cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Emoji feelings🦋

The channel is about Feeling 😂😤🤤😭💃❤️💔 photograph¥📷 New musics🎼🎧 Join and share Ya all much love and respect ❤️🙏🏾🙏🏾

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
656
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
Показать все...
🎉✈️️️️️️️️Ethiopian Airlines 75th Anniversary Transportation Subsidy!✈️💵️

✈️💸️️️️️✈️💸️️️️️Click on the link to claim your transportation allowance!💸🎁✈️️️✈️️️

Показать все...

Показать все...

​🌿‍ የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣5️⃣ ደራሲ፡- የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ "በይማ ንገሪኝ ልስማሽ እስቲ አንቺ፡፡"...ነርሷ እንባዋን እየጠራረገች ቀጠለች፡፡ ..."ታስታውሺ እንደሆን አንቺ ለመውለድ የገባሽበት ክፍል ውስጥ ሌላ ምጥ ላይ የነበረች ሴትዮ ነበረች፡፡" የልጁ እናት ታስታውስ እንደሆን በአይኖቿ እየመረመረች፡፡ "አዎ በሚገባ አንዲት ከበርቴ ሴት ከጎኔ ነበረች፡፡" ሴትየዋ መለሱ፡፡ እኔ ሁኔታው በብዙ እየጨነቀኝ ነው፡፡ ነገሮች ከማስባቸውና ከምጠብቃቸው በላይ እየተወሳሰቡ ነው፡፡ "ከጎንሽ የነበረችው ሴትዮ እዛ ሆስፒታል ውስጥ ለመውለድ ስትመጣ ለአራተኛ ጊዜ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ለመውለድ በመጣችባቸው ጊዜያት አንድም ህይወት ያለው ልጅ አልወለደችም ነበር፡፡ ከዚህ በሗላ ለማርገዝ አንድ እድል ነው ያላት፡፡ እሱም ካልተሳካ ሌላ መሞከር በራሱ ለሴትየዋ በህይወቷ ላይ መፍረድ ነው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በአራቱም የወሊድ ወቅት እናቴ በቦታው ነበረች፡፡ በመጨረሻው ፅንስ ላይ ግን የማዋለዱንም ስራ ራሷ ነበር ያከናወነችው፡፡ የሴትየዋን የልጅ ጉጉት በሚገባ የምታውቀው እናቴ ሴትየዋ በዚህ ወቅት የሚተነፍስ ጨቅላ ካልተገላገለች እድሜ ዘመኗን ተጎድታ ልጅ አልባ ሆና እንደምትኖር አውቃለች፡፡ እንደፈራችውም የተወለደው ጨቅላ እስትንፋስ አልነበረውም፡፡ በዛ ወቅት አንቺ መንታ ልጆችን ተገላገልሽ፡፡ ሜርሲን እና አንድዓለምን፡፡"...የሴትየዋ ቅጭም አለ፡፡ የኔን ማን አስተዋለው እንጂ...ቅዠት እየመሰለኝ የሰማሁት ነገር እውነት ወደመሆኑ እያዘገመ ነው፡፡ ያለምክንያት በዚህ አልተሰባሰብንም ለካ፡፡ "ከዛም እናቴ ሴትየዋ እንዳትጎዳ ብላ ጓደኟቿን አማክራ ሁለቱም ልጆችሽ ማጅራት ላይ ምልክት አድርጋ ሴቲቱን ለሷ ወድየውን ላንቺ ተወችልሽ፡፡ የኑሮ ሁኔታሽንም ስለምታውቀው ማገዝም መስሎ ተሰምቷት ነበር በወቅቱ፡፡".... ማጅራቴ ላይ ያለው ጠበሳ እንደሁ አልነበረማ፡፡ እዚህ ክፍል ያየሁት የጨቅላ ልጅ ፎቶ የወንድሜ ነው ለካ፡፡ በዛ በስቃይ ወቅት መዳፉ ሲነካኝ የማውቀው የቅርቤ ሰው የመሰለኝ ለካ ወንድሜ ኖሮ ነው፡፡ የእናቱን ፀዓዳ ቀሚስ የተወደደውንም ሽቱ የነሰነሰብኝ እህቱ መሆኔን አውቆት ለካ፡፡ በደመነፍስ እየተጓዘ እንኳ አልዘነጋኝም፡፡ እንባዬ በዝምታ ወረደ፡፡ የሞት እንጆቹ ያልጠነከሩብኝ...ጨካኝ ልቡ ያልተቆጣኝ...