cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot

Больше
Рекламные посты
1 455
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ከዕለታት በአንዱ ቀን ነብያችን ﷺ ታላላቅ ከሚባሉት ሰሃቦች ጋር መስጂድ ውስጥ ተቀማምጠው ሳለ አንዲት ሴት ድንገት በሩ ላይ ብቅ አለች ፡፡ በቀጥታም ነብያችን ﷺ ወደተቀመጡበት አምርታ ከፊት ለፊታቸው ቆመችና ሃያዕ በተጫነው ድባብ ‹‹ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ.......
Показать все...
........
ሙሉውን ለማግኘት
እስልምናን ከተቀበለ ከደቂቃዎች በኋላ ሸሂድ የሆነው ጀግና ማነው?
Показать все...
ካሊድ ኢብኑ ወሊድ
አቡ ጧሊብ
ኢማሙ አህመድ
ኢብኑል ቀይም
መልሱ አልተጠቀሰም
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ አምስት (የመጨረሻው ክፍል) (ሂባ ሁዳ) . . ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ። <<ማሂ እሺ አሁንስ?>> <<አሁንማ... አሁንማ ኢብቲ...ተስፋ የቆረጠ ሰው አታውቂም?...ራሱን የጠላ ሰው?... መኖር የሰለቸው? ....እየኖረ የሞተ?.... ህልሙን ቅዠት የሆነበት?... ከራሱ ርቆ በሌሎች የተደበቀ.... ልቡን ላለማድመጥ ጩኸት የሚፈጥር?... ከኑሮ ለመሸሽ በጪስ የተወሸቀ?...ኢብቲ ከፊትሽ ያለው ለሴቶች ክብር ብሎ የሚጣላው ማሂር እኮ አይደለም። የሴቶችን ክብር የሚወስድ እንጂ..>> ድምፁ በሲቃ ታፈነ አይኖቹ መሸከም ያልቻሉትን ዕንባዎች ሲለቋቸው ቁልቁል ፈሰሱ። ከዚህ በላይ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም። ድንዝዝ ያሉት እጆቼ ዕንባዬን መጥረግ ተሳናቸው። ምንም ቃል መናገር አልቻልኩም የማሂ ዕንባ እያይሁ ከማንባት ውጪ። እንደምንም ራሱን አረጋግቶ ግንባሩን በሁለት እጆቹ ደጋፍ አደረገ <<ኢ.ብ..ቲ>> ድምፁ መቆራረጥ ጀመረ። <<አ.ል.ች.ል.ም እንዲህ መኖር አህ.ህ.ህ>> እጆቹ እንደመንቀጥቀጥ አደረጋቸው። <<ማሂሬ ደና ነህ?>> በጣም ደንግጫለው አይኑን ይጨፍናል መልሶ ይገልጣል .. <<ማሂ ማሂሬ?>>ድምፁ ጠፋብኝ <<ትንሽ ደቂቃ ብቻ... ይ.ተ.ወ.ኛ.ል ..>> . <<ኢብቲ አየሽ አይደል እዚህ ድረስ ነኝ.. በሰዐቱ ካልተጠቀምኩ እንዲህ ነው የሚያደርገኝ መውጣት ማልችለው ሱስ ውስጥ ወድቄያለሁ። ኢብቲ ከዚህ ቡኃላ የኔ የምለው ምንም አይነት ነገር የለኝም፤ የኔ ቀርቶ እኔም አልኖርም። እኔ እኮ አሁን አንቺን ማግኘቴ ደስ ብሎኛል። ቢያንስ እንደኔ ሌላ ሰው ሰው በማጣት የህልሙ ብርሃን ጭላንጭል ሲሆን... ጭላንጭሉን ወደ ብርሃን እንዲቀየር እንደምታግዥው ለራሴ ቃል ትገቢልኛለሽ። ከአሁን በኃላ ሰሚ ላጡ አባሽ ለሚፈልጉ ዕንባዎች እንደ አሁኑ አብረሻቸው ከማልቀስ ይልቅ መፍትሄ እንደምታመጪላቸው እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ። ኢብቲ ያለፈው ፀፅቶሻል? ጎድቶሻል አይደል? በሌሌች አስተካኪው። ከመስማት ማድመጥን ልመጂ። ማየት ብቻ ሣይሆን በመመልከት አስተውዪ ...>> <<ማሂሬ እንዴት ልቻለው? ይሄን ሁሉ ከመሆኑ በፊት እኮ..ማሂ ይሄ ሁሉ በኔ እኮ ነው! ራሴን ምን ብዬ ላሳምነው?>> ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልኩም ስቅስቅ ብዬ ከማልቀስ ውጪ። <<ኢብቲ ነገርኩሽ እኮ... በቃ ያለፈ ታሪክ ነው። ያገኘሁሽ ሁላ በኔ ምክንያት መጨነቅሽን ትተሽ ሰላምሽን እንድታገኚ ነው።>> <<ማሂ ለዚህ ሁሉ ስህተት ምንድነው ይቅርታው?>> <<ኢብቲዬ ማርፈድ ከትምህርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል። በኔ ህይወት አንቺ አልዘገየሽም፤ እኔ ቸኮልኩ እንጂ.. እኔን እርሺኝ ከአሁን በኃላ የሚመጡትን ማሂሮችን እርጂያቸው። ከዚህ በላይ ስታለቅሺ የማየት አቅሙ የለኝም። ማንም አንቺን ባያስከፋሽ ምኞቴ ነው። በኔ ምክንያት እንድታለቅሺ ከቶ አይቻለኝም። ቃል እንድትሰጭኝ ፈልጋለሁ ማሂን በድዬዋለሁ ብለሽ እንደማታለቅሽ..>> <<ማሂ ጭራሽ ከአዕምሮዬ በላይ ሆንክብኝ እኮ። ያልከኝን ሁሉ አደርጋለሁ ግን በጣም ይ.ቅ.ር.ታ...ስለሁሉም>> ድምፄ ታፈነ ማውራት እየፈለኩ ግን አንደበቴ ተሳሰረ። ከሚቆራረጠው ትንፋሼ በቀር .. <<ማ.ማማ..ሂ.እኔ... >> ወደኔ ተጠጋ ሊያባብለኝ ሞከረ፤ ግን አልሆነለትም። ዕንባዎቹ እየተሽቀዳደሙ መሰለኝ። ለመጥረግ ብሞክርም እንደ አዲስ የሚፈሱት እጄን አረጠቡት። እንደ ትኩስ ውሃ ቢያቃጥለኝ፤ ልቤ ከሚለበልበው ህመሜ በላይ የሱ ሲቃ ገዘፈብኝ። እጄን ከፊቱ ላይ አወረዳቸው ወደ ጆሮዬ ተጠጋ። <<ኢብቲ እኔ ከአሁን በኃላ የለሁም። ስለኔ ብለሽ ሌሎች ማሂሮችን እርጂያቸው ስለኔ ስታለቅሺ ከዚህ በላይ ማየት አልችልም>> ለመጨረሻ ጊዜ ከማሂ የወጡ ቃላት ነበሩ። ማሂ እያየሁት በምን ፍጥነት በር ጋር እንደ ደረሰ እኔንጃ ብቻ በር ጋር ሲደርስ አንዴ ዞር ብሎ አይቶኝ ከአይኔ ሸሸ። . ከደቂቃዎች ቡኃላ ተረጋጋሁና አካባቢዬን አስተዋልኩ፤ ጠረዼዛው ላይ ማሂ ሂሳብ አስቀምጧል በኩባያ ሙሉ ወተት አለ። ማሂ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ውሃ ሰማያዊ ጂንስ ጃኬት አለ አንስቼ ያዝኩት፤ የማሂሬ ነበር። ለትናንቱ ህመሜ ዛሬ ማስታገሻ አጊቻለሁ...ትናንት ላይ የባከኑት ቀናት ዛሬ ላይ ዋጋ አስከፍለውኛል ያውም በማሂሬ! . ሁላችንም ውስጥ ትላንት አለ፤ ትናንታችን ውስጥ ደግሞ ስህተቶች አሉ፡፡ ምናልባት የኛ ምናልባትም ደግሞ በህይወታችን ዉስጥ የገባ የሌላ ሰው ስህተት አለ፡፡ ከትላንት ስህተታችን ለመታረም መቁረጥ አለብን፡፡ እኛ ህይወት ውስጥ ስህተት የሚፈጠረው በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በእኛ ምክንያት ነው፡፡ ባለማወቅ ሰዎችን ብዙ ጎድተና፤ እንዲያዝኑ አድርገናል፤ በእርግጥ ሰዎችን ከልክ በላይ የሆነ ቦታ እንዲሰጡን የሚያደርጉ ነገሮች አሉ፡፡ ግና ትክክል ነው ብለው አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የነሱን የህይወት ፈተና ማለፊያ ያደርጉናል... አልያም እናደርጋቸዋለን፡፡ ይሁና.......! ሁሉም በየራሱ መንገድ ትክክል ነው፡፡ በቃ...አሁን ዛሬ ላይ ነን። ምናልባት ነገ ብለን ትናንት ተስፋ ያደረግነው ነገር ዛሬ ላይ ፀፀት ሆኖ ይሆናል፤ ግን አልፎዋል አራት ነጥብ፡፡ ያ ሁሉ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እምነት፣ ስህተት ....በቃ ሁሉም ትላንት ነው፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው! አዲስ ከስህተት ተምረን የምንለወጥበት ባለፉ ስህተቶች ድጋሚ የማናልፍበት። ሌላ ከኖርነው እድሜ ላይ የተጨመረችልን ልዩ ቀን። ያለፈው ይሁና.......! ይሄን ሁሉ አልፈን እንድንቆም ለረዳን አላህ ምስጋና አቅርበን ነጋችንን የምንስልባት ባለ ፀሀይ ቀን፡፡ እርግጠኛ ነኝ ነገ ከትላንት ይሻላል፡፡ የሄደው ነገር ሁሉ ለመልካም ነው፡፡ ዛሬዬን ያዘጋጀልኝ ጌታዬ ነገዬን የተሻለ እንደሚያደርግልኝ አምናለው፡፡ ምናልባት አልሄድንም ይሆናል ፤ አልመጣንም ይሆናል ፤ ግን ፈቀቅ ብለናል ፡፡ ቅድም ማሂ በሰጠኝ ወረቀት ጀርባ መሞነጫጨር ጀመርኩ... ምን አልባትም ለማሂ የፃፍኩት የመጨረሻ ቃላቶቼ ናቸው። #ግራጫ_ቀናቶች ~~~~ ጣዕም የለሽ ህይወት ትርጉም አልባ ኑሮ ፤ ቀንም ሆነ ምሽት የሳግ እንጉርጉሮ ፡፡ በጥቁር ደመና እንባን ያቀረሩ ፤ በሳቅ በትወና ባዷቸውን የቀሩ ፤ ወይ ከነጭ አልሆኑ ወይ ደግሞ ከጥቁሩ ፤ ብዙ ቀኖች አሉኝ በመሃል የቀሩ ፡፡ የፃፍኩትን ወረቀት ሳጣጥፍ ከጀርባው ሌላ ፁሁፍ በትናንሹ ተፅፎ አይሁ ለማንበብ ወረቀቱን ዘረጋሁትና ማሂ እንዳለኝ በአትኩሮት ለማንበብ ራሴን አብሰብ አደረኩ። ❝ግን በመሄድና በመምጣት የጊዜ ርዝማኔ ውስጥ የተስፋ ስብራቶች፣የልብ ቁስሎች ፣ የአእምሮ መላሸቆች ስንት ይሆኑ...? ባለመኖር እውነታ ውስጥ ስንት የመኖር ህልም ይሞት ይሆን.....? በትናንት ህመም ውስጥ ስንት ዛሬዎች ባከኑ፤ የነገ ህልሞች ደቀቁ............❞ አንብቤ ስጨርስ እንደ ጀት ቅርፅ ሰራሁበት ከካፌው እንደወጣሁ ወደ ሰማዩ ለቀኩት..በአንዱ መስመር ሲሄድ እኔ በሌላኛው መስመር ሄድኩ .... ተፈፀመ •••••• t.me/Habibacalligraphy
Показать все...
Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot

#ትዝታ . . ትዝታ እኮ ሳቅ ነው ቢኖረውም ትካዜ፤ ትዝታ ታሪክ ነው የማይረሱት ጊዜ፤ እኔም ኑሪያለሁኝ በትዝታ አለም፤ ስለአንች በማሰብ ስለአንቺ በማለም። መኖር ከተባለ እኔም ኑሪያለሁኝ፤ በዝምታ አለም ሁሌ እየፈራሁኝ፤ በአይናፋር አንደበት ዝምታን መርጬ፤ ከመናገር ይልቅ በሀሳብ ቀጭጬ፤ ራሴን በመደበቅ ማውራትን ፈርቼ፤ በስቃይ ኑሪያለሁ ግራ ተጋብቼ። . ራሴን በመውቀስ ራሴን በመስደብ፤ በዚች አስቸጋሪ በዚች ፈታኝ አለም፤ በተመስጦ ታሪክ በሚመስል የህልም፤ እውነት ኑሪያለሁኝ 'ኔነቴን በማሰብ። . <<ግጥም እንደምትፅፍ አላውቅም ነበር።>> ግጥሙን አንብቤ ቀና እያልኩ። <<ምንም አታውቂም አልኩሽ ኮ ..ብዙ ፅፌ ነበር ግን የሆነ ቦታ ቁጭ ስል እንዲበሩ እለቃቸዋለሁ እስካሁን ምንም አላገኘሽም እንዴ...>> ፈገግ ለማለት ይሞክራል። <<እሺ ማሂ ያለፈውን ታሪክ አወራን፤ እሱ እንደግጥምህ ነው.. ትዝታ ልንለው እንችላለን። አሁንስ እሺ ማሂ አትደብቀኝ እባክህን..>> <<ኢብቲ ላንቺ ምንም አይጠቅምሽም አውቃለሁ። ነገራቶችን ለማስተክልከል ትፈልጊያለሽ ግን የማይስተካከል ህይወት አለ>> <<ማሂ በናትህ ህመሜን ቀንስልኝ...>> ንግግሬን አላስጨረሰኝም <<እናቴ ብትኖር እዚህ ነገር ውስጥ የምገባ ይመስልሻል? ተያ ኢብቲ... በቃ አንቺ እንደምታስቢኝ አይነት ማሂር አይደለሁም፤ ልሆንም አልችልም። መጥፎ ሰው ነኝ፤ አሁን ምንም አላማ የለኝም። እውነቱን ልንገርሽ? ያኔ በረመዳን ሚሪንዳ ስጠጣ እንደዛ ለደነገጥሽው ለምነግርሽ ነገር ምን ልትሆኚ እንደምትቺ ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር። ስለኔ ከአሁን በኃላ እንድትጨነቂ አልፈልግም ኢብቲ። እኔ ማሂ በአሁኑ ሰዐት አልንገርሽ ያኔ በምታውቂኝ ማሂ ኑሪበት..>> አይኖቹ እንባ አቀረሩ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ ልናገረው አልችልም፤ ብቻ እንደምንም ራሴን ለመቆጣጠር እታገላለሁ። <<በመጀመሪያ ኢብቲ እወቂ.. በጣም እንደምወድሽ። እንዲህ ስልሽ ግን ባልሆነ መንገድ እንዳትረጂኝ ምን አልባት እህት ስለሌለኝም ይሆናል። እናቴን በልጅነቴ ማጣቴም ይሆናል። እነሱን የምትተኪልኝ ይመስለኝ ነበር፤ ከአንቺ ጋር እህትና ወንድም ሁነን እንዴት እንደምንሆን እንደምናድግ ብዙ ጊዜ አስበው ነበር። አለ አይደል የራሳችን ላይፍ ኖሮን ሁላ እንደ ፍሚሊ ልንኖር.. ብቻ ብዙ ብዙ ሃሳብ ሆኖ ቀረ እንጂ፤ እስካለፉት ሶስት አመታት ድረስ..>> አይኑን ማየት አልቻልኩም አንገቴን ከመሰብር ውጪ። ዝምታው ያስፈራል፤ ረጅም ደቂቃ ዝም አለ። <<ማሂ እሺ አሁንስ?>> . . የመጨረሻው ክፍል... ነገ ይቀጥላል... t.me/Habibacalligraphy
Показать все...
Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot

የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ አራት (ሂባ ሁዳ) . . ለማሂ በቴሌግራም መልዕክት ላኩለት <<ሰላም ማሂሬ...>> <<ወዬ እንዴት ነሽልኝ ውድ አለሽልኝ?>> <<አልሃምዱሊላህ አለሁልክ እ..አወቅከኝ? ኢብቲሳም ነኝ ..>> <<ኧረ እንዴት ሆኖ አንቺን እረሳለው.. እየጠበቁሽ ነበር ትመጪያለሽ ብዬ የሚለውን ግጥም ታውቂዋለሽ ሃሃሃሃ>> <<ሃሃሃ አላውቀውም.. እና እንዴት ነክ ሁሉ ሰላም?>> <<የዋህ ምን ይሆናል ብለሽ ነው አለሁልሽ>> <<መኖር ደግ ነው...እና ቤተሰብ ሰላም ነው ናቸው?>> ኡፍ ከምን ጀምሬ ማውራት እንዳለብኝ እንጃ... <<እኔ እያለሁ ምን ሊሆኑ..አንቺ ጋርስ ?ሁሉ ሰላም ነው?...>>ስለ በፊቱ አንዳንድ ነግሮችን አንስተን ስንስቅ ትንሽ ቆየን። <<በቃ ኢብቲ ደክሞኛል ልተኛ ነው ነገ እናወራለን...>> <<እሺ ሰላም እደር ...>> ከኦን ላይን ወጥቼ ማሂን እንዴት ማውራት እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ መሽቶ ነበርና ከሃሳቤ ጋር በዛው አሸለብኩ። * ከሰኞ ጀምሮ በተከታታይ የፋይናል ፈተና ስለነበረኝ ኦንላይን ብዙም አልኖርም። ከማሂ ጋርም ሰፊ የማወራበት ሰዐት አላገኘሁም። እንደምንም እየገባሁ መልዕክት አስቀምጥለታለሁ። ግን ምላሹ ሁሉ ቀልድ ነው፤ አልያም ወሬ ይቀይራል። ነገራቶችን ሸፋፉኖ ማለፉ ምንም አልተዋጠልኝም፤ የሚጠቀማቸው ቃላት ጭራሽ የማላውቀው ሰው እያወራሁ ይመስለኛል። ፈተና ስጨርስ ሊያገኘን እንደሚችል ጠየቀኝ... ሳላመነታ ተስማማሁ። ግን ሳገኘው ማሂር ወፍሮ ይሁን..ወይንስ ረዝሞ..ያ ፈገግታው ይኖር ይሁን...ወይስ...ኮስታራ ሆኖዋል..ማሂ የተሻለ ሂወት ውስጥ ይሁን...ወይስ መጥፎ ሂወት እየገፋ ይሁን..አሁን ደስተኛ ነው ...አልያም ብሶተኛ.. ማሂ ምን አይነት ህይወት ውስጥ ይሁን? * #ከሳምንት_ቡኃላ #ዕለተ_ቅዳሜ_8:00 #ጦር_ሃይሎች * <<ሰላም ምን ልታዘዝ?>> ከወገቡ ጎንበስ እንደማለት እያለ አፈራርቆ ያየናል፤ አስተናጋጁ። <<ኢብቲ ምን ይሁንልሽ ምሣ ምናምን ...?>> <<አይ ማሂ በልቻለሁ ወተት ይሁንልኝ..>> <<በቃ ለኔ ማኪያቶ..>> <<ወተቱ በትልቁ በትንሹ ?>> አስተናጋጁ ደግሞ ጠየቀ። <<በትልቁ አድርግላት ድመት ነገር ናት ..>> <<ሳፊ ወይስ ...>> <<ዉይ ኖርማል አድርግላት በቃ!>> አስተናጋጁ ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ። <<በፈጣሪ ካልዲስ ደግሞ አያዝጉ። ትልቅ፤ ትንሽ...ሳፊ ምናምን ከዛ ደግሞ ከአንድ ሰዐት በኃላ ይዘው ይመጣሉ..>> <<ያው እያወራህ ከሆነ ችግር የለውም ከቸኮልክ ነው የሚያበሳጨው...>> <<ኧረ ኢብቲ እኔ ትግስት የለኝም መጠበቅ ምናምን ኡፍፍፍ። አንቺ ፀሃይዋ አንቺ ልከሻት ነው በረታችብኝ እኮ>> ከላይ የለበሰው ውሃ ሰማያዊ ጃኬት አውልቆ ወንበሩ ላይ አንጠለጠለው። <<ምነው?>> አይኔ ወዳረፈበት እጁ ግራ በመጋባት ተመለከተ። <<ኦውውው ይሄን አይተሽ ነው እንዴ>> እጁ ላይ ወደ ተሳለው ታቶ እያመላከተኝ <<አያምርም እንዴ?>> <<አይ ገርሞኝ ነው...>>ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ እየተጋባሁ.. <<አንዴ መጣሁ ..>> ወደ ውጪ መራመድ ሲጀምር በደንብ ለማየት ሞከርኩ። ፀጉሩ ተንጨባሯል፤ ሰውነቱ ከስቷል፤ እስካሁን ምንም አልነገረኝም ምን ውስጥ ሊሆን ይችላል? ብዙ ነገራቶች ለአፍታ ተፈራረቁብኝ.. . <<ኢብቲ ወዴት ሄድሽ?>> <<ኧረ አለሁ ከመቼው ተመለሰክ ..>> <<አይ ስገባ አይቼ ነበር ቀድመሽኝ እንዳትገቢ ስቸኩል አልፌው መጣሁ። አሁንም እንደምትወጂ እርግጠኛ ነኝ..>> ሎሊፖፕ አቀበለኝ። <<እውነት ነው በሎሊፖፕማ አልጨክንም አንተ ደግሞ አትረሳም ሃይ ጎበዝ ነህ...>> <<አይ ኢብቲ እንዴት ይረሳል>> ሌላ ሃሳብ ውስጥ ሲገባ አትኩሬ ተመለከትኩት። በፊት በኩል ጥቁር ፀጉሩ አሁን በሌላ ቀለም ተቀይሯል፤ ድቅድቅ ብሎ የተሳሰረ የሚመስለው ቅንድቡ በአንዱ በኩል ተቆርጦ መሃል ላይ ክፍተት ተፈጥሯል፤ ከንፈሩ አካባቢ በልዟል... ከዛ በላይ መመልከት አልቻልኩም ማሂ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንደገባ አሰብኩ። እኔ ማስበው እንዳይሆን ፈራሁ.. <<ማሂ?