cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣ አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣ ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው። @MentalCounsel ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል! ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ! 🏠Welcome to your Home! 🏘 Personal Contact: @epha_aschalew Insta: instagra.com/epha_aschalew

Больше
Рекламные посты
41 985
Подписчики
-2424 часа
-1247 дней
-90730 дней
Время активного постинга

Загрузка данных...

Источники трафика
  • Подписчики 90.47%
  • Каналы 3.25%
  • Через ссылку 0.36%
  • Группы 3.14%
  • Поиск в Telegram 0.08%
  • Прямые сообщения 2.61%
  • Прочее 0.08%
Анализ публикаций
ПостыПросмотры
Поделились
Динамика просмотров
01
በቴሌግራም ገቢ ማግኛ መንገዶችን መማር ይፈልጋሉ?? 🪙 ስለ Notcoin 🪙 ስለ Toncoin 🪙 ስለ Bitcoin 📊📈 ስለ Forex Trading በየቀኑ የሚወጡ መረጃዎችን እንዲሁም በቂ ትምህርቶችን ማግኘት ትፈልጋለችሁ?      ቻናላችንን ተቀላቀሉ 👇👇             @Crypt_currencies             @Crypt_currencies             @Crypt_currencies
2722Loading...
02
ስጦታህን አታሳንስ! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ ምድራችን ላይ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እናንተም ከየትኞቹ ጎራ እንደሆናችሁ እወቁ። ማስተካከል የምትችሉትንም ለማስተካከል ጊዜ አታጥፉ። በአንደኛው ጎራ የሚመደቡ ሰዎች ከተቀሩት ጋር ሲነፃፀሩ ጥቁት የሚባሉ ናቸው። በእነዚህ ሰዎች መመስገን ከፈለጋችሁ ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ትልቅ ስጦታ ገዝቶ መስጠት፣ ከባዱን ችግራቸውን መፍታት፣ ሁሌም ከስራቸው አለመጥፋት፣ ንብረታችሁን ሁሉ አሳልፋችሁ መስጠት ወይም የዘወትር አድናቂያቸው መሆን አይደለም። አነዚህ ሰዎች ለሰጣቿቸው ጠብታ ውሃ ከልብ ያመሰግኗችኋል፣ ከእናንተ ጋር ለሚያሳልፏት ትንሽ ጊዜ ያመሰግኗችኋል፣ ምንም ባታደርጉላቸው በሃሳባችሁ ብቻ ይደነቃሉ፣ የእነርሱ የእናንተ እቅድ አካል መሆን ልባቸውን ያሞቀዋል፣ ደስታውንም ይሰጣቸዋል። በትንሽ ነገር ይደሰታሉ። በሌላኛው ጎራ የሚመደቡ ሰዎችስ ምን አይነት ሰዎች ናቸው? እነዚህ ሰዎች በፍቃዳችሁ የምታደርጉት የትኛውም ነገር አይዋጥላቸውም። ምንም አድርጉላቸው ግዴታችሁ እንደሆነ ያስባሉ። ለምትሰጧቸው የዉሃ ጠብታ አይደለም ባህሩን እንኳን ብትሰጧቸው አይረኩም፣ ሊያመሰግኗችሁም አይፈልጉም። የምታደርጉላቸውን እያንዳንዱን ነገር እንደ ግዴታ ይወስዱታል ከዛም በላይ በፍፁም አያመሰግኟችሁም። አዎ! እራስን ከነዚህ ሁለት አይነት ሰዎች ጎራ ነጥሎ ከመመልከት በፊት እናንተ ከየትኞቹ እንደሆናችሁ እወቁ። እንደ አንደኞቹ በተደረገላችሁ ትንሽ ነገር የምትደሰቱና የምታመሰግኑ ከሆነ ዓለም የእናንተ ነች፣ ነገር ግን ልክ እንደ ሁለተኞቹ ምንም ቢደረግላችሁ የማትረኩና ለማመስገን ፍቃደኛ የማትሆኑ ከሆነ ህይወት በጣም ከባድ ትሆንባችኋለች። እርካታ ሲባል የተሰጣችሁ ነገር በቂና የልብ የሚያደርስ ሆኖ ሳይሆን ከመደረጉ በላይ ስለታሰበላችሁና በትንሹም ቢሆን ትኩረት ተሰጥቷችሁ ስለተደረገላችሁ የሚሰማችሁ ውስጣዊ ስሜት ነው። ሰዎች ከሚያደርጉላችሁ በላይ እራሳችሁ ለእራሳችሁ ማድረግ ትችሉ ይሆናል፣ እርሱንም በፈለጋችሁት ጊዜና መጠን ልታደርጉት ትችላላችሁ። ከሰው የሚመጣው ግን ትኩረትን፣ ፍቅርንና ክብርን ይዞ ይመጣል። ምንም ነገር ቢሰጣችሁ በክብር የመቀበልን ልማድ አዳብሩ፣ ለሚደረግላችሁ ነገር ቦታ ስጡ። ከእቃው ትንሽነት በላይ በሰጪው ዘንድ ስላላችሁ ቦታ አስቡ። በፍቃድ የሚሰጣችሁ የትኛውም ነገር ከግዴታ የተነሳ ሳይሆን ከውዴታ እንደሚመነጭ እወቁ። አዎ! ጀግናዬ..! ስጦታህን አታሳንስ! ጠብታ ውሃም ሆነ ሙሉ ውቂያኖስ ለተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን። በትንሹ ያላመሰገነ ትልቅም ቢደረግለት አያመሰግንምና በጥቃቅን ስጦታዎችህ ማመስገኑን ተለማመድ። ማንም የሰጠው እንዲረክስበት አይፈልግም፣ ማንም አስቦና አቅዶ ያዘጋጀው ፕሮግራም ሲናቅበት አይወድም። አንዳንዴ ድግሱ ባይጥመንም፣ ምግቡ አንጀታችንን ባያርስም፣ መሰተንግዶው የልብ ባያደርስም ለደጋሹ ካለን ክብርና ቦታ የተነሳ ተደስተንና አመስግነነው የምንወጣበት ጊዜ ይኖራልተ። ከምግብና መጠጡ በላይ አክብሮ ስለጠራን ብቻ እንደሰታለን። የተሰጠህ ነገር ላንተ ብዙም ዋጋ የሌለው ቢሆንም ለሰጪው ብለህ ዋጋ ልትሰጠው ይገባል። ወዳጅነት እንዲዳብር፣ ፍቅር እንዲጎለብት፣ አንድነትም እንዲፀና ልባዊ ምስጋናና አድናቆት ያስፈልጋል። በእጁ ከያዘው ቁስ በላይ በልቡ ያለህን ቦታ ለመረዳት ሞክር፣ ከኪሱ አውጥቶ ከሚሰጥህ ገንዘብ በተሻለ ለሚሰጥህ ውድ ጊዜው ቦታ ስጥ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
6193Loading...
03
Media files
5600Loading...
04
አይመለከተኝም! ፨፨፨////////፨፨፨ ከራስጋር ንግግር፦ "ህይወቴ መቼ መቀየር እንደጀመረ አስታውሳለሁ። ድሮ የሰው ነገር አብዝቶ ያስጨንቀኝና ያሳስበኝ ነበር። ማን ምን አደረገ፣ ማን ከማን ጋር ሆን፣ ማንስ ምን ለበሰ፣ ምን ጀመረ እያልኩ የባጥ የቆጡን አወርድ ነበር። ማሰብ ከጀመርኩ ስለሰው ነው፣ የማወራው ስለሰው ነው፣ የምሰራው ለሰው ብዬ ነው፣ ከራሴ በላይ የምጨነቀው ስለሰው ነው። በአጠቃላይ የምኖረው ለሰው ነበር። ለሰው መኖር ምንያህል እራስን እንደሚያሳጣ በሚገባ አውቃለሁ። የፍረሃቴ ምንጭ በራሴ ላይ ሰውን ማንገሴ ነው፣ በሰው ዘንድ የበታች ተደርጌ የምታየው በየሔድኩበት ሁሉ ከራሴ በላይ ለሰው የበዛ ቦታ በመስጠቴ ነው። ሰው ሲመራኝ፣ ሰው ሲወስንልኝ፣ እኔም በሰው መንገድ ስመላለስ ከረምኩኝ። ዛሬ ግን ስነቃ አንድ ነገር ገባኝ። "የሰው ነገር የእኔ ጉዳይ አይደለም፣ ዋናው ጉዳዬ እኔና እኔ ነኝ።" ለእራሴ መኖር ሳልችል፣ ለእራሴ ሳልበቃ፣ እራሴን ሳላድን እንደቀድሞ ለሰው ልኑር ብል ከውድቀት በቀር የማገኘው ነገር አይኖርም። ስለማን ምን በላ፣ ስለማን ምን ጠጣ፣ የት ሔደ፣ ከማንጋር ሄደ መጨነቅ ሳቆም የዓለምን ሌላ ገፅ መመልከት ቻልኩ። አዎ! እኔ የእራሴ ወሳኝ ጉዳይ አለኝና የሰዎች በፈለጉት መንገድ መጓዝ አይመለከተኝም፣ የሰዎች እንደምርጫቸው መኖር ጉዳዬ አይደለም። እነርሱ እንደፈለጉ ይኖራሉ፣ እኔም እንደዛው የመኖር መብቱ አለኝ። ስለማይመለከተኝ የሰው ጉዳይ እየተጨነኩ የማሳልፈው ጊዜ አብቅቷል። አሁን ለውጤን የማጣጥምበት ጊዜ ነው። ሰውን ለማስደሰት ስጥር ደስታዬን አጥቼያለሁ፣ ስለሰው ሳስብ የሚያስብልኝ አጥቼያለሁ። እንትና እንደዚ አደረገ ስባል ከእኔ ህይወት ጋር ባይገናኝም እንዲሁ ስደነግጥ፣ እንተና ይሔንን ስራ ጀመረ ሲባል ከሰውዬው ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር ባይኖር ስለርሱ ሳወጣ ሳወርድ ዘመናት አልኀዋል። የሚመለከተኝንም የማይመለከተኝንም ስሰማ፣ ሳወራ፣ ሳዳንቅ፣ ሳብላላ ከርሜያለሁ። ነገር ግን ምንም ጠብ የሚል ነገር አላገኘውበትም። ከሰው ህይወት የበለጠ የሚመለከተኝ የእራሴ ህይወት እንደሆነ ገብቶኛልና ከአሁን ቦሃላ በእራሴ የግል ጉዳይ ተጠምጄያለሁ፣ ማንንም ምሰማበት ለማንም የምደነግጥበት ምክንያትም ጊዜም የለኝም። እራሴን ካዳንኩ ለሰውም መድረስ እችላለሁና አሁን ትኩረቴ እራሴና እራሴ ብቻ ነው።" አዎ! ጀግናዬ..! አንዳትሸወድ፣ ከምንም ጉዳይ የሚበልጠው የእራስህ ጉዳይ ነው። ትኩረትህን እራስህ ላይ ብቻ አድርግ። እንትና በዚህ ወጣ፣ እገሌ እንትን በላ፣ እንትና እዛ ገባ የሚሉ ትርኪሚርኪ ወሬዎች ጉዳይ አይደሉም፣ አይመለከቱህም። ወሬ ስታመላልስ ብትኖር ከወሬ ነጋሪነት የዘለለ ሙያ ሊኖርህ አይችልም። ከሰው ጥቃቅን ተግባር በላይ የእራስ ትላልቅ አጀንዳዎች እንዳሉብህ እወቅ። የሰውን ተግባር እያዳነክ፣ ጥቃቅን አጀንዳዎችን እያጎላይ፣ የማይረባ ወሬ እየሰበሰብክ፣ በበሬ ወለደ ዜና እየተገረምክ የእራስህን ህይወት ልትኖር አትችልም። የማይመለከትህን ጉዳይ "አይመለከተኝም!" ብለህ የመመለስን ልምድ ፍጠር፣ ያንተ ጉዳይ ባልሆነ ነገር መብሰልሰል አቁም። ዞር ዞር የምትለው እራስህን ለማሰማር እንጂ በምታየውና በምትሰማው ሁሉ ለመጨነቅ እንዳልሆነ አስታውስ። የእራስህን ህይወት ኑር፣ በቅድሚያ የግል አጀንዳህን ከዳር አድርስ፣ ችግሮችህንም ፍታ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 1197Loading...
05
✅ ህይወትን በጥበብ መምራት! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/7_BhRxMX5ao?si=VFZuqz8ViQPe_-NO
1 2692Loading...
06
ኤቨረስት ሆይ፣ አሸንፍሃለሁ! ፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨ አንድ ሰው ተሸነፈ የሚባለው መቼ ነው?  በቃኝ ብሎ ሲያቆም ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ የለፉለት ነገር ድል ሲቃረብ ተስፋ በመቁረጥ ጥለውት ይሄዳሉ፡፡ በነበራቸው ጥረት ውስጥ ያዳበሩትን ጥንካሬ አያስተውሉትም፡፡ ብዙ ሞክሮ አለመሳካት ያለማቆም እንጂ የማቆም ምክንያት ሊሆን አይገባውም፣ ምክንያቱም በተሞከረው ሙከራ የመጣው ጥንካሬ፣ የባህሪይ ጽናትና የልምምድ ብስለት ከመሞከራችን በፊት የነበረንን የማሸነፍ ብቃት  በብዙ  እጥፍ  ስለሚጨምረው ነው፡፡ ሞክረን ስንሸነፍ፣ ራሳችንን አሻሽለን እንደገና ብንሞክረው እንደምናሸንፈው ማረጋገጫችን እንደሆነ ማወቅ አንዱ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡ ሰር ኤድመንድ ሂለሪ (Sir Edmund Hillary) ለመጀመሪያ ጊዜ የኤቨረስትን ተራራ ጫፍ የረገጠ ሰው ነው፡፡ ይህንን ተራራ በድል ተወጥቶት ጫፍ ከመድረሱ በፊት በነበረው የቀድሞ ሙከራው ቡድኑ ተራራውን መውጣት አቅቶት አንድ ሰው ሞቶባቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ከዚያ አሳዛኝ ሙከራቸው ሲመለሱ በለንደን በነበረው ሪሰብሽን ግብዣ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ ነበር፡፡  ቆሞ ንግግር  ከሚያደርግበት መድረክ ጀርባ የኤቨረስት ተራራ ምስል በትልቁ ተቀምጧል፡፡ በንግግሩ ወቅት ወደዚህ የተራራ ስእል ዘወር በማለት እንዲህ አለ፣ “ኤቨረስት ሆይ፣ አሁን አሸንፈኸናል፡፡ ነገር ግን ጠብቀኝ እመለስና አሸንፍሃለሁ ምክንያቱም አንተ ያው ነህ፣ እኔ ግን አድጌና በርትቼ እመለሳለሁ”፡፡ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ ነበር የሚያስፈልገውን ዝግጅት አድርጎ ቀድሞ ያሸነፈውን ተራራ ሄዶ ያሸነፈው፡፡ “ታላቁ ክብራችን ያለው ባለመውደቅ ውስጥ አይደለም፣ በወደቅን ጊዜ ሁሉ ተነስተን በመቀጠላችን ውስጥ ነው እንጂ” - Ralph Waldo Emerson መራመድ እስካለ ድረስ መውደቅ አለ፣ መነገድ እስካለ ድረስ መክሰር አለ፣ መውደድ እስካለ ድረስ መጎዳት አለ፣ መማር እስካለ ድረስ ፈተና መውደቅ አለ … ይህ የማይለወጥ የሕይወት ህግ ነው፡፡ “ምን ይበላሽ ይሆን?” በሚለው ፍርሃት ታስሮ መንቀሳቀስ አለመቻል በሕይወት እያሉ መሞት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሕይወቴ ያልፍ ይሆናል ብለው ከመፍራታቸው የተነሳ ሕይወትን ሳይጀምሯት ያልፋሉ፡፡ ሕይወት ግን አዳዲስ ነገሮች የሚሞከሩባት፣ ሲሳካ የምንደሰትባት፣ ሳይሳካ ደግሞ ራሳችንን ከወደቅንበት አንስተንና አቧራችንን አራግፈን እንደገና የምንቀጥልባት ጎዳና ነች፡፡ ሕይወት ማለት በዚህ ምድር ላይ “መከሰትና” ምንም ነገር እንዳይደርስብን ራሳችንን መጠበቅ አይደለም፡፡ “ለአደጋ” ሊያጋልጡን የሚችሉትንና ማንነታችንን የሚፈቱትን ነገሮች ከመሞከር ውጪ ሕይወት ባዶ ነች፡፡ ለዚህ እውነታ ልባችንን በመክፈት አዳዲስ “ተራራዎችን” በመውጣት፣ ሰው ያልሞከረውን በመሞከርና በማንነታችን ውስጥ የታመቀውን ድብቅ ብቃት የሚወጣበትን እድል ልንሰጠው የግድ ነው፡፡ 1.  ማድረግ እንዳለባችሁ እያወቃችሁት ከፍርሃት የተነሳ ያላደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው? 2.  እናንተ በሙሉ ልብ እያመናችሁበት ከሌሎች ሰዎች ግፊት የተነሳ ያመነታችሁበት ነገር ምንድን ነው? 3.  ከዚህ በፊት ሞክራችሁ ስላልተሳካ ብቻ ድገማችሁ ላለመሞከር ወስናችሁ የተዋችሁት ነገር ምንድን ነው? /25 የስኬት ቁልፎች መጽሐፍ/ ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
1 83220Loading...
07
ሳታይ አትፍረድ! ፨፨፨///////፨፨፨ ከውድቀት ተነስተው የክፍታውን ጣሪያ የተቆናጠጡ ሰዎች አሉ፤ በድህነት ላይ ተረማምደው የሃብት ማማ ላይ የደረሱ ሰዎች አሉ፤ ችግርን ተጋፍጠው ለውጤት የበቁ ሰዎች አሉ፤ ህመሙን ችለው፣ ስቃዩን ተቋቁመው፣ ጫናውን አልፈው የሚያኮራቸውንና የማይበገረውን ማንነት የገነቡ ሰዎች አሉ። ለድካም ሳይበገሩ፣ ለችግር እጅ ሳይሰጡ የሚፈልጉትን የሰውነት አቋም የገነቡ ሰዎች አሉ። ቀላል ስለሆነ ግን አይደለም፤ ምንም ስለማይፈልግም አይደለም። ስቃዩን፣ ክብደቱን፣ መከራውን ሁሉ ሞክሮ ያየው ብቻ ያውቀዋል። ዋጋው ከባድ ቢሆንም ስላመኑበት እስከጥግ ተጋፍጠው አሳክተውታል። ውጪ ሆኖ ለሚመለከት ግን ሁሉም ነገር ቀላል ይመስለዋል፤ ላልሞከረ ነገሮች ሁሉ ወዲያው የሚገጣጠሙና አልጋ በአልጋ የሚሆኑ ይመስለዋል። ነገሩ ግን እንደሚታሰበው አይደለም። አዎ! ጀግናዬ..! ሳታይ አትፍረድ፤ ሳትሞክር አትናገር። ከየትኛውም ንግግርህ በፊት እውቀትን አስቀድም፤ አዳምጥ፤ መርምር፤ ተረዳ፤ ግፋ ሲልም ሞክረህ እየው። አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ የሰውነቱን አቋም ለማስተካከል የሚጥር ሰው ላይ አስተያየት ለመስጠት እርሱ የሚጋፈጠውን ስቃይ ማየት አለብህ፤ የሚገፋውን ክብደት መሞከር ይኖርብሃል። አንድ በየጊዜው ለተከታዮቹ የሚመጥን ፖሮግራም ለማዘጋጀት የሚጥር ሰው ላይ ህፀፅና ድክመቱን ከማውጣትህ በፊት ሃሳቡን ኬት እንደሚያመጣው፣ ፖሮግራሙን እንዴት እንደሚሰራው፤ ምንያክል ጊዜ እንደሚፈጅበት፣ ምን ምን እንደሚያነብ ለማወቅና ለመረዳት ሞክር። እንደምታስበው ቀላል እንደሆነ የምታውቀው በስራው ውስጥ ስታልፍ ብቻ ነው። አዎ! ማንም የጥረትህን ዋጋ እንዲያሳንሰው እንደማትፈልገው ሁሉ ማንም ለአመታት ለፍቶ ያመጣውን ውጤት ዋጋ አታሳጣው። ይብዛም ይነስም ለፍቶ የሚያድር ሰው የሚለፋ ሰው ላይ አይፈርድም። ሁላችንም የተለያየን ሰዎች ነንና ምርጫችን ይለያያል፣ የሚጥመንና ቅድሚያ የምንሰጠው ነገርም እንዲሁ ለየቅል ነው። አንተ የምትወደውን ነገር ስላላደረገ ስህተት የሚሆን ሰው የለም፤ ባንተ መንገድ ስላልተጓዘ የሚወድቅና ወደኋላ የሚመለስ ሰውም የለም። ለየትኛውም ሰው ምርጫ ክብር ይኑርህ፤ በተለይ በእራሱ መንገድ ለሚጥርና እራሱን ለማሻሻል ለሚደክም ሰው ልባዊና የተለየ ከበሬታህን ለግሰው። ማንም ህይወቱን ለማሸነፍ በየፊናው የሚደክመው ወዶ ላይሆን ይችላል። ህይወት ግን ያለመስራት ምርጫ አትሰጥምና ምንም ነገር መስራቱ የግድ ነው። ከቻልክ ከጀርባ ያለውን ነገር አታውቅምና ማንም ላይ አትፍረድ፤ ካልቻልክ ድግሞ ሳታይና ሳትሞክር ማንም ላይ አትፍረድ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 0419Loading...
08
✅ ለራሳችሁ ታዘዙ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/fh3XtKJ-poQ?si=wEKz9MXzSJ1uGEuw
1 7432Loading...
09
ስንብትን ልመድ! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ አዳዲስ ክስተቶች የህይወት ልዩ መገለጫዎች ናቸው፤ ከተለመደው የኑሮ ዘይቤ ስትለይ ውስጥህ ሊረበሽ፣ ቅር ሊልው፣ ምናልባትም የሚገጥሙህ ፈተናዎች ሊያስጨንቁህ፣ የሚጠብቁህ ውጣውረዶችም ሊያሳስቡህ ይችላሉ። እነዚህ ግን አዲስ ከባቢን እንዳትላመድና ከተለየ የህይወት ጉዞ ሊያቅቡህ አይችሉም። አንተ ብቻ ያየሃቸው መዳረሻዎችህ ከእነዚህ ፈተናዎች የተለዩ አልነበሩም፤ አዲሱ ከባቢህ ለአዲስ ፈተና ማጋለጡ እሙን ነው። የሔድክበት ሁሉ አልጋ በአልጋ ላይሆን ይችላል፤ የፈለከው ሁሉ ቀርቦልህ፣ የሚጠቅምህን አግኝተህ ጉዞ እስክትጀምርም ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። እንዲሁ ተመችቶህ፣ ሁሉ ባለበት ሆኖ ግን አንዳች የሚቀየርና የሚያድግ ነገር የለም። አዎ! ጀግናዬ..! ስንብትን ልመድ! መጥፎ ላማዶችህን መለየት ልመድ፤ ጎጂ እይታዎችህን መጣል ልመድ፤ ባላመንክበት አለመጓዝን ልመድ፤ ከተለየ ከባቢ ጋር እራስህን ማስማማት ልመድ፤ ከአዳዲስ ውሳኔዎችህ ጋር ተስማማ። የተሻለ ነገር ለማግኘት፣ ወደ ክፍታው ለመጓዝ ጠንካራ የውሳኔ ሰው ሁን። ስንብትን በመልመድ ለአዲስ መንገድ እራስህን አዘጋጅ። እንኳን ለተሻለ ኑሮ ይቅርና ህይወትን በሙሉ የምትሳነበት ጊዜ ስለመኖሩ አስታውስ። ውጣውረድ ባለበት ምድር የተለመዱ ነገሮችን አለመሰናበት አይቻልም። ለውጥና እድገት፣ ከፍታና ዝቅታ፣ ማግኘትና ማጣት በሚፈራረቅበት ህይወት ለአዲስ ለውጥ እራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ልብህ ካልወሰነ፣ አንጀትህ ካልቆረጠ፣ መጨከን ካልቻልክ ስለ አንተነትህ እውነተኛ ሃይል ልታውቅ አትችልም። አዎ! ብዙ አደጋ ይጋረጥብህ፣ ለፈተናዎች ተጋለጥ፣ ስቃይ ይብዛብህ ነፃነትህን ፍለገህ፣ ዘላቂ ምቾትን መርጠህ ግን ሁሉን የመቋቋምና የማለፍ ብርቱ ሃይል እንደለህ እወቅ። የተለየ መንገድ በመረጥክ ቅፅበት ብዙ የምታጣቸውና የምትለያቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ልማዶች አሉ። የልዩነትህ ውጤትም ለተሻለ ነገርና ለአመርቂ ውጤት ነው። ባለህበት ቦታ ነገሮች የማይቀየሩ ከሆነ መተው ያለብህን መተው፣ መለየት ያለብህን መለየት፣ እንዲሁም ማቆም ያለብህን ማቆም ይኖርብሃል። ስንብት ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ትርጉም ከሌለው ቆይታና ከውጤት አልባ በላይ ግን አይከብድም። ባለህበት ሆነ ተፈጥሮ የምታድለህ፣ ሰውነትህ የሚለግስ ብርቱ ሃይል ይኖራል፣ ይህም አዲስን ተግባር ትላመድ ዘንድ፣ የተሻለ ከባቢን እንድፈጥር፣ ከፍ እያልክ፣ እያደክ፣ እየተቀየርክ እንድትሔድ ያደርግሃል። አጉል ልማድህን መሰናበት ልመድ፣ የማይጠቅሙህ ሰዎችን የመለየት ድፍረት ይኑርህ፣ አሉታዊ እሳቤዎችህን የመተው ልማድ አዳብር። በአዲስ እርምጃ አዲስ ከባቢን ፍጠር። ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 29417Loading...
10
መጥፎዎች ነን! ፨፨፨///////፨፨፨ አንዳንዴ እንደዚህ ነው። ሁላችንም በሆኑ ሰዎች ታሪክ ውስጥ መጥፎ ሰዎች ነን። እንደተጎዳን፣ እንደተከዳንና እንደተገፋን ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ከእኛ ሀሳብ በተለየ ሌሎችም እኛ እንደጎዳናቸውንና ችግር ውስጥ እንደከተትናቸው ሊናገሩ ይችላሉ። የሰው ልጅ እራስወዳድ ነውና አውቆም ይሁን ሳያውቅ እራሱን ለመጥቀም ብሎ ሌላውን ሰው ሊጎዳ ይችላል። ከዛም በላይ በእውን ባይጎዳም በሀሳብ እንደጎዳ ተደርጎ ይወሰዳል። እያንዳንዱ የህይወት ምዕራፎች ታሪኮቻችን ይሆናሉ። አስተውለንም ይሁን ሳናስተውል የሰውን ስሜት መጉዳታችንም በመጥፎነት ከሚያስፈርጁን አሉታዊ ታሪኮቻችን ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው። እኛ ለሰዎች ስለጎዱን ሰዎች ልናወራ እንችላለን፣ በእኛ የተጎዱ ሰዎችም ይህንኑ ያደርጋሉ። ዓለም የተጎዱ ሰዎች ስብስብ ብቻ እስክትመስል ድረስ በየሔድንበት የምንሰማው የተጎጂውን ሮሮ እንጂ የጎጂውን ፀፀት አይደለም። ብዙ ሰው ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ተጠቂነቱን ይነግራችኋል። እራሱን ጥሩ ሰው ወደ ህይወቱ ገብቶ የወጣውን ሰውም መጥፎ አድርጎ ይስልላችኋል። ሰውነት በራሱ ለእራሱ እንዲያደላ ያደርገዋል። ተጠቂ እንደሆነ ሲናገር እንዲታዘንለት ፈልጎ ነው፣ ጉዳቱን ሲያስተጋባ የተለየ ጥቅምና እንክብካቤን ፈልጎ ነው። አዎ! መጥፎዎች ነን! ምንምያህል ደግና መልካም ሰው ብንሆንም በሆኑ ሰዎች ታሪክ ውስጥ የመጥፎ ሰው መገለጫዎች እኛ ነን፣ ምንምያህል ልበቀኖችና አዎንታዊ ሰዎች ብንሆንም በሆኑ ሰዎች ዘንድ በከሃዲነትና በጨካኝነት ተስለናል። ክፋትና ጭካኔያችን የእውነት ላይሆን ይችላል ሰዎች በሚረዱን መንገድ ግን እውነት ያደርጉታል። መቀየር ከማንችለው እውነታ ውስጥ ይሔ አንዱ ነው። ፍላጎታችሁን አዳምጣችሁ፣ ለእራሳችሁ አዝናችሁ፣ ምቾታችሁን ፈልጋችሁ፣ ፍቅርን ገፍታችሁ፣ ቸልተኝነት አብዝታችሁ፣ ከሌላ ሰው በላይ ለእራሳችሁ የተለየ ቦታ ሰጥታችሁ ሰዎችን ብትርቁ ወይም ብትለዩ በእነዛ ሰዎች ዘንድ መጥፎ ሰዎች ናችሁ። የህይወት አሰራር እንዲ ነው። ለእራሳችሁ ደግ ከሆናችሁ ለሰዎች ክፉ ሆኖ የመታየት እድላችሁ ይሰፋል፣ እራሳችሁን እሺ ካላችሁ ሰዎችን እምቢ ለማለት ትገደዳላችሁ። ምናልባትም ቅድሚያ ለእራስ መኖራችሁ እንደ ክፋት ሊታይባችሁ ይችላል። እራስህን መውደድ ሌሎችንም ለመውደድ መሰረት መሆኑን ብዙዎች ባይረዷችሁም ማድረጋችሁን ቀጥሉ። አዎ! ጀግናዬ..! መጥፎ ስለመባልህ ሳይሆን የእውነት መጥፎ ሰው ስለመሆንህ አስብ፣ በክፉ ከመፈረጅህ በላይ የምርም ክፉ መሆንህ ያስጨንቅህ። አንዴ ባለፈ ታሪክ ከሚሰጥህ ስም በላይ አሁን ያለህበት ቦታና ደረጃ ይበልጥ ዋጋ አለው። ታሪክህን ባትወደው የምታስተካክለው ወደኋላ ተመልሰህ ሳይሆን ዛሬህ ላይ በመስራት ነው። የሰው ልጅ ሁሌም ደግ ላይሆን ይችላል፣ እንዲሁ ሁሌም ክፉ ላይሆን ይችላል። ሰው ይሻሻላል፣ ሰው ይቀየራል፣ ሰው በአካል፣ በአዕምሮ ይበስላል ያድጋል። ባለፈው ታሪክህ ውስጥ በሰዎች ህይወት ላይ መጥፎ ጠባሳን ጥለህ ያለፍክ እንደሆነ በጊዜ እርማትን ውሰድ፣ ድጋሜም ከመፈፀም ተቆጠብ። ብልህ ከስህተቱ ይማራል፣ ሞኝ ግን ስህተቱ ደጋግሞ እንዲያስተምረው ይፈቅዳል። በሰው ዘንድ በበዳይነት መነሳት ለምንም አይነት አዎንታዊ ውጤት አያበቃም። በቻልከው ልክ ህይወትህ ውስጥ ለገባ ሰው ሁሉ መልካም ሁን፣ ከሚሰጥህ መጥፎ ስም በላይ ለእራስህ ማንነት ብለህ ጎጂ ባህሪያትህን አስወግድ። ከእያንዳንዱ የዛሬ ተግባርህ በሚገባ ተማር፣ ስምህንም በሚገባ ጠብቅ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 34015Loading...
11
✅ ወደኋላ አትመለሱ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/28qA3lADFBw
2 1714Loading...
12
✅ ወደኋላ አትመለሱ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/28qA3lADFBw?si=g-EhQOH3AS-xGE_9
400Loading...
13
ማንንም አትጠይቁ! ፨፨፨፨////////፨፨፨፨ ውስጣችሁ የሚነግራችሁ አንድ ነገር አለ። እርሱንም ማድረግ የምትችሉት እናንተ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ። ስለዚህ ማድረግ ካለባችሁ ማንንም ሳታማክሩ ዝም ብላችሁ አድርጉት። ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ማማከር ይቅርባችሁ። የብዙ ሰዎችን ስህተት አትድገሙ። ጥቂት የማይባል ሰው ምን ያደርጋል? በግሉ የመጣለትን ሀሳብ በሙሉ ለሚመለከተውም ለማይመለከተውም በማጋራት ጊዜውንና ኢነርጂውን ያባክናል። አንድ ስራ መጀመር አስባችሁ እናንተ ያሰባችሁት ስራ እንደማይዋጥለት ከምታውቁት ሰው ጋር ለምን ትወያያላችሁ? እቅዳችሁ የሶሻል ሚድያ ስራ መጀመር ሆኖ ስለሶሻል ሚድያ ምንም እውቀት የሌለው፣ ቪድዮ ከማየት በስተቀር እንዴት እንደሚሰራ ምንም እውቀቱ የሌለው ሰው በምን ሚዛን የእናንትን የContent Creation ሀሳብ እንዲደግፍ ትጠብቃላችሁ? ወደዳችቹም ጠላችሁም ዋናው ጉዳይ ማለቅ ያለበት እራሳችሁ ጋር ነው። ምንም ነገር ለመጀመር ስታስቡ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ለማስገባት አትቸኩሉ። ብዙ ሰው ባማከራችሁ ቁጥር ብዙ ሀሳብ ታገኛላችሁ የበዛው ሀሳብ ደግሞ ግራአጋብቶ የእናንተን መነሻ ሀሳብ ዋጋቢስ የማድረግ ከፍተኛ እድል አለው። አዎ! ማንንም አትጠይቁ፣ ከአቅማችሁ በላይ ካልሆነ በቀር ማንንም አታማክሩ። የውሳኔ ሰው ሁኑ፣ ሃላፊነት ውሰዱ፣ ከከሰራችሁም ክሰሩ ትማሩበታላችሁ፣ ከተበላሸም ይበላሽ ድጋሜ በተሻለ መንገድ ትሰሩታላችሁ፣ ከወደቃችሁም ውደቁ ዳግም መነሳት እንደሚቻል ውስጣችሁን አሳምኑት። የዓለም እውነታ ይሔ ነው፣ በጣም ብዙ ሰው በሀሳባችሁ አይስማማም፣ ከምትጠይቁት አብዛኛው ሰው ሀሳባችሁ አይዋጥለትም፣ ሊደግፋችሁም ፍቃደኛ አይሆንም። ስለዚህ ይሔንን እውነታ ተረድታችሁ እቅዳችሁን ማባከንና መና ማስቀረት ካልፈለጋችሁ በስተቀር ድጋሜ እቅዳችሁን ለማንም አታማክሩም፣ ለማንም አትናገሩም። ከማንም በሚመጣ ሀሳብ ለመሞላትም ሆነ ማንም የሚነግራችሁን ሀሳብ ተቀብላችሁ ለመፈፀም ጊዜ የላችሁም። ያላችሁ ጊዜ በጣም ጥቂት ነው። ጊዜያችሁን የእራሳችሁን ሀሳብ ወደ ምድር በማምጣት ተጠቀሙት። ማንንም የማባበል ግዴታ የለባችሁም፣ ማንም እንዲደግፋችሁ የማስገደዱም መብት የላችሁም። ውሳኔው በእጃችሁ ነው። የሚደግፋችሁን ሰው እስክታገኙ ሰዎችን መጠየቃችሁን መቀጠል ወይም በሀሳባችሁ ተማምናችሁ ወደ ተግባር መግባት። አዎ! ጀግናዬ..! ማንንም ጣልቃ አታስገባ፣ እንዴትም ውጫዊ ግፊትና ጫና ሀሳብህን እንዲያስቀይርህ አትፍቀድ። ሀሳብህን እንደ ሀሳብ በልብህ ያዘው፣ እቅድ አውጣለት፣ ከእራስህ ጋር ተማከርበት፣ አዋጭነትቱን በሚገባ አጥና፣ በደምብ እወቀው፣ ግልፅም አድርገው። ላንተ ግልፅ እስከሆነ፣ አንተ እስከተረዳሀውና አንተ እስካመንክበት ድረስ የማንም ድጋፍ እንደማያስፈልግህ እወቅ። የማያዳግም ቆራጥ ውሳኔ መወሰን ከፈለክ ብዙ ሰው ማማከር አቁም፣ ሀሳብህን ወደ ተግባር መቀየር ከፈለክ ለማንም ማብራራት ሳይኖርብህ በልበሙሉነት አድርገው። የምታማክረው ሰው ብትወድቅ አብሮህ አይወድቅም፣ ሀሳብ የምትጠይቀው ሰው ብትከስር አብሮህ አይከስርም፣ የሚያስፈራራህ ሰው ሃሳብህ መና ቢቀር ካንተ ጋር አይጎዳም። በስተመጨረሻ ከሀሳብህም ሆነ ከውጤትህ ጋር የምትቀረው አንተ ብቻ ነው። በእርግጥ ሰውን ማማከር ትልቅ ጥቅም አለው፣ ነገር ግን የምታማክረው ሰው በሀሳብህ እንደሚስማማና የተሻለ አማራጮችን እንደሚጠቁምህ እርግጠኛ ካልሆንክ ባታማክረው ብታተርፍ እንጂ አትጎዳም። ውስጥህን አዳምጥ፣ እርምጃ ውሰድ፣ ማድረግ ያለብህን በጊዜ አድርግ፣ መውሰድ ያለብህን ትምህርትም በተግባር ውሰድ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 62121Loading...