ለካ... ሴትየዋ አብዝታ ተቆጣች፡፡ "በኔ ልጆች ፃድቅ የምትሆን ያንቺ እናት ማነች፡፡ በኔ ደም የከበርቴዎችን መቃን ምታባብስ እሷ ማነች፡፡ እኔ በተሸከምኩት ፅንስ ልጄን የምትመፀውት በሰው ሰው አዛኟ ማነች፡፡ እውነት እልሻለሁ ዛሬ ከጎኗ ምትጋደሚበት ቀንሽ ነው፡፡ የሷን ጥፋት አንቺ ትከፍዪዋለሽ፡፡ ነፍስሽን ከነፍሷ እቀላቅለዋለሁ፡፡" አይኗን አጉረጥርጣ ተነሳችባት፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ መሃላቸው ገባሁ፡፡ በእናትነት አይን ተመለከተችኝ፡፡ ውስጤ የሚንኳኳ እልፍ ጥያቄዎች ቢኖሩም ላሁኑ ዝም ብያለሁ፡፡ "በይ ዞር በይ፡፡ ታከብሪኝ እንደሁ ተከበሪ፡፡ አለዚያ..." ተናገረችኝ፡፡ "ዳግም ልጅሽን ማጣት ከወደድሽ ያሻሽን አድርጊ፡፡ ይሄን ሚስጢር እሷ ባትነግርሽ ከማን ትሰሚው ነበር፡፡ ላንቺ ብላ ያልሆነችውን መሆኗ መሰቃየቷ የእናቷን በደል አይቀንሰውምን፡፡ የእናቷን በደል ይሄ አይቀንሰውም ካልሽ ይኸው የአብራክሽን ክፋይ እኔን መለሰችልሽ፡፡ እቺ ልጅ ምንም በማታውቀው ውለታ በዋለች ስለምን ትቀጣለች?"...ነገሩን ለማርገብ እንደሆኔታው ሆንኩኝ፡፡ የነበረው ጡዘት በረደ፡፡ ልጅቷም እስከዛሬ ለብቻዋ የተሸከመችውን ሚስጢር በመተንፈሷ እፎይ ያለች ይመስላል፡፡ የዛሬዉን ያህል ደንቆኝ አያውቅም፡፡ እኔ ልጅ የተባልኩት እና እናት ተብዬዋ ጊዜ እስከያዋህደን ላሁኑ እንደሩቅ ሰው ነን፡፡ ደጁ በፖሊስ መኪና ሳይረን ታውኳል፡፡ ነፍሰ በላው የጠፋው ሬሳ ሲምዘገዘግ ወጣ እናትየውም ተከተለችው እኔና ልጅቷም ከበስተሗላቸው፡፡ እንደለመደው መጥረቢያውን ቀስሮ ሲገሰግስ በታጠቀ ፖሊስ ጭንቅላቱ ተበትኖ በጀርባው ተዘረጋ፡፡ እናት እዬዬዋን፡፡ እጇ ላይ ካቴና አኖሩባት፡፡ ነርሷንም ጭምር፡፡ ቤተሰቦቼና ሜርሲ ከአንዱ መኪና ሲወጡ አየሗቸው፡፡ ሮጬ እንባዬን እያዘራው ተጠመጠምኩባቸው፡፡ ያልጠበኩት ታሪክ ያላሰብነው ሰቆቃ በዚ ተቋጨ፡፡ መደሰትን ፈልገን ወዳጆቻችንን ተነጥቀን ተመለስን፡፡ እሱ ሁሌም ልክ ነው፡፡ አይከሰስ፡፡ ልቤ ከራራላት እናቴን ማረሚያ እየሄድኩ ጠይቃት ይሆናል፡፡ ማሚን እናቴ አይደለሽም ብሎ ለማሰብ ያዳግተኛል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ አሳድጋኛለች፡፡ በቃ እኔና እኔ የምናውቀው ሁለት እናት ይኖረኛል፡፡ ..............ተፈፀመ......
Показать все...

​🌿‍ የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣4️⃣ ደራሲ፡- የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ....የሰማውን ለመቀበል ልቤ ተንኮታኮተ፡፡ "ለነገሩ ምትናገሪውን ታውቂዋለሽ" ቆጣ ብዬ ወደ ምትዘላብደዋ ነርስ ፊቴን ከፊቷ ደንቅሬ፡፡ "አዎ ሜርሲ እዚህ ድረስ የሚያንከራትተኝ እኮ ይህንን እውነት ማወቄ ነው፡፡ እንጂ ሰው ሆኖ እዚህ ጦስ ውስጥ ማን ሊገባ ይወዳል ብለሽ፡፡" እንባዋ በማን አለብኝነት ይወርደዋል፡፡ ነገሮች ከቁጥጥሬ ውጪ ቢሆኑም ሁሉም ለምክንያት እና በምክንያት ነው፡፡ ግን ይሄንን በየትኛው ፅኑ አቅሜ ልሸከመው እችላለሁ፡፡ "አንቺ ልጅ ምንድነው ምትዛብሪው፡፡ አስተውይ እንጂ፡፡ እስከዛሬም እንደዚ ያለ ቅዠት ውስጥ አልዋተትሽ፡፡ ዛሬ ምን ተገኘ?...ትልቋ ሴትዮ ባለማመን ውስጥ ሆና በጥያቄ ጎነተለቻት፡፡ "ዶ/ር አበራሽን አታውቂያትም?"...ነርሷ መልሳ ጥያቄ፡፡ ለልጁ እናት "ማናት ደግሞ ዶ/ር አበራሽ? እኔኮ ማውቃቸው ከዘነጉኝ ያየሗቸው ከረሱኝ ዓመታት አዝግመዋል፡፡ አላውቃትም፡፡" "ኸረ የልብ ወዳጅሽ ነች፡፡ እንደውም ወንድ ልጅሽን ልትገላገዪ ጤና ጣቢያ ያዋለደችሽ ዶ/ር?"...ይሟገታሉ፡፡ እኔም ከራሴ ጋር እተካተካለሁ፡፡ እያክላላው እንደነሱ ባወራና የውስጤ በወጣ፡፡ ግን አሁንም እፈራለሁ፡፡ አዘናግተው አንዳች ሊያረጉኝ ይመስለኛል፡፡ "እስቲ ዝም በይ፡፡ ምንም የማውቀው ዶ/ር የለም፡፡...እንዴ እንዴ..." ትልቋ ሴትዮ የሆነ ነገር ያስታወሱ መሰለኝ፡፡ ይቀጥላሉ፡፡ "ስሟን በውል ባላስታውሰውም እየተመላለሰች የምትጠይቀኝ መልካም ዶ/ር ነበረች፡፡ እሷ ትሆን እንዴ?"...መልሰው ይጠይቋታል፡፡ "አዎ እንደውም መሉ የህፃን ልብስ ያመጣችልሽ..." ትልቋ ሴትዮ እንድታስታውስ ነርሷ እየታተረች ነው፡፡ እኔ ደግሞ ነገሮች እዚህ ጋር ባበቁ እያልኩ እየተመኘሁ ነው፡፡ "አዎ አዎ ልክ ነሽ፡፡ ሚስጢሬን ሁሉ አጫውቻት ደግ ወዳጄ ሆና ነበር፡፡ እንደሁ ከጊዜ በሗላ ምን ውጧት ይሆን ጠፋች፡፡ ባፈላልጋትም ላገኛት አልቻልኩም ነበር፡፡ ታዲያ አንቺ በምን አወቅሻት?"...የጦፈ ወግ ላይ ገቡ፡፡ በዚህ መሃል እኔና አረመኔው ተዘንግተናል፡፡ በቦዘዙ የሴትየዋ አይን ውስጥ የመልካም ቀን ትውስታ እንባ ሊወርድ ይመቻቻል፡፡ የሗሊት የነጎደው ምናባቸው ከእንባ ቋታቸው ጋር ይታገላል፡፡ "እኔ ልጇ ነኝ፡፡ ለሷ ብዬም ነው እዚህ የቁም ስቅል የመኖር ሞት፡፡ በድን መሃል ምታትረው፡፡" ሴትየዋ ከንግግሯ ፊታቸው ሲለዋወጥ ይታየኛል፡፡ "አንቺ እንደምታስቢው የልጅሽ ፍቅረኛ ወይም እጮኛ አይደለሁም፡፡"... "አንቺ ባለጌ ወረዳ፡፡ እና ምን ትሆኚ አነፍንፈሽ ከኮቴ ደረሽ?"...ትልቋ ሴትዮ በገነች፡፡ ንዴቷ እንደነበልባል ሲንቦገቦግ ይታወቃል፡፡ ከመቀመጫዋ ተነስታ ወደ ነርሷ አመራች፡፡ ሁኔታው አላምር አለኝ፡፡ ተነስቼ በመካከላቸው ገባሁ፡፡ "መጀመሪያ አድምጪኝ፡፡ እንዳታለልኩሽ አውቃለሁ፡፡ ግን ምክንያት ነበረኝ፡፡ ይሄን ሁሉ የማደርገው ለአንድ እናቴ ስል ነው፡፡ ያለፉትን አመታት ያለምክንያት በስቃይ ካንቺጋ ማሳለፌ እንዴት አይታይሽም?...ነርሷ እንባዋ አይቆምም፡፡ "ዞር በይ አንቺ እኔና እሷ የጀመርነውን እኛው እንጨርሰዋለን፡፡ በማይመለከተው የሚገባ ነው ተጎጂው፡፡" ሴትየዋ ልታስጠነቅቀኝ ሞከረች፡፡ "መቼም እናት ነሽ፡፡ እሷም ልጅሽ ትሆናለች፡፡ አንዴ አድምጫት ከዛ የወደድሽውን ታደርጊያለሽ፡፡" ለማግባባት ሞከርኩ፡፡ "እኔን እንደዚ ታናግሪኝ ዘንድ ማነሽ፡፡ የሰማሽው ነገር የልብ ልብ ሰቶሽ ከሆነ ታቀቢ፡፡ አንቺ የኔ የአብራክ ክፋይ አይደለሽም፡፡ ወድሜ ነው ብለሽ አስበሽ ከሆን፡፡"...ሴትየዋ ፍፁም ተጋግማለች የሚያበርዳትም ያለ አይመስልም፡፡ እሷን ሊደግፍ ልጇ ከበስተሗላዋ ትዕዛዟን ይጠብቃል፡፡ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም፡፡ ዞር አልኩላቸው፡፡ "እናቴ ዶ/ር አበራሽ እንደቀድሞው እየመጣች እንዳትጠይቅሽ በጠና ታመመች፡፡ ለአመታት የአልጋ ቁራኛ ሆና ህይወቷ አለፈ፡፡ ከዛም አሁን ድረስ ከናንተ ጋር የሚያንከዋትተኝን ውሸት የሚመስል እውነት አሸከመችኝ፡፡ እኔም የነፍስ አደራ ሆኖብኝ የገባችሁበት ገብቼ ከናንተው ጋር አመታትን አዘገምኩ፡፡ ግን ውስጤን እያመመኝና ነፍሴን እየጨነቃት ነበር፡፡ ግን የማውቀውን ማወቅ ነበረብሽ፡፡ ለዛም ማልችለውን ሁሉ ችዬ በባዘናችሁበት ባዘንኩ፡፡ በዳከራችሁበት ዳከረኩ፡፡ የነፍስን ስቃይ እንደ ባሌት ሙዚቃ ኮመኮምኩት፡፡ ያለ ለኔ እልፍ ስቃይ ነበር፡፡ ሰው ሆኖ ሰው ሲበለት እንደማየት ምን ሊያም ይችላል፡፡ ሁሌም አለቅሳለሁ፡፡ እዚህ መሃል የዶለኝን እድሌን እና ፈጣሪን እያማረርኩ፡፡ ትቻችሁ መሄድ እችላለሁ፡፡ ግን ልቤ ላይ የፀነስኩትን እውነት እምን እከተዋለሁ፡፡" ሴትየዋ እስክትረዳት ነርሷ መለፈፏን አላባራችም፡፡ "ትዝ ካለሽ ለመውለድ ጤና ጣቢያ ስትሄጂ፡፡ ዕለተ ሐሙስ ቀኑ 16 1986 ሰኔ ወር ላይ ነበር፡፡" ሴትየዋ በአውንታ አንገቷን ነቀነቀች፡፡ ፊቷን ቅጭም አድርጋ፡፡ የደነቃትም ነገር እንዳለ ሁሉ በአግራሞት ሆና "አንቺ ይሄን ሁሉ ሚስጢር በምን አወቅሽ?"...ጥያቄዋን አስከተለች፡፡ "ያዋለደችሽ ዶ/ር እናቴ ነች፡፡ በዛን ምሽት መንታ ልጆችን ነበር የተገላገልሽው፡፡" አሁን አንዳች ሊፈነዳ ነው፡፡ "ምን?" ትልቋ ሴትዮ አምባረቀች፡፡...ይቀጥላል እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን፡፡ ቀጣይ እና የመጨረሻው ክፍል 👍100 ሲሞላ ይለቀቃል፡፡
Показать все...

​‍ 🌿የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣3️⃣ ደራሲ፡- የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ....ከተቀመጥኩበት መዝለል በሚመስል መውረግረግ ተመንጭቄ ተነሳሁ፡፡ ቃል ሳልተነፍስ ጥያቄ ባዘሉ አይኖቼ አጉረጠረጥኩባት፡፡ ምትናገረውንም በቅጡ ያወቀች አልመሰል አለኝ፡፡ አኔገቷን አነቃንቃ ስለተናገረቸው አረጋገጠችልኝ፡፡ በእርግጥም ጥያቄዬን ለመረዳት ቃሌን አልጠበቀችም፡፡ "ማናት ሜርሲ?" የልጁ እናት በመደነቅ እና ባለማወቅ፡፡ ይቀጥላሉ..."እኔ ከአንድዬ በቀር ልጅም ወዳጅም የለኝም በቁም ሞቱ እኔና አንቺን አወዳጀን አበቃ፡፡ የቁም ቅዠትሽን አስክኚው፡፡" ቁጣ የተቀላቀለበት ትዕዛዝ ለሲስተር፡፡ አይኖቿ እንባ እንዳጋቱ የሚረዳት እንዳጣች ሁሉ ተኮራምታ ተቀመጠች፡፡ አይኗ ከእንባዋ ይልቅ እውነትን አዝሏል፡፡ የሴትየዋ ንግግር ትንሽ ልቤን ቢያለዝበውም ሲስተር የኔ ጅምር ታሪክ እንዳለ ጠርጥሬያለሁ፡፡ ተመልሼ ቁጭ አልኩ፡፡ ሲስተር ለነፍሷ የሰጋች ይመስል የሴትየዋን ቁጣ አዘል ንግግር ሰምታ ተሸብባ ታነባለች፡፡ ምን ልበል? እኔስ እዚ መሃል ሰሚ ይኖረኛል? ለወዳጅ ብሞክር ቃሌን ማን ያደምጣል? ዝም ብል ይሻለኛል፡፡ ፀጥ፡፡ ነገሮች በጊዜ ጉዘት ይንጎዱ፡፡ የባርሰናይትን መምጣት በጉጉት እየጠበኩ ነው፡፡ ከዚ የሞት ዳንክራ ውዝዋዜ መሃል የሰላም አለም ውስጥ እንዳየሗት ሁሉ፡፡ ሲስተር ስቅ ስቅ ብላ ታነባለች፡፡ እሷጋ ልክ የሆነ ነገር አለ፡፡ ስሜን እንዲሁ በዘበት አታውቀውምና፡፡ ሴትየዋ ገፍተው ሊጠይቋት አለመፈልጋቸው አስገርሞኛል፡፡ ሰው ልጅ አለህ ሲባል እንዲህ ነው እንዴ ሚኮነው? የልጅ ዋጋውስ ምን ያህል ነው?...የልጅ ፍቅር ፊት ለፊቴ እያየሁት ነው፡፡ ከቁም ሬሳ የሰው ልጅ ተወዳጅቶ፡፡ የስጋ ክፋይ ሳይንጋለል እየተነፈሰ በስብሶ ከሰው ጋር አይቼዋለሁ፡፡ ፍቅር ፊት ለፊቴ ነው፡፡ ነርሷ እንዳለችው ከሆነ ይሄ አረመኔ የኔ ወንድም? አይሆንም፡፡ መቀበል አልችልም፡፡ ሶስቱንም ገረመምኳቸው፡፡ እናትና ልጅ በሚግባቡት ቋንቋ ይንሾካሾካሉ፡፡ ነርሷ በነሱ ቁጥጥር ስር እንዳለች ተገለጠልኝ፡፡ ካፈነገጠች ሞት እንደተዘጋጀላት ተረድቶኛል፡፡ ለዛም ነው በሃሳብ ያልተጣረሰቻቸው፡፡ የሚሏትን ከማድረግ ውጪ ያለችውን ለማድረግ አልታደለችም፡፡ ስለምን ራሷን በቁም አሰረች? መሸሽንስ ስለምን አልመረጠችም?...ዞር ባሉልኝና ምነው ባወጋሗት፡፡ እናትና ልጅ ወደ ውስጠኛው ክፍል ዘለቁ፡፡ አሁን ላወራት ደጁ ክፍት ነው፡፡ ግን ቃል እንዴት ላውጣ፡፡ የክፍሉ ጭርታ የቃላችንን ጉምጉምታ ሊያሳብቅ አሰፍስፏል፡፡ "አንቺም አታም...ኚኝም?" ቃሏን ሳግ እያደነቃቀፈው፡፡ ዝም ብዬ አየሗት፡፡ በሆነ ነገር ላይ ፅፌ ባወራት ተመኘው፡፡ ግን እንቅስቃሴዬም የተገደበ ነው፡፡ አወይ ጭንቀት፡፡ "እኔ ልሰማሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ የምትዪውን ባላውቅም ባላምንበትም እንኳ ብሰማሽ ደስ ይለኛል" እያንሾካሸኩኝ መለስኩላት፡፡ ቃል ልትሰነዝር ከንፈሯን ስታላቅቅ ሁለቱም ወዳለንበት ዘው ብለው ገቡ፡፡ ሴትየዋ በጥርጣሬ አይን እኔና ነርሷን ገረመመችን፡፡ ድጋሜ ፀጥታ፡፡ አሁን እኔን ምን ሊያደርጉኝ ይሆን? እንዲሁ ሲያወሩ እየሰማሁ እስከመቼ? ከራሴ ጋር ንግግር፡፡ አናግረው ዘንድ በዚህ ማንም የለማ፡፡ "ለምን ያልገደላት ይመስልሻል?" አክላላች፡፡ ሳላስበው አንባርቃ ልቤን ከስጋዬ አናጠበችው፡፡ ከተቀመጠችበት ተነስታለች የሆነ እልህ ይታገላታል፡፡ የሴትየዋ አይን አንዴ ከእኔ አንዴ ከነፍሰ በላው ላይ ይንከላወሳል፡፡ ድንጋጤዬን እንጂ ያለችውን ልብ አላልኩትም ነበር፡፡ ግን ለምን አልገደለኝም?.....ይቀጥላል እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን፡፡ እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን #100👍 ሲሞላ ቀጣይ ክፍል ይለቀቃል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
Показать все...

​🌿‍ የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣2️⃣ ደራሲ፡- የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...ሞት ራሱ ይሙት የታባቱ፡፡ ከእግሩ ሸብረክ ብሎ ከነትቢያው የረጋ ደሙን አግበሰበሰ፡፡ ብርቱም ሆኖ ቀና አለ፡፡ ስፈራ ስቸር ተጠጋሁት፡፡ አልተተናኮለኝም፡፡ ልጄ የቁም ሬሳ ሆነ፡፡ ተንቀሳቃሽ በድን፡፡ ደመ ነፍስ የሚዘውረው ያልተቀበረ ሙት፡፡ እጁን ይዤ አነሳሁት፡፡ ይውተረተራል፡፡ ሰው ሳያይ ሸሽጌ እቤት ወስጄ አለበስኩት፡፡ የተወጋው አካሉ ገና አልጠገገም፡፡ እነዛ ነፍሰ በላዎች ይሄኔ እየተጫጫሱ ነው፡፡ "ግደላቸው" አዘዝኩት ይሰማኝ እንደሁ ለማወቅ፡፡ ሳያመነታ ደጃፉን ስቦ ወደ ውጪ ወጣ፡፡ ተከተልኩት፡፡ መንደራችን ውስጥ ወዳለው አነስተኛ የመጠጥ ግሮሰሪ አመራ፡፡ ጭፈራው ለጉድ ነው፡፡ ፌሽታው ጫጫታው ለኔ ብቻ ነበር ሀዘኑ፡፡ ለማንም ግድ አልነበረም፡፡ ቀጥ ብሎ ገባ፡፡ ፊት ለፊት ያገኘውን ክፍል ትቶ ወደ ቀኝ ታጠፈ፡፡ ጠርሙስ ሰብሮ አደኛው ጎሮሮ ላይ ሰቀሰቀበት፡፡ እሰይ እልል አልኩ በውስጤ የልጄ ነፍስ ፍትህ በማግኘቷ፡፡ ሌላኛው ሴት ጭን መሃል ተወሽቆ ቤርጎ ውስጥ አገኘው፡፡ በካቻ ቢቴ አይኑን ጎልጉሎ አስቃይቶ ገደለው፡፡ ይሄን ሁሉ ትዕይንት በቅርብ ርቀት እያየሁ ነበር፡፡ ያስጨከነኝ ጭካኔያቸው ነው፡፡ አውሬ ያረገኝ አውሬነታቸው ነው፡፡ ባይነኩት ባልተነካካን ነበር፡፡ የነሱም እናቶች ከኔ እኩሌታ እንባን ይዩት፡፡ ፅዋውንም ይጎንጩት፡፡ ቢመርም፡፡"... "እውነት አለሽ" በውስጤ አጉተመተምኩ፡፡ ሰቆቃዋ ሰቀቀኝ፡፡ ህመሟ አጥንቴን ሰርስሮ ተሰማኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ሚስጢር ለኔ ስለምን ይነግሩኛል? እሰማው ዘንድስ ማን መረጠኝ?...ሴትየዋ አላቁሙም አሁንም ያትታሉ፡፡ "ደስታዬ ድርብ ባይሆንም ሀዘኔን ይቀንስልኛል፡፡ በድኑ ጋር ኩርምት ብሎ ተቀመጠ፡፡ አካባባቢው በጩኸት ናውዟል፡፡ ደሜ እንደ ክረምት ጎርፉ ይወርደዋል፡፡ የአንቡላንስ ድምፅ የፖሊስ ውርውርታ የወደመ ከተማ አስመስሎታል፡፡ እጁን ይዤ ብወጣ እና ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግና አልችልም፡፡ ከደቂቃዎች በሗላ አጠገቡ የነበረውን ሬሳ እላዩ ላይ ተለጥፎ በጥም እንደነደደ ሁሉ የሟቹን ደም ተጋተው፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ከተባለው የመስዋዕት ሰዓት ዘግይቻለሁ፡፡ ልጄ እድሜ ዘመኑን የሰው ስጋ እየበላ እንዲኖር ፈረድኩበት፡፡ ራሴን ጠላሁት፡፡ ከሞቱ ይልቅ ቆሞ በመራመዱ የሸለምኩትን ስቃይ ሳስበው ለራሴ ይቅርታ ለማረግ አቅሙን አጣሁ፡፡ ከበድኑ ላይ መንጭቄ አነሳሁት፡፡ ከፊት ለፊቱ በጥድፊያ ተራመድኩ ተከተለኝ፡፡ "እሱ ነው"፡፡ "ይሄ ነው ገዳዩ"፡፡ ከዚም ከዚያም ልጄን ከሳሽ ድምፁን አሰማ ወንዱም ሴቱም፡፡ ቢረፈርፋቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ ፖሉሶች ተከተሉን፡፡ በዛ ውድቅት ጫካ ለጫካ እያሳበርን ዝም ብለን ተጓዝን፡፡ ይህን ሁሉ ነገር ስንከውን ሲስተር አድማሴ እየተከታተለች ትመለከተን ነበር፡፡ እኛ አላየናትም፡፡ ንጋት ለመቃረቡ የሰማዩ መወገግ ያሳብቃል፡፡ ከአንዱ ዛፉ ስር አረፍ አልኩኝ፡፡ ጀርባውን ሰቶኝ ተቀመጠ፡፡ ያነፈንፋል፡፡ የሆነ እግዳ ሽታ እንደሸተተው ሁሉ፡፡ ከዛም ተነስቶ መተረማመስ ጀመረ፡፡ ተከተልኩት፡፡ ሲስተርን ከጥሻው መንቅሮ አወጣት፡፡ "እንዳትነካት!" አክላላሁበት፡፡ ለቀቃት፡፡ ወደኔ ጠራሗት፡፡ ምን ታረጊያለሽ እዚ? ስትከተይን ነበር አይደል "አዎ ተከትያችሁ ነው ግን አሁን ሳይሆን ከሬሳ ክፍል ተነስቶ ከወጣ ጀምሮ ነው፡፡" አንገቷን ደፍታ እጇን እያፍተለተለች፡፡ "እኮ ለምን ተከተልሽው?" "ሁኔታው አስደኔግጦኝ ነው፡፡ የማረገው ጠፋኝ፡፡ ለሰው እንዳልናገር የሆነ ነገር አንደበቴን ሸበበው፡፡ በቃ ዝም ብዬ ነበር የተከተልኩት፡፡ ምክንያት የለኝም፡፡ እኔን የሳበበት አንዳች ሚስጢር አለው፡፡" አልጠረጠርኳትም አመንኳት፡፡ ሚስጢራችንን ማወቋ ለኛ አደጋ ቢሆንም እንድትሞት አልፈለኩም፡፡ "ያወቅሽው ነገር ያጠፋሻል ይሄ መቼም ላንቺ እንግዳ አይሆንም፡፡ ግና ካልተጎራበጥሽን ምን አይነካሽም፡፡ በዚህ ቃል ከገባሽ አንዳች አትሆኚም" አይኖቿን እያየሁ አስጠነቀኳት፡፡ በአንገቷ ንቅንቄ እሺታዋን ገለጠች፡፡ ከዛች እለት ጀምሮ አብራን ነች፡፡ የኛ ፍፁም ወዳጃችን፡፡ ይሄን የቆየ እና የተዘጋ ሆስፒታል በጉዟችን መሃል አገኘነው፡፡ ከአዲስ አበባ ድረስ በእግራችን ተጉዘን እዚ ደረስን፡፡ ራሳችንን ሰውረን፡፡ በቃ ልቤ ደነደነ፡፡ ልጄ ሁሌም ሰው ያድናል፡፡ ለመድኩት ሀዘን ይሰብረኝ ዘንድ አቅም አጣ፡፡ ጨከንኩ፡፡ ከአረመኔ እጥፍ ጭካኔ፡፡ ሲስተር ለኔና ለራሷ ምግብ ታዘጋጃለች፡፡ የሱን እንደምታውቂው ነው፡፡ ለኔ ልጄ ነው፡፡ አሁንም ድረስ አልጠየፈውም፡፡ እያለ እያለ አመት ከአንድ ወር ሞላን፡፡ በቃ እንዲሁ የቁም ሞት ቅዠት ውስጥ ስንዋልል፡፡ አዋቂውን ልማጠነው ባፈላልገው አላገኘሁትም፡፡ ጊዜው ደርሶ እስኪያሸሌብ ከልጄ ጎን ነኝ፡፡" ሲስተር ተብዬዋ የሴትየዋን ንግግር አቋረጠቻት፡፡ "ሜርሲም ልጅሽ ናት" አለች፡፡...ይቀጥላል እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን፡፡ እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን፡፡
Показать все...

​🌿‍ የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣1️⃣ ደራሲ፡-የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...መዝጊያው አልተሸጎረ ኖሮ ዝም ብዬ ዘለኩ፡፡ ለጥበቃው ሰላምታ ጊዜም አልነበረኝ፡፡ በቀጥታ ወደ ሬሳ ክፍል ገባሁ፡፡ ስፍራውን ነፍሴ ተጠየፈችው፡፡ ከምድር የተሰናበቱ ሙታን መሃል መቆም ሙት መሆን መስሎ ተሰማኝ፡፡ እንዳሌ በነጭ ከፈን ተጋርደዋል፡፡ ከነዚህ መሃል የቱ ነው አንድዬ? አላውቅም፡፡ የክፍሉን በር ዘግቼ እየገለጥኩ ልፈልገው ወሰንኩ፡፡ ከአጠገቤ ጀመርኩ፡፡ አሃዱ ከማለቴ ሰቅጣጭ በድን ተመለከትኩ፡፡ ታርዶ የሞተ ወጣት፡፡ አፌን በነጠላዬ አፍኜ ጩኸቴን ዋጥኩት፡፡ ስልቅጥ፡፡ ከዚህ በሗላ ያሉትንስ እንዴት አያቸው ይሆን፡፡ በውድቅት ለሊት በድን መሃል መሆኔን ሳስበው ፈጥሮ የረሳኝን አምላክ ለመራገም ቃጣኝ፡፡ ሲጀመር አምላክ አለ እንዴ? አለ ለማለት ሰው እንዴት ቻለበት? የፍጡራን በምድር ላይ መርመስመስ ነው አለ ያስባለው ወይስ ነግቶ መምሸቱ የዕለት ፍርቅታው? ማንስ አይቶ ዳሰሰው መገኘቱንስ አወቀ? እንደው በደፈናው አምላክ አለ ተባለ እንጂ እኔ በዘመኔ ፈፅሞ አላውቀውም፡፡ እንባዬ ሲዝረበረብ ግድ ካልሰጠው...መኖሩ እምኑጋ ነው፡፡ ሰማይ ላይ ነው ወይስ ምድር ላይ? ሰማይ ከላይ መሆኑንስ ማን አወቀ? ምድር ላይ ቢሆንስ...? ከውጪ በኩል ወደሬሳው ክፍል የሚያመራ የኮቴ ድምፅ ሰማሁ፡፡ ብርግግ፡፡ እምን ውስጥ እሰወራለሁ ጨነቀኝ፡፡ ከአንዱ አስክሬን ካዘለው አልጋ ስር በደረቴ ተሰጣሁ፡፡ የሆነ ነገር የሚገፉ አይነት ድምፅ ይሰማኛል፡፡ ልክ ነበርኩ ሌላ አስክሬን በተሽከርካሪ አልጋ ላይ አንጋለው እያስገቡ ነው፡፡ ሁለት ወንዶች እየተነጋገሩ፡፡ "ከሰዓታት በፊት በዘራፊዎች ተገደለ የተባለው ቤተሰቡ እንዲያውቅ ተደርጓል?" ድምፀ ጎርናናው ጎረምሳ ጠየቀ፡፡ "በሚገባ ግን እናትየው ከመቅፅበት ነበር የሄዱት፡፡ ምን እንደተፈጠረ አላወቅንም፡፡ ራሳቸውን የሆነ ነገር እንዳያረጉ ሰግተናል" ሁለተኛው መለሰ፡፡ እያወሩ ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡ ጊዜ ሳላጠፋ ፍለጋዬን ጀመርኩ፡፡ ጥቂት