cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethiomix❤️🎁

Join us in telegram =>For new wallpapers, motivation quotes, psychological quotes,life style, drawing , Instagram photos...... For cross promotion @mercyamy And @amennbe

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
179
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል። ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦ 1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል። 2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል። (ትምህርት ሚኒስቴር) @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል። በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል። ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል። ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል። በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል። በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል። በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል። ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል። ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል። በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል። ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል። ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር @tikvahethiopia
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ። ንግድ ባንክ " መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም " ብሏል። ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም #ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ገልጿል። የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ተገልጿል። ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውን እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ብሏል ባንኩ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለው ትክክል እንዳልሆነ ባንኩ ገልጿል። " ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት ፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ " ሲል ማሳወቁን #ሸገር_ኤፍ_ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ ደንበኞቹ እስከ መጋቢት 2 ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ ከመጋቢት 2 በኃላ ግን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ እንዲሁም የATM እና የፖስ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ብሎ እንደነበር አይዘነጋም። @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ ይንራል " - ፑቲን የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በቴሌቪዥን በተላለፈ ስብሰባ ላይ ምዕራባውያኑ በሀገራቸው ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ ዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንር እንደሚያደርግ አስጠንቅቀዋል። ሩስያ ከዓለም ሀገራት በማዳበሪያ አምራችነቷ ከቀዳሚዎቹ መካከል ትመደባለች። ፑቲን ሩሲያና ቤላሩስ በዓለም ትልልቆቹ የማዳበሪያ አቅራቢዎች መሆናቸው ተናግረው " ለዕቃዎቻችን አቅርቦት የፋይናንስና ሎጂስቲክስ ችግር መፍጠራቸውን ከቀጠሉ ዋጋው ይጨምራል። እናም ይህ በመጨረሻው ምርት ፣ በምግብ ምርቶች ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል " ሲሉ ተደምጠዋል። ከዚህ ባለፈ ፕሬዜዳንቱ ሀገራቸው እየተጣለባት ባለው ማዕቀብ የሚፈጠረውን ጫና ተቋቁማ እንደምታልፍ ገልፀው " ምዕራባውያኑ እየጣሉ ያሉት ማዕቀብ መጨረሻው ነፃነታችንን ፣ ራሳችንን መቻል እና ሉዓላዊነታችንን ያጠናክረዋል፤ ይጨምረዋል " ብለዋል። ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ ፈፅማለች ያሉት ምዕራባውያን እስካሁን ሩስያን ያዳክማል ያሉትን ማዕቀብ ሁሉ ያወረዱባት ሲሆን አሁንም ተጨማሪ ሌሎች ማዕቀቦችን ለመጣል እያውጠነጠኑ ነው። የሃያላኑ ሀገራት ግብግብ በታዳጊ ሀገራት ላይ እያሳደረ ያለው ጫና ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ነው። @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ተፈርዶባታል ናዝራዊት አበራ በቻይና ሀገር ያለአግባብ ከዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ እንድትከሰስ እና እንድትታሰር ያደረገቻት ጓደኛዋ ስምረት ካህሳይ አንተሀቡ ላይ የቅጣት ዉሳኔ ተላልፎባታል። ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የካቲት 25/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው። ስምረት በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ነው የተወሰነው። ስምረት ካህሳይ በአሁን ሰዓት #ተሰውራ እንደምትገኝ የተገለፀ ሲሆን ፍ/ቤት የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ ወደ ውጭ ሀገር ስትወጣ ወይም ሀገር ውስጥ ስትገባ ተከታትሎ በመድረስ ለፌደራል ፖሊስ አሳልፎ እንዲሰጥና የፌደራል ፖሊስ ተከሳሿን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር ተከሳሽ ስምረት ያለችበትን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ከፍትህ ጎን በመቆም ለፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ እንደያደርግ አሳስቧል። ናዝናዊት ላይ የሆነው ምንድነው ? ጓደኛዋ ስምረት ህዳር 2011 ወደ ሀገር ያስገባችውን 5 በሻምፖ እቃ የታሸገ ኮኬን ዕፅ ለናዝራዊት ወደ ቻይና አብረን እንሂድ ብላ በማግባባት ቪዛ እና የአየር ትኬት ካስጨረሰች በኋላ ታህሳስ 11/2011ዓ.ም ለናዝራዊት አበራ የሂውማን ሄር ማጠቢያ ነው ቻይና ውሰጅልኝ ብላ ከላከቻት በኋላ እሷ የአባቷን ሞት ምክንያት በማድረግ ትቀራለች፡፡ ናዝራዊት ቻይና ደርሳ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባት ፍተሻ የያዘችው 5 ሻምፖ መሰል 5 ኪ.ግ የሚመዝን የኮኬን ዕፅ መሆኑ ተደርሶበት ለእስር ተዳርጋለች። በዚህም ነው ስምረት ክስ ተመስርቶባት ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር ገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ የተወሰነው። ያንብቡ፦ telegra.ph/JM-03-09 ፎቶው ፦ የናዝራዊት @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba📍 የምግብ ዘይት በ #መፀዳጃ_ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ። በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል። ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል። ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን "ሌባን ሌባ " ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል። በአግባቡ በስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፍቃድ መሰረዝን ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች ይወሰዳል ሲል ክፍለ ከተማው አስጠንቅቋል። @tikvahethiopia
Показать все...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
Фото недоступноПоказать в Telegram
#AmharaRegion ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህፃናት ህይወት ጠፋ። በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውኃ በተባለ ቀበሌ ለመንገድ አገልግሎት የተቀመጠ ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናት ህይወት ማለፉን አሚኮ የወረዳውን ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። አደጋው የተከሰተው በቀን 27/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ገደማ ነው። አደጋው የተከሰተው በሱር ኮንስትራክሽን አማካኝነት ሲሰራ በነበር የመንገድ ፕሮጀክት የቁሳቁስ ካምፕ ላይ ሲሆን በዚህ ውስጥ የአካባቢው ህጻናት ለጭዋታ ሲገቡና ሲወጡ እንደነበር ፓሊስ ገልጿል። ፖሊስ ኅብረተሰቡ ህጻናት ወደ ካምፑ እንዳይገቡና ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል። @tikvahethiopia
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Aye Ethiopia
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.