14
Media files
2 1312Loading...
15
የግል ትቺትህን አስወግድ! ፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨ በራስመተማመመን የሁሉ ሰው ምኞት ነው፣ በእራሱ የሚተማመነው ግን እራሱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ልበአዋቂ ነው። ሰውነት በእራሱ ክፍተት አለበት፣ ማናችንም የእራሳችን ድክመት አለብን። ህይወት ደግሞ ለደካሞች የተለየ መመዘኛ አታስቀምጥም። ጠንካራ ሆንክ ደካማ፣ ልፍስፍስ ሆንክ በእራሱ የሚተማመን፣ ባለራዕይ ሆንክ መደበኛ የምትዳኘው በአንድ ምድራው ህግ ነው። ህጉም ይሔ ነው፦ "በራስህ ካልተማመንክ በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች አገልጋይ ትሆናለህ።" ህጉ ግልፅና አጭር ነው። በራሳቸው የሚተማመኑ ብርቱ ሰዎች ሁሌም ገዢዎች ናቸው። በራሳቸው የማይተማመኑ ልፍስፍስ ሰዎች ሁሌም ተገዢዎች ናቸው። ተፈጥሮ ጊዜ ወስደው፣ አስበው፣ አውጥተው አውርደው፣ ተጨንቀው እራሳቸው ላይ ለሚሰሩ ሰዎች ታዳላለች። ሁሌም የምትሸልመው እነርሱን ነው፣ ሁሌም ሰው ፊት የምታቆመው፣ ለስኬት የምታበቃው፣ ዋጋቸውን የምትጨምረው፣ ህይወታቸውን በፍቅርና በደስታ የምትሞላው እነዚህን ሰዎች ነው። እራሳቸው ላይ እስከሰሩ ድረስ የተለየ ቦታን ታዘጋጅላቸዋለች፣ እራሳቸውን እስከወደዱ ድረስ በሌሎችም ተወዳጅ ታደርጋቸዋለች። አዎ! ጀግናዬ..! የግል ትቺችህን አስወግድ፣ ለእራስህ የምትሰጠውን ቦታ አስተካክል፣ ለገዛ ስሜቶችህ መጨነቅ ጀምር። ከሰዎች አድናቆትና ጭብጨባ በላይ በራስመተማመንህን የሚገነባው ለእራስህ የምትሰጠው ቦታ ነው። ብዙዎች ሰው ፊት እራሳቸውን ስላዋረዱ ተፈላጊ የሚሆኑ ይመስላቸዋል፣ ብዙዎች በትነሹም በትልቁም እራሳቸውን ስለወቀሱ ህይወታቸው የሚቀየር ይመስላቸዋል፣ ጥቂት የማይባሉትም በራስመተማመንን ሰዎች የሚሰጧቸው ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ የተለየ ነው። ክብር፣ ተፈላጊነት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ በራስመተማመንና ስኬት ሁሉም የሚገኙት እኛው እራሳችን ለእራሳችን ከምንሰጠው ቦታ ነው። መቼም እራስህን እየተቸህ ተፅዕኖ ፈጣሪ ልትሆን አትችልም፣ እንዴትም የራስ ግንዛቤህን ሳታሻሽል የበራስመተማመን ደረጃ ላይ ልትገኝ አትችልም። አንድ ነገር በጀመርክ ቁጥር "ይሔ ነገር ለእኔ አይሆንም፣ እኔ አልችለው፣ አቅሙ የለኝም" እያልክ ጥረትህን ብታሳንስና ዋጋ ባትሰጠው በራስመተማመንህን የምትሸረሽረው እራስህ ነው። እራስህን በሚገባ ታውቃለህ፣ አቅምህ እንዴት እንደሚገነባ፣ በራስመተማመንህን እንዴት እንዴት እንደምታሻሽል ታውቃለህ። አዎ! ብክነትህን ቀንስ፣ ህይወት የምትኖረው የምር ነው። ማንንም ለማስደሰትና በማንም ዘንድ ቦታ ለማግኘት የምትኖረው ህይወት የልህም። ቀልድና ጫወታውንም ቢሆን እያንዳንዱን የህይወት ክፍልህን በቁብነገር መመልከት ጀምር። "እኔ ጀግና ነኝ፣ እኔ እችላለሁ፣ እኔ ጠንካራ ነኝ፣ እኔ ሀብታም ነኝ" እያልክ ብቻ የምትገነባው በራስመተማመን የለም። በባዶ ጩሀት የሚሻሻል ህይወት የለም። ምንም ለመገንባት ተግባር ያስፈልጋል፣ ምንም ለመቀየር ቆራጥነት የግድ ነው። ለራስህ እንደምትነግረው አሉታዊ ነገር አሳስሮ የሚያስቀምጥህ መጥፎ ሀይል አይኖርም። እራስህን መግዛት አንድም ስሜትን መቆጣጠር ሌላም አሉታዊውን የግል ንግግር ማስወገድ ነው። ሰዎች የሚነግሩህ አይደለም የገዛ ማንነትህ የሚነግርህ ጎጂና አሉታዊ ንግግር ካለ በጊዜ አስወግደው። እራስህን የምትሰማው እስከተቀመህና እስከገነባህ ድረስ ብቻ እንደሆነ እወቅ። የግል ትቺትህን አስወግድ፣ እራስህን ገስፅ፣ በሂደት ውስጣዊ አቅምህን ገንባ፣ አዎንታዊ ሀሳቦች ላይ አተኩር፣ ከሰው በፊት ለእራስህ መድረሱን ቻልበት፣ በራስመተማመንህንም ከሀሳብ ጀምሮ በተግባር ወደማነፅ ግባ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 47118Loading...
16
✅ ምቾታችሁን ጠብቁ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/Hh2YF85BmrQ?si=tcK0Z5H7xHHSFiJ9
2 4605Loading...
17
እራስህን አታዘግየው! ፨፨፨፨//////////፨፨፨፨ የውስጥ ፍቃድን የሚፈልጉ ፈታኝ የህይወት ውሳኔዎች ይኖሩሃል፤ እነርሱን ለማዳመጥ፣ የእራስህን የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ ረጅም የተባለ ጊዜ ትወስዳለህ። ጊዜህ ሲሔድ፣ ለውሳኔ ስትቸገር፣ እውነተኛውን አቅምህን ስታሳንስ፣ ግራ ሲገባህ፣ ብርታት ሲያጥርህ፣ ጥንካሬ ሲጎድልህ ትመለከታለህ። ወደኋላ ለመቅረትህ መወቀስ ካለብህ ቀዳሚው ተወቃሽ አንተ ትሆናለህ፤ እራስህን ለማዘግየትህ፣ በሚገባህ ስፍራ ላለመገኘትህ፣ የተሻለ የህይወት ደረጃ ላይ ላለመድረስህ ተጠያቂ የምትሆነው አንተ ነህ። ለእራስህ ህይወት ሃላፊነት መውሰድህ የእድገትህ መሰረት ነው። በዘፈቀደ የምትኖረው፣ እግረመንገድህን የምታሳካው ትልቅ ህልም የለህም። ህልምህ በአግባብ፣ በስረዓት፣ እራስህን ሰውተህለት፣ ጊዜ ሰተሀው፣ ትኩረት አድርገህበት የምትፈፅመው የህይወትህ ግብ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን አታዘግየው! የተጠና አካሔድ፣ ሚዛኑን የጠበቀ ጉዞ፣ ሁሉንም የህይወት ዘርፍ ያማከል ለውጥና እድገት ተገቢ ሆኖ በሰበብ አስባቡ፣ ምክንያት በመደርደር ተገቢ ከሚባለው የህይወት ደረጃ በታች መኖር ግን አስፈላጊ አይደለም። መኖር ዛሬን ነው፤ የዛሬ ኑሮህ ግን መጪውን ጊዜ የሚያስተካክልና የሚያሳምር መሆን ይጠበቅበታል። ቀላል መንገድ ብዙ አያለፋህም፤ ብዙ አያደክምህም፣ ብዙ ዋጋም አያስከፍልህም፣ ዛሬህንም በቀላሉ እንድትኖር ሊያደርግህ ይችላል። ነገር ግን መጪዎቹ ጊዜያት በዚው ልክ የሚቀጥሉና የሚከሰቱ አይደሉም። ጠንከር ካላልክ ማንም አይፈልግህም፤ ተፈትነህ ካልወጣህ በእራስመተማመን አይኖርህም፤ ከባዱን ካልተጋፈጥክ ትክክለኛውን አቅምህን አታውቀውም። የሚሰራህ የመረጥከው መንገድ እንጂ የምትደርስበት መዳረሻህ አይደለም። አዎ! የተህይወትህ መሰረት በእጅህ ላይ ነው፤ አዋጩን አቅጣጫ የምትመርጠው አንተ ነህ፤ አይነተኛውን መሪህን የምትይዘው አንተ ነህ። ታላላቆች የእድገታቸው እንቅፋት የገዛ ሃሳባቸው ከሆነ እንዴት ሊያስወግዱት እንደሚችሉ ያውቃሉ፤ ወደኋላ የሚጎትቷቸው በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ከሆኑ እንዴት ከእነርሱ መለየት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። እጅግ ብዙ ሳታስበው የሚያደናቅፉህ ከባድ እንቅፋቶች ባሉበት ለእረስህ ሌላ ሸክምና እንቅፋት አትሁን። መሆን የምትችለውን ላለመሆንህ፣ ያሰብክበት ላለመድረስህ ዋነኛውን ተጠያቂ እራስህን አድርግ። ለመዘግየትህ እራስህ ሃላፊነት ውሰድ። የጉዞ አቅጣጫህን ትክክለኛነት ሳታረጋግጥ ብትፈጥንም እንኳን ከግብህ አትደርስምና መዘግየትህ ላይ እርምጃ ከመውሰድህ በተጨማሪ የጉዞ አቅጣጫህን አስተካክል፤ የእራስህ ብርታትና ጥንካሬ ሆነህም መንገድህን ቀጥል። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 81512Loading...
18
Media files
2 4161Loading...
19
ስማቸው፣ በማስተዋል ተረዳቸው! ፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨ በማይሆን አኳሃን፣ በማይሆን ስፍራ፣ ከማይሆን ሰው ጋር መገኘትን የፈለከው አንተ ነህ፤ የማይጠቅምህን ማድረግ፣ የማያተርፍህን ልማድ ማከናወን የመረጥከው አንተ ነህ። ከማትወደውና ከማይሆንህ ልማድና ድርጊትም የምትላቀቀው አንተ ፈቅደህ ነው። የሚያዝንልህ ሰው ሲያዝንልህ ይግባህ፤ ሲያስብልህ ለማስተዋል ሞክር፤ በተቻለህ መጠን ተረዳው፤ በገባህ ልክ ሃሳቡን በአዎንታዊነት ተቀበለው። ሲሆን ሲሆን ለእራስህ መወገን፣ የሚጠቅምህን መምረጥ፣ እራስህንም ማስቀደም ሲኖርብህ፣ በሚመጥንህ ስፍራ መገኘት ሲገባህ ምርጫውን ብትጥል፣ ስፍራህን ባታውቅ ቢነገርህና ብትገሰፅ ምንም ክፋት የለውም። አዎ! ለእራስህ ተብሎ የሚነገርህን ምክረ ሃሳብ አመዛዝነህ ተቀበል። ወዳጄና አሳቢዬ ነው የምትለውን ሰው ካለመስማት መስማቱ የተሻለ እንደ ሆነ አስተውል። ጥሩና የሚገባህ ደረጃ ላይ እንዳልሆንክ ታውቃለህ፤ የማይሆንህንና የማይጠቅምህን ነገር እያደረክ እንደሆነ ካንተ በላይ ማንም ሊያውቀው አይችልም፤ በጊዜያዊ ስሜት ብዙ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እነደገባህ በደምብ ታውቃለህ። ነገር ግን ስላወክ ብቻ የማይሆንህን ተግባር ከመፈፀም አለተቆጠብክም፤ መገኘት የማይገባህ ስፍራ መገኘቱን አላቆምክም፤ ጎጂና አልባሌ ልማዶችህን መግታት አልቻልክም። "ለእራሴ እኔ አውቃለሁ፤ ማንም በውሳኔዬ ጣልቃ እንዳይገባ" በሚለው ጭፍን እሳቤ መመራትህ አንድ ቀን ዋጋ እንደሚያስከፍልህ ይገባሃል። አዎ! ያንተ ጉዳይ ከማወቅ፣ ከመግባትና ከመረዳት በላይ ሲሆን እገዛ እንደሚያስፈልግህ እወቅ፤ የሃሳብም ሆነ የተግባር ድጋፍ እንደሚያሻህ ተረዳ። ለእራስህ ማሰብና ማዘን ካልቻልክ ቢያንስ እንዲታሰብልህና እንዲታዘንልህ እድሉን ፍጠር። ወዳጅ የምትላቸው ቅን አሳቢዎችህን መስማት ጀምር፤ ሃዘኔታቸው ይግባህ፤ ስስታቸውን ተረዳ። የሰውን ምክር ሰምትህ እንደምትስት ሁሉ መንገድ እንደምትይዝም አስታውስ። በእራስህ ከተማመንክና በትክክለኛው መንገድ ላይ እያለህ የሰዎች ሃሳብ አሰናካይና የማይጠቅም መስሎ ከታየህ አለመቀበልህ ልክ ሊሆን ይችላል፤ የማይሆን ነገር እየፈፀምክ እንደሆነ እያወክ ሃሳብን መናቅና መግፋት ግን መቼም ትክክል ሊያደርግህ አይችልም። አዎ! ጀግናዬ..! ጆሮ ስጣቸው፣ ስማቸው፣ በማስተዋል ተረዳቸው፤ በበጎነት ተቀበላቸው። ማወቅህ ማድረግ የማይገባህን ከማድረግ አላገደህም፤ ለስሜትህ መገዛትህን መረዳትህ የሚጠቅምህን ተግባር ለመፈፀም አላበቃህም፤ ከስህተቶችህ አለመማርህን ማወቅህ ድጋሜ እንዳትሳሳት አላደረገህም። በተደጋገመ ድክመትህ የበለጠ ዋጋ ከመክፈልህ በፊት ትክክለኛ መንገድ ጠቋሚህን መስማት ጀምር፤ ለወዳጅህ ምክር ጆሮ ስጥ፤ ከመጥፋትህ በፊት ከሚያስብልህ ቅርብ ሰው ድጋፍ ጠይቅ። የእርዳታ መንገዶችህን ክፈት፤ ሃሳቦችን መስማት እንደሚጠቅምህ፣ ጠቃሚውንም መተግበር ብለሃት እንደሆነ ተረዳ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 88115Loading...
20
✅ እውነቱን አውጡ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/70ZUzs2eDFY?si=Z_YARWsaVoNwWvQ0
2 5754Loading...
21
ስንፍናህን ቅበረው! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ ታሪክህ አኩሪም ይሁን አሳፋሪ እንደ ማንኛውም ሰው ታሪክ አለህ፣ ትናንት የነበርክበት ስፍራ አለ። ስንፍና፣ ግዴለሽነት፣ ዋጋቢስነትና ቀሎ መገኘትም የቀደመ ታሪክህ ክፍሎች ናቸው። ስንፍናን ይዘህ እንደማትከበር ታውቃለህ፣ በግዴለሽነት ህይወትህን እንደማታሻሽል ታውቃለህ፣ ዋጋህን አሳንሰህና ቀለህ በመገኘት ዓለምን ልታሸንፍ እንደማትችል ታውቃለህ። ስንፍናህ ከምን አስቀርቶሃል? ግዴለሽነትህ ምን አሳጥቶሃል? በሰው ዘንድ ቦታ ለማግኘት፣ በሰዎች ለመወደድና ለመፈለግ ዋጋቢስና ቀላል ሆኖ መገኘት ምን አተረፈልህ? ማንም ዋጋው የገባው ሰው ሰንፍና መገለጫው እንዲሆን አይፈቅድም፣ ማንም ወደፊቱን መገንባት የሚፈልግ ሰው በግዴለሽነት መንገድ አይጓዝም። "የህይወት አሰራር ገብቶኛል፣ የዘራውትን እንደማጭድ አውቃለሁ፣ ቦታዬን የምወስነው እራሴው ነኝ" ብለህ የምታምን ከሆነ ማንን አስቀድመህ ማጥቃት እንዳለብህ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ወደኋላ ከመቅረትህ በስተጀርባ፣ ሰበበኛና አማራሪ የመሆንህ ቀንደኛ ምክንያት ምን እንደሆነ የተሸሸገብህ አይደለም። አዎ! ጀግናዬ..! ስንፍናህን ቅበረው! ከግዴለሽነት ተላቀቅ፣ በጥቃቅን ሃሳቦች መታወክህን አቁም፣ ከአጉል የወረዱ ልማዶች ተፋታ። ህይወትህ በእጅህ ነው። የምትወደውን ህይወት ለመኖር የማትወደውን ነገር እንደምትወደው አድርገህ የመስራት ግዴታ አለብህ። አንዳንድ ስሜትአልባ ተግባሮች ይኖሩ ይሆናል፣ አንዳንድ በጊዜው ትርጉም የማይሰጡ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆናል ነገር ግን የግድ መሆን ካለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ሁሌም እድገት ህመም አለው፣ ለውጥ ስቃይ ነው፣ ህልምን የመኖሩ መንገድ በከፋው ውጣውረድ የተሞላ ነው። ነገር ግን ስቃዩም ሆነ ህመሙ የጉዞው አንድ አካል ናቸውና የግድ መታለፍ ይኖርባቸዋል። ስላንተ ህመምና ስቃይ ማን ግድ የሚሰጠው ይመስልሃል? ስላንተ ያለእንቅልፍ ማደር፣ ስላንተ ቀንከሌሊት መትጋት፣ ስላንተ ደጋግሞ ወድቆ መነሳት ማን የሚጨነቅ ይመስልሃል? እራስህን እያሳነስክ፣ ዋጋህን እያወረድክ ስነፍ ብትሆን ለእራስህ ነው፣ በራስመተማመንህን በመጨመር ብርቱና ጠንካራ ብትሆንም ለእራስህ ነው። ይሔንን አስታውስ "ያንተ ስሜት የማንም ጉዳይ አይደለም።" ደስታህ የእራስህ ሀላፊነት ነው፣ ውስጣዊ ሰላምህ፣ ተነሳሽነትህ፣ የመንፈስ ጥንካሬህ፣ ልባዊ ንቃትህና መረጋጋትህ በሙሉ የእራስህ ጉዳይ ነው። አዎ! ስንፍናህንና ጥንካሬህን የሚለየውም ለእያንዳንዱ ስሜትህ የምትሰጠው ምላሽና እነርሱን የምትረዳበት መንገድ ነው። ሰነፎች ነገሮችን በተለየ መንግድ የመመልከት አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ የላቸውም። ሰነፎች አሸናፊ መሆን አይችሉም፣ አሸናፊዎችም ሰነፎች አይደሉም። ሽንፈትና ድልህን የሚወስንልህ ወደኋላ ያስቀሩህ ነገሮች ላይ የምትወስደው እርምጃህ ነው። ስንፍናህን አስቀድመህ ካልቀበርከው ያለምንም ቅድመሁኔታ እርሱ እንደሚቀብርህ እወቅ። ግዴለሽንተህ ላይ እርምጃ ካልወሰድክ እያደር እርሱ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድብህ ተረዳ። መዳረሻ ኖሮህ ሰነፍ መሆን አትችልም፣ ህልም ኖሮህ እንዴትም ግዴለሽ ልትሆን አትችልም። አንዳንድ ቀኖች በተለየ መንገድ ጫናዎችን ያበዙብሃል፣ አንዳንድ ጊዜያት በተለየ መንገድ ተነሳሽንትህን ይፈትናሉ። ጠዋት ስትነሳ ሁለት ምርጫ ይኖርሃል። አንድ ስንፍናህን አዳምጠህ የሞላሀውን አላርም ማጥፋት፣ ሁለት ስንፍናህን ቀብረህ በሞላሀው ሰዓት ተነስተህ ማድረግ ያለብህን ነገር ማድረግ። ከመነሳት ውጪ ምርጫ ባይኖርህ ስንፍናህን የምትሰማ ይመስልሃልን? በጠዋት ተነስቶ ስራህን ከመስራት ውጪ ሌላ ምርጫ ባይኖርህ ግዴለሽ የምትሆን ይመስልሃልን? በፍፁም። ስንፍናህን አርቆ ከመቅበር በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለህ እመን፣ የግዴለሽነትህ ተጠቂ ከመሆንም እራስስሀን አድን። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 22924Loading...