በድኖችን ከገረመምኩ በሗላ አገኘሁት፡፡ እዬዬን አስነካሁት አነባው አረርኩ ድብን ብዬ ቆሰልኩ፡፡ አካሉ ላይ በምን አቅሜ ስለት ላሳርፍ ጨነቀኝ ጠበበኝ፡፡ የሞት ሞቴን ሸረከትኩት፡፡ ወደ ብልቃጡ አንቆረቆርኩ፡፡ በድኑ ልጄን ግንባሩን ስሜ ተሰናበትኩት፡፡ የተባልኩትን አደረግሁ፡፡ ለአዋቂው ሰጠሁት፡፡ "በስውር የሚሰራ ነው እደጅ ጠብቂ" ደጃፉን ሊሸጉር መዝጊያውን ይዞ እንድወጠሠ እያመላከተኝ፡፡ ወጣሁ፡፡ አይዞህ ባይ የሌለው እምባዬ ይወርደዋል፡፡ በዛች ቅፅበት አለም ለኔ ብትበቃኝ ምነኛ በታደልኩ፡፡ ዕድሌን ተጠየፍኩት፡፡ ራሴን አጥፍቼ በመኖሬ ያስከፋኝን አለ ብለው ማላየውን ፈጣሪማ አላስደስትም፡፡ አቅሌንም ስቼ ጨልዬም ቢሆን እኖራለሁ፡፡ ቀና ያልኩት ጎጆዬ ከዘመመ ምንስ ይኖረኛል፡፡ "ነይ ግቢ" ከሀዘን አቀበት አናጠበኝ፡፡ ፊቴን በነጠላዬ አባብሼ ዘለኩ፡፡ "ይኸውልሽ አሁን በድኑ ከክፍሉ ወጥቷል፡፡ ማንንም አይተናኮልም፡፡ የተገደለበት ቦታ ይመጣል፡፡ ከአፈር የተደባለቀ የረጋ ደሙን ይልሰዋል፡፡ ከዛም ገዳዮቹን አሳዶ ያሉበት ሄዶ ይገድላቸዋል፡፡ አንድ ነገር አስተውዪ፡፡ ዛሬውኑ መስዋዕት ማስገባት ይኖርብሻል"፡፡...መቀነቴን ፈታሁ፡፡ "አሁን አይደለም ሰዓቱን ተመልከች ለሰባት እሩብ ጉዳይ ነው፡፡ ከሰላሳ ደቂቃ በሗላ ስለቱን ካላስገባሽ በድኑ ዕድሜ ዘመኑን የሰው ስጋ ሲመገብ ይኖራል፡፡ ግን አንቺን ይሰማሻል፡፡ ያላመድሽውን ይለምዳል፡፡ ያጠመድሽውን ያደምጣል፡፡ ለሰከንድ ሽራፊ ብተዘገዪ ተሳስተሽ እንዳትመጪ፡፡ ቁጣዬ ባንቺ ላይ ነው"፡፡ አይኑን አጉረጥርጥ አስጠነቀቀኝ፡፡ እኔ ግን ከቁብም አልቆጠርኩት፡፡ አይኔ የቃበዘው ገዳዮች ሲሞቱ ማየትን ነው፡፡ በድኑ የተገኘበት ስፍራ ስገሰግስ ደረስኩ፡፡ ከደቂቃዎች በሗላ እንደ ልከኛ ሰው የማይራመድ አንገቱን የሰበረ አካሉ አልታዘዝ ያለው እርቃናም ሰው ወዳለሁበት ስፍራ ያዘግማል፡፡ ራሴን ለመሸሸግ የሆነ ጥሻ ስር ተጠጋሁ፡፡ አሁንም ልቤ አላምን አለኝ፡፡ ጠዋት ምሳ ቋጥሬ የሸኘሁት ልጄን መሞቱን መቀበል ፍፁም ለነፍሴ ከብዷታል፡፡ ....ይቀጥላል እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን 👍100
Показать все...

​🌿‍ የጠፋው ሬሳ🌿 ምዕራፍ 2️⃣ ክፍል 2️⃣2️⃣ ደራሲ፡- የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...ሞት ራሱ ይሙት የታባቱ፡፡ ከእግሩ ሸብረክ ብሎ ከነትቢያው የረጋ ደሙን አግበሰበሰ፡፡ ብርቱም ሆኖ ቀና አለ፡፡ ስፈራ ስቸር ተጠጋሁት፡፡ አልተተናኮለኝም፡፡ ልጄ የቁም ሬሳ ሆነ፡፡ ተንቀሳቃሽ በድን፡፡ ደመ ነፍስ የሚዘውረው ያልተቀበረ ሙት፡፡ እጁን ይዤ አነሳሁት፡፡ ይውተረተራል፡፡ ሰው ሳያይ ሸሽጌ እቤት ወስጄ አለበስኩት፡፡ የተወጋው አካሉ ገና አልጠገገም፡፡ እነዛ ነፍሰ በላዎች ይሄኔ እየተጫጫሱ ነው፡፡ "ግደላቸው" አዘዝኩት ይሰማኝ እንደሁ ለማወቅ፡፡ ሳያመነታ ደጃፉን ስቦ ወደ ውጪ ወጣ፡፡ ተከተልኩት፡፡ መንደራችን ውስጥ ወዳለው አነስተኛ የመጠጥ ግሮሰሪ አመራ፡፡ ጭፈራው ለጉድ ነው፡፡ ፌሽታው ጫጫታው ለኔ ብቻ ነበር ሀዘኑ፡፡ ለማንም ግድ አልነበረም፡፡ ቀጥ ብሎ ገባ፡፡ ፊት ለፊት ያገኘውን ክፍል ትቶ ወደ ቀኝ ታጠፈ፡፡ ጠርሙስ ሰብሮ አደኛው ጎሮሮ ላይ ሰቀሰቀበት፡፡ እሰይ እልል አልኩ በውስጤ የልጄ ነፍስ ፍትህ በማግኘቷ፡፡ ሌላኛው ሴት ጭን መሃል ተወሽቆ ቤርጎ ውስጥ አገኘው፡፡ በካቻ ቢቴ አይኑን ጎልጉሎ አስቃይቶ ገደለው፡፡ ይሄን ሁሉ ትዕይንት በቅርብ ርቀት እያየሁ ነበር፡፡ ያስጨከነኝ ጭካኔያቸው ነው፡፡ አውሬ ያረገኝ አውሬነታቸው ነው፡፡ ባይነኩት ባልተነካካን ነበር፡፡ የነሱም እናቶች ከኔ እኩሌታ እንባን ይዩት፡፡ ፅዋውንም ይጎንጩት፡፡ ቢመርም፡፡"... "እውነት አለሽ" በውስጤ አጉተመተምኩ፡፡ ሰቆቃዋ ሰቀቀኝ፡፡ ህመሟ አጥንቴን ሰርስሮ ተሰማኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ሚስጢር ለኔ ስለምን ይነግሩኛል? እሰማው ዘንድስ ማን መረጠኝ?...