>> <<ወዬ...ተመሰጥኳ? ታውቂያለሽ ኢብቲ ያ ጊዜ ደስ ይል ነበርኮ..>> <<ማሂ አሁን እንዴት ነህ በአላህ? ደህና ነህ?>> <<ደህና አልመስልማ? ምነው አስፈራሁሽ እንዴ?..ባይሆን ጠጪ እስቲ>> <<ማሂ የተገናኘነው ሻይ ቡና ለማለት አይደለም...እንድናወራ ነው። ...እስቲ አውራኝ እንዴት ነህ..>> <<ለምን ስለኔ ትጨነቂያለሽ? ትወጂኛለሽ እንዴ?..>> ማሂ አይን አይኔን ሲያየኝ ይባስኑ አጨናነቀኝ። <<እንዴ ማሂ ለምን እጠላሃለው? ለምን አሎድህም?>> <<እንደሱ ነው እንዴ>> ከልብ በማይመስል ፈገግታ መለሰልኝ። <<ማሂ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ። ማውቄ እኔን ጎድቶኛል ምክንያቱም ያኔ ምንም ላደርግልህ አልቻልኩም ነበር። አሁን ግን...>> <<አሁን ምን? እስቲ ምን ታውቂያለሽ? ሃሃሃ... ምን ታውቂያለሽ ከስሜ ውጪ..?>> <<እሺ አንተ ንገረኝ ማላውቅ ከሆነ..>> <<ከምን እስከ ምን ኢብቲ? ብታውቂስ ቆይ ምን የምትለውጪው ነገር አለ? ሰምተሽ አይዞህ ልትዪኝ ነው? አመሰግናለሁ..>> ማኪያቶውን በሁለት ትንፋሽ ጨለጠው፤ ፊቱ መቀያየር ጀመረ። ዛሬ ምንም ቢፈጠር ለመቀበል ዝግጁ ሁኜ ነው የመጣሁት ብቻ በትዕግስት ማሂን መቆጣጠር አለብኝ። . <<ማሂ ስላንተ ባቢ እና አቤላ ሁሉንም ነገር ነግረውኛል። ወላሂ ማሂሬ ያን ጊዜ አንተን ማግኘት አልቻልኩም። በርግጥ እስኪነግሩኝ መጠበቅ አልነበረብኝም፤ አንተ በተግባር ብዙ ልታሳየኝ ጥረህ ነበር። ግን እኔ አልገባኝም አለ አይደል.. ወተት ነጭ ነው እስክባል ድረስ። ማሂ አውቃለሁ በኔ ላይ ተስፋ ነበረህ፤ ያን ተስፋ አጨለምኩብህ አይደል? ማሂ ከተለያየን በኃላ እኮ ብዙ ፈልጌህ ነበር፤ ግን አላገኘሁክም። አውቃለሁ ሳንለያይ በፊት ቁጥርህን ስትሰጠኝ አልተቀበልኩህም። እኔ ይሄ ሁሉ ይፈጠራል ብዬ አላስብኩም ነበር። ማሂ እኔ ስላንተ በማሰብ ራሴን ተወቃሽ አድርጌ ላለፉት አመታት በፀፀት ውስጥ አለሁ። እባክህን ማሂ አንድ ነገር እንኳን እንዳደርግ ፍቀድልኝ...ቢያንስ አሁን ያለህበትን ሁኔታ ንገረኝ።>> አይኑን ከኔ ላይ አነሳና ወደ ጠረዼዛው አጎነበሰ። <<ኢብቲ ታውቂያለሽ? እንደ አሁን ሰዐት በራሴ ተስፋ የቆረጥኩበት ጊዜ የለም። ያኔ እኮ በቃ መሉ ለሙሉ የምፈልገውን ህይወት የማገኝ መስሎኝ ነበር። ቆይ ኢብቲ አንድ ሰው ወዶ አላዋቂ ይሆናል እንዴ? እኔ እኮ እምነቴን ለማወቅ ብዙ ቦታዎች ሄጄ ነበር። ለካ ለማወቅም ትንሽ ማወቅ አለብሽ። <ገና ጀማሪ ነህ..እንዴት ትንሽ እንኳን አታውቅም? ምናምን.. እስቲ ስገድ> እህህ! ስርአቱን አውቄ ለመስገድ አይደል እንዴ እነሱ ጋር መሄድ የፈለጉት? ቆይ ሌሎችስ ስለ እምነቴ አላውቅም አስተምሩኝ ማለት የሌሎች መሳለቂያ ሙድ መያዣ ማድረግ ምን ይጠቅማል? ኢብቲ በናትሽ ስለተውኩት ነገር አታስወሪኝ። ..ብቻ ያኔ ካንቺ ብዙ ጠብቄ ነበር፤ በቃ አልሆነም ደግሞ እንደማገኝሽ እርግጠኛ ነበርኩ። ግን እንዲ ከረፈደ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ይሄን አንብቢው እስቲ ከዋሌቱ ላይ ከሁለት ወረቀት አንዱን አውጥቶ ሰጠኝ ወረቀቱ እጥፍጥፍ ብሏል በዛ ላይ የቆየ ይመስላል። ተቀብዬ ከፈትኩት
Показать все...
■ እነዚህን አራት ነገሮች እንጠንቀቅ ● الافراط في العطاء يعلم الناس استغلالك ከመጠን በላይ መስጠት ሰዎች ያለአግባቡ እንዲጠቀሙብህ ያስተምራል ● الافراط في التسامح يعلم الناس التهاون في حقك ከልክ በላይ መቻቻል ሰዎች እንዲዳፈሩህና መብትህን እንዲጋፉ መንገድ ይከፍታል ● الافراط في الطيبة يجعلك تعتاد الانكسار ከልክ በላይ ለሰዎች ደግ መሆን የልብ ስብራትን እንድትለምድ ያደርግሃል ● الافراط في الاهتمام بالاخرين يعلمهم الاتكالية ለሌሎች ከልክ ያለፈ አሳቢነት ጥገኛ እንዲሆኑ ያስተምራል። 🎨 @Habibacalligraphy
Показать все...
