cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️

"ይህ በደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የመሰረተ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ። መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት @narrrry @Yidna https://www.facebook.com/MHiwot2

Больше
Рекламные посты
583
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-1230 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#ጰራቅሊጦስ "ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል" (ዮሐ.፲፬፥፲፮) እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ! የቤዛነት ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲያርግ ለሐዋርያት የሰጣቸው ተስፋ አጽናኝና የእውነት መንፈስ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን አብ እንደሚልክላቸው፣ እርሱም አጽናኝ የሆነ ጰራቅሊጦስ እንደሆነ ለዘለዓለሙም ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ነግሯቸው ነበር፡፡ ጌታችን እንደተናገረውም በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ባረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሣ ደግሞ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ‹‹ወአነ እስእሎ ለአብ ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ ካልአ ዘይሄሉ ምስሌክሙ ለዓለም፤ እኔም አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ ሌላ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል›› እንዲል፡፡ (ዮሐ.፲፬፥፲፮) ይህንንም መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን ቀን በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን እናከብረዋለን፤ ከጌታ ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፡፡ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ወይም ለመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ሌላኛው ስሙ እንደሆነ ከርእሳችን እንረዳለን፡፡‹‹ጰራቅሊጦስ መንፈሰ አብ ወወልድ ስቡሕ፤ ጰራቅሊጦስ የተመሰገነ የአብና የወልድ መንፈስ ነው›› በማለት አምላክነቱን በአንድነት በሦስትነት ጸንቶ የሚኖር እውነተኛ አምላክ፣ ከአብ የሠረጸ የእውነት መንፈስ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ (ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ) ጰራቅሊጦስ ማለት ‹‹መንፈስ ቅዱስ፣ አጽናኝ፣ አስታራቂ፣ አሳምሮ የሚያናግር ማለት ነው›› ይላል፡፡ (ሕያው ልሳን) አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ‹‹ጰራቅሊጦስ›› ማለት ‹‹ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፍስሒ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በዓለ ሃምሳ፣ የትንሣኤ ሃምሳኛ፣ የዕርገት ዐሥረኛ፣ እሑድ ቀን የሚውል ወዘተ…›› እያሉ ይተረጉሙታል፡፡ (ገጽ ፱፻፯) በጥቅሉ ጰራቅሊጦስ ማለት መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያዘኑትን የሚያጽናና፣ የራቁትን የሚያቀርብ፣ የተሰወረውን የሚገልጥ፣ የረቀቀውን የሚያጎላ፣ የተከፉትን የሚያስደስት፣ ለመምህራን አንደበት የሆነ መጽንዒ፣ የሚያጸና፣ መንጽሒ የሚያነጻ ኃጢአትን ይቅር የሚል የሚደመስስ የእውነት መንፈስ፣ የእውነት አምላክ ነው፡፡ ጌታችን እርሱን እስኪልክላቸው ኃይልን ብርታትን እስኪላበሱ አላዋቂዎችን አዋቂ የሚያደርግ ከሣቴ ምሥጢር፣ ፈሪዎችን ደፋር (ጥቡዓን) የሚያድርጋቸው፣ በአሕዛብ በዓላውያን ፊት ያለ ኀፍረት፣ ያለ ፍርሃት እንዲመሰክሩ፣ በእሳቱ፣ በስለቱ እንዳይሸማቀቁ የሚያደርጋቸውን የእውነት መንፈስ እንደሚልክላቸውና እርሱም ለዘለዓለሙ አብሯቸው እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ እንዲህም ብሏቸዋልና፤ ‹‹ዘኢይክል ዓለም ነሢኦቶ፤ ዓለም እኔን ለሕማም ለሞት አሳልፎ እንዲሰጠኝ ለሕማም ለሞት አሳልፎ ሊሰጠው የማይቻለው፤ እስመ ኢይሬእዮ ወኢየአምሮ፤ አያየውም፤ አያውቀውምና፤  ወአንትሙሰ ተአምርዎ፤ እናንተ ግን ታውቁታላችሁ፤ አድሮባችሁ ይኖራልና በውስጣችሁም ይኖራልና፡፡›› አድሮባቸው የሚኖረውን፣ ሕማመ ሥጋ፣ ድካመ ሥጋን የሚያርቅላቸውን፣ የምሥራቹን ለዓለም ሁሉ የሚያደርሱበትን ኃይል ጸወን የሚሆናቸውን እውነተኛ የሆነ የራሱንና የአባቱን መንፈስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ባረገ በዐሥረኛው ቀን በዕለተ እሑድ ጰራቅሊጦስ  የተባለውን የእውነት መንፈስ ላከላቸው፡፡ እርሱ የእውነት መንፈስ ነው አለ፤ የሐሰት መንፈስ አለና ሲለይ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በ፻፳ው ቤተ ሰብ ላይ እንደወረደ፡- ‹‹እንዘ ሀለዉ ኩሎሙ ኅቡረ አሀተኔ መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምፅ ከመ ድምፀ ነፋሰ ዓውሎ፤በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጉዶ ተሰማ …›› (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስትና ሰባ ሁለቱ አርድእት መቶ ሃያው ቤተ ሰብ በኅብረት በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም፤ እናንተ ግን ከሰማይ ኃይል እስክትለብሱ ማለትም ሰማያዊ ሀብትን፣ ሰማያዊ ዕውቀትን፣ ሰማያዊ ኃይልን እስክትለብሱ  በኢየሩሳሌም ቆዩ››  ብሏቸው ነበርና በኅብረት ይኖሩና፣ በኅብረት ይጸልዩ፣ የተስፋውንም ቃል ይጠብቁ ነበርና ድንገት በተሰበሰቡበት እንደ ዓውሎ ነፋስ ያለ ታላቅ ድምፅ አሰምቶ የተቀመጡበትን ቤት ሞላው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፪) ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት መስሎም ታያቸው፤ በሁላቸውም ላይ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፡፡ በዚህም ኃይል የሚሆናቸውን፣ ሀብት የሚሆናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ ሁሉም በየራስ በየራሳቸው ሰባ ሁለት ቋንቋ መናገር ጀመሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያትና በሌሎቹ ላይ እንደ ነፋሰ ዓውሎ ሆኖ ነው የወረደው፡፡ ምክንያቱም ነፋስ ረቂቅ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም ረቂቂ ነውና፤ ነፋስ ኃያል ነው፤ ፍሬውን ከገለባው ይለያል፤ መንፈስ ቅዱስም ጻድቃንን ከኃጥአን ይለያልና፡፡ ነፋስ በምልዓት ሳለ አይታይም፤ አይታወቅም፤ ነገር ግን የሚታወቀው ባሕር ሲያናውጥ፣ ዛፍ ሰያወዛወዝ፣ ቅጠሉን ሲያረግፈው፣ አቧራውን ሲያስነሣው በሥራው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም በምልአት ሳለ አይታወቅም፤ ነገር ግን ቋንቋ ሲያናግር፣ ምሥጢር ሲያስተረጉም ይታያልና፡፡ ነፋስ መዓዛ ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስም መዓዛ ጸጋን ያመጣልና በነፋስ ተመስሎ ወርዷል፡፡ ሰባ ሁለት ቋንቋ ሲናገሩም ከልዩ ልዩ ቦታ የተሰበሰቡና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ አይሁድ በዚያ (በኢየሩሳሌም) ነበሩና አደነቁ፤አንዳንዶቹ እንዲያውም ግራ ተጋብተው ‹‹እነዚህ ሰዎች ሁላቸውም የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንደምን እንሰማቸዋለን›› እያሉ ያደንቁ ነበር፤ አንዳንዶቹ ግን ይስቁባቸው ነበር፡፡ምክንያቱም ከከተማ የመጡ እኩያን አይሁድ ሰቃልያነ አምላክ  ናቸውና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ላለማድነቅ በሐዋርያት ላይ ሳቁባቸው፤ ‹‹እሊህ ያልፈላ ጉሽ ጠጅ ጠጥተው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› ብለው ተሳለቁ፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፲፫) እንደ እውነቱ ከሆነ ያልፈላ ጉሽ የወይን ጠጅ የጠጣ፣ ጠጥቶም የሰከረ ሰው፣ እንኳን የማያውቀውን ቋንቋ ሊናገር ቀርቶ የሚያውቀውንም በተናገረው አይናገረም፤ ስካር አንደበትን ያስራል፤ ትንፋሽን ያሳጥራል እንጂ አዲስ ቋንቋ፣ ሁላቸውም የሚሰሙት የሀገራቸውን ቋንቋ ሊናገሩ አይችሉም ነበር፡፡ አይሁድ ግን ክፉዎች ነበሩና እውነቱን መቀበል አይሹም፡፡ የዘመናችን መናፍቃንም ወንጌል ተከድኖባቸው፣ እውነቱ ተሸፍኖባቸው፣ በዕውቀት የተራቀቁትን፣ መንፈስ ቅዱስ ተመልተው ምሥጢር የሚያመሠጥሩትን፣ ክብሩን የሚገልጡትን በመንፈስ ቅዱስ የሚመሩ መምህራንን፣ ሊቃውንትን እንደሚያቃልሉትና እንደሚያሾፉ ዓይነት ማለት ነው፡፡ ግን ጊዜው የስካር አይደለም፤ ምክንያቱ ገና ንጋት (ነግህ) ነውና፤ ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረው ቢፈጸም ነው እንጂ፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ መንፈሴን አሳድርበታለሁ›› ያለው ጌታ አስቀድሞ በነቢዩ የተናገረው ትንቢት መፈጸሙ የእግዚአብሔር መንፈስ በእነርሱ ላይ ስለ መውረዱ አዲስ ዕውቀትን እንደገለጠላቸው ነገራቸው፤ ገሠጻቸው፤ ስለ ጌታችን ወደዚህ ዓለም መምጣት፣ አይሁድ ግን በክፋት እንደሰቀሉት፣ እርሱ ግን በሥጋ ሞቶ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ስለ መነሣቱና ስለማረጉ ለዚህም ምስክሮቹ መሆናቸውን ጭምር ሰበከ፡፡
Показать все...
በዚህ ስብከት ልባቸው ተነካ፤ ጴጥሮስንና ሌሎእንም ‹‹ምን እናድርግ›› አሏቸው፡፡ ጴጥሮስም ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይሰረይላችሁ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ›› አላቸው፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፪፥፭-፴፰) ቋንቋ የሚያናግረውን፣ በጥበብና በዕውቀት የሚሞላውን፣ በሀብቱ ስቦ በረድኤት አቅርቦ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ የኃጢአት ስርየትም የሚገኝበትን በክርስቶስ አምኖ በመጠመቅ የሚገኘውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንዲቀበሉ መከራቸው፡፡ ቃሉንም የሰሙ፣ ሰምተውም ያመኑ ብዙ ነፍሳት ተጠመቁ፤ ቁጥራቸውም ሦስት ሺህ ያህል ነበሩ፡፡ እናም በዓለ ጰራቅሊጦስ እያልን ከዕርገት በዐሥረኛው ቀን፣ ከትንሣኤው በሃምሳኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ በዓል መሠረቱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሰማያት የወረደበት፣ ለጌታ ቤተ ሰቦች የተገለጠበትና በእያንዳንዳቸው ላይ ያደረበት፣ በዚህም ሕይወት የሚሰጠውን አምላካዊ ዕውቀት ያገኙበት፣ ዓለምን ተዘዋውረው ያስተምሩበትና ተአምራት መንክራት ያድርጉ ዘንድ ሕዝቡንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚጠሩበትን የዓለም ቋንቋ የገለጠበት፣ በዚህም የመንፈስ ቅዱስን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት ልባቸው የተነካ ብዙዎች በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የተጠመቁበትና ወደ በረቱ የተሰበሰቡበት ድንቅ የተአምራትና የምሥጢር ቀን በመሆኑ እንድናከብረው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡ መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት ‹‹በበዓለ ሃምሳ ሥራ አትሥሩ፤ ነገረ ክርስቶስን ባመኑ ምእመናን ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ ተገልጦበታልና›› ይላል፡፡ (ፍት.ነገ.አን.፲፱፥፯፻፵) እናም እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ታላቅ የበረከት በዓል፣ ይህንን የተቀደሰ ቀን ስናከብረው እንዴት ይሆን? በወይን ጠጅ ሰክረን ወይስ ኃጢአታችን ይሰረይልን ዘንድ ንስሓ ገብተን ወይስ በሌላ ሁኔታ? ጰራቅሊጦስ ነፍስና ሥጋን የሚያጸና፣ ለንጹሐን የክብር አክሊልና ሞገስ ነው፤ ይህን የእውነት መንፈስ በእኛ ላይ ያድር ዘንድ፣ ስብራታችን እንዲጠገን፣ ጎደሏችን እንዲሞላ፣ ድንቁርናችንን እንዲያስወግድ፣ ከኀዘናችን እንዲያጽናናን፣ እንለምነዋለን ወይስ በምግበ ሥጋ ተጠምደን ጨለማውን የማያርቀውን ዕውቀት የማይገልጸውን፣ ኀዘንና ትካዜ የሚጨምረውን የበዓል አከባበር እናከብራለን? ራሳችንን እንድናይ፣ ንስሐን የሚቀበል፣ ኃጢአትንም ይቅር የሚል፣ የሚያነጻ መንፈስ (ጰራቅሊጦስ) በእውነት ይርዳን! ተቀድቶ የማያልቅ የዕውቀት መጠጥ ነው፤ ምሥጢር ገላጭ በመሁኑ ምሥጢሩን እንዲገልጽልን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ያድር ዘንድ አእምሮውን፣ ማስተዋሉን እንዲሰጠን መልካም ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Показать все...
🎲 Quiz 'ስለ ቅዱስ ዮሐንስ እንወቅ' ይህ በየሳምንቱ ከቅዱስ ዮሐንስ ህይወት ታሪክ አውጥተን ከምንልካቸው ጥያቄዎች አምስተኛው ክፍል ነው:: በየሳምንቱ ጥያቄዎችን በመስራት እንድትሳተፉ እንጋብዛለን 🖊 6 questions · ⏱ 1 min
Показать все...
Start this quiz
Start quiz in group
Share quiz
#ዮሐንስን_እንወቅ ንጉሡ ርጉም ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት ሄሮድያዳን በማግባቱ መምህር ወመገሥጽ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ሄዶ ንጉሡን ‹‹የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም›› ብሎ ገሠጸው፡፡ ስለሌላውም ክፉ ሥራው ሁሉ ይዘልፈው ስለነበር ንጉሡ ቅዱስ ዮሐንስን አሠረው፡፡ በንጉሡም የልደት በዓል ቀን ትልቅ ድግስ አዘጋጅቶ የገሊላን መኳንንት፣ ሹማምንቱን፣ መሣፍንቱን ሁሉ ጠራቸው፡፡ የሄሮድያዳም ልጅ ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች፡፡ የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በጽኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ ‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?›› እያለ በመሐላ በጠየቃት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ የንጉሡም ወታደሮች የዮሐንስ ራሱን ቆርጠው በወጭት አድርገው ለዚያች ዘፋኝ ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጧት፡፡ እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠቻት፣ እናቷም በዮሐንስ ራስ ላይ ክፉ ልታደርግ ወዳ ነበር፣ "ንጉሡን እና እመቤቲቱን በአደባባይ ታዋርጂ የነበርሽ ምላስ፣ ይህ ንጉስን እና እመቤትን የሚደፍር ምላስሽ፣ ትዕቢትሽ እና አለብላቢነትሽ ዛሬ ወዴት አለ?" እያለች በሰፌድ መስፊያዋ ምላሱን ልትወጋ ስትል የዮሐንስ ራስ ዕለቱን ክንፍ አውጥታ ከሄሮድያዳ እጅ ላይ ተነሥታ ወደ አየር ስለበረረች ታላቅ ድንጋጤ ