cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Больше
Рекламные посты
76 203
Подписчики
-1924 часа
-1297 дней
-51430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ የትሞህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናና ኦላይን ለመስጠት ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በወረቀት ከሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ጎን ለጎን በቴክኖሎጁ ተደግፎ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመሆኑም ፈተናው እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ከተሞች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ወ/ሮ አየለች አሳስበዋል። በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ከወዲሁ በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ወላጆች ስለፈተናው የተሻለ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ልጆቻቸውን እንዲደግፉና በራስ መተማመን ወደፈተናው ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ሊፈጥሩ እንደሚገባም አመላክተዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በኦን ላይን የሚሰጠውን ፈተና በተሻለ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናን ለተማሪዎች በኦንላይን መስጠት ምቹና ቀላል መሆኑን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል። @Addis_News
Показать все...
ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ዘጋች በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶች መታሸጋቸው ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 9 ወራት የህብረተሰቡን ሰላም አውከዋል ባላቸው የተለያዩ ስራዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የውርርድ ቤቶችን ጨምሮ ጫት ማስቃም፣ ሽሻ ማስጨስና የመሳሰሉ ጉዳዮች ይፈፀሙባቸው የነበሩና የወንጀል ድርጊት የሚታይባቸው ተግባራት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስተጓጉሉ የነበሩ ናቸውም ተብሏል። የከተማዋ አስተዳድር ከዘጋቸው ተቋማት መካከል 6 ሺህ 726 የሚሆኑ የስፖርታዊ ውርርድ  ቤቶች መታሸጋቸውን አስታውቋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊዋ አክለው ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤት ቅጣት ጥሎባቸው ከታሸገ በኋላ እቃውን እንዲያወጡ ተጠይቀው ፍቃደኛ ባልሆኑት ላይ ፖሊስና የደንብ ማስከበር አካላት ከሰላምና ጸጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ህግን ለማስከበር እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የከተማው አስተዳድር ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ ባወጣው ሪፖርት ከ3 ሺህ በላይ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶችን ዘግቶ ነበር፡፡ @Addis_News
Показать все...
👍 14🔥 1
ኢትዮጵያ አሁን ከመፍረስ የመዳን እድሏ "ከ20/ከ30 በመቶ አይበልጥም"- ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የፖለቲካዊ ኃይሎች የሚሳተፉበት ውይይት ሊያዘጋጁ ነው ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው 'የሃሳብ ገበታ" ከተባለ የዩ ትዩብ ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአገሪቱ ከመፍረስ የመዳን ዕድል አሳሳቢ እየሆነ መሆኑን ተናግረዋል።  አንድ ፖለቲከኛ ወጥቶ ሃሳቤን ተቀበሉኝ ሲል እንደንቀት ሊቆጠር ቢችልም የአገሪቱ ሁኔታ ይህን ያስገድዳል በማለት መልዕክታቸውን የጀመሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሊቀ መንበር ልደቱ አያሌው፤ "እስኪ ዛሬ ስሙኝ" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። "ዛሬም ተቀባይነት እያገኙ፣ እየተደመጡ ያሉ ሰዎች ስህተቱን ደጋግመው የሰሩት ሰዎች ናቸው፤ ድሮ ቅንጅት ሆነው ትክክል ነን ሲሉ የነበሩት፣ አርበኞች ግንባር ሆነው ትክክል ነን ሲሉ የነበሩ ሰዎች፣ ኋላ ደግሞ የብልጽግና ደጋፊ ኢዜማ ሆነው ትክክል ነን ሲሉ የነበሩ ሰዎች አሁንም ፋኖ ሆነው ትክክል ነን እያሉ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። "አብዛኛውን ሚዲያዎች የተቆጣጠሩ ኃይሎች" የጥፋቱን መንገድ ደግመው ደጋግመው ሲያካሄዱ የነበሩ ናቸው ያሉት ፖለቲከኛው "የእነሱ ተደማጭነት ነው ያለው አሁንም፤ በዚህ ሁኔታ የትም ድረስ መሄድ አንችልም" ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ አሁን ከመፍረስና ከመዳን የትኛው እድሏ የሰፋ ነው ቢባል "የመፍረስ እድሏ ነው፤ 20/30 ፐርሰንት (በመቶ) የመዳን እድል የለንም" ያሉት ልደቱ አያሌው፤ "ምክንያቱም ሁላችንም ወደጥፋቱ አቅጣጫ ነው እየገፋን ያለነው። ከጥፋቱ ወደሚያወጣን አቅጣጫ የሚገፋ ኃይል የለም" ብለዋል። ከጥፋት የሚያወጡ ኃይሎች ቢኖሩም እንዳሉ አይቆጠርም አልያም ተቀባይነትም አላገኙም ያሉት ልደቱ አያሌው፤ "ጦርነትና ብሔርተኛነት ነው ተቀባይነት ያለው፤ ችግሩ በተፈጠረበት መንገድ ደግሞ ችግሩ አይፈታም" ሲሉ አሳስበዋል።   ይህ በእንዲህ እንዳለ ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው በቅርብ ጊዜ ውስጥ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውውይት መድረክ እንደሚያዘጋጁ መረጃዎች ተሰምተዋል። ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በፌደራል መንግሥት "በውጭ አገራት ሆነው ግጭት በመፍጠር የክልል እና የፌደራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል" በሚል ተላልፈው እንዲሰጡት ማዘዣ ከወጣባቸው ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆኑት ልደቱ አያሌው፤ በወቅቱ ክስ ከተመሠረተባቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አስታውቀው ነበር። ልደቱ አያሌው ለመገናኛ ብዙኀን ባሰራጩት መልዕክት 1ኛ. መቋጫው! የችግራችን ምንጭ፣ ያለንበት ሁኔታና የመዳኛው መንገድ፤ እንዲሁም 2ኛ. ምን ዓይነት የሽግግር ሂደት? ለምንና አንዴት? በሚሉ ርዕሶች ላይ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። Via:አዲስ ማለዳ @Addis_News
Показать все...
👍 19😐 4🕊 3
በቻይና አውራ ጎዳና ተደርምሶ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ በቻይና ጓንግዶንግ ግዛት ለቀናት በጣለው ከባድ ዝናብ በአንድ ተራራ ዳር ላይ የሚገኝ አውራ ጎዳና ተደርምሶ የ24 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡አደጋዉ ረቡዕ እለት በሜይሎንግ የፍጥነት መንገድ ላይ የደረሰ ሲሆን ሌሎች 30 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ባለስልጣናት የችግሩን መንስኤ አልገለጹም። በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚታዩ ምስሎች ከፍጥነት መንገዱ  በታች ባለው ጫካ ውስጥ በደን የተሸፈነው ተራራ ላይ ከፍተኛ የሆነ መፈራረሽ አሳይቷል፡፡በሆስፒታል ውስጥ የሚገኙት 30 ሰዎች “በአሁኑ ጊዜ ለከፋ አደጋ የተጋለጡ አይደሉም” ሲል የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የግዛቱመንግስት 500 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ወደ ስፍራው ልኳል። የመንግስት ሚዲያዎች መጀመሪያ ላይ 19 ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉን ዘግበው ነበር፡፡ ነገር ግን የአካባቢው ባለስልጣናት 24 ሰዎች መሞታቸውን እና የተጎዱት ሰዎች ቁጥር 30 መድረሱን ተናግረዋል፡፡በአጠቃላይ 20 ተሽከርካሪዎች በተደረመሰው የመንገዱ ክፍል ውስጥ መውደቃቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል። በቻይና በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችው ጓንግዶንግ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ ተመትቶ አራት ሰዎች ሲሞቱ 110 ሺ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል።የጎርፍ አደጋው በደርዘኖች የሚቆጠሩ ቤቶችን ወድመዋል፣ ትምህርት ቤቶችን ተዘግተዋል፣ የበረራ መሰረዝ እና መጓተትን አስከትሏል።በከባድ አውሎ ነፋሱ በጓንግዙ ግዛት ዋና ከተማ የፋብሪካ አውራጃ ላይ ባስከተለዉ አደጋ አምስት ሰዎችን ሲገድል 33 ሰዎች ቆስለዋል።የጎልፍ ኳሶችን የሚያክል የበረዶ ድንጋይም በከተማዋ ላይ ሲዘንብ ታይቷል። @Addis_News
Показать все...
👍 17🤔 2
#ADVERTISEMENT 📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች ➠ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ ➠ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ ➠ የ ድርጅት ማስታወቂያ ➠ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ ➠ ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ ✔የትምህርት ተቋማት…... ✔የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…... ✔የትራንስፖርት አገልግሎት….... ✔የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች…… ✔ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች...... ➲ እንዲሁም የተለያዩ የ Business ስራወችን ከእኛ ጋ መስራት ለምትፈልጉ አናግሩን ምርትና አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለ 45 ሺህ በላይ ኢትዮጲያዊያን ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ። አሁኑኑ ያናግሩን 👇 ለማናገር 👇 @Addisnegermereja_bot
Показать все...
👍 1
በአዲስ አበባ ከተማ በገበያ ማዕከላት ውስጥ ሽንኩርት በኪሎ ከ35 እስከ 45 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ በአዲስ አበባ ከተማ አምራቾችን ከሸማቾች በሚያገናኙ ሶስት ማዕከላት ውስጥ የአትክልት እና ፍራፍሬ ዋጋ ቅናሽ እንዳለው እና ሽንኩርት አንደኛ ጥራት ካለው ጀምሮ ዋጋው ከ35 እስከ 45 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታዉቋል። በኮልፌ ፤በአቃቂ ቃሊቲ እና በለሚኩራ የግብርና ማዕከል ውስጥ  86 አምራቾች ወደ ገበያ ማዕከላት ውስጥ መግባታቸውን ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩትየአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ሰውነት አየለ   አሁን ላይ  በማዕከላቱ ምርቶች በስፋት እየቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ አምራቾች በምርቶቻቸው ላይ ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ አድርገው ይሸጣሉ፡፡ ማዕከላቱ በሙቀት የሚበላሹ ምግቦችን በማቀዝቀዝ እና በቅዝቃዜ የሚበላሱሹ ምግቦች ደግሞ የሚያሞቅ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡በሶስቱ ክፍለ ከተሞች በሚገኙት ማዕከላቱ ወፍጮ ቤቶችን ያካተተ አገልግሎት ለመስጠት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማግኘት ክፍያዎች መፈፀማቸውን ገልፀዋል፡፡ በተለያ ምርቶች ላይ ከመደበኛ ገበያው በማዕከላቱ ውስጥ የዋጋ ቅናሽ እንዳለ እና  ጥራቱ የተጠበቀ ሽንኩርት በ45 እስከ 35  ብር  እንደሚሸጥ እንዲሁም ቲማቲም በ20 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ማዕከላቱ ላይ የሚኖሩ የዋጋ ጭማሪዎችን ለማጣራት በሳምንት ሶስት ጊዜ ሰኞ፤ዕሮብ አእና አርብ የማጣራት ስራ  እንደሚሰራ አቶ ዮሀንስ አየለ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡ ከመደበኛ ገበያዎች የጤፍ ዋጋ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የ3ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው ከዚህ ቀደም ብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ @Addis_News
Показать все...
👍 11
" የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30 ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30 እንዲተገበርና እነዲፈፀም ስምምነት ተደርሶ ወደ ተግባር ተገብቷል " - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕረዜዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በመግለጫቸው ፥ " በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ላይ መሰረት ያደረገ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከፌደራል መንግስት ጋር የሁለት ቀን ውይይት በማድረግ የአፈፃፀም ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።  " በውይይቱ የማጠቃለያ ስምምነት መሰረት የትግራይ ደቡባዊ ዞንና ፀለምት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ፤ የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም  እንዲተገበርና እንዲፈፀም ስምምነት ተደርሷል " ሲሉ ተናግረዋል። " ትጥቅ ማን ይፈታል ? ፣ እንዴት ይፈታል ? የትኞቹ አስተዳደሮችስ ይፈርሳሉ ? እንዴት ያሉ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ ? በሚሉ ነጥቦች ውይይት ተካሂዶ ዝርዝር እቅድ ወጥቶሎታል " ሲሉ ገልጸዋል። የእቅዱ አፈፃፀም በአፍሪካ ህብረት የክትትልና ቁጥጥር ቡድን እንዲመራና እንዲተገበር ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክተዋል።    " በትግራይ አመራር መካከል በፕሪቶሪያ የውል ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ' ሰላም ፈላጊና ጦርነት ፈላጊ አለ ' በሚል እየተፈጠረ ያለው ትርክት ስህተት ነው " ያሉት ጄነራሉ " ትርክቱ ስህተት መሆኑን ለፌደራል መንግስት ገለፃ ሰጥተናል " ብለዋል። በትግራይ በኩል የፕሪቶሪያ ውል ለመተግበር እስከ ታች የአስተዳደር መዋቅር ድረስ መግባባት ተደርሶ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ተመቻችቷል ሲሉ አሳውቀዋል። " የፌደራል መንግስትም የስምምነቱ ትግበራ እስከ ታች ድረስ እንዲያወርደው እንጠብቃለን " ብለዋል። " የፕሪቶሪያው ውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ከማንኛውም አይነት ግጭት በፀዳ መልኩ ተፈፃሚ ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም ፤ አሁን መሬት ላይ ካለው ሁኔታ በመነሳት እንዳችም ለግጭት የሚጋብዝ ሁኔታ የለም  " ሲሉ ገልጸዋል። @Addis_News
Показать все...