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ ሶስት (ሂባ ሁዳ) . . (ከአምስት አመታት በኃላ) * * <ምንም የምወደውም የምጠላውም ነገር የለኝም። የወደድኩትን ጠልቼ፣ የጠላሁትን ወዶጄ ተምታቶብኛል። ማንንም ስለማልወድ ሌሎች እኔን አይወዱኝም ብል፤ ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው ማለት ይቻለኛል?> የዛሬው የፌስቡክ ጥያቄዬ ነው። . ዛሬ ቀኑ ድብልቅልቅ ብሎብኛል፤ ምን እያሰብኩም ሆነ እየሰራሁ እንደሆነ ራሱ አልገባኝም። ለዛም ነው በደመ ነፍስ እንዲህ ፌስቡክ ላይ ፖስት አድርጌ የወጣሁት... ምን አልባት ሰሞኑን እቤት ስለዋልኩ ተጫጭኖኝ ይሆናል ብዬ ወጣ ለማለት ወሰንኩ። ከሰፈሬ ስወጣ ወደ ዊንጌት ታክሲ ለመያዝ አስፋልቱን ለመሻገር ከፊት የሚመጣ መኪና ለማየት ዞር ዞር ስል አንድ የማውቀው የሚመስል ሰው ፊት አየሁ። ከብዙ ሰው ጋ ተመሳሰለብኝ ወደ እሱ እየቀረብኩ ስመጣ ግን ልቤ ምቷን ከእርምጃዬ ጋር ጨመረች። * <<ይ..ቅር.ታ አ..ቤ..ላ..ማለቴ አቤል?>> <<እንዴ እንቺ! በፈጣሪ ኢብቲሳም ነሻ>> <<እእ አዎ ወዬኔ ግን እንዴት ነህ በአላህ?>> <<አለሁልሽ... በስማም! በሂወት ግን አለሽ ኢብቲ? ተዐምር ነው የሆነብኝ..>> <<በጣም ተቀይረሃል። ትልቅ ሰው መሰልክ እኮ ፂም ምናምን እየሞካከርክ ነው.. ሃሃሃሃሃ>> ፊቱ ላይ ጣል ጣል ያሉትን ፀጉሮች እያየሁ ሳኩበት። <<እና አሁንማ ግብዲያ ሆነናል አንቺ ራሱ.. አይ ግን ለኔ ምንሽም አልተቀየረብኝም። ነይ እንግባ ቦታ አለ..>> ሁለታችንም ገቢና ገብተን ማውራታችንን ቀጠልን። <<እና ከየት ወዴት ምናምን በናትሽ እስቲ አውሪኝ>> <<እኔ ከሰፈር ወደ ጓደኛዬ ሰፈር እያሄድኩ ነው ..አንተስ..>> <<ጓደኛ ስቲ.. እነዛ ሁለቱ ደህና ናቸው? በናትሽ ማን ነበር ስማቸው?..ያቺ እብዷ ..ራቢያ ነበረች መሰለኝ>> ፊቱን ጭምድድ እያረገ። <<ሃሃሃሃ አሁንማ እብድ አደለችም። እእ ደህና ናቸው በአምስት አመት ውስጥ አለመርሳትህ ሲገርም..>> <<ኧረ እንዴት ይረሳል ..ከማሂሮ ጋር እኮ በተገናኘን ቁጥር ነው የምናነሳው ያን ጊዜ..>> ማሂ ስሙ ሲጠራ የሆነ ንዝረት ነገር ተሰማኝ። <<ማሂርን ታገኘዋለህ? ደህና ነው?>> <<አዎ ብዙም ባይሆን ደህና ነው ኧረ እሱ ተመችቶታል..>> <<ስታገኘው ሰላምታዬን አድርስልኝ እሺ በናትህ..>> <<ኧረ አያሳስብሽ..አባ ወራጅ! አልፌው መጣሁ እኮ። ኢብቲ በቃ እናወራለን እሺ>> የገቢናውን በር ዘግቶ ከመኪናው ወደ ታች መራመድ ጀመረ። . <<አንድ ሰፈር አደላችሁም እንዴ?>> ሹፌሩ በጎን በኩል ሊያየኝ እየሞከረ። <<አይ አይደለንም..>> <<እና ትምህርት ቤት ነው የምትተዋወቁት? ከገባቹ ጀምሮ ኮ ስታወሩ በጣም ቅርብ መስላችሁኝ ሁኔታችሁ..>> <<ሳይሆን ስምንተኛ ክፍል አብረን ነበር የምንማረው እና ዛሬ ተገናኘን ከአምስት አመት በኃላ>> <<ዋው! ደስ ስትሉ አምስት አመት ረጅም ነው እኮ..>> <<አዎ ረጅም ጊዜ ነበር>> ብዙ ነግራቶች እንደየጊዜው ተቀያይረዋል። አንዳንድ ሰዎች መጥተዋል፤ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ሄደዋል። እኔ ጋር በራሱ ስንት ነገር ተቀያየረ... ራቢ ስራ ጀምራለች፤ ኢክሩም ስራ ና ክላስ አንድ ላይ እያጧጧፈች ነው፤ ዩሲ ደግሞ ዩንቨርስቲ ሄዳ የጊቢ ተማሪ ሆናለች። ነገራቶች ምን ያህል እንደተቀየሩ ለአፍታ ውልብ ውልብ አሉብኝ። <<እና አምስት አመት ማለት አንቺ አሁን የጊቢ ተማሪ ነሽ ማለት ነዋ ምንድነው የምትማሪው?>> <<አይ እዚሁ ኮሌጅ ነው የምማረው ፋርማሲስት..በዛው እዚህ ጋር ያዝልኝ..>> <<ደረሽ እንዴ? በቃ ቆንጅዬ መልካም ቀን..>> እጁን አውሎብልቦልኝ ጉዞውን ቀጠለ። * ዊንጌት መናፈሻው ውስጥ ቁጭ እንዳልኩ አንድ ቴክስት ደረሰኝ <<ኢብቲ በጣም ይቅርታ.. ክላስ አስቸኳይ ፈተና እንዳለብን ነግረውን ወደዛ እየሄድኩ ነው..>> ከሰፈር እሷን ለማግኘት ቢሆንም የመጣሁት እዛው ትንሽ ሰዐታት ለማሳለፍ ወሰንኩ። በመሃል አቤላ ትዝ አለኝ ኡፍፍፍ ለካ ስልክ ቁጥር አልተቀያየርንም ኦህ ሲያበሽቅ!! በቃ እንደውም ወደ ቤት ብመለስ ይሽለኛል። ሂጃቤን አስተካክዬ ከመናፈሻው ወጣሁ። * እቤት እንደደረስኩ ለአመታት ልቤን ሲያስጨንቀኝ የነበረው ነገር እንደ አዲስ ነገራቶችን ይመላለሱብኝ ጀምሯል። ማሂር ለመጨረሻ ጊዜ ሲያየኝ የነበረው ቅፅበት ታወሰኝ። ወደ ግንባሩ ድፍት ካለው ፀጉሩ ጋር ትላልቅ አይኖቹ ከነሽፍሽፍታቸው፣ ፈገግ ሲል ስርጉድ ከሚለው ዲንፕሉ ያ ውብ የሆነው ፈገግታው አሁንም አይኔ ላይ ይመላለሳል። አሁንም እንደዛ ይሁን ወይንስ ተቀይሮ? ማሂሬ በአንድ አጋጣሚ ለአፍታ ብቻ ባየው ብዬ ተመኘሁ። በተቀመጥኩበት ብዙ አሰብኩ ነገራቶችን አለመርሳቴ ለራሴ አስገረመኝ። ዛሬ ከአቤላ ስልኩን እንዴት አልተቀበልኩም?..ግን ብቀበለውስ ደውዬ ምን ልለው ነበር? <ማነሽ? ምን ፈለግሽ?> ቢለኝስ?...እንደምንም ስለትናንት ይቅርታ መጠየቅ ብችል ና ልቤን ከፀፀት በገላገልኳት። * #ዕለተ_እሁድ_ከምሽቱ_3:30 * <<ሃይ እንዴት ነሽ ሰላም ነዋ?>> <<እኔ ደህና ነኝ>> ከማላውቀው አካውንት የተላከልኝን መልዕክት እየመለስኩ። <<ኢብቲዬ ሰላምታሽ ደርሶኛል እ የኢሜል አካውንትሽን በግድ ነው ያገኘሁት በዚህ ስልክ ቁጥር በቴሌግራም ከተመቸሽ መልዕክትሽን ላኪልኝ እጠብቃለሁ። ማሂር ..>> የደረሰኝን መልዕክት ማመን አቃተኝ። ማለት ማሂር..? ማሂ.. እንዴት? ወይኔ ደስ ሲል... ቆይ ምንድነው ያለኝ? ደግሜ አነበብኩት። ልክ የዛሬ ስድስት ቀን አካባቢ ነበር አቤላን ያገኘሁት ሰሞኑን ስለ ማሂ ሳስብ ነበር፤ አሁን ደግሞ መልዕክት ደርሶኛል። ወድያውኑ በመልዕክት መለስኩለት። <<ሰላም ማሂ ኧረ ቆይ ቲጂ መጣሁልህ...>> ጊዜ አልፈጀሁም ስልኩን መዘገብኩና ቴሌግራም ላይ አካውንቱን አመጣልኝ። ምን አልባት ያለበትን ሁኔታ ከገለፀልኝ ብዬ ፕሮፋዬሉን በረበርኩ ምንም የሚገልፅልኝ ነገር ሳጣ መበርበሬን ተውኩት። ልቤ ፈራ ምን ልለው ነው?...ምንስ ሊለኝ ይሁን?..... ለአመታት ባገኘሁት ስል እንዳልነበር አሁን ግን አመነታሁ ....ልክ እንደ "ግራጫ ".... ግራጫ የራሱ የሆነ ቀለም እንደሌለው ሁሉ ....እኔም ውሳኔ የለኝም ...ግራጫ ልክ ሁለቱንም በአንድ አጣምሮ እንደያዘ.. የኔም ሃሳብ አንዱ ላይ አረጋም.... ግራጫ ለአንዱ እንደሚያዳላ ሁሉ ...የኔም ሃሳብ ላውራው አላውራው ብሎ ሁለቱንም ቢይዝም... እንደ ግራጫ ወደ አንዱ አዳልቶ አዘንብሏል። . . ይቀጥላል... t.me/Habibacalligraphy
Показать все...
Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን 💔 😥 በዘመኑ ፍጻሜ የኡለማዎች ሞት ይበዛል፤ ጅህልናም ይስፋፋል፡- “አላህ እውቀትን ከሰዎች ነጥቆ አይቀማም ነገር ግን ኡለማዎችን በመውሰድ ዕውቀት እንዲነሳ ያደርጋል።አንድም አሊም በማይተውበት ጊዜ ፣ ሰዎች አላዋቂ መሪዎችን ይወስዳሉ፣ ከዚያም ይጠየቃሉ ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፣ ተሳስተው፣ ያሳስታሉ። ሼይኽ ሰዒድን ዛሬ ሸኝተናል 💔💔 ነገ ተራው የኛ ነው...አላህ በጀነቱል ፊርደውስ ይቀበላቸው 🤲 @Habibacalligraphy
Показать все...
😥 12
❤ 3
የባከኑ ቀናት ክፍል አስራ ሁለት (ሂባ ሁዳ) . . ከአቤላ ጋር ቁጭ ካልን በኃላ ..ምን አለ የማሂም እንዲሁ ቀልድ ነው ብላችሁኝ ደስታዬ ሙሉ ቢሆን እያልኩ አስባለሁ። እነ ዩሲም ምርጥ ውጤት ስላመጡ በጣም ደስ ብሏቸዋል። ሶስታችንም የትምህርት ቤቱ ሰቃይ ሆነናል። እኔ ግን ልቤ ላይ ሌላ ጭንቀት አለ እሱም ማሂር ነው። በቃ በአንድ አጋጣሚ ተገናኝተን በሌላ አጋጣሚ ተለያየን ማለት ነው? እኔ ግን እጣፈንታን ተቀየምኳት.. ራሷ አገናኝታን ራሷው አለያየችን። አሁን ማሂር ምን ይሁን የሚሆነው.. <<ኢብቲ ማሂ ስለወደቀ ከፋሽ አ? እኔም ደብሮኛል የሌለ አብሬው ብወድቅ ነው ያልኩት>> አቤላ እንዲህ ሲለኝ ስለ ማሂ እያሰብኩ ስለነበረ ደነገጥኩ። <<አዎ አቤላ አሳዘነኝ.. ሁኔታውን አይተኸዋ። እኔ ምልህ እስቲ ስለ እሱ ንገረኝ... ፋሚሊዮቹ ምን አይነት ናቸው?>> <<አይ ስለወደቀ እንኳን አይቆጡትም አያሣስብሽ..>> የጠየኩት ጥያቄ የገባው አልመሰለኝም። <<ሣይሆን አላይደል እምነታቸው ላይ...>> <<እእ እሱን ነበር እንዴ የጠየቅሽኝ... አንድም እኮ የጓዳው እሱ ነው። ለዛ ነው ቶሎ ሆድ የሚብሰው፤ ሰውም ብዙ የማይቀርበው እንዳያጣ ስለሚፈራ ነው። ኡፍፍ ብራዘር ምርጥ ልጅ ኮ ነበረ>> <<ማለት አቤላ ቤተሰቦቹ ላይ ችግር አለ? ማለቴ አይስማሙ?>> <<ሣይሆን እናቱ ከሞተች ቆየት ብሏል። ያኔ ጩጬ ነበር፤ ፈታ ብሎ ነበር የሚያድገው። እናቱ ከሞተች በኃላ ነገራቶች ተቀየሩ ፋዘሩም ሌላ ሚስት አገባና ከአዲሱ ሚስቱ ጋር እምነቱን ቀየረ፤ በፊት ኮ ምርጥ ሼኪ ነበር ይባላል። በቃ ማሂሬም ትምህርት ቤት ብቻ አስገብተው ላሽ አሉት፤ ግን ፋዙካው የሌለ ነው የሚወደው። እንዲከፋው ምናምን አይፈልጉም ግን የሚፈልገውን አላሟሉለትም። አለ አይደል ከመሰረታዊ ነገር ውጪ እሱ በጣም የሚያስጨንቀው እምነቱ ነበር። በፊት ብዙም አያርፍም ነበር ሲቆይ ሲቆይ ግን የሌለ ይሸምመው ጀመረ። አብሶ ሙስሊሞችን ሲያይ ሽምቅቅ ነው የሚለው፤ አንዳንዴ ምን እንደሚሉት አይገባውም። ከነርሱ ጋር እንደፈለገ ፈታ ብሎ አያወራም፤ ምክንያቱም እነሱ ከሚያውቁት ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ሲጠይቃቸው ደግሞ <እንዴት አታውቅም ለስሙ ሙስሊም ነህ> ብለው ሙድ መያዣ ያደርጉታል። ለዛም ነው ከኔና ከባቢ ጋር ብቻ የምታይው፤ እኛ ከድሮም አብረን ስለተማርን ሁሉንም ነገር እናውቃለን። ምንም አንደባበቅም.. በቃ እኔ ማሂሮ የመጭ ነው የሚያሳዝነኝ፤ የሌለ ምርጥ ልጅ እኮ ነው በናትሽ። አንድ ጥሩ ሰው ቢገጥመው እኮ የሌለ ደስተኛ መሆን ይችላል።>> <<አቤላ እኔ ግን ምን አይነት ሰው ነኝ? እንዴት ምንም ማድረግ ያቅተኛል..>> <<ኢብቲሣም ምንአልባት ከዛሬ ቡኃላ አንገናኝም ይሆናል ከመለያየታችን በፊት ግን ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ ...>> አቤላ እጁ ላይ ያለውን ክር እያሽከረከረ ንግግሩን ቀጠለ። <<ኢብቲ በመጀመሪያ ያሳለፍነው ጊዜ መቼም ልረሳው አልችልም። ለኔ ሁላችሁም ምርጥ ነበራችሁ፤ ትለዩብኛላችሁ። ሁሌ አብረን ብንሆን ምነኛ ደስ ባለኝ ግን መለያየት ልክ እንደመገናኘት ነው ፈልገሽ ሣይሆን መሆን ስላለበት ብቻ የሚሆን። እና ደግሞ ኢብቲ ሁላችንም እናከብርሽ ነበር ባቢም ማሂሮም ስለሌሉ እነሱንም ሁኜ ነው የምነግርሽ። በተለይ ለኔና ለባቢ በጣም ለውጠሽና፤ ብዙ ነገሮችን እንድናይ ረድተሽናል። የሰው ክብር ከምንም በላይ አሳውቀሽናል። ብቻ ብዙ ነገር.. ታዲያ ግን ይሄን ለኛ ባደረግሽ ጊዜ ካንቺ ሌላ ነገርን ጠብቀን ነበር። መጠበቅ ብቻ ሣይሆን ታደርጊዋለሽ ብለን ነበር..ግን ምን ያደርጋል፤ አንዳችን አርፍደናል አልያም ዘግይተናል። መቼስ ገብቶሻል አይደል? ስለ ማሂር ነው። በጣም እንድትቀራረቡ ከባቢ ጋር ብዙ ነገር ፈጣጥረን ነበር። እንድታወሩ ብዙ አጋጣሚ መሳይ ነገሮችን ስንፈጣጥር ነበር። የኛ ልፋት ውጤቱ ላይ ሳይደረስ ቀረ። ለምን? አንድም ማሂር ፈሪ ስለሆነ፤ ከዛሬ ነገ አወራታለሁ ሲል። ሌላው ደግሞ ያንቺ ትኩረት አለመስጠት ነው። እንዴ ኢብቲ ብዙ አጋጣሚዎች ላይ እኮ ማሂ ስለእምነቱ እንደማያውቅ ካንቺ መማር እንደሚፈልግ ነግሮሽ ነበር። ግን አንቺ ሁሌ ቀልድ እየመሰለሽ ታልፊዋለሽ። ከዛሬ ነገ ቀኑ እየሄደ ሲመጣ ማሂር ሁሉንም እንዲነግርሽ በግድ አሳምነን ላክነው። ግ'ና ምን ያደርጋል..እቸኩላለው ብለሽ ልታዳምጭው ፍቃደኛ አነበርሽም፤ ሌላ ስብራት ፈጠርሽበት። ትዝ ይልሻል አይደለ? ከቀናት በአንዱ ቅዳሜ ቀን ነበር። የዛኔ ያየሁትን የማሂን ተስፋ ማጣት ምንም ላይ ደግሜ የማየው አይመስለኝም። ሁላችንም ባንቺ እምነት ነበረን፤ ነገራቶችን ታስተካኪያለሽ ብለን... ደግሞ እኔ ወይ ባቢ ከምንነግርሽ ራሱ ቢነግርሽ እንደሚሻል አስበን ነው። ብቻ ኢብቲ አውቃለሁ፤ በጣም ጎበዝ ልጅ ነሽ፤ በትምህርትም በእምነታችሁም። እኔ በአስራ አራት አመቷ ወንድ አልጨብጥም የምትል ሴት ካንቺ ውጪ አላውቅም። በዛ ላይ በጣም ተግባቢም ልጅ ነሽ። ግን አንድ ነገር ይጎልሻል፤ ሰዎችን ማድመጥ፣ በዙሪያሽ ላሉት ትኩረት መስጠት.. ይሄን ባህሪሽ በናትሽ እንደምንም አስተካኪው። ድጋሚ የማሂን አይነት ሰው ትኩረት እንዳትነፍጊ። ኢብቲ የምር በጣም አመሰግናለሁ። ያው እኔ ከባቢ ና ማሂሮ ተለይቼ ያለፍኩት ካንቺ ስለሰራሁ ነው። የዛሬውን ቀን እንዲ አልጠበቅናትም ነበር። ከነ ማሂሮ ጋር ፈታ እንላለን ብለን ነበር አልሆነም። የስምንተኛ ክፍል ላይፍ ለኔ ከየትኛውም የትምህርት ቤት ላይፍ በላይ ነው። ፈጣሪ መልካሙን ያድርግልን፤ ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ እንገናኝ ይሆናል።>> ከተቀመጠበት ተነሳ። እኔ ምን አይነት ስሜት ውስጥ እንደሆንኩ አላውቅም... አቤላ እንዲህ ቁም ነገራቶችን ያወራል ብዬ አልጠበኩም ነበር። እኔም ተነሳሁ። <<ቻው ኢብቲ በቃ>> <<አቤላ..>> <<ወዬ>> ፊቱን ሙሉ ለሙሉ ወደኔ አዞረ። <<በጣም ይቅርታ ስለሁሉም..>> ታምቆ የተያዘው ዕንባዬ ቀደመኝ። እኔ ከዕንባዬ ጋር ስታገል አቤላ እየሮጠ ወደ በሩ ሸሸ። ከአቤላ መሸሽ ጋር የኔም ህልምና ተስፋ ላይመለስ አብሮ ሸሸ፤ ፀፀቱ እኔው ጋር ቀረ። . አንድ አመት ሙሉ ከኔው ጋር እየዋለ ለሚሄድ፤ በየቀኑ ከጎኔ ለማገኘው.... ተስፋውን በኔ ላይ ጥሎ መሰበሩን ለሚያሳየኝ ሰው.... መጠገን ትቼ ተስፋውን ገደል መክተቴ... ምን ያህል የባከኑ ቀኖች.... ከኔ ጋር እንደነበሩ አሁን ገባኝ ....ቢገባኝስ ምን ሊፈይድ... ከነስብራቱ ተስፋውን ጥሎ... ማሂሬ ሄደ እኮ!.. . . ይቀጥላል... t.me/Habibacalligraphy
Показать все...
Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot

. <<ኢብቲ ተማሪው እኮ ተቀበለ እኛ ብቻ ቀረን እእ እንቀበል በቃ ቁርጣችንን እንወቀው>> ራቢ ከገባሁበት ሃሳብ መለሰችኝ እሺ ተባብለን ለመቀበል ተስማምተን ወደ በሩ ጋ ስንደርስ አቤላ እየወጣ ተገጣጠምን የውጤቱን ካርድ ሳይ ልቤ ምቱን ጨመረብኝ። <<እእ አቤላ እ.ን.ዴ.ት ነው..>> <<አቦ ተይኝ እኔ ደግሞ አልፋለው ማለቴ ድሮም ካንቺ ሰርቼ>> <<ማለት?>> ዩሲ ደንገጥ ብላ ወረቀቱን ለማየት ስትጠጋው። <<ቲ! ያው ናችሁ። ምን የወደኩበትን ለማየት ምን አስቸኮለሽ ዞርበይ ከዚህ ሲያስጠሉ>> ሶስታችንንም ገልመጥ አድርጎ አየን። <<በናትህ አቤላ ንገረኝ ወደቅን ነው የምትለኝ? ድምፄ ከፍ እያለ መጣ።>> <<አቤላ አትበይኝ ዱዝ! አቤል ነው ስሜ። አው እንኳን ደስ አለሽ እኔ ወደኩኝ ከሌላው ብሰራስ አንቺን አምኜ ሙሉ ካንቺ መስራቴ..>> ከዚህ በላይ አልሰማሁትም፤ እየተቻኮልኩ ወደ ቢሮው ገባሁ <<ይቅርታ የኔን ወረቀት ..>> <<እንዴ ኢብቲሳም የት ጠፍተሽ ነው እስካሁን?>> ባይሎጂ አስተማሪያችን ስሜን እየፈለገ። <<እሲቲ ቁጭ በይ እስከዛው>> እንድቀመጥ ጋበዘኝ። ቢለኝም እዛው መቆምን መረጥኩ... እስኪያገኘው ጨነቀኝ። አንድ ወረቀት ነጥሎ እንደያዘ። <<ምን ነክቶሽ ነው ግን ምን ሁነሽ ነበር?>> <<ማለት ቲቸር? መቼ?>> ግራ እየተጋባሁ ጠየኩት ... <<መቼ? ለፈተናው ነዋ። ጥሩ ጎበዝ ልጅ አልበርሽ እንዴ? በአንዴ ምንድነው እንደዚህ የቀየረሽ>> አስተማሪው አፈጠጠብኝ <ምነው ባልገባሁ> አልኩኝ በውስጤ። <<ቲቸር ም.ን.ድ.ነው እ ውጤቴ?>> የሞት ሞቴን ጠየኩት። <<እኛማ ብዙ ተስፋ የጣልንብሽ ልጅ ነበርሽ፤ የትምህርት ቤቱንም ስም ታስጠሪያለሽ ብለን ጠብቀን ነበር አዝናለሁ ኢብቲሳም። አሉኝ ከምላቸው ዋነኛዋ ተማሪ እንዲህ አልጠበኩም ነበር አፍሬብሻለው...>> አይኖቼ በዕንባ እየተሞሉ ልቤ ምቱን ላይ በላይ ሲደጋግመው በሰማሁት ነገር ልዘረር ምንም አልቀረኝም። <<እና ወ.ድ.ቀ.ሻ.ል ነው..>> <<በሚያሳዝን ሁኔታ አዎ>> በተቀመጠበት ወንበር ወደ ኃላ ለጠጥ ብሎ እየተቀመጠ የምሆነውን ያያል። በምን ሃይል እንደሆነ ባይገባኝም ወረቀቴን ስጠኝ ብዬ ጮኽኩበት። በር አካባቢ የነበሩት ዩሲና ራቢ ገቡ። እሱ ከቦታው ሳይንቀሳቀስ.. <<ብሰጥሽስ ምን ያደርግልሻል>> ብሎ የሹፈት ፈገግ አለ። እነ ራቢ ደንግጠው እርስ በርሳቸው ይተያያሉ። ይባሱኑ ብሽቅ አልኩና <<ወረቀቴን ስጠኝ ብወድቅስ ምን አገባህ>> ብዬ ከእጁ ላይ መንትፌው ወደ ውጪ ወጣሁ። ራቢ ተከትላኝ ወረቀቱን ተቀበለችኝ፤ ራቢ ለዩሲ <<ነይ! ነይ!ቶሎ በይ>> ስትል ዩሲ ምንድነው ብላ ራቢ ጋር መጣች። እኔ መቆም አቅቶኝ ከዚህ ወደዚያ እሽከረከራለሁ፤ በመሃል ራቢ <<የስሥሥሥሥሥሥሥሥ>> ብላ ስትቀውጠው ከዩሲ ጋር ተቃቀፉ። <<ኢብቲ ነይማ አፍጥኝው>> ብላ ወደኔ መጣች። እጇን ወረቀቱ ላይ እየጠቆመችኝ ትስቃለች፤ 96 ይላል ፁሁፉ። <<እእ.. ደስ ይላል ራቢ። ያንቺ ነው የዩሲ?>> ብዬ ሁለቱንም አፍራርቄ ሳይ ይስቃሉ አብራቼው ፈገግ ለማለት ስሞክር <<ኢብቲ እይማ>> ብላ ድጋማ ከወረቀቱ ላይ ሌላ ነገር አስነበበችኝ። <ኢብቲሳም ማህሙድ> ይላል። <<ማለት?>> ሁለቱም ላይ አፈጠጥኩባቸው። <<ያንቺ ኮ ነው 96 የኔ ውድ ነቀነቅሽው ኮ!>> ብላ ጥምጥም ስትልብኝ ደግሜ አየሁት ዩሲም ተጨመረች። በመሃል <ሰርፕራይዝ> ሚል ድምፅ ሰማን። ዞር ስል አቤላ እየሳቀ ነበር፤ እኔ አልፌ እሱ መውደቁ ትዝ ሲለኝ ወረቀቱን ለራቢ ሰጥቻት ወደሱ ሄድኩ፤ <አቤላ..> ስለው ምንም ሣይመልስልኝ ወረቀቱን ሰጠኝ የማየውን ማመን ስላቻልኩ እሱን አየሁት <<አዎ ነቀነቅነው 92>> ብሎ ሳቀ <<ውይኔ ደስ ሲል>> ብዬ ስጮኽ <<ተጫወትንብሻ ከቲቸር ጋ!>> ብሎ ከት ብሎ ሳቀብኝ። ብሽቅ አልኩና ልመታው ማሯሯጥ ጀመርኩ። . . ይቀጥላል... t.me/Habibacalligraphy
Показать все...
Habiba Calligraphy

ይህ ኢስላማዊ የሆኑ የ ካሊግራፊ ስራዎች(Islamic Calligraphies) ወደእናንተ የሚደርሱበት ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት 👇👇👇 @Habibaartbot