22
Media files
2 4500Loading...
23
ከተገደበው ወደ ተለቀቀው! ፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨ ከዚህ በታች የሚገኘውን ንጽጽር በማንበብና ተግባራዊ በማድረግ ከተገደበ ንግግር፣ አመለካከትና ሕይወት ለስኬት ወደተለቀቀ ሕይወት የመሸጋገርን ጎዳና ጀምር፡፡ የተገደበው፡- “ይህንን ነገር ለማድረግ ብቃቱ ስለሌለኝ ማድረገ አልችልም።” የተለቀቀው፡- “አሁን ብቃቱ የለኝም ሆኖም ብቃቱን በማዳበር ማድረግ እችላለሁ።” የተገደበው፡- “ይህንን ነገር ለማድረግ ስሞክር ካልተሳካ ችግር ውስጥ እገባለሁ።” የተለቀቀው፡- “አሁን ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ብዙ ወድቀውና ተነስተው ነው እዚህ የደረሱት፡፡ እኔም እንደዚያ አደርጋለሁ።” የተገደበው፡- “ይህንን እና ያንን እየሞከርኩ ባለመሳካቱ ክብሬን ከማስነካ ራሴን ጠብቄ ብኖር ይሻለኛ።” የተለቀቀው፡- “አዲሱን የእድገት ጎዳና ካልሞከርኩት ባለሁበት መቅረት ይከተላል፡፡ ባሉበት በመቅረት ውስጥ ደግሞ ምንም ክብር የለም።” የተገደበው፡- “እድለኛ ብሆን ኖሮ አሁን የት በደረስኩ ነበር።” የተለቀቀው፡- “እድለኛ የምሆነው ጠንክሬ ስሰራና ካለማቋረጥ ስሞክር ነው።” የተገደበው፡- “ገንዘብ ቢኖረኝ ኖሮ ብዙ የፈጠራ ስራዎችን እሰራ ነበር።” የተለቀቀው፡- “ገንዘብ የፈጠራ ስራን አያመጣም፣ የፈጠራ ስራን ብጀምር ግን ፈጠራዬ ገንዘብን ያመጣ።” የተገደበው፡- “ሰዎች ይህንና ያንን ባያደርጉብኝ ኖሮ ብዙ እራመድ ነበር።” የተለቀቀው፡- “ለሆነብኝ ነገር ሁሉ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ ከሰዎችና ከሁኔታዎች አጉል ተጽእኖ በላይ መኖር እችላለሁ።” /ከእይታ ገፆች/ ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 90417Loading...
24
✅ በቀላሉ አትበገሩ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/S6bKO-tIYLA?si=K9S9nkRt22xTWGmG
2 4881Loading...
25
👩‍👧‍👦እናትነት ፀጋ ነው፤ 👨‍👩‍👧‍👦እናትነት ክብር ነው፤ 👩‍👧‍👦እናትነት መመረጥ ነው። ለእናትነት ክብር የበቃችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ። ካደረጉልን ነገር አንፃር እጅጉን ያነሰና ኢምንት ቢሆንም ከሌላው ቀን በተለየ ዛሬ ለሁሉም እናቶች ያለንን ክብር፣ ፍቅርና መልካም ምኞት በተለየ ሁኔታ እንግለፅላቸው። 👩‍👧‍👦🌺🌹 መልካም የእናቶች ቀን! 🌹🌺👨‍👩‍👧‍👦 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
2 8908Loading...
26
ፍቅርህ ማረከኝ! ፨፨፨///////፨፨፨ ከራስ ጋር ንግግር፦ "በእርግጥ ሰው ነኝና ኑሮዬ እንደ ሰው ነው፣ ሀሳቤ እንደ ሰው ነው፣ ግብሬም እንዲሁ እንደ ሰው ነው። ከማንም የተለየው አይመስለኝም፣ ከማንም የበለጥኩ ከማንም ያነስኩ አይመስለኝም። ማነስ ሲባል አንድም በመንፈሳዊ ልኬት ዝቅ ማለት፣ በትህትና መውረድ፣ ለአገልግሎት መፋጠን ነው። ሌላም ማነስ በስጋዊው እይታ ከሰው ሁሉ የበታች መሆን፣ በሰው ተጎጂ፣ በሰው ተጠቂ መሆንና ከሰው ክብር አንሶ መገኘት ነው። ምናልባት በመንፈሳዊው ልኬት የማንሰው በጥቂቱም ቢሆን ክብርን ከአምላኬ ለማግኘት፣ ፀጋው እንዲበዛልኝና በዝቅታ ውስጥ ለከፍታ እንድበቃ ነው። በስጋዊው እይታ ግን ዝቅ የምልበትና አንሼ የምገኝበት ምክንያት አይኖርም። ከማንም ብወረድ በፍቃዴ እንጂ ማንም ዝቅ አድርጎኝና አሳንሶኝ አይደለም። በራስመተማመኔን የምገነባው የበታችነቴን እያስተጋባው፣ በበላይነቴም እየተኩራራው አይደለም። ውስጤን አውቀዋለው ከፍታዬም ዝቅታዬም የአምላኬ ፍቅር ነው። በትህትና ዝቅ ስል እግዚአብሔር በሞገስ ከፍ ያደርገኛል፣ ክብሩን ልመሰክር ስራውንም ልናገር ከፍ ስልም በፀጋው ሙሉና ብርቱ ያደርገኛል። አዎ! ፍቅርህ ማረከኝ፣ ግብርህ ገዛኝ፣ አንተነትህ ወዳንተ ሳበኝ። እፀልያለሁ፣ አንድም በምስጋና ሌላም በተማፅኖ በልመና። ያደረክልኝ ብዙ አለ፣ እኔ ፈልጌው አንተ ግን ስላልመረጥክልኝ ያላደረክልኝ ብዙ አለ፣ ወደፊትም እንዲሁ የሚገባኝን እንደምታደርግልኝ አምናለሁና ከልብ አመሰግንሃለሁ። ልመናዬም ጥያቄ ነው። "እመን፣ ጠይቅ፣ ተቀበል" የሚለውን አስተምህሮ ከልቤ ተቀብዬዋለሁና አምናለሁ፣ እጠይቃለሁ፣ እቀበላለሁ። እማፀንሃለሁ፣ እንደ ልጅነቴ ከስርህ ወድቄ እጠይቅሃለሁ። አንዴም አሳፍረሀኝ አታውቅም፣ አንዴም ጠይቄህ ያጣውት ነገር የለም። እምቢታህም ቢሆን ምላሼ ነው፣ ብዙ ብታስጠብቀኝም በጥበቃ ውስጥ የምትሰጠኝ እንደሚበልጥ አውቃለሁ። እኔን መጠየቅ አይደክመኝም፣ አንተም መስጥት አይሰለችህም፣ እኔ መነጫነጭ አያሳፍረኝም አንተም እኔን መቻል አልከበደህም። ካንተ በቀር ማን ይረዳኛል? ካንተ በቀር ማን ሀሳብ ጭንቀቴን ያቀልልኛል? ካንተ ውጪ ማነው መሸሸጊያዬ፣ ካንተ ሌላ ማነው ደጋፊዬ? ማነው ጠበቂዬ? ማንም። በፍቅርህ ገዝተሀኛልና ዘወትር ከእግርህ በታች፣ ሁሌም በእቅፍህ እንድኖር አበርታኝ፣ ከአይንህም እንዳልርቅ አድርገኝ።" አዎ! ጀግናዬ..! ከባዶነት የሚያወጣህ የአምላክ ፍቅር ነው፣ ከዓለም ሸክም የሚያሳርፍህ የልብህ ቀናነት ነው፣ ንፁውን የህይወት እስትንፋስ እንድትተነፍስ የሚያደርግህ ትህትናህ፣ ለፍቅር መገዛትህ፣ በእግዚአብሔር እቅፍ መመላለስህ ነው። ማንም ሰው በትንሽ ነገር ልቡ ይደነድናል፣ በትንሽ ነገር ያምፃል፣ ከሰው በላይ ከአምላኩ ጋር ግብግብ መግባት ይዳዳዋል፣ በትዕቢት ይሞላል፣ ከተደረከለት በላይ ባልተደረገለት እይታው ይጋረዳል፣ የፈጣሪውን ፍቅር ለመመልከት ጊዜ ያጣል። የትዕቢት መጨረሻዋም ሞት ነውና በስጋው ባይሞት እንኳን ነፍሱን ይገድላታል፣ ልቡን ያቆስለዋል፣ ውስጡን ሰላም ይነሳዋል። ከሰማዩ አባትህ ጋር ግብ ግብ ውስጥ አትግባ፣ ከነፍስህ ጌታ፣ ከአንተነትህ አስገኚ ጋር አትቀያየም። "እኔ ምስኪን ባሪያህ ነኝና አንተ ያልከው ብቻ ይሁንልኝ" የማለትን ድፍረት ተላበስ። ውስጥህን በትህትና አንፀው፣ ልብህን ለስለስ አድርገው፣ ቀላሉን በማክበድ፣ ግልፁን በማወሳሰብ አትጠመድ። የትም ሄድክ የት ፈሪሃ እግዚአብሔርን በልብህ አንግስ፣ ልብህን በማደንደን የድፍረት ሀጢያት ውስጥ አትግባ። ብትስትም ለይቅርታ ፍጠን፣ ብትወድቅም ፈጣሪህ እንዲያነሳህ ከልብህ ዝቅ ብለህ ተማፀን። ከፍቅሩ ተቋደስ፣ ከበረከቱም ተካፈል። ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 97122Loading...
27
አንድ ሰው! ፨፨/////፨፨ ምንም የሰው ብዛት፣ የጓደኛ ጋጋታ፣ የዘመድ ብዛት አያስፈልጋችሁም። የሚያስፈልጋችሁ አንዱ ሰው ብቻ ነው። ይህ ሰው ነገሮች ቢበላሹም ከጎናችሁ ይቆማል፣ ብትወድቁም ያነሳችኋል፣ ብትሳሳቱም ያርማችኋል፣ በዝቅታችሁ ጊዜ ሁሉ አብሯችሁ ዝቅ ይላል፣ ስትነሱም አብሯችሁ አለ። የዚህን ሰው መኖር ስታስቡ ደስ ይላችኋል፣ እርሱ ስለተሰጣችሁ ብቻ እግዚአብሔርን ታመሰግናላችሁ። እርሱ አንድ ሰው ነው ለእናንተ ግን አለማችሁ ነው፣ እርሱ ለሌላው ሰው እንደ ማንኛውም ሰው ነው ለእናንተ ግን የሰው ልካችሁ ነው። ከልባችሁ ታምኑታላችሁ፣ ከልብ ትኮሩበታላችሁ፣ ካደረገላችሁ መልካም ነገር አንፃር ምንም ቢሳሳት ትችሉታላችሁ። ይሔም ሰው የቅርብ ጓደኛችሁ ሊሆን ይችላል፣ የፍቅር ወይም የትዳር አጋራችሁ ሊሆን ይችላል፣ አባት፣ እናት፣ ወንድም፣ እህት፣ ልጅ ወይም ሌላ የቅርብ ዘመዳችሁ ሊሆን ይችላል። በህይወታችሁ ለዚህ ሰው የምትሰጡት ቦታ እጅጉን የተለየ ነው። ብታወሩለት አትጠግቡም፣ ብታስደስቱትም አትረኩም። የምርም የእናንተ እንደሆነ በልበሙሉነት የምታወሩለት ሰው ነው። አዎ! ሰው አታብዙ፣ የሚያስፈልጋችሁ ጥቂት ወይም አንድ ትክክለኛ ሰው ብቻ ነው። ይሔን ሰው በልበሙሉነት "የእኔ ነው፣ እርሱ አለልኝ፣ በእርሱ አላፍርም" ለማለት ቅንጣት ታህል ሀፍረት አይሰማችሁም። በዚህ ሰው ምክንያት የሰው ዋጋ ይገባችኋል። እንደዚህ አይነት ሰው ያላቸው ሰዎች ህይወትን በፍቅር ይኖሯታል፣ እያንዳንዷ ከእርሱ ጋር የሚያሳልፏት ሰዓት የተለየ ትርጉም አላት። የእኔ የምትሉትን ሰው አጥብቃችሁ ያዙ፣ መጠቀም እስካለባችሁ ድረስ ተጠቀሙበት፣ በመኖሩ አትርፉ፣ ከአብሮነቱ አግኙ፣ ውስጣችሁን አሳርፉ፣ ልባችሁን አስደስቱ። ህይወት ከትክክለኛው ሰዎች ጋር የተለየ ጠዓም አላት። ፈተናዎችዋ ቢበዛ፣ ችግር ቢያይልባት፣ መገፋት፣ መገለል፣ መጠላት ቢበዛባት እንኳን አንድ የእኔ የምትሉት ሰው ካለ ሁሉንም ውጣውረዶች በድል እንድትወጡ ያግዛችኋል። አንድ ሁኖ ሁሉነገራችሁ መሆን የሚችል ሰው ማግኘት በእርግጥ መታደልም መመረጥም ነው። ይሔ ሰውም ታማኝና ለእናንተም ተመሳሳይ ቦታ ያለው ከሆነ ይሔ ከስጦታም በላይ በረከታችሁ ነውና አጥብቃችሁ ያዙት፣ እያለላችሁ አመስግኑበት፣ አብሯችሁ እያለ ክብርና ቦታውን ንገሩት። አዎ! ጀግናዬ..! ዓለም በሰዎች ተሞልታለች፣ አንደኛውም አንተ ነህ። የልብ ወዳጅህም ከእዛ ውስጥ አንደኛው ነው። ለሰዎች ባለህ ክብርና ቦታ አንፃር ትክክለኛውን ሰው ወደ ህይወትህ ትስባለህ። ተጫዋች፣ አጫዋች፣ ስረዓት አልባ፣ ሰዎችን ለመጠቀም ብቻ የምትቀርብ፣ ሰብዓዊነትን የተውክ፣ ከሰው በላይ ጥቅምና ጥቅምህን ብቻ የምታስቀድም ከሆነ የምትስበው ሰውም ያንኑ ሰው ነው። ብዙ ጊዜ አብረው የሚሆኑ ሰዎች አብረው እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው የተለየ የስብሀት ሀይል አለ። የእኔ የምትለውን ሰው ወደራስህ ለማምጣት በቻልከው መጠን አንተ ያንን ሰው ለመሆን ሞክር። ከብዙ ጥራት የሌለው ግንኙነት አንድ ጥራት ያለው፣ ልብ ለልብ የሆነ፣ በፍቅርና በመተሳሰብ የታጠረ፣ አብሮነት አንድነትን ያነገበ፣ በአዎንታዊነት የተሞላ ግንኙነት ይሻላል። ችግርህን ለምታውቀው ሰው ሁሉ አታማክር፣ ይልቅ ለችግርህ መፍትሔ መስጠት ከፈለክ ችግርህ የሚገባው፣ ሁኔታህን የሚረዳ አንድ ሰው በቂ እንደሆነ እወቅ። የሩቅ ወዳጅ አታብዛ፣ ከብዙው አንድ የልብ ሰው መያዙን እወቅበት። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 03731Loading...
28
✅ እራሳችሁን ተከተሉ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/QswJrA5CUbU?si=lzjONHJXK01oxg_k
2 8151Loading...
29
ትስማማላችሁ? "የሰው ዋጋ ከፍላጎቱ ዋጋ አይበልጥም።" "A man's worth is no greater than the worth of his ambitions." - Marcus Aurelius ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
2 8607Loading...
30