❤‍🔥 2🤔 1
በለንደን ሁለት የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች የጎራዴ ጥቃት ተፈጸመባቸዉ በለንደን ሰሜን ምስራቅ ሃይናኦት በህዝብ እና በፖሊስ መኮንኖች ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ሰይፍ የያዘ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታዉቋል።የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በለንደን ምስራቃዊ ሀይናኦልት ውስጥ አንድ ሰይፍ የያዘ ሰው ከባድ ጥቃት ፈጽሟል ብሏል፡፡ ተጠርጣሪው በሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እና ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ማድረሱ የተመላከተ ሲሆን አምስት ተጎጂዎች ሆስፒታል ገብተዋል፡፡የ36 ዓመቱ ሰው ጥቃት በፈጸመበት ስፍራ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡የኢልፎርድ ሰሜን የጥላ ጤና ፀሐፊ እና የፓርላማ አባል የሆኑት ዌስ ስትሪትዲንግ የአደጋ ጊዜ አገልግሎቱ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን እና አንድ ወንድ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል ። ፖሊስ ድርጊቱ ከሽብር ጋር የተያያዘ አይመስልም ብሏል።የለንደን ከንቲባ ሳዲቅ ካን ፖሊስ እና የድንገተኛ አደጋ አገልግሎቶች "ወደ አደጋ ስፍራዉ ገብተዋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከንቲባዉ አክለዉ ዛሬ ጥዋት ከሀይናኡል በተሰማው ዜና በጣም ተናድጃለሁ። ከፖሊስ ኮሚሽነር ጋር ያለማቋረጥ እመክራለሁ። አንድ ሰው ተይዞ አካባቢው በጥበቃ ይቆያል ብለዋል፡፡ @Addis_News
Показать все...
👍 19🤔 1
የግድያ መረጃዎች 1,በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ ሁለት የስራ ኃላፊዎች ትናንት ማክሰኞ ኩልመስክ ተብሎ ወደሚጠራ ከተማ ህዝብ አወያይተው ወደ ላልይበላ ሲመለሱ በተከፈተባቸው ድንገተኛ ተኩስ ህይወታቸው አልፏል። ትናንት ሚያዚያ 22/2016 ጥቃት የተፈፀመባቸውና ህይወታቸው ያለፈው አቶ ጌታቸው መልሴ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ እና አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ የላስታ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ ናቸው ተብሏል። 2,ከአንድ ወር በፊት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ከበረ ገብረየሱስ ትላንት ምሽት 12 ሰአት ላይ ወደ ቤቱ በመግባት ላይ እያለ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል ተብሏል። @Addis_News
Показать все...
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሕይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብቶች በመንግስት ኃይሎች ጭምር እየተጣሱ ነው- ኢሰመጉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በአዲስ አበባ ከተማ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሕይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብቶች አደጋ ውስጥ መሆናቸውን አሳሰበ። አዲስ ማለዳ ጉባዔው ትላንት ምሽት ካወጣው አስቸኳይ መግለጫ እንደተመለከተችው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሰቡ ሲሬ ወረዳ ሞቶ ቀበሌ ሚያዚያ 06 ቀን 2016 የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች 12 የአካባቢው ነዋሪዎች ተገድለዋል። በምዕራብ አርሲ ዞን ደግሞ የታጠቁ ኃይሎች በሰዎች ላይ ግድያ፣ እገታ እና የአካል ጉዳት መፈፀማቸውን እንደቀጠሉ ነው ሲል ኢሰመጉ አስታውቋል። ኢሰመጉ "ስለጉዳዩ ከመንግስት አካላት ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ሊሳካ አልቻለም" ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች። በአማራ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ በሰዎች ላይ የሚደርስ ግድያ፣ እገታ፣ የጅምላ እስር፣ የንብረት ውድመት፣ በየከተሞች ቦንብ ፍንዳታና የመንገዶች መዘጋት መቀጠሉ ተገልጿል። የአካባቢው ማህበረሰብም ከቦታ ቦታ በነፃነት መንቀሳቀስ እንደማይችልና አሽከርካሪዎች ከእገታ ባለፈ በየቦታው የማለፊያ (የኮቴ) እየተባለ ክፍያ እንደሚከፍሉ የመብቶች ጉባዔው አመላክቷል። የሕግ ባለሙያ አበራ ንጉሴ መጋቢት 20 ቀን 2016 በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአዋሽ አርባ በእስር ላይ እንደሚገኝ ኢሰመጉ የገለጸ ሲሆን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአባይ ህብር ብሔራዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት ይታያል በላይ ከሁለት ወር በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቢውሉም እስካሁን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ታስረው እንደሚገኙ ገልጿል። በራያ አላማጣ ወረዳ ከሚያዚያ 05 ቀን 2016 ጀምሮ በአካባቢው በተከሰተው ግጭት "ከፍተኛ" ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ወደ ቆቦ እና ሰቆጣ ከተማ የተፈናቀሉ ሲሆን በቂ የሰብዓዊ እርዳታ እና መጠለያ የሌለ ቢሆንም የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ግን አሁንም ካለው በላይ ሊጨምር እንደሚችል ኢሰመጉ በመግለጫው ማሳሰቡን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። ኢሰመጉ በመንግስት ኃይሎች እና በታጠቁ አካላት የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶች በአስቸኳይ እንዲታረሙ እና ፍትህ እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል። @Addis_News
Показать все...
👍 19