cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Больше
Рекламные посты
114 610
Подписчики
+8724 часа
+9147 дней
+3 20130 дней
Архив постов
በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በአሸናፊ ከበደ የክዋኔ ጥበባት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመታደሜ ደስ ብሎኛል። አሸናፊ ከበደ ከያኒ ብቻ ሳይሆን የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ነበር። የአዲሱ ማዕከል ዳይሬክተር ግርማ ይፍራሸዋ ደግሞ በቀደመው እና በአሁኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃ መካከል ድልድይ በመሆን ያገለግላል። ይህን መሰል ድልድይነት እና ቀጣይነት በሁሉም ተቋሞቻችን አስፈላጊ ነው። ሙዚቃ ኃይል አለው። ይህን ኃይል ለወጣቶቻችን አብርሆት ልንጠቀምበት ይገባል። ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይህን ዐቅም በምሉዕነት መጠቀም ይገባናል። I am pleased to witness the inauguration of the Ashenafi Kebede Performing Arts Center at the Yared School of Music. Ashenafi Kebede was not only an artist but also the first director of the Yared Music School. The new center’s director, Girma Yifrashewa, serves as a bridge between the past and the future of music in Ethiopia. Such continuity and linkage are essential in all our institutions. Music is powerful, and we must use this power to enlighten our youth. The arts play a vital role in shaping future generations and enhancing our city’s capacity to attract tourism. We must fully utilize this potential.
Показать все...
05:36
Видео недоступноПоказать в Telegram
Singapore ቆይታ
Показать все...
106.62 MB
ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በኢስታና ላደረጉልኝ አቀባበል አመሰግናለሁ። በቅርቡ ለጀመሩት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነትም እንኳን ደስ አለዎ ለማለት እፈልጋለሁ። ሁለቱ ሀገሮቻችን እርስ በርስ የሚማማሩት ብዙ ጉዳይ አለ። የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታችንን ከፍ ለማድረግ፣ በአቅም ግንባታ፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በላቀ የማኑፋክቸሪንግ ስራ እና ቱሪዝም ልማት ትብብራችንን ለማጠናከር ተስማምተናል። የወዳጅነት ትብብራችንን ይበልጥ ለማስፋት የምንሰራም ይሆናል። Thank you to Prime Minister Lawrence Wong for the warm reception today at the Istana. I also take this opportunity to congratulate him for recently assuming office. Our two nations have a lot to learn from each other and we have agreed with President Wong to enhance our people to people ties; capacity development; civil service cooperation; technology; advanced manufacturing and tourism development. I look forward to building on this partnership.
Показать все...
ዛሬ ከሲንጋፖር ፕሬዝዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር በኢስታና ተገናኝተን በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ በመለዋወጣችን ደስ ብሎኛል። የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር ተስማምተናል። Pleased to meet Singapore President Tharman Shanmugaratnam today at the Istana, where we exchanged views on political, economic, and social issues. We agreed on the need to strengthen our bilateral relations and explore new areas of cooperation.
Показать все...
08:10
Видео недоступноПоказать в Telegram
ደቡብ ኮሪያ እና አፍሪካ South Korea and Africa
Показать все...
43.55 MB
03:55
Видео недоступноПоказать в Telegram
የደቡብ ኮሪያ ቆይታ South Korea
Показать все...
313.31 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
ማንበብ ባህል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው። የንባብን ባህል ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው። በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ለ አንድ መቶ ቀናት ንባብን ሲያበረታታ ቆይቷል። ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ። መጪው ክረምት ነው። ብዙ ወጣቶች ዕረፍት ላይ ይሆናሉ። ጊዜያቸውን በንባብና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያሳልፉ በብርቱ ልንሠራ ይገባል።
Показать все...
ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ለአደረጉልን አቀባበል አመሰግናለሁ። የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ ትስስር ከስድሳ አመታት በላይ ያስቆጠረ ነው። የመጪው ጊዜ ግንኙነታችንም የበለጠ ጠንካራ እና ዘርፈ ብዙ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ የፀና ነው። Thank you President Yoon Suk Yeol for receiving us today. Our countries share a long history spanning over six decades, rooted in Ethiopia's support during the Korean War. I am confident that we will work together to further enhance our partnership.
Показать все...