cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Amleset Muchie

She is the winner of titles Miss University 2004, Miss World Ethiopia 2006, she is an actress, a model, film director and writer. she Studied film making at New York Film Academy and Journalisme at uuc.

Больше
Рекламные посты
1 355
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
የዘለዓለም ሰንደቅ 💚💛❤️ ከ126 ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ሰንደቅ አላማ ስር በዓለም አደባባይ ታፍሮና ተከብሮ ይኖራል። ይህችን ባንዲራ ዓለም ያከበራቸው ታላላቅ ኢትዮጵያውያኖች በየመድረኩ ከፍ አድርገው በመያዝ በኩራት ቆመዋል። ሀገር ጠሎች የ‍እህቸ‍ን አርማ እንዳያዋርዷት ታላላቆች አክብረዋታል። የዛሬ ውሪዎች እንዳያሳንሷት የጥንት ኃያላኖች አንጸዋታል። አፍሪካ ሲባል ጥንተ ሉአላዊት ኢትዮጵያ ነች ገዝፋ የምትታየው። ኢትዮጵያ ሲባል የነ አጤ ቴዎድሮስ ብርታት የሆነች ከዘመነ ኖኽ ጀምሮ በሰማይ የተሳለች የሀገሬ ሰንደቅ ነች በሁሉ ልቦና ቦግ ብላ የምታበራው። ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር። 🔥💚💛❤️🔥 “አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል” ✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንበሳዬ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ ያብዛው። ዘዳዊት ቴዎድሮስ ካሳሁን 😍😘
Показать все...
ቀኑ ደርሶ በሀገር አንጻራዊ ሰላም ነግሶ ይኼንን የሙዚቃ ክር ከክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እስክንታደል ድረስ የኔም ጉጉት ትልቅ ነው። ቴዲ አፍሮም መቼ እንደሚለቅ በጠየኩት ጊዜ የሀገራችን ሁኔታ ጥሩ በሆነ ጊዜ ነበር ያለኝ። ቴዲ አፍሮን በተመለከተ ለሌላው ጊዜ እንዲህ ያሉ መረጃዎች ከየትም በኩል ብትሰሙ ታማኝ ምንጮችን እንድትፈትሹ፥ በተለይም የቴዲ አፍሮን ህጋዊ የፌስቡክ ገጽ እና Teddy Afro Net የተሰኘውን ገጾች እንድትከታተሉ በትህትና ለመጠቆም እወዳለሁ። ወደ ኢትዮ ቴሌኮም እንመለስ። ስለ ቴዲ አፍሮ አልበም የጠቀሰውን ዜና ከሰዓታት በኋላ ከገጹ ላይ ያስወገደ ቢሆንም ከድርጅቱ እንዲህ ያሉ የሀሰት ዜናዎች በሀገር ደረጃ ሲያሰራጩ ይኽ የመጀመሪያው ባይሆንም ህዝብ በሚያከብረው እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው አርቲስት ስም አንደ የሀገር በቀል ድርጅት የሀሰት ዜናውን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ማሰራጨቱ ትልቅ ነውር መሆኑን ለድርጅቱ የበላይ አመራሮች እና ለሚመለከተው አካል ስጠቁም ተግባራቸው እንደየ ሁልጊዜ ህዝብን ያላከበረ በመሆኑ በድርጅቱ ዳግም የሆነ ትልቅ ሀፍረት እንደተሰማኝ በመጠቆም ጭምር ነው። ሌላ አማራጭ ቢኖረንና ከዚህ ተቋም ጋ ለዘለዓለም ደንበኝነታችንን ብናቋርጥም በተለየ መልኩ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማኝ በዚሁ ለመጠቆም እወዳለሁ። በስተ-መጨረሻም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ሙዚቃዎቻቸውን ለለቀቁ የሀገራችን ዘፋኞች በጠቅላላ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። ከዚሁ ጋ በማያያዝ ቴዲ አፍሮ እገሌ ላይ አልበም ደረበ (ሊደርብ ነው) የሚል ስጋት ያደረባችሁ ግለሰቦችም ሆናችሁ ሌሎች አካሎች ይኼንን የሀሰት መረጃ በማመናችሁ ብቻ ይሄ ስጋት ሊሰማችሁ እንደቻለ በመረዳት ያሞኛችሁን ድርጅት ወቅሳችሁ የሀገሬ ክር እስኪለቀቅ በእጃቹ የደረሱትን ዘፈኖች አድምጡ ስል እመክራለሁ። ✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የተደራጀ ውሸት። የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እዮሪካ የተሰኘ አልበም ሊለቅ ነው የሚል የሀሰት ዜና Ethio Telecom ከ1.2 ሚሊየን በላይ ተከታይ ባለው በህጋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ከለቀቀ በኋላ የተለያዩ ግለሰቦች ሀሳቡን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየተቀባበሉት ይገኛሉ። እርግጥ ነው ቴዲ አፍሮ እጅግ የሚደንቁ ዘፈኖች የተከማቹበት ክር እያዘጋጀ መሆኑን አውቃለሁ። ከሰማኋቸው ዘፈኖች ውስጥ አብዛኛዎቹ አሁንም ድረስ በልቤ ውስጥ የሚሯሯጡትን ዜማዎቹን በማስብ ጊዜ፥ ልክ በረሃ ላይ ደክሜ እንደ ነብዩ ዮናስ ጥላ አግኝቼ ያረፍኩ ያህል ደስ እሰኛለሁ። ከዜማዎቹ ትዝታ ስላቀቅ ደግሞ ዳግም እንደ ጥላዋ መጠውለግ ስሜቴን ሁሉ ብል ይወረዋል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቴዲ አፍሮ አራተኛ ልጅ የሆነው ዘዳዊት ቴዎድሮስ ከእናቱ ጋ…😍🥰😘
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቴዲ አፍሮ ሽማግሌ ሚያዝያ 10/1965 ዓ.ም (የዛሬ 50 አመት) ሺ አለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተወለደባት ዕለት ነች። ሀይሌ ገብረሥላሴ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በዓለም ላይ ከፍ አድርጎ ያውለበለበ ታላቅ አትሌት ነው። ሩጫን ከጀመረባት ዘመን እስከ አሁኗ ቅጽበት ድረስ ኃይሌ ገብረሥላሴ በዓለም ላይ ያለው ክብር ወደር የማይገኝለት ሲሆን ኢትዮጵያን በዘመኑ በትልቅ ክብር ለዓለም ህዝብ አስተዋውቋል። የዓለማችን ትልቁ የመገናኛ ብዙሃን ጣቢያ /DSTV/ ስለ ሺ አለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ጀብድ በተደጋጋሚ ይዘግባል። ትልልቅ የዓለም መጽሔቶችም ኃይሌን አወድሰውታል። በተጨማሪም ኃይሌ ገብረሥላሴ ሽማግሌ ሆኖ ከዳራቸው ጥንዶች ውስጥ ቴዲ አፍሮ እና አምለሰት ሙጬ ተጠቃሽ ናቸው። ሺ አለቃ አትሌት ኃይለ ገብረሥላሴ (የሀገር ሽማግሌ) አገርህን ያስከበርክ ሰንደቋንም ከፍ አድርገኽ ያውለበለብክ ታላቅ ሰው ነህና እንወድሃለን። በታላቅ ክብርም እናከብርሃለን። ጥቁሩ የዓለማችን አንበሳ ሆይ እንኳን በምትወዳት ሀገርህ ላይ ተወለድክልን። መልካም ልደት። "እዩት ንጉሡ ግርማ ሞገሱ ዘውዱን ሸለመው ሰጠው ለአዲሱ" ✍@tataafro_official (ነፃ ብዕር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ETHIOPIA ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ኢትዮጵያ የተሰኘው የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ነጠላ ዜማ በህጋዊ የዩትዩብ ቻናሉ ከተለቀቀ ዛሬ ስድስተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ ውስጥ ሙዚቃው በመዳረሱ ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ባህላዊ ዘፈን ይኼ ሙዚቃ በስፋት ሲደመጥ አነጋ። በዕለቱ በመዲናይቱ የተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር። ይህ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተወዳጅ ሙዚቃ ከተለቀቀ በስድስት አመታት ውስጥ ይሄንን መረጃ እስከ-ለጠፍንበት ሰዓት ድረስ በዩትዩብ ብቻ ሀያ አራት ሚልየን ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ሺ አንድ መቶ አድማጮችን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል እጀባ ብዙ ተመልካቾችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው። በተጨማሪም ባለፉት አመታቶች ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የሙዚቃ ሰንጠረዦች ላይ ክብረ-ወሰኖችን የሰበረ የዓለማችን ተወዳጅ ሙዚቃ ለመሆን በቅቷል። ይኽ ሙዚቃ በወቅቱ በፈጠረው ትልቅ የሚዲያ ንቅናቄ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ለቴዲ አፍሮ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ዛሬም ድረስ BBC, CNN, Al Jazeera, CGTN Africa, BBC Africa, የቻይናው CC TV እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቴዲ አፍሮ በአፍሪካ እና በዓለም ላይ በሚገኙ አድናቂዎቹ ባለው ሰፊ ተቀባይነት ምክኒያት ስለሱ መዘገብ አትራፊ መሆኑን ተረድተው ስለሱ አዳዲስ መረጃዎችን መዘገብ ቀጥለዋል። ✍ @TataAfro_official (ነፃ ብዕር)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዕለተ ዓርብ፣ ዕለተ ስቅለት፣ መልካሙ ዓርብ በዚህች ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል የተሰቀለባት ዕለት ናትና “ዕለተ ስቅለት”የእግዚአብሔር መልካምነት ለሰው ልጅ ድኅነት በፍቃዱ ራሱን አሳልፎ ለሞት በመስጠቱ የተገለጠባት ናትና “መልካሙ ዓርብ” ይባላል። ዓርብ ነግህ (ሲነጋ) በዚህች ዕለት በነጋ ጊዜ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ኢየሱስን ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያወጡት፣ ለጲላጦስ አሳልፈው ይሰጡት ዘንድ እንዲሁም በፍርድ አደባባይ ይሰቅሉት ዘንድ የተማከሩበት ዕለት ነው። “ሲነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ጌታችን ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት” እንዲል። (ማቴ.፳፯፥፩-፪) መልካሙ ዐርብ 🙏🙏🙏
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የክብር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እንዲህ ብሎ ነበር። «የተማረ እንጂ የተባረከ መሪ ከለመንን ቆይተናል። የተማረ ከተገኘማ ጥሩ ነው የተባረከ ይሁን እንጂ። የተባረከ መሪ ግን ከተገኘ በጣም ጥሩ ነው ባይማርም እንኳን።»
Показать все...
የቴዲ አፍሮ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ቁርኝት ክፍል (፩) በኢትዮጵያ እንደ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለወገኖቹ የወገነ ፖለቲከኛም ሆነ የኪነጥበብ ሰው የለም። በተለያዩ ወቅቶች ለህዝባቸው ድጋፍ ለመሆን እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ መድሎዎችን ለመቋወም የተነሱ ግለሰቦች እና ተቋሞች በሚደርስባቸው ጫና አልያም በጥቅም የጀመሩትን ሳይጨርሱ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። ከሀገር ውጪ ይኖሩ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችም ሆኑ ጭቁኑን አገዛዝ በመሳሪያም በዲፕሎማሲም እንገረስሳለን ያሉ የግንቦት ሰባት ዋና አመራሮች ሳይቀሩ ትግሉ ተጠናቋል ብለው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆነው ህዝባቸውን የራስህ ጉዳይ ካሉት አመታቶች ተቆጠሩ። ቴዲ አፍሮ ግን ያለፉትን 20 አመታቶች ያለማንገራገር ከምስኪን ወገኖቹ ጋ ጸንቶ በመቆሙ ብዙ ከባድ የሆኑ መስዋዕትነቶችን ለብቻው ተጋፍጧል። ቴዲ አፍሮ በልዩ ሁኔታ በግል ህይወቱ ላይ አልያም በስራዎቹ ዙሪያ የሚፈጠሩ አልመግባባቶችን ተጎድቶም ቢሆን በጊዜ የመቋጨት ልማድ ያለው ብልህ ሰው ነው። በወገኖቹ ላይ የሚደርሱ በመንግስታዊ እና በሌሎች በተደራጁ ቡድኖች የሚደርሱ መድሎዎችን፣ ዘር ተኮር ማፈናቀሎችን፣ ማንነት ላይ ያተኮሩ ጭፍጨፋዎችን፣ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን፣ ህገመንግስታዊ ስህተቶችን ብሎም የመብት ጥሰቶችን በግልጽ እና በቀዳሚነት በመቋወሙ ለአመታቶች ብቻውን ሲጨቆንና ኢፍትሃዊ የሆኑ ድርጊቶች በገዢው ቡድን ሲፈጸሙበት ቆይቷል። ከነዚህም ውስጥ በሀሰት ክስ ለ18 ወራቶች በእስር መቆየት፣ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ የኮንሰርት ስራዎቹን ያለበቂ ምክኒያት መከልከል፣ በሚዲያዎች ላይ የኪነጥበብ ስራዎቹ እንዳይተላለፉ ማገድ፣ ከሀገር ለስራ የመውጣት መብቱን በመንፈግ በተደጋጋሚ ከኤርፖርት መመለስ እንዲሁም የአልበም የምረቃ ስነስርዓቱን እንዳይፈጽም ፍቃድ የለህም በሚል አግባባዊ ባልሆነ አካሄድ በዕለቱ (በምረቃው ዕለት) ቦታው ላይ በመገኘት በሀይል መሰረዝና በየመንገዱ እየተከታተሉ ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ ብሎም የስነልቦና ጉዳት ለማድረስ እና ውስጡን ሞቾት እንዲነሳው በማሰብ በሚንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች ሁሉ የተለያዩ መከናዎችን በመመደብ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች እንዲከታተሉት ማድረግ እና የመሰሉ መንግስታዊ ውንብድናዎች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። እንደ ሚታወቀው በቴዲ አፍሮ ልክ ግዙፍ ኮንሰርቶችን በኢትዮጵያ ያዘጋጀ አርቲስትም ሆነ መንግስታዊ ተቋም አልያም ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮሞተሮች የሉም። የቴዲ አፍሮ ኮንሰርቶች በአገር ቤት በሚዘጋጁበት ወቅት በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኮንሰርቱን ለመታደም በማሰብ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ። እንዲሁም ከክፍለ ሀገርም ኮንሰርቱ ወደተዘጋጀበት ከተማ ይጓዛሉ። ይሄ ደግሞ የከተማውን ገበያ የሚያነቃቃ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ለምሳሌ ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው ኮንሰርት ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ከመጡ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከአዲስ አበባ፣ ከጎንደር፣ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች ወደ ከተማዋ በመግባታቸው በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ አልጋቸው ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተይዞ ቆይቷል። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም በልዩ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱ ነበር። የምግብ ሰጪ ድርጅቶችም ከወትሮው በተለየ መልኩ በሰዎች ተሞልተው ነበር። ይኼንን በወቅቱ ቦታው ላይ ተገኝቼ አስተውያለሁ። እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ባዘጋጃቸው መድረኮችም ተመሳሳይ ነገሮች ተፈጥረዋል። ልጁ ለአንድ አዳጊ ሀገር ትልቅ ሀብት ነው። ሆኖም ግን ይኼንን ውድ ሀብት ጨቋኞች አምርረው ተጣሉት። ከነርሱ የሚፈልገው አንዳች ቢኖር ድሃ ወገኖቹን ሠላም ሰጥተው፣ መብታቸውን አክብረው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲያኖሩለት ብቻ ነው። ቴዲ አፍሮ ሀገር ውስጥ ሊያዘጋጃቸው አስቦ የተሰረዙበት ኮንሰርቶች በቅድሚያ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አሟልቶ ፍቃድ ተሰጥቶት ብዙ ሚሊዮኖችን ወጪ ካደረገባቸው በኋላ በድንገት ከሚመለከተው አካል የሚደረጉ የኮንሰርት ክልከላዎች ቴዲ አፍሮን ምን ያህል እንዳከሰሩት ላሰላ ሰው በግለሰብ ደረጃ ይሄንን ሁሉ ኪሳራ መቋቋም በጣም ከባድ እንደሆነ ይረዳል። ቴዲ አፍሮ ግን በዚህ ሲያማርርና ሲቆጣ ተስተውሎ አያውቅም። ተደጋጋሚ ኪሳራዎች ደርሰውበትም ለህዝቤ ስል ያጣሁን ገንዘብ በካሴት ሽያጭ አገኘዋለሁ ብሎ በማሰብ እንኳን ካሴቱ ላይ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጎ አያውቅም። ይልቁንም አንድ ጀማሪ ሙዚቀኛ በሚያከፋፍልበት ዋጋ ነው ስራውን ገበያ ላይ የሚበትነው። እሱማ ቢቻለው ለሁሉ በነጻ ቢያደል ደስታው ነበር። ኮንሰርቶቹንም ስንመለከት ከሱ በታች ተከታይ ያላቸው የሀገራችን ሙዚቀኞች የመግቢያ ዋጋቸውን ለመደበኛ 600 ብር ለVIP ደግሞ እስከ 3000 ብር ድረስ ሲያስከፍሉ አስተውለናል። ቴዲ አፍሮ ግን መደበኛ የመግቢያ ዋጋ 300 ብር የVIP ደግሞ 500 ብር ነበር ትልቁ የትኬት መሸጫ ዋጋው። ይኼም በዛ ብሎ ከአዘጋጆች ጋ ሲከራከር ነበር። ምን ያህል ህዝቡን ቢረዳው እና ቢወደው ነው ኪሱ የሚገባው ብር ሳያጓጓው በጣም እርካሽ በሚባል ዋጋ ያንን የመሰለ የመድረክ ስራን የሚያቀርብልን ብዬ ሳስብ አንዴ ጅማ ለኮንሰርት ሄዶ የተናገራት አንዲት ቃል ትዝ አለችኝ። "በከፈላችሁት ልክ ሳይሆን በምወዳችሁ ልክ ነው የምዘፍንላችሁ" ሲል ሙዚቃውን ሊታደሙ ለመጡ አድናቂዎቹ ተናግሮ ነበር። እውነትም በሚወደን ልክ አዜመልን። በሚወደን ልክ በመከራችን ወቅት ለምን ብሎ ቆመልን። በያንዳዷ የችግራችን ወቅት ፊትአውራሪ ሆነልን። አንደበታችን ተይዞ አቅማችን ተዳክሞ ተስፋ በቆረጥን ጊዜ እሱ ጉልበት ሆነን። ቴዲ አፍሮ ሸክማችንን እንደ ግል ሸክሙ ቆጥሮ ጨቋኞችን ተጋፈጠ። ክፍል ሁለት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይለጠፋል ✎✍#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Показать все...