ሴትየዋ አላቁሙም አሁንም ያትታሉ፡፡ "ደስታዬ ድርብ ባይሆንም ሀዘኔን ይቀንስልኛል፡፡ በድኑ ጋር ኩርምት ብሎ ተቀመጠ፡፡ አካባባቢው በጩኸት ናውዟል፡፡ ደሜ እንደ ክረምት ጎርፉ ይወርደዋል፡፡ የአንቡላንስ ድምፅ የፖሊስ ውርውርታ የወደመ ከተማ አስመስሎታል፡፡ እጁን ይዤ ብወጣ እና ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ግና አልችልም፡፡ ከደቂቃዎች በሗላ አጠገቡ የነበረውን ሬሳ እላዩ ላይ ተለጥፎ በጥም እንደነደደ ሁሉ የሟቹን ደም ተጋተው፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ከተባለው የመስዋዕት ሰዓት ዘግይቻለሁ፡፡ ልጄ እድሜ ዘመኑን የሰው ስጋ እየበላ እንዲኖር ፈረድኩበት፡፡ ራሴን ጠላሁት፡፡ ከሞቱ ይልቅ ቆሞ በመራመዱ የሸለምኩትን ስቃይ ሳስበው ለራሴ ይቅርታ ለማረግ አቅሙን አጣሁ፡፡ ከበድኑ ላይ መንጭቄ አነሳሁት፡፡ ከፊት ለፊቱ በጥድፊያ ተራመድኩ ተከተለኝ፡፡ "እሱ ነው"፡፡ "ይሄ ነው ገዳዩ"፡፡ ከዚም ከዚያም ልጄን ከሳሽ ድምፁን አሰማ ወንዱም ሴቱም፡፡ ቢረፈርፋቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ ፖሉሶች ተከተሉን፡፡ በዛ ውድቅት ጫካ ለጫካ እያሳበርን ዝም ብለን ተጓዝን፡፡ ይህን ሁሉ ነገር ስንከውን ሲስተር አድማሴ እየተከታተለች ትመለከተን ነበር፡፡ እኛ አላየናትም፡፡ ንጋት ለመቃረቡ የሰማዩ መወገግ ያሳብቃል፡፡ ከአንዱ ዛፉ ስር አረፍ አልኩኝ፡፡ ጀርባውን ሰቶኝ ተቀመጠ፡፡ ያነፈንፋል፡፡ የሆነ እግዳ ሽታ እንደሸተተው ሁሉ፡፡ ከዛም ተነስቶ መተረማመስ ጀመረ፡፡ ተከተልኩት፡፡ ሲስተርን ከጥሻው መንቅሮ አወጣት፡፡ "እንዳትነካት!" አክላላሁበት፡፡ ለቀቃት፡፡ ወደኔ ጠራሗት፡፡ ምን ታረጊያለሽ እዚ? ስትከተይን ነበር አይደል "አዎ ተከትያችሁ ነው ግን አሁን ሳይሆን ከሬሳ ክፍል ተነስቶ ከወጣ ጀምሮ ነው፡፡" አንገቷን ደፍታ እጇን እያፍተለተለች፡፡ "እኮ ለምን ተከተልሽው?" "ሁኔታው አስደኔግጦኝ ነው፡፡ የማረገው ጠፋኝ፡፡ ለሰው እንዳልናገር የሆነ ነገር አንደበቴን ሸበበው፡፡ በቃ ዝም ብዬ ነበር የተከተልኩት፡፡ ምክንያት የለኝም፡፡ እኔን የሳበበት አንዳች ሚስጢር አለው፡፡" አልጠረጠርኳትም አመንኳት፡፡ ሚስጢራችንን ማወቋ ለኛ አደጋ ቢሆንም እንድትሞት አልፈለኩም፡፡ "ያወቅሽው ነገር ያጠፋሻል ይሄ መቼም ላንቺ እንግዳ አይሆንም፡፡ ግና ካልተጎራበጥሽን ምን አይነካሽም፡፡ በዚህ ቃል ከገባሽ አንዳች አትሆኚም" አይኖቿን እያየሁ አስጠነቀኳት፡፡ በአንገቷ ንቅንቄ እሺታዋን ገለጠች፡፡ ከዛች እለት ጀምሮ አብራን ነች፡፡ የኛ ፍፁም ወዳጃችን፡፡ ይሄን የቆየ እና የተዘጋ ሆስፒታል በጉዟችን መሃል አገኘነው፡፡ ከአዲስ አበባ ድረስ በእግራችን ተጉዘን እዚ ደረስን፡፡ ራሳችንን ሰውረን፡፡ በቃ ልቤ ደነደነ፡፡ ልጄ ሁሌም ሰው ያድናል፡፡ ለመድኩት ሀዘን ይሰብረኝ ዘንድ አቅም አጣ፡፡ ጨከንኩ፡፡ ከአረመኔ እጥፍ ጭካኔ፡፡ ሲስተር ለኔና ለራሷ ምግብ ታዘጋጃለች፡፡ የሱን እንደምታውቂው ነው፡፡ ለኔ ልጄ ነው፡፡ አሁንም ድረስ አልጠየፈውም፡፡ እያለ እያለ አመት ከአንድ ወር ሞላን፡፡ በቃ እንዲሁ የቁም ሞት ቅዠት ውስጥ ስንዋልል፡፡ አዋቂውን ልማጠነው ባፈላልገው አላገኘሁትም፡፡ ጊዜው ደርሶ እስኪያሸሌብ ከልጄ ጎን ነኝ፡፡" ሲስተር ተብዬዋ የሴትየዋን ንግግር አቋረጠቻት፡፡ "ሜርሲም ልጅሽ ናት" አለች፡፡...ይቀጥላል እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን፡፡ እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን፡፡
Показать все...

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.