አፍህን ዝጋ! ፨፨///////፨፨ ከገዛ ምላሳችሁ የሚበልጥ ጠላት የላችሁም። ታወራላችሁ፣ ትተነትናላችሁ፣ ለሰው ታስረዳላችሁ ነገር ግን ከጊዜ ቦሃላ ያወራችሁትን ሁሉ ትረሱታላችሁ፣ ተነሳሽነታችሁን ታጣላችሁ፣ ሀሳባችሁ ይበተናል፣ እቅዳችሁ እርስበእርሱ ይምታታል፣ ነገ እደርስበታለሁ፣ ነገ አደርገዋለሁ ብላችሁ ያሰባችሁትን ነገር ከነጭራሹ ትረሱታላችሁ፣ መንቀሳቀስ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ነገር ግን ዛሬም እዛው ናችሁ፣ ቆም ብላችሁ ስታስቡ ምቾታችሁ ስቃይ፣ ምላሳችሁም ጠላት እንደሆነባችሁ ትረዳላችሁ። ማናችንም በቁጥር አንድ የስኬትና የለውጣችን ጠላት ተጠቂ ነን። እያወራን እንኖራለን ወይም ዝም ብለን እየሰራን እንጓዛለን፣ እውቅናን ፍለጋ እንኳትናለን ወይም ለእራሳችን እውቅና ሰጥተን ጥረታችንን እንቀጥላለን፣ ቆመን ጊዜያችንን እንጠብቃለን ወይም እራሳችን ወደ ጊዜያችን እንቀርባለን፣ አሸናፊነትን መመኘት እንጀምራለን ወይም አሸናፊ ሆነን ለመታየት እለት እለት እንታትራለን። በቀጭኗ የምርጫ ገመድ ላይ እየተንገዳገድንም ቢሆን የመጓዝ ሃላፊነት አለብን። አዎ! ጀግናዬ..! አፍህን ዝጋ፣ የሆድህን በሆድህ ያዝ፣ ወሳኙን ጉዳይህን ልብህ ላይ አንግሰው፣ የገዛ ሚስጥርህን ጠብቅ። የምትጠላውን ነገር ግን ማድረግ ያለብህን፣ በጊዜው የማያስደስትህን ከጊዜ ቦሃላ ግን በውጤት የሚያሸበርቅህን፣ በሰዓቱ ስቃይ የሆነብህን ከሰዓታት ቦሃላ ግን ስኬት የሚሆንን ጉዳይ በልብህ ይዘህ ስራበት። ዝቅ በል፣ አንገትህን ስበር፣ ውስጥ ለውስጥ ስራህን አጣድፍ፣ እዚህ ስትጠበቅ እዛ ተገኝ፣ ከእነዚህ ጋር ነህ ስትባል ከእነዛ ጋር ሁን፣ ማንም አሳዶ የማያገኝህ ሰው ሁን፣ ለእያንዳንዱ ስሜትህ ግድ ይኑርህ። ለይስሙላ መኖር ስታቆም ህይወትህ በቁብነገር እንደሚሞላ እወቅ። የሚያዩህ ሁሉ በቀላሉ የሚያውቁህ ከሆነ፣ ለቀረቡህ ሁሉ ገመናህን የምትገልጥ ከሆንክ፣ በየሔድክበት ሁሉ አፍህን የምትከፍት፣ ላገኘሀው ሁሉ እራስህን የምታብራራ፣ ታሪክህን፣ እቅድህን፣ ስራህን፣ ገቢህን ወጪህን ሁሉ የምትዘረዝር ከሆነ በገዛ ፍቃድህ የበላይነትህን አሳልፈህ እየሰጠህ እንደሆነ እወቅ። ድብቅ ነገር ያጓጓል፣ የተሰወረ ነገር ይበልጥ ቦታና ክብር አለው። ማንም በተገላለጠ ነገር ለጊዜው ደስ ሊለው ይችላል ነገር ግን የሚፈልገው የተሸፈነውን ነው፣ ማንም ወሬ ሊወድ፣ የሚነገረውንም ሊያዳንቅ ይችላል ክብርና ቦታ የሚሰጠው ግን ከንግግር ውጪ በድብቅ የሚፈፀመውን ተግባር ነው። አዎ! ካንተ በላይ ለእራስህ የሚያውቅልህ ሰው የለም፣ ካንተ ውጪ ቀዳሚው የህይወት አጀንዳው የሆንከው ሰው የለም። በምንም መንገድ ልታደርገው ትችላለህ፣ እንዴትም ልታደርገው ትችላለህ እራስህን የመጠበቅ ሃላፊነቱ የእራስህ ነው። እራስህን አደባባይ ላይ በማስጣት እራስህን ልትጠብቅ አትችልም፣ የግል ጉዳይህን አይን ውስጥ በማስገባት ነፃ ልትወጣ አትችልም፣ ሰዎችን ለማስደነቅ እየሰራህ መቼም ለእራስህ ቦታ ሊኖርህ አትችልም። ጠቢባንን በአፅንዖት ተመልከት ረጅሙን ጊዜያቸውን የሚያጠፉት በማውራት ሳይሆን በጥልቀት በማሰብ ነው፣ ትልቁ ክህሎታቸው ንግግር ሳይሆን የማዳመጥ አቅማቸው ነው፣ ብዙዎች የሚቀኑባቸው ከአንደበታቸው በሚወጡ ቃላት ወይም በጥድፊያቸው አይደለም ይልቅ በእርጋታቸውና በብስለታቸው ነው። ካንተ ውጪ ወደፊትህን የሚያጨልም፣ ከገዛ እርምጃህ በቀር ህይወትህን የሚያከብድ፣ ከእራስህ ንግግር ውጪ እቅዶችህን በአጭር የሚያስቀራቸው ነገር የለም። በምላስህ ውድቀትህን አትጥራ፣ በገዛ እጅህ የማትወጣው መቀመቅ ውስጥ አትግባ። ከባድ ቢሆንም ተግባርህን በምላስህ አትቅደመው፣ ውጤትህን በንግግርህ ዋጋ አታሳጣው። በጨለማ መራመድ ተለማመድ፣ በብረሃኑም እራስህን ግለፅ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 23823Loading...
31
Media files
2 5000Loading...
32
እድል ስጪው! ፨፨፨/////፨፨፨ በእርሷ የሚሞላ ክፍተት ሊኖርብህ ይችላልና እድል ስጣት። በእርሱ ሊሻሻል  የሚችል ድክመት ይኖርሻልና እድል ስጪው። አብሮ መሆን ክፍተቶችን ለቃቆሞ ለማውጣት፣ ለትልቅ አጀንዳ ለማብቃትና የሰፈር ወሬ ለማድረግ ሳይሆን ተሸፋፍኖ፣ ተሞላልቶ፣ ተሳስቦ፣ ተግባብቶ በፍቅር አብሮ ለመኖር ነው። ከድክመት ፈላጊው ጀምሮ ድክመት የሌለበት ሰው የለም፤ ከስህተት አሳሹ ጀምሮ የማይሳሳት ሰው የለም። የሆነው ሆኖ ሰው ሲወደድ ከነስህተቱ፣ ሲቀበሉትም  ከነድክሙ ነውና ለምን ተሳሳተ፣ ለምን ደከመው ብሎ ቅሬታ ማብዛት፣ በወቀሳ ማስጨነቅ ተገቢ አይደለም። ድጋፍን ፍለጋ የመጣን ሰው ከመደገፍ ባሻገር አለኝታነትን ማሳየት ተመራጭ ነው። ፍቅርን ፈልጎ የመጣን ሰው ከፍቅር ባሻገር የልብ ውህደትን መስጠት መልካም ነው። ብዙዎችን ትቶ ስለመጣ ከብዙዎች የማያገኘውን ከእኛ ማግኘት እንዲችል ማድረግም የእኛ ድርሻ ነው።  አዎ! ጀግኒት..! ክፍተቱን ከማጉላት፣ ድክመቱን ከማክበድ፣ ስህተቱን ከመድገም ይልቅ እድል ስጪው። ክፍተቱን ይሙላ ካልቻለም አንቺ ሙይለት፣ ድክመቱን ያሻሽል ካቃተውም አንቺ ደግፊው፣ ከስህተቱ ይታረም ከከበደው አንቺ አርሚለት። በአብሮነት ውስጥ መልካም ትዝታዎች፣ ያለፉ የፍቅር ጊዜያት፣ ጣፋጭ አጋጣሚዎች ለክፉ ጊዜ ትልቅ ስንቅ ናቸው። በጋራ ህይወት አለመግባባት፣ አለመስማማት፣ ይባስም ሲል መቃቃርና መለያየት ያሉ ነገሮች ናቸው። ነገር ግን ተቀራርቦ፣ ተነጋግሮ፣ ሃሳብ ተለዋውጦ መግባባትና መለያየቱን ማስቀረት ይቻላል። ያልተካበደና ያልተጋነነ ነገር ሁሌም የተሻለ መፍትሔ አያጣም። አዎ! ጀግናዬ..! ክፍተቶችን ማጥፋት አትችልም መሙላት ግን ትችላለህ፤ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግ አትችልም ማረም ግን ትችላለህ፤ ድክመቶች እንዳይኖሩ ማድረግ አትችልም ማሻሻልና ማስተካከል ግን ትችላለህ። ከሰው እንከን ብትፈልግ ያለምንም ድካም ታገኘዋለህ፣ በግንኙነትህ ውስጥ የሚያለያይ ነገር ብትፈልግ ወዲያ ይገለጥልሃል። ማየት የምትፈልገው ነገር ሁሌም ቅርብህ ነው፣ ማየት ትችላለህ ማግኘትም ትችላለህ። ነገር ግን የፈለከውና ያየሀው ድክመትና ክፍተት ትልቅ ነገር ከመሆኑና ግንኙነቱንም ከማንገዳገዱ በላይ መታረምና መሞላት እንደሚችል አስታውስ። አዎ! ላንተ ትልቅ ጉዳይ የሆነብህ ነገር አብሮህ ላለ ሰው አንሶ ሊገኝ ይችላል፣ ያንተም ቀላል ነገር በተቃራኒው ገዝፎ ሊታይ ይችላል። ክፍተቶችም በዚህ መልክ ይፈጠራሉ፣ በሂደትም እያደጉ ትልቅ አደጋን ያስከትላሉ። ክፍተት እንዳለ አምነህ ለማጉለት ሳይሆን ለማጥበብ ተዘጋጅ፣ ችግር መኖሩን ተቀብለህ ለማባባስ ሳይሆን ለማርገብ፣ ለመፍታት ሞክር፣ ድክመት እንዳለ አውቀህ ለመደገፍ፣ ለማበርታትና ከጎን ለመቆም ተሰናዳ። ከአባባሽና አድማቂነት ይልቅ  የመፍትሔ ሰው ሆነህ ተገኝ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 10632Loading...
33
✅ ለራስህ ድረስ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/6OzOc_e_96E?si=Jl9HA_SWbNFgSEt7
2 8874Loading...
34
መንፈስህ አይሰበርም! ፨፨፨፨///////////፨፨፨፨ ተስፋህ ሊጨልም ይችላል፤ ገንዘብህ ሊዘረፍ ይችላል፤ ሰዎች ሊርቁህ ይችላሉ፣ ብቻህን ልትቀር፣ ደጋፊ ልታጣ፣ አበርታች ላታገኝ ትችላለህ ነገር ግን በእርግጥ ከእውነተኛው መንፈስህ ጋር ከሆንክ፣ ከትክክለኛው ስሜትህ ጋር ከተዋሃድክ ያጣሀውን ሁሉ ማግኘትህ፣ ጎደለኝ የምትለውን በሙሉ ማስመለስህ የማይቀር ጉዳይ ነው። ማንነትህ የሚለካው ውስጥህ በሚመላለሰው ውስጣዊ ሃይል ነው። ብዙ ጊዜ ውጫዊ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና በየሰዓቱ ይቀያየራሉ፤ ውስጣዊና ትክክለኛው ነገር ግን የሚቀየር ሳይሆን የሚሻሻል፣ የሚያድግና የሚጨምር ነው። ስለ እውነተኛው ማንነትህ ማውራት ብትፈልግ ትክክለኛው የውስጥ ስሜትህን፣ መንፈስህን ጠንቅቀህ እወቀው፤ በእርሱም ላይ ተደገፍ፤ እርሱን እመን፤ በእርሱ ተመራ። አዎ! ጀግናዬ..! መንፈስህ  አይሰበርም!በአሉታዊ ሰዎች ብትከበበ፣ ተስፋ አስቆራጭ ቃላት ቢሰነዘሩብህ፣ መጠቋቆሚያ ብትሆን፣ መጥፎ አስተያየት ቢሰጥህ፣ ዝቅ ተደርገህ ብትታይ፣ ብትናቅ፣ ብትታማ፣ ብትገፋ በእርግጥ ከውስጣዊ ስሜትህ ጋር እየተጓዝክ ከሆነ፣ ትርጉም የሚሰጥህን ነገር እያደረክ ከሆነ የተግባርህ መነሻ መንፈስህ ነውና እዴትም ተሰብረህ ልትቆም አትችልም። ምንም ስታደርግ በእርግጥም የመጣው ከውስጥህ መሆኑን እርግጠኛ ሁን። የጀመርከው በውጫዊ ግፊት ወይም ከምታየው ጊዜያዊ ነገር ብቻ እንዳልሆነ ተማመን። መንፈስ በማንም በምንም ሊቆም አይችልም፤ ትክክለኛው የውስጥ ስሜት እንዴትም ሊሰበርና ተንኮታኩቶ መቅረት አይችልም። አዎ! በእርግጥም የመንፈስ ስብራት ቀላል እንዳልሆነ የምታውቀው ውጫዊውን ጫጫታ መስማት ስታቆም፣ ትኩረትህን በሙሉ እራስህና ተግባርህ ላይ ስታደርግ፣ የጉዞህን ፍጥነት ስትጨምር ነው። የተባረክበት አንድ ነገር አለ፤ አምላክ የሚሰራብህ አንድ ተግባር አለ፤ ብቻህን ሳይሆን ከፈጣሪህ ጋር የምታሳካው፣ ከፍ የምትልበት፣ የምትታወቅበት፣ የምትደነቅበት፣ የምትኮራበት አንድ ያንተ ብቻ የሆነ ነገር አለህ። በጫና ሳይሆን እራስህ ማቆም ብትፈልግ እንኳን ልታቆመው አትችልም፤ ልትለየው ብትፈልግ እርሱ አይለይህም። ምክንያቱም ድርጊትህ ከማንነትህ ጋር ተዋህዷልና ነው፤ ምክንያቱም መነሻው ውስጥህና መንፈስህ ስለሆነ ነው። መፍቀድ ብትችል ትክክለኛው የውስጥ ስሜትህ በነፃነት ይፈስ ዘንድ፣ ተገልጦ ይታይ ዘንድ፣ አምላካም ስራውን ይሰራበት ዘንድ ፍቀድ፤ ሌላኛውንና ትክክለኛውን ማንነትህንም አሳይ።  ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን! 🔺🔻 SUBSCRIBE NOW https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪
3 32019Loading...
35
✅ ጥረታችሁን ጨምሩ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/Ttn07HC4kiQ
3 0463Loading...
36
"እጣህ ቦግ ይበል"❤ የአከባቢያችን እናቶች የሰፈር ልጆችን ሲመርቁ  " እጣህ ቦግ ይበል!"እጣሽ ቦግ ይበል" በማለት ይታወቃሉ።   በሰአቱ የምርቃቱ ትርጉም ብዙ ባይገባኝም  "አሚን"እላለሁ ።   ህይወትን መረዳት ከጀመርኩ በኋላ የድካሙን ያህል ውጤት የማያገኝ፣ የማያገኘውን በመመኘት የሚንከራተት፣ የሚወደውን ሰው ፍቅር የተነፈገ፣ ግማሽ ኢማኔ ሞላ እልልልልል ብሎ ሳይጨርስ ትዳሩ የሚፈርስበት፣ የወላድ መካን የሆነ፣ በመጦሪያ እድሜው ሀላፊነት የተሸከመ፣ አምነዋለሁ ያለው የሚክደው፣ ወዳጄ ያለው ሰው ጠላቱ የሆነበት፣ የነካው ሁሉ እየተበላሸ ተስፋ ያስቆረጠው ፣ እድለቢስ ነኝ ብሎ ያመነ ሰው ሳይ የምርቃታቸው ትርጉም እና ክብደት ሲገባኝ እንኳንም አሚን አልኩ እላለሁ። ልክ ነበሩ! አላህ እጣውን ቦግ ያደረገለትን ሰው ማን ሂወቱን ሊያጨልምበት ይችላል? በወሎ አነጋገር "እጣህ ቦግ ይበል! " ማለት እድልህ ይመር እንደማለት ነው። አላህ እጣችንን ቦግ ያድርገው!🤲 ዝክረ ኸሚስ💚 Semir sophi የፈትያዬ❤
3 0708Loading...
37
ስራህን ስራ! ፨፨//////፨፨ አወጣህ አወረድክ፣ ታመምክ ተሰቃየህ፣ በላህ አልበላህ፣ አየህ አላየህ፣ አሳካህ አላሳካህ፣ ደረስክ አልደረስክ ማንም ሰው አይመለከተውም። ሃሳብህ፣ ህልምህ ራዕይህ ያንተ ነው። የጠለቀ ግነንኙነት ቢኖርህም አንድ ቀን ትረሳለህ፣ ለረጅም ጊዜ ብትለፋም ውጤት ታጣለህ፣ ከአቅምህ በላይ ብትታገልም ያሰብከውን አታገኝም። የሚለፉ፣ የሚደክሙ፣ የሚታትሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፣ ስኬታማና ደስተኞች ግን እጅግ ጥቂት ናቸው። ስለመዳረሻህና ወደፊት ስለምታሳካው ግብህ እያሰብክ ደስታና ስኬትን ልታገኝ አትችልም። ምንም ትልቅ ነገር ልታደርግ ትችላለህ፣ ህልምህን ልታሳካ፣ ግብህንም ልትመታ ትችላለህ የትኛውም መዳረሻ ግን የእራሱ መንገድ አለው፤ እርከን አለው፤ ሂደት አለው። ገና ለገና ከሰማይ የምታወርደው ስኬትና ደስታ ያለ ይመስል እርሱን በመጠበቅ ጊዜህን አትፍጅ። እርሱ መምጣት ካለበት የሚመጣው ስለጠበከው ሳይሆን ሆነሀው ስለተገኘህ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ስራህን ስራ የፈለከው ነገር በጊዜው እራሱ ይሰራል፣ ይመጣል። ያሰብከውን ነገር አድርግ፤ የታሰርክበትን ሰንሰለት በጥስ፤ ጥቃቅኗን ነገር በጥልቀት አድርጋት፣ በእርምጃህ ውስጥ ስሜትን ፍጠር። ስኬትን መመኘት ሳይሆን ሆነሀው ተንቀሳቀስ፣ ደስታን መናፈቅ ሳይሆን ፈጥረሀው ኑርበት። በተዓምራት የሚከሰት ትልቅነት እንደሌለ ታውቃለህ፣ በአንዴ የሚፈጠር ስኬት እንደማይኖርም ይገባሃል። ውስጥህ ያልፈጠርከው ነገር ኬትም እንደማይመጣ አስተውል፤ ማረፊያ ያላዘጋጀህለት፣ አምነህ ያልጀመርከው፣ ጣሪያ ያላበጀህለት፣ ተንትነህ በግልፅ ያላስቀመጥከው ስኬትም ሆነ ከፍታ በፍፁም ሊመጣ አይችልም። ምናልባት ያላሰብከው የመሰለህ ነገር በህይወትህ ተከስቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሳታስበውና በውስጥህ ምንም ነገር ሳይኖር በህይወትህ የሚከሰት አንዳች ነገር አይኖርም። ሃሳብ ያደክማልና አንድ ስሞን አስበህ ትተሀው ይሆናል፣ በሌላ ሃሳብም ተክተሀው ይሆናል። አንተ ብትረሳውም ሰውነትህ ግን አይረሳውም፤ ያኔ በሃሳብህ ውስጥ ሰውነትህ የተሰማው ስሜት በሂደት ባልገመትከው መንገድ ወደ ቀድሞ ሃሳብህ እውንነት መርቶሃል። አዎ! አስበህ፣ አምነህ፣ ተቀብለህ በህይወትህ ውስጥ እውን እንዲሆን የምታደርገው ነገር ይኖራል። አንድን እሳቤ አስተውል፣ " የምትፈልገውና የሚያስፈልግህ ነገር እንዲከብህ ማድረግ ሊከብድህ ይችላል፤ ነገር ግን የሚያስፈልግህንና የምትፈልገውን ነገር በውስጥህ መፍጠር ትችላለህ።" ቀላልና ከባድ፣ አዝናኝና አሳዛኝ፣ አሳራፊና አድካሚ የሚባሉ የህይውት አጋጣሚዎች ይኖራሉ። ምንም ይሁኑ ግን የህይወትህ አንድ አካል ናቸው። ተቀብለህ የማስተናገድ ግዴታ አለብህ። ስሜቱን ባትፈልገውም ከባድ፣ አሳዛኝና አድካሚ የሆኑትን ክስተቶችም ማጣጣም ይኖርብሃል። ከባዱን ካልተሻገርክ ቀላሉን አታገኝም፤ አሳዛኙን ካላሸነፍክ አስደሳቹ ጋር አትደርስም፤ አድካሚውን ካልተወጣህ ረፍትህን አታጣጥምም። በእያንዳንዱ እርምጃህ ውስጥ ነፍስን ፍጠር፣ ስሜት አግኝ። ሰረተህ ስትጨርስ፣ ሃላፊነትህን ከተወጣህ ቦሃላ ሳይሆን እየሰራህ፣ ሃላፊነትህንም እየተወጣህ ደስተኛና ስኬታማ እንደሆንክ አምነህ ተንቀሳቀስ። ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 43223Loading...
38
Media files
2 8600Loading...
39
ጊዜ ይወስዳል! ፨፨፨//////፨፨፨ መራር እውነት በአቋራጭ መበልፀግ ለሚፈልጉ፣ መቼም ሊቀይሩት የማይችሉት የተፈጥሮ ህግ "የትኛውም ምርጥ ነገር ጊዜ ይወስዳል።" አንድን ክህሎት መርጦ መማር፣ ከህይወት ውጣውረተድ ተምሮ ጥበበኛ መሆን፣ አዲስ ልማድ መገንባት፣ ጥሩ ስሜት ውስጥ መሆን፣ አዕምሮን ከበካይ አስተምህሮዎችና እምነቶች ማፅዳት፣ እጅግ ወሳኝ ምርጥ ግንኙነት መገንባት ጊዜ ይወስዳል። ምርጥ ህይወት ለመኖር ያለህ ምርጫ አንድ ነው። ወመጠበቅ ያለብህን ጊዜ በመጠበቅ በጊዜው ምርጡን ህይወት መኖር። አቋራጭ ውስጥ ውበት የለም፣ ጀምሮ ማቆም ውስጥ እርካታ የለም፣ ሀሳብን አግዝፎ ከተግባር ርቆ ተነሳሽነትን አጥቶ በስንፍና ታጥሮ፣ ተስፋን አጥቶ፣ እምነትን ገድቦ እውነተኛ ደስታ የለም። ምርጡ ስጦታህ የዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግልህን ይፈልጋል። ሁሌም ቢሆን ዝግጁ ከሆንክ ባልተጠበቁ ችግሮች ህይወትህ እስከመጨረሻው ሊቀየራል። ጊዜ የሚወስድ፣ ከባድ ተጋድሎን የሚጠይቅ፣ ውጣውረድ ያለውን ምርጫን መምረጥ ካልቻልክ ህይወትህ ነፃ ሊሆን አይችልም። ጀምሮ ለማቆም እራስህን ማነቃቃት አይጠበቅብህም፣ በአሉታዊ ሃሳቦች ለመደናቀፍ፣ እዛው ወድቀህ ለመቅረት ምንም ማበረታች አያስፈልግህም። ንቃትም ሆነ ብርታት የሚፈልገው የህይወትህ ክፍል በስተመጨረሻ ምርጡን ስጦታ በእጅህ የሚያስገባው ተግባርህ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! የተፈጥሮን እውነታ ለመቀየር አትታገል። ወደድክም ጠላህም የዓለም ምርጡ ነገር ጊዜ ይወስዳል፣ ጥረትን ይጠይቃል፣ ያደክማል፣ አብዝቶ ይፈትናል። ከምንም በላይ ያለምንም እረፍት ለረጅም ጊዜ መትጋትን ይጠይቃል። የዛሬ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተፅዕኗቸው የመጣው በአንድ ሰሞን እድለኝነት ወይም የሆነ ቀን በወጣላቸው የሎተሪ እጣ አይደለም። ከዛሬው ተፅዕኗቸው ጀርባ የትናንት ትጋቶች ነበሩ፣ ከዛሬ ስኬታቸው ጀርባ የዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል አለ። ሰዎች ሲያዮአቸው እድለኞች ቢመስሉም እድለኛ ያስባላቸው ግን ጥረታቸውና ጥረታቸው ብቻ ነው። አስተሳሰብህ ያነግስሃል፣ አስተሳሰብህ ያወርድሃል። ከፍ ማለት ምኞት፣ ለውጥና እድገትም ፍላጎትህ ከሆነ ነገሮችን ማወሳሰብ አቁም፣ ሰበብ መደርደር አቁም። እነዚህን ነገሮች ብቻ አድርግ። እራስህ ላይ መስራት ጀምር፣ እራስህን በማብቃት ቢዚ ሁን፣ ማንነትህን በማደስ ተጠመድ፣ ቀዳሚውን የህይወትህን አጀንዳ እራስህን አድርግ። ምንም ባልተለወጠበት ዓለም ውስጥ የተለየ ውጤት የሚያመጣ ተዓምር የለም። ለመኖር ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ለማኖር፣ ለብዙዎች ለመድረስ ከፈለክ ጊዜ ቢወስድም በከባዱ መንገድ መጓዝ ጀምር። አዎ! የጉዞህ መንገድ ሩቅ ነው መዳረሻህ ግን ከማንም የተለየ ነው፤ ክፍያህ ከፍተኛ ነው ትርፍህ ግን የብዙዎች መኞት ነው፣ ጥረትህ ከማንም በላይ ነው ውጤትህ ግን ማንንም ያስቀናል። ብዙ ጥቃቅን ድምፆች ከውስጥህ ያቃጭላሉ፣ በዙ ለውድቀት የሚያመቻቹ፣ ነገን የሚያጨልሙ፣ ተስፋን የሚያንኮታኩተው፣ እሴትን የሚደመስሱና ተነሳሽነትን የሚገድሉ አሉታዊ ሀሳቦች በዙሪያህ ያስተጋባሉ። የትኛውን መስማት እንዳለብህ በሚገባ መርምር። ከቻልክ ካንተ ከማይሻል፣ የሚያስተምርህ ነገር ከሌለው፣ የተሻለ ሰው መሆኑን ካላሳመነህ፣ ድፍረትና ንቃተ ህሊናው ከወረደ ሰው ሙሉ ሃሳብ አትቀበል። ረጅም የጉዞ መንገድ ከርዝመቱ ጀምሮ ፈተናው ብዙ ነው። የስሜት መዋዠቅ፣ ያልተጠበቁ መሰናክሎች፣ የሰዎች ጫና፣ የግል ጉዳይ፣ የግንኙነት ነገርና የመሳሰሉ ብዙ ፈተናዎች እየተፈራረቁ ይመጣሉ። ምርጡን ነገር ለማግኘት ደግሞ ለእያንዳንዱ ለእነዚህ መሰናክሎች መፍትሔ ልታበጅ ይገባል። እነርሱ ሰርተው የሚበሉና የተሰራን ምግብ የሚመገቡ ሰዎች ስለምግቡ እኩል መረዳት የላቸው፣ ጠዓሙን መቀየር ቢፈልጉም ሁለቱም በተመሳሳይ ሊያጣፍጡት አይችሉም። ላንተ ህይወት ሃላፊነቱ የእራስህ ነው። ጊዜን በጊዜ ማታለል አቁም፣ አቅምህን በአቋራጭ መንገድ አታባክነው፣ በትንሽ ጥረት፣ እንዲሁም "በምናብና በምኞት ብቻ ምርጥ ህይወት መኖር እችላለሁ" የሚለውን ሃሳብ ከውስጥህ አውጣ። የፈጀውን ቢፈጅም፣ ያስወጣህን ቢያስወጣህም ምርጡን ህይወት ለመኖር የጀመርከውን የተግባር ጉዞ በፍፁም አንዳታቆም። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
3 68320Loading...
40
✅ ጥድፊያችሁን ቀንሱ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/9pex-fh_aKg?si=-PqOx4WbEbM7Nu3d
3 1033Loading...
በቴሌግራም ገቢ ማግኛ መንገዶችን መማር ይፈልጋሉ?? 🪙 ስለ Notcoin 🪙 ስለ Toncoin 🪙 ስለ Bitcoin 📊📈 ስለ Forex Trading በየቀኑ የሚወጡ መረጃዎችን እንዲሁም በቂ ትምህርቶችን ማግኘት ትፈልጋለችሁ?      ቻናላችንን ተቀላቀሉ 👇👇             @Crypt_currencies             @Crypt_currencies             @Crypt_currencies
Показать все...
ስጦታህን አታሳንስ! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ ምድራችን ላይ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እናንተም ከየትኞቹ ጎራ እንደሆናችሁ እወቁ። ማስተካከል የምትችሉትንም ለማስተካከል ጊዜ አታጥፉ። በአንደኛው ጎራ የሚመደቡ ሰዎች ከተቀሩት ጋር ሲነፃፀሩ ጥቁት የሚባሉ ናቸው። በእነዚህ ሰዎች መመስገን ከፈለጋችሁ ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ትልቅ ስጦታ ገዝቶ መስጠት፣ ከባዱን ችግራቸውን መፍታት፣ ሁሌም ከስራቸው አለመጥፋት፣ ንብረታችሁን ሁሉ አሳልፋችሁ መስጠት ወይም የዘወትር አድናቂያቸው መሆን አይደለም። አነዚህ ሰዎች ለሰጣቿቸው ጠብታ ውሃ ከልብ ያመሰግኗችኋል፣ ከእናንተ ጋር ለሚያሳልፏት ትንሽ ጊዜ ያመሰግኗችኋል፣ ምንም ባታደርጉላቸው በሃሳባችሁ ብቻ ይደነቃሉ፣ የእነርሱ የእናንተ እቅድ አካል መሆን ልባቸውን ያሞቀዋል፣ ደስታውንም ይሰጣቸዋል። በትንሽ ነገር ይደሰታሉ። በሌላኛው ጎራ የሚመደቡ ሰዎችስ ምን አይነት ሰዎች ናቸው? እነዚህ ሰዎች በፍቃዳችሁ የምታደርጉት የትኛውም ነገር አይዋጥላቸውም። ምንም አድርጉላቸው ግዴታችሁ እንደሆነ ያስባሉ። ለምትሰጧቸው የዉሃ ጠብታ አይደለም ባህሩን እንኳን ብትሰጧቸው አይረኩም፣ ሊያመሰግኗችሁም አይፈልጉም። የምታደርጉላቸውን እያንዳንዱን ነገር እንደ ግዴታ ይወስዱታል ከዛም በላይ በፍፁም አያመሰግኟችሁም። አዎ! እራስን ከነዚህ ሁለት አይነት ሰዎች ጎራ ነጥሎ ከመመልከት በፊት እናንተ ከየትኞቹ እንደሆናችሁ እወቁ። እንደ አንደኞቹ በተደረገላችሁ ትንሽ ነገር የምትደሰቱና የምታመሰግኑ ከሆነ ዓለም የእናንተ ነች፣ ነገር ግን ልክ እንደ ሁለተኞቹ ምንም ቢደረግላችሁ የማትረኩና ለማመስገን ፍቃደኛ የማትሆኑ ከሆነ ህይወት በጣም ከባድ ትሆንባችኋለች። እርካታ ሲባል የተሰጣችሁ ነገር በቂና የልብ የሚያደርስ ሆኖ ሳይሆን ከመደረጉ በላይ ስለታሰበላችሁና በትንሹም ቢሆን ትኩረት ተሰጥቷችሁ ስለተደረገላችሁ የሚሰማችሁ ውስጣዊ ስሜት ነው። ሰዎች ከሚያደርጉላችሁ በላይ እራሳችሁ ለእራሳችሁ ማድረግ ትችሉ ይሆናል፣ እርሱንም በፈለጋችሁት ጊዜና መጠን ልታደርጉት ትችላላችሁ። ከሰው የሚመጣው ግን ትኩረትን፣ ፍቅርንና ክብርን ይዞ ይመጣል። ምንም ነገር ቢሰጣችሁ በክብር የመቀበልን ልማድ አዳብሩ፣ ለሚደረግላችሁ ነገር ቦታ ስጡ። ከእቃው ትንሽነት በላይ በሰጪው ዘንድ ስላላችሁ ቦታ አስቡ። በፍቃድ የሚሰጣችሁ የትኛውም ነገር ከግዴታ የተነሳ ሳይሆን ከውዴታ እንደሚመነጭ እወቁ። አዎ! ጀግናዬ..! ስጦታህን አታሳንስ! ጠብታ ውሃም ሆነ ሙሉ ውቂያኖስ ለተሰጠህ ነገር አመስጋኝ ሁን። በትንሹ ያላመሰገነ ትልቅም ቢደረግለት አያመሰግንምና በጥቃቅን ስጦታዎችህ ማመስገኑን ተለማመድ። ማንም የሰጠው እንዲረክስበት አይፈልግም፣ ማንም አስቦና አቅዶ ያዘጋጀው ፕሮግራም ሲናቅበት አይወድም። አንዳንዴ ድግሱ ባይጥመንም፣ ምግቡ አንጀታችንን ባያርስም፣ መሰተንግዶው የልብ ባያደርስም ለደጋሹ ካለን ክብርና ቦታ የተነሳ ተደስተንና አመስግነነው የምንወጣበት ጊዜ ይኖራልተ። ከምግብና መጠጡ በላይ አክብሮ ስለጠራን ብቻ እንደሰታለን። የተሰጠህ ነገር ላንተ ብዙም ዋጋ የሌለው ቢሆንም ለሰጪው ብለህ ዋጋ ልትሰጠው ይገባል። ወዳጅነት እንዲዳብር፣ ፍቅር እንዲጎለብት፣ አንድነትም እንዲፀና ልባዊ ምስጋናና አድናቆት ያስፈልጋል። በእጁ ከያዘው ቁስ በላይ በልቡ ያለህን ቦታ ለመረዳት ሞክር፣ ከኪሱ አውጥቶ ከሚሰጥህ ገንዘብ በተሻለ ለሚሰጥህ ውድ ጊዜው ቦታ ስጥ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Показать все...
👍 5 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
አይመለከተኝም! ፨፨፨////////፨፨፨ ከራስጋር ንግግር፦ "ህይወቴ መቼ መቀየር እንደጀመረ አስታውሳለሁ። ድሮ የሰው ነገር አብዝቶ ያስጨንቀኝና ያሳስበኝ ነበር። ማን ምን አደረገ፣ ማን ከማን ጋር ሆን፣ ማንስ ምን ለበሰ፣ ምን ጀመረ እያልኩ የባጥ የቆጡን አወርድ ነበር። ማሰብ ከጀመርኩ ስለሰው ነው፣ የማወራው ስለሰው ነው፣ የምሰራው ለሰው ብዬ ነው፣ ከራሴ በላይ የምጨነቀው ስለሰው ነው። በአጠቃላይ የምኖረው ለሰው ነበር። ለሰው መኖር ምንያህል እራስን እንደሚያሳጣ በሚገባ አውቃለሁ። የፍረሃቴ ምንጭ በራሴ ላይ ሰውን ማንገሴ ነው፣ በሰው ዘንድ የበታች ተደርጌ የምታየው በየሔድኩበት ሁሉ ከራሴ በላይ ለሰው የበዛ ቦታ በመስጠቴ ነው። ሰው ሲመራኝ፣ ሰው ሲወስንልኝ፣ እኔም በሰው መንገድ ስመላለስ ከረምኩኝ። ዛሬ ግን ስነቃ አንድ ነገር ገባኝ። "የሰው ነገር የእኔ ጉዳይ አይደለም፣ ዋናው ጉዳዬ እኔና እኔ ነኝ።" ለእራሴ መኖር ሳልችል፣ ለእራሴ ሳልበቃ፣ እራሴን ሳላድን እንደቀድሞ ለሰው ልኑር ብል ከውድቀት በቀር የማገኘው ነገር አይኖርም። ስለማን ምን በላ፣ ስለማን ምን ጠጣ፣ የት ሔደ፣ ከማንጋር ሄደ መጨነቅ ሳቆም የዓለምን ሌላ ገፅ መመልከት ቻልኩ። አዎ! እኔ የእራሴ ወሳኝ ጉዳይ አለኝና የሰዎች በፈለጉት መንገድ መጓዝ አይመለከተኝም፣ የሰዎች እንደምርጫቸው መኖር ጉዳዬ አይደለም። እነርሱ እንደፈለጉ ይኖራሉ፣ እኔም እንደዛው የመኖር መብቱ አለኝ። ስለማይመለከተኝ የሰው ጉዳይ እየተጨነኩ የማሳልፈው ጊዜ አብቅቷል። አሁን ለውጤን የማጣጥምበት ጊዜ ነው። ሰውን ለማስደሰት ስጥር ደስታዬን አጥቼያለሁ፣ ስለሰው ሳስብ የሚያስብልኝ አጥቼያለሁ። እንትና እንደዚ አደረገ ስባል ከእኔ ህይወት ጋር ባይገናኝም እንዲሁ ስደነግጥ፣ እንተና ይሔንን ስራ ጀመረ ሲባል ከሰውዬው ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር ባይኖር ስለርሱ ሳወጣ ሳወርድ ዘመናት አልኀዋል። የሚመለከተኝንም የማይመለከተኝንም ስሰማ፣ ሳወራ፣ ሳዳንቅ፣ ሳብላላ ከርሜያለሁ። ነገር ግን ምንም ጠብ የሚል ነገር አላገኘውበትም። ከሰው ህይወት የበለጠ የሚመለከተኝ የእራሴ ህይወት እንደሆነ ገብቶኛልና ከአሁን ቦሃላ በእራሴ የግል ጉዳይ ተጠምጄያለሁ፣ ማንንም ምሰማበት ለማንም የምደነግጥበት ምክንያትም ጊዜም የለኝም። እራሴን ካዳንኩ ለሰውም መድረስ እችላለሁና አሁን ትኩረቴ እራሴና እራሴ ብቻ ነው።" አዎ! ጀግናዬ..! አንዳትሸወድ፣ ከምንም ጉዳይ የሚበልጠው የእራስህ ጉዳይ ነው። ትኩረትህን እራስህ ላይ ብቻ አድርግ። እንትና በዚህ ወጣ፣ እገሌ እንትን በላ፣ እንትና እዛ ገባ የሚሉ ትርኪሚርኪ ወሬዎች ጉዳይ አይደሉም፣ አይመለከቱህም። ወሬ ስታመላልስ ብትኖር ከወሬ ነጋሪነት የዘለለ ሙያ ሊኖርህ አይችልም። ከሰው ጥቃቅን ተግባር በላይ የእራስ ትላልቅ አጀንዳዎች እንዳሉብህ እወቅ። የሰውን ተግባር እያዳነክ፣ ጥቃቅን አጀንዳዎችን እያጎላይ፣ የማይረባ ወሬ እየሰበሰብክ፣ በበሬ ወለደ ዜና እየተገረምክ የእራስህን ህይወት ልትኖር አትችልም። የማይመለከትህን ጉዳይ "አይመለከተኝም!" ብለህ የመመለስን ልምድ ፍጠር፣ ያንተ ጉዳይ ባልሆነ ነገር መብሰልሰል አቁም። ዞር ዞር የምትለው እራስህን ለማሰማር እንጂ በምታየውና በምትሰማው ሁሉ ለመጨነቅ እንዳልሆነ አስታውስ። የእራስህን ህይወት ኑር፣ በቅድሚያ የግል አጀንዳህን ከዳር አድርስ፣ ችግሮችህንም ፍታ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Показать все...
👍 17 3🥰 3🤩 2🔥 1👏 1
ህይወትን በጥበብ መምራት! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/7_BhRxMX5ao?si=VFZuqz8ViQPe_-NO
Показать все...
ለምን በራሳችሁ መተማመን አቃታችሁ? ስለማታውቁት ነገር አታውሩ! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ትኩረታችሁን አትበትኑ! ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivational Video | Ethiopian motivation | amharic motivation | አነቃቂ ንግግሮች | አነቃቂ ምክሮች | inspire Ethiopia | dawit dreams | shanta | daggy's life class | manyazewal podcast | inspire podcast | dawit dreams podcast #making_money #sidehustle #business #ethiopianmotivation #inspire_ethiopia #inspirationalvideo MOTIVATION + DISCIPLINE = UNWAVERING SUCCESS! @mikre_aimro 🔶 ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ይመልከቱ፡ 👇👇 ♦️

https://youtu.be/HntYXoAUrN4

ቪድዮውን ላይክ 👍 ማድረግ እንዳይረሱ! ቻናላችንን ሰብስክራብ ያድርጉ! የደውል ምልክትን ይጫኑ! Comment ያስቀምጡልን!እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏 Social Media: INSTAGRAM:

https://www.instagram.com/epha_aschalew

YOUTUBE:

https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1

FACEBOOK:

https://www.facebook.com/EthioMentalCounsel

TELEGRAM:

https://t.me/MentalCounsel

TIKTOK:

https://www.tiktok.com/@mentalcounsel

Music from #InAudio:

https://inaudio.org/

Track Name. inaudio - Infraction - Action inaudio - Infraction - Majestic Vision inaudio - Infraction - Rebellion motivational አነቃቂ ጥቅሶች አነቃቂ ንግግሮች አነቃቂ ዘፈኖች አነቃቂ አጭር ልቦለድ አነቃቂ ቪዲዮ motivational ethiopia motivational music motivalional motivationalmotivalional motivational speech motivalional songs motivational short story motivational video ethiopia yosan getahun oromo music 2023 motivational videos for students tointerview study hard motivalional songs with lyrics motivate me speaker motivate little mix motivation motivate motivation video motivate molivate motivational eshetu manyazewal motivational manyazewal eshetu manyazewal eshetu in schoolkeysofmoon inspire ethiopia inspire people manyazewalinspire ethiopia new video inspire ethiopia new inspire ethiopia motivation Anki andbet,Manyazewal,Dawit dreams,እነቃቂ,አላማ,Inspire,Motivated,Motivate 2 ethiopia EBS Motivate ethiopia,Inspire Ethiopia,Ethiopia,Success,Motivations,Motivational,Motivation,Manyazewal eshetu,motivational video,motivational speech,motivation,motivational songs,abel birhanu

