ልወልድልህ ነዉ" እያለች እጆቿን ወደ ሆዷ ሰዳቸዉ ሆዷን በቀስታ መዳበስ ጀመረች ፍፁም መልስ ሳይሰጣት አብረዉ ያደሩበትን ቀን አስታወሰ ተሽሎት ከሆስፒታል የወጣቀን አሰላዉ አንድ ወር ከሳምንት አካባቢ "እርግጠኛ ነሽ ሀኪም ቤት ሄደሽ ነበር? " ጠየቃት በማመን እና ባለ ማመን መሀል ባለ ግር የማለት ስሜት ዉስጥ ሆኖ ቤዛዊት ፊቷን ከላይ ወደ ታች እየነቀነቀች "አዎ የአንድ ወር ከሰባት ቀን ልጅ ሆዴ ዉስጥ አለ" ፍፁም ጥርጣሬዉ እነደጉም በኖ ጠፋ በቤዛዊት እና በእሱ አንድ አምሳል እንዳለ ልቡ አሰየነገረዉ ፊቱ በደስታ እየፈካ ጣቶቹን በአጥሩ ላይ እደገፈ ባይነካኩም እሷም በሱ ትይዩ እጆቿን ዘረጋች "እወድሻለሁ " ሲል በቀስታ አወራ "እኔም እወድሃለሁ " የእሷ ድምፅ ከሱ በጣም ቀንሶ በዉስጡ አብረሀኝ ከጎኔ ብትሆን ልጃችንን አብረን እናሳድግ የሚል አስተያየት አብሮት ነበረ። ይቀጥላል... ሌሎች ክፍሎችን ለማግኘት👇 SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር ፡ ምዕራፍ_ሁለት . #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ...ከማን ይሆን ብለዉ እየተጠራጠሩ የቤዛዊት ቤተሰቦች ቤዛዊትን ፈልገዉ አስፈልገዉ ስላጧት ወደ ተስፋ መቁረጥ እየተጠጉ እናቷ ነጋ ጠባ ስታለቅስ ከቤት ወጥታ የጠፋች የታመመች ልጃቸዉ በድንገት ስትደዉል ተአምር ነዉ የሆነባቸዉ አባቷ ያለችበትን እንደሰሙ ከተቀመጡት ተነስተው ወደ ዉጪ በፍጥነት እየተራመዱ ወደ መኪናቸዉ አመሩ እናቷና እህቷ እየተደናገጡ እየተደሰቱም እኋላ ኋላ እያሉ ተከትለዋቸዉ መኪናው ዉስጥ ገብተዉ እንደተቀመጡ አባቷ መኪናዉን አስነስተዉ ወደ ቤዛዊት ገሰገሱ የነገረቻቸዉ አካባቢ መኪናውን አቁመው ሁሉም ከመኪናዉ ወርደዉ የታመመች የተጎሳቆለች ወጣት ሴት እየጠበቁ ቤዛዊት የእማማ ስንቅህን የቆየ ቀሚስ ለብሳ ደንዳና ሴት ወይዘሮ መስላ ፊቷ እንደ ልጅነቷ ብርሀን እየፈነጠቀ ፊት ለፊታቸዉ ደርሳ ቆመች እናቷ እንባ እያነቡ እላይዋ ላይ ተጠመጠሙባት "ምን ነዉ ልጄ ምን በደልኩሽ" እንባቸው እየወረደ ነው "አረ ምንም አረ ምንም " ትላለች ቤዛዊት የእናቷ ማልቀስ እሷንም ሆድ እያስባሳት ማልቀስ ጀምራ እናቷ ለደቂቃወች አቅፈዋት ቆይተዉ ሲለቋት ታላቅ እህቷ በተራዋ አቀፈቻት "ደህና ነሽ አደል ቤዚ" የታናሽ እህቷን ጉንጭ እየሳመች ቤዛዊት እህቷን ትጠላት እንደነበር ከአይምሮዋ ስላልተደበቀ "ይቅርታ አርጊልኝ" እያለች ታላቅ እህቷን ለመነቻት "ምንም አደል አንቺ ብቻ እንኳን ሰላም ሆንሽ" ስትል ታላቅ እህቷ የቤዛዊትን ጉንጮች መሳም ጀመረች። አባቷ ሁሉንም እጃቸውን አጣምረዉ ሲመለከቱ ቆይተዉ "መቼም ከዚህ በኋላ ህፃን አደለሽም በምርጫሽ አልገባም" እያሉ ሊያቅፏት ተጠጉ አንዳንዴ ነገሮች ከተበላሹ በኋላ ሰዉ ሊረዳን ሊያግዘን ይሞክራል በወቅቱ ግን አይደርስልንም ፍፁም ሳይታሰር አባቷ ፍላጓቷን ቢያከብሩላት ይሄ ሁሉ ባልተፈጠረ አባቷ እጇን ይዘዉ ወደ መኪናዉ ሊያስገቧት ሲሉ ቤዛዊት "ሁለተኛዋ እናቴን ላስተዋዉቃችሁ እያለች ወደ እማማ ስንቅነሽ ቤት ይዛቸዉ ገባች። "እሳቸዉ ናቸዉ ለዚህ ያበቁኝ" ስትል አንድ በአንድ እማማ ስንቅነሽን ለቤተሰቧቿ ማስተዋወቅ ጀመረች። እማማ ስንቅነሽ በነደፈ ነጠላቸዉ ሸፍነዋታል ቁራሽ ዳቦ አካፍለዋታል በእድሜዋ ሙሉ ከፍላ የማታገኘዉ ደግነት ሰጥተዋታል ቤዛዊትም ጥላቸዉ መሄድ ስታስብ ዉስጧ ቅር እየተሰኘ እማማ ስንቅነሽን "እኛ ቤት አብረን እንሂድ እንከባከቦታለሁ" ስትል በስስት አይን እያየቻቸዉ በመሀል በሀሳብ ጭልጥ ብለዉ የጠፉት የቤዛዊት መለወጥ ጤናዋ መመለሱ ያስገረማቸዉ አባቷም "እባኮን እሺ ይበሏት ለኛም እናት ይሆኑናል ሸክም እሆንባችሁዋለሁ ብለዉ አያስቡ" ብለዉ ጨመሩበት እማማ ስንቅነሽ በሞጨሞጮ አይናቸዉ ቤታቸዉን እየቃኙት ሲያስቡ ቆይተዉ "ምን አረኩልሽና ዉለታ ዋሉልኝ ብለሽ አታስቢ የሰማይ መግቢያዬን እያደላደልኩ ነዉ" ብለዉ በነጠላቸዉ አይናቸዉ አካባቢ ዳበስ እያረጉ "ስትችይ እኔም ስለምትናፍቂኝ እየመጣሽ እይኝ " አሉና መምጣት እንደማይችሉ በሚገልፅ አኳሀን አንገታቸዉን አቀርቅረዉ ቀሩ። በልባቸዉ ልጃቸዉ ዉልብ እያለችባቸዉ ላለማሰብ እየታገሉ ቤቱ ዉስጥ የነበሩት ሁሉ በሀዘን ተነክቶ ቤቱ በዝምታ ተዋጠ በመሀል እማማ ስንቅነሽ ተነስተዉ ቆመዉ "ምግብ ላቅርብ በልታችሁ ሂዱ" አሉ ፊታቸዉ ላይ የፈገግታ ምልክት እየታየ "ልጃችሁ ከሰዉ እኩል አርጋኛለች" ሲሉ ከባንክ አዉጥታ የሰጠቻቸዉን ብርና ያሞላችላቸዉን የቤት ቁሳቁስ አስበዉ ቤዛዊትን እያመሰገኗት ቤዛዊት እማማ ስንቅነሽን ስማ ተሰናብታቸዉ ወደ መኪና ዉስጥ ስትገባ እየመጣች ልትጠይቃቸዉ ቃል ገብታ ነበር። መኪናዉ ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር እማማ ስንቅነሽ በጭላንጭሉ አይናቸዉ መኪናዉን እያዩ ተክዘዉ ቀሩ መኪናዉ እርቆ ሄዶም በሀዘን ተዉጠዉ ቆመዉ እያሰቡ ነዉ። ይቀጥላል... SHARE @loves_letters SHARE @loves_letters
Показать все...