cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ይህ ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘ የቴሌግራም ስብስባችን ነው:: • በእርጅናና በተለያየ ምክንያት ጤናቸው የተጓደለና በየመቃብር ቤቱ የወደቁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ለመንከባከብ • የአብነት ትምህርት መምህራንን: ተማሪዎችን ለመርዳት እንዲሁም የትናንቱን ለነገ ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ልጆች የሚመክሩበት የቻናል ገፅ ነው::

Больше
Рекламные посты
34 692
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

✍️✍️✍️ ❝አትገረምም!❞ ********* አየህ አገልግሎት ገደብ የለውም! ዕድሜ፣ ቦታ፣ ስራ፣ ትዳር፣ ሁኔታ፣ ሌላውም ምክንያት አይገድበውም። ይህን መልዕክት የምትመለከተው ወንድሜ ሆይ ያኔ በልጅነት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳለፍከውን ጊዜ አስብ፤ መልዕክቱን የምታነቢውም እህቴ፣ ያን የማይረሳ የአገልግሎት ዘመን አስቢው! ዝማሬ ለመቆም፣ መዝሙር ለማጥናት፣ ያሬዳዊ ዝማሬን አጥንቶ ለማቅረብ፣ ድራማ እና ጭውውት ለመስራት፣ አልባሳት ለብሶ ለመዘመር፣ በየበዓላቱ በአልባሳት ደምቆ ቄጤማ እና ዘንባባ ይዞ በየከተማው እየዘመሩ ለመሄድ፣ በየወርሃዊ የዝክር መርሐግብሮች ላይ ጸበል ጸድቅ ለመቃመስ፣ በየልቅሶው ቤት አጽናኝኝ እመአምላክ እያሉ እየዘመሩ ሐዘንተኞችን ለማጽናናት፣ የታመሙትን ድውይ ነኝ አንተ አድነኝ እያሉ እየዘመሩ በሽተኞች በሽታቸውን እንዲረሱ ለማድረግ፣ በየሰርጉ ላይ መርአዊ ሰማያዊ እያሉ ለማጀብ፣ በየንግሱ ታቦታቱን በአልባሳት አሸብርቆ ለማጀብ ያለህን ፍቅር እና ፍላት ቅናት እና መነሳሳት አስበው ወንድሜ። እስኪ ትዝ ይበልሽ እህቴ! ዛሬስ? ዛሬማ ትልቅ ሆንና! መንግስት ሰራተኞች ደመወዝተኞ ሆንና! ዛሬማ ጊዜ የለንማ፣ ትላልቆች ሆነን አግብተን ወልደን ከበድና፣ ዛሬማ ዕድሜያችን ገፍቶ አልባሳት ለብሶ ማገልገል ያሳፍረናላ፣ ጡረታ ወጣና! ያሳዝናል። ግን የቤተክርስቲያን ፍቅር እና አገልግሎት በእውቀት ለገባው ምንም ነገር ላለማገልገል ምክንያት አይሆነውም። ብዙዎች መንፈሳዊው እውቀት ላይ ደካሞች ስለሆኑ ተበተኑ። የገባቸው ግን ምንም አይገድባቸውም። ልክ እንደኚህ አባት! ለአባታችን ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን! ንሽኩር ረቢና! 24/11/2013 ዓ.ም (ቅዳሜ)
Показать все...
የ "ሳ" ቤት ግጥም ነው  !! ~ ብልጽግና-በዻዺና ማሸነፉን በሰማሁ ጊዜ በደስታ ብዛት ግጠም ግጠም ብሎ ግራ ትከሻዬን ሲሸክከኝ ጊዜ የገጠምኩት ግጥም ነው። • ብርቱካን ሚደቅሳ   ~ ሳ • ለማ መገርሳ          ~ ሳ • ሽመልስ አብዲሳ    ~ ሳ • ሕዝቅኤል ጋቢሳ     ~ ሳ • ሄኖክ ጋቢሳ           ~ ሳ • ኦቦ ዳውድ ኢብሳ   ~ ሳ • አዲሱ ረጋሳ           ~ ሳ • ፀጋዬ አራርሳ          ~ ሳ • ቀጀላ መርዳሳ         ~ ሳ • ይልማ መርዳሳ       ~ ሳ • ፈይሳ ሌሊሳ           ~ ሳ • ቶሎሳ ኢብሳ           ~ ሳ • መስፍን ፈይሳ         ~ ሳ • ኩማ ደምቅሳ          ~ ሳ … የቀረ ካለ እናንተው ጨምሩበትሳ~ሳ ~ ዐቢይ አሕመድ ሳ?      የሃገሩ አንበሳ     ምነው ተረሳ ሳ?     ብለህ የጠየቅከኝ ከአሩሲ ቀርሳ … እዚህ ጋር የግጥሙን መዝጊያ ቤት መምቻ ስላጣሁ ዘልዬ ወደ ሌላ ስንኝ ተሸጋግሬአለሁ። ይቅርታ! የወንዜው ሳቢሳ የወንዜው ሳቢሳ ተጋሩ ተነሣ ዐማራም ተነሣ ጠመንጃህን አንሣ ተኩሳ ተኩሳ ተተኳኮሳ ተፈረካከሳ አናት አናትህን ተበረቃቀሳ አርገው ምድርህን ሬሳ በሬሳ ሲደክምህ ደቅሳ … ኦሮሞም ተነሣ ትራክተርህን አስነሣ እርሻህን እረሳ ምርትህን እፈሳ ! ኮንዶህን ውረሳ እየበላህ ሳንቡሳ አግሳ እንደ አንበሳ ርችቱን ተኩሳ ዕድሜ ለለማ መገርሳ ለብርቱካን ሚደቅሳ ! ሃይ አቦ ምንድነዋ ሳ!  … እነ ባሮ ቱምሳ … ቄስ ጉዲና ቱሙሳ … ሃጫሉ ሁንዴሳ ~ እኒህ ሦስቱ ግን አርፈዋል። ነፍስ ይማር። … እንኳን ደስ ያለን ! ከ436 መቀመጫ እስከአሁን ባለው ቆጠራ 410 መቀመጫ ኢትዮጵያ አሸንፋለች። የእነ ሱዳን… የእነ ግብጽ… የእነ የመን ገና አልተረጋገጠም። • ኢትዮጵያ ትስዕር  !! 
Показать все...
ተወዳጆች ሆይ !! … ለሁላችሁ ይድረስ ዘንድ ከዋልድባ አባቶች የመጣውን መልእክት እና የጻፉትን ደብዳቤም እነሆ ለጥፌላችኋለሁ። የዋልድባ አባቶች የችግራቸውን ዝርዝር ሁኔታ አንድ ሁለት ብለው ገልጸውላችኋል። የባንክ ደብተራቸውንም ልከዋል። እናም በተጠቀሰው የባንክ አካውንት በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያላችሁ እስከ ነገ ረቡዕ ድረስ እያስገባችሁ ጠብቁኝ። ገንዘቡ በሦሥተኛም በሁለተኛም ሰው እጅ አይነካካም። በዚያ በኩል ስጋት አይግባችሁ። … እናንተ ከያላችሁበት ሆናችሁ የተቻላችሁን አስገቡላቸው። አስገቡና ያስገባችሁበትን ሪሲቱን የክርስትና ስማችሁን እየጻፋችሁበት በውስጥ መስመር ላኩልኝ። ነገ ረቡዕ በመረጃ ቲቪ፣ በኢትዮ ቤተሰብ፣ በዘወንጌል እና ( አግኝቼ አላስፈቀድኩትም ነገር ግን በኋላ ደውዬ እነግረዋለሁ) በወንድሜ በዲን ዓባይነህ ካሤ የፅዋዕ የዩቱዩብ ቻናሎች ላይ ለታላቁ ገዳማችን ለዋልድባ አብረንታንት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢያ እናደርግላቸዋለን። … እግዚአብሔር የፈቀደልን አሁኑኑ መስጠት እንጀምር። ከበረከቱም ለመሳተፍ እንሽቀዳደም። ጀምሩ … እንጀምር። … ማነው?  የዋልድባ ወዳጅ የመጀመሪያው ፈር ቀዳጅ? እኔ ነኝ በልማ። ፍጠን፣ ፍጠኚ። ጎንደር ዐቢይ ቅርንጫፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000018796779 SWIFT = CBETETAA ዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር
Показать все...
“አሁንም፦ አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና።” ሐዋ 27፥22
Показать все...
… እንዴት ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም !! “ …ወትሮም ቢሆን እኔ ዘመዴ በሁሉም ነገር ሁልጊዜም ደስተኛ ነኝ። ... ቢሆንም ቢሆንም ግን እንደ ዛሬ ቀን ከወትሮው በተለየ መልኩ እጅግ በጣም ደስስ ብሎኝ አያውቅም። ደስስ ብሎኝ ነው የዋልኩት፣ ያመሸሁት፣ ያደርኩትም። ... ከምር በጣም ነው ደስስ ያለኝ። በሰማዕቱ በቅዱስ ቂርቆስ የመታሰቢያው ዕለት፣ በእናቴ፣ በአማላጄ፣ በቅድስት ኪዳነ ምህረት ዋዜማ በጣም ደስስስ ብሎኝ ነው የዋልኩት ያመሸሁትም። ” … ጋሬጣውም ለጊዜው ተነሥቷል፣ ወጥመዱም ስብርብር ብሏል።” ሳቅን፣ እኔና ቤተሰቦቼ ዛሬ ሳቅናት። ከወትሮው በተለየ መልኩ ነው ተረጋግተን የሳቅናት። በውጥረት መሃል ሐሴትም አደረግን። አጅሬው ሆዬ የፈተናውን መልክ ቀይረህ ና እኛም ተዘጋጅተን እንጠብቅሃለን። ይኸው ነው። … ቂርቆስ ያላችሁ ወንድሞቼ እስኪ አንድ ፍሬ ሻማ ነገ በስሜ በሰማዕቱ ስም አብሩልኝ። ... ነገ ኪዳነምህረት የምትሄዱ ጓደኞቼም እንዲሁ አንድ ፍሬ ሻማ ወይ ጧፍ ለኪዳኗ አስገቡልኝ። ከቻላችሁ አበዛኸው አትበሉኝና በአቅም ለደከሙ አረጋውያን አንድ ዳቦ መግዣ ሳንቲም ዝምብላችሁ ስጡልኝ። በማርያም። ሉሌ ቋንቋዬነሽ ሰምተሃል !! ጠዋት ኪዳነምህረት ሂድልኝማ ወንድምዓለሜ። እ ሉሌ ! ሰምተሃል። … ዝርዝር የደስታዬን ምንጭና ምክንያቱንም ጊዜው ሲደርስ እነግራችኋለሁ። እተርክላችኋለሁም። ለአሁኑ ግን ያልኳችሁን ፈጽሙልኝ። በማርያም። ... ነገም የላይካ ካርድ ሞልተን “ ነጭነጯን ከዘመዴ ጋር ” በመረጃ ቴቪ እናወጋለን !! የነገ ሰው ይበለን። ደህና እደሩልኝ።
Показать все...
+ ለምን ትቀናለህ? + በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡ አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡ ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው:: ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡ ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡ ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡ የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡ ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡ የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡ ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡ ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡ በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡ ‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ ጥር 5 2013 ዓ.ም. መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ
Показать все...
የማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ?
Показать все...