🔥 5👍 1
ኤቨረስት ሆይ፣ አሸንፍሃለሁ! ፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨ አንድ ሰው ተሸነፈ የሚባለው መቼ ነው?  በቃኝ ብሎ ሲያቆም ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ የለፉለት ነገር ድል ሲቃረብ ተስፋ በመቁረጥ ጥለውት ይሄዳሉ፡፡ በነበራቸው ጥረት ውስጥ ያዳበሩትን ጥንካሬ አያስተውሉትም፡፡ ብዙ ሞክሮ አለመሳካት ያለማቆም እንጂ የማቆም ምክንያት ሊሆን አይገባውም፣ ምክንያቱም በተሞከረው ሙከራ የመጣው ጥንካሬ፣ የባህሪይ ጽናትና የልምምድ ብስለት ከመሞከራችን በፊት የነበረንን የማሸነፍ ብቃት  በብዙ  እጥፍ  ስለሚጨምረው ነው፡፡ ሞክረን ስንሸነፍ፣ ራሳችንን አሻሽለን እንደገና ብንሞክረው እንደምናሸንፈው ማረጋገጫችን እንደሆነ ማወቅ አንዱ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡ ሰር ኤድመንድ ሂለሪ (Sir Edmund Hillary) ለመጀመሪያ ጊዜ የኤቨረስትን ተራራ ጫፍ የረገጠ ሰው ነው፡፡ ይህንን ተራራ በድል ተወጥቶት ጫፍ ከመድረሱ በፊት በነበረው የቀድሞ ሙከራው ቡድኑ ተራራውን መውጣት አቅቶት አንድ ሰው ሞቶባቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ከዚያ አሳዛኝ ሙከራቸው ሲመለሱ በለንደን በነበረው ሪሰብሽን ግብዣ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ ነበር፡፡  ቆሞ ንግግር  ከሚያደርግበት መድረክ ጀርባ የኤቨረስት ተራራ ምስል በትልቁ ተቀምጧል፡፡ በንግግሩ ወቅት ወደዚህ የተራራ ስእል ዘወር በማለት እንዲህ አለ፣ “ኤቨረስት ሆይ፣ አሁን አሸንፈኸናል፡፡ ነገር ግን ጠብቀኝ እመለስና አሸንፍሃለሁ ምክንያቱም አንተ ያው ነህ፣ እኔ ግን አድጌና በርትቼ እመለሳለሁ”፡፡ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ ነበር የሚያስፈልገውን ዝግጅት አድርጎ ቀድሞ ያሸነፈውን ተራራ ሄዶ ያሸነፈው፡፡ “ታላቁ ክብራችን ያለው ባለመውደቅ ውስጥ አይደለም፣ በወደቅን ጊዜ ሁሉ ተነስተን በመቀጠላችን ውስጥ ነው እንጂ” - Ralph Waldo Emerson መራመድ እስካለ ድረስ መውደቅ አለ፣ መነገድ እስካለ ድረስ መክሰር አለ፣ መውደድ እስካለ ድረስ መጎዳት አለ፣ መማር እስካለ ድረስ ፈተና መውደቅ አለ … ይህ የማይለወጥ የሕይወት ህግ ነው፡፡ “ምን ይበላሽ ይሆን?” በሚለው ፍርሃት ታስሮ መንቀሳቀስ አለመቻል በሕይወት እያሉ መሞት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሕይወቴ ያልፍ ይሆናል ብለው ከመፍራታቸው የተነሳ ሕይወትን ሳይጀምሯት ያልፋሉ፡፡ ሕይወት ግን አዳዲስ ነገሮች የሚሞከሩባት፣ ሲሳካ የምንደሰትባት፣ ሳይሳካ ደግሞ ራሳችንን ከወደቅንበት አንስተንና አቧራችንን አራግፈን እንደገና የምንቀጥልባት ጎዳና ነች፡፡ ሕይወት ማለት በዚህ ምድር ላይ “መከሰትና” ምንም ነገር እንዳይደርስብን ራሳችንን መጠበቅ አይደለም፡፡ “ለአደጋ” ሊያጋልጡን የሚችሉትንና ማንነታችንን የሚፈቱትን ነገሮች ከመሞከር ውጪ ሕይወት ባዶ ነች፡፡ ለዚህ እውነታ ልባችንን በመክፈት አዳዲስ “ተራራዎችን” በመውጣት፣ ሰው ያልሞከረውን በመሞከርና በማንነታችን ውስጥ የታመቀውን ድብቅ ብቃት የሚወጣበትን እድል ልንሰጠው የግድ ነው፡፡ 1.  ማድረግ እንዳለባችሁ እያወቃችሁት ከፍርሃት የተነሳ ያላደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው? 2.  እናንተ በሙሉ ልብ እያመናችሁበት ከሌሎች ሰዎች ግፊት የተነሳ ያመነታችሁበት ነገር ምንድን ነው? 3.  ከዚህ በፊት ሞክራችሁ ስላልተሳካ ብቻ ድገማችሁ ላለመሞከር ወስናችሁ የተዋችሁት ነገር ምንድን ነው? /25 የስኬት ቁልፎች መጽሐፍ/ ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Показать все...
👍 19 5🥰 1😁 1🙏 1
ሳታይ አትፍረድ! ፨፨፨///////፨፨፨ ከውድቀት ተነስተው የክፍታውን ጣሪያ የተቆናጠጡ ሰዎች አሉ፤ በድህነት ላይ ተረማምደው የሃብት ማማ ላይ የደረሱ ሰዎች አሉ፤ ችግርን ተጋፍጠው ለውጤት የበቁ ሰዎች አሉ፤ ህመሙን ችለው፣ ስቃዩን ተቋቁመው፣ ጫናውን አልፈው የሚያኮራቸውንና የማይበገረውን ማንነት የገነቡ ሰዎች አሉ። ለድካም ሳይበገሩ፣ ለችግር እጅ ሳይሰጡ የሚፈልጉትን የሰውነት አቋም የገነቡ ሰዎች አሉ። ቀላል ስለሆነ ግን አይደለም፤ ምንም ስለማይፈልግም አይደለም። ስቃዩን፣ ክብደቱን፣ መከራውን ሁሉ ሞክሮ ያየው ብቻ ያውቀዋል። ዋጋው ከባድ ቢሆንም ስላመኑበት እስከጥግ ተጋፍጠው አሳክተውታል። ውጪ ሆኖ ለሚመለከት ግን ሁሉም ነገር ቀላል ይመስለዋል፤ ላልሞከረ ነገሮች ሁሉ ወዲያው የሚገጣጠሙና አልጋ በአልጋ የሚሆኑ ይመስለዋል። ነገሩ ግን እንደሚታሰበው አይደለም። አዎ! ጀግናዬ..! ሳታይ አትፍረድ፤ ሳትሞክር አትናገር። ከየትኛውም ንግግርህ በፊት እውቀትን አስቀድም፤ አዳምጥ፤ መርምር፤ ተረዳ፤ ግፋ ሲልም ሞክረህ እየው። አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ የሰውነቱን አቋም ለማስተካከል የሚጥር ሰው ላይ አስተያየት ለመስጠት እርሱ የሚጋፈጠውን ስቃይ ማየት አለብህ፤ የሚገፋውን ክብደት መሞከር ይኖርብሃል። አንድ በየጊዜው ለተከታዮቹ የሚመጥን ፖሮግራም ለማዘጋጀት የሚጥር ሰው ላይ ህፀፅና ድክመቱን ከማውጣትህ በፊት ሃሳቡን ኬት እንደሚያመጣው፣ ፖሮግራሙን እንዴት እንደሚሰራው፤ ምንያክል ጊዜ እንደሚፈጅበት፣ ምን ምን እንደሚያነብ ለማወቅና ለመረዳት ሞክር። እንደምታስበው ቀላል እንደሆነ የምታውቀው በስራው ውስጥ ስታልፍ ብቻ ነው። አዎ! ማንም የጥረትህን ዋጋ እንዲያሳንሰው እንደማትፈልገው ሁሉ ማንም ለአመታት ለፍቶ ያመጣውን ውጤት ዋጋ አታሳጣው። ይብዛም ይነስም ለፍቶ የሚያድር ሰው የሚለፋ ሰው ላይ አይፈርድም። ሁላችንም የተለያየን ሰዎች ነንና ምርጫችን ይለያያል፣ የሚጥመንና ቅድሚያ የምንሰጠው ነገርም እንዲሁ ለየቅል ነው። አንተ የምትወደውን ነገር ስላላደረገ ስህተት የሚሆን ሰው የለም፤ ባንተ መንገድ ስላልተጓዘ የሚወድቅና ወደኋላ የሚመለስ ሰውም የለም። ለየትኛውም ሰው ምርጫ ክብር ይኑርህ፤ በተለይ በእራሱ መንገድ ለሚጥርና እራሱን ለማሻሻል ለሚደክም ሰው ልባዊና የተለየ ከበሬታህን ለግሰው። ማንም ህይወቱን ለማሸነፍ በየፊናው የሚደክመው ወዶ ላይሆን ይችላል። ህይወት ግን ያለመስራት ምርጫ አትሰጥምና ምንም ነገር መስራቱ የግድ ነው። ከቻልክ ከጀርባ ያለውን ነገር አታውቅምና ማንም ላይ አትፍረድ፤ ካልቻልክ ድግሞ ሳታይና ሳትሞክር ማንም ላይ አትፍረድ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Показать все...
👍 17🥰 3🔥 1
ለራሳችሁ ታዘዙ! 👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏 https://youtu.be/fh3XtKJ-poQ?si=wEKz9MXzSJ1uGEuw
Показать все...
እራሳችሁን አስቀድሙ፤ ሰው በመከተል መንገዳችሁን አትሳቱ! | ድንቅ የህይወት ትምህርት | Inspire Ethiopia | | MIKRE AIMRO

ራሳችሁን አዳምጡ! ፍላጎታችሁን አሳኩ!@mikre_aimro ቪድዮውን 👍 LIKE ስለምታደርጉና ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ስለምትሆኑ ከልብ እናመሰግናለን! Motivational Speech in Amharic | Amharic Motivat...

🔥 4👏 2
ስንብትን ልመድ! ፨፨፨፨//////፨፨፨፨ አዳዲስ ክስተቶች የህይወት ልዩ መገለጫዎች ናቸው፤ ከተለመደው የኑሮ ዘይቤ ስትለይ ውስጥህ ሊረበሽ፣ ቅር ሊልው፣ ምናልባትም የሚገጥሙህ ፈተናዎች ሊያስጨንቁህ፣ የሚጠብቁህ ውጣውረዶችም ሊያሳስቡህ ይችላሉ። እነዚህ ግን አዲስ ከባቢን እንዳትላመድና ከተለየ የህይወት ጉዞ ሊያቅቡህ አይችሉም። አንተ ብቻ ያየሃቸው መዳረሻዎችህ ከእነዚህ ፈተናዎች የተለዩ አልነበሩም፤ አዲሱ ከባቢህ ለአዲስ ፈተና ማጋለጡ እሙን ነው። የሔድክበት ሁሉ አልጋ በአልጋ ላይሆን ይችላል፤ የፈለከው ሁሉ ቀርቦልህ፣ የሚጠቅምህን አግኝተህ ጉዞ እስክትጀምርም ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። እንዲሁ ተመችቶህ፣ ሁሉ ባለበት ሆኖ ግን አንዳች የሚቀየርና የሚያድግ ነገር የለም። አዎ! ጀግናዬ..! ስንብትን ልመድ! መጥፎ ላማዶችህን መለየት ልመድ፤ ጎጂ እይታዎችህን መጣል ልመድ፤ ባላመንክበት አለመጓዝን ልመድ፤ ከተለየ ከባቢ ጋር እራስህን ማስማማት ልመድ፤ ከአዳዲስ ውሳኔዎችህ ጋር ተስማማ። የተሻለ ነገር ለማግኘት፣ ወደ ክፍታው ለመጓዝ ጠንካራ የውሳኔ ሰው ሁን። ስንብትን በመልመድ ለአዲስ መንገድ እራስህን አዘጋጅ። እንኳን ለተሻለ ኑሮ ይቅርና ህይወትን በሙሉ የምትሳነበት ጊዜ ስለመኖሩ አስታውስ። ውጣውረድ ባለበት ምድር የተለመዱ ነገሮችን አለመሰናበት አይቻልም። ለውጥና እድገት፣ ከፍታና ዝቅታ፣ ማግኘትና ማጣት በሚፈራረቅበት ህይወት ለአዲስ ለውጥ እራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ልብህ ካልወሰነ፣ አንጀትህ ካልቆረጠ፣ መጨከን ካልቻልክ ስለ አንተነትህ እውነተኛ ሃይል ልታውቅ አትችልም። አዎ! ብዙ አደጋ ይጋረጥብህ፣ ለፈተናዎች ተጋለጥ፣ ስቃይ ይብዛብህ ነፃነትህን ፍለገህ፣ ዘላቂ ምቾትን መርጠህ ግን ሁሉን የመቋቋምና የማለፍ ብርቱ ሃይል እንደለህ እወቅ። የተለየ መንገድ በመረጥክ ቅፅበት ብዙ የምታጣቸውና የምትለያቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ልማዶች አሉ። የልዩነትህ ውጤትም ለተሻለ ነገርና ለአመርቂ ውጤት ነው። ባለህበት ቦታ ነገሮች የማይቀየሩ ከሆነ መተው ያለብህን መተው፣ መለየት ያለብህን መለየት፣ እንዲሁም ማቆም ያለብህን ማቆም ይኖርብሃል። ስንብት ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ ትርጉም ከሌለው ቆይታና ከውጤት አልባ በላይ ግን አይከብድም። ባለህበት ሆነ ተፈጥሮ የምታድለህ፣ ሰውነትህ የሚለግስ ብርቱ ሃይል ይኖራል፣ ይህም አዲስን ተግባር ትላመድ ዘንድ፣ የተሻለ ከባቢን እንድፈጥር፣ ከፍ እያልክ፣ እያደክ፣ እየተቀየርክ እንድትሔድ ያደርግሃል። አጉል ልማድህን መሰናበት ልመድ፣ የማይጠቅሙህ ሰዎችን የመለየት ድፍረት ይኑርህ፣ አሉታዊ እሳቤዎችህን የመተው ልማድ አዳብር። በአዲስ እርምጃ አዲስ ከባቢን ፍጠር። ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 (Epha A.) ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋 🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን! SUBSCRIBE NOW! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1 ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪
Показать все...
👍 22 6🔥 2

👍 14 13🔥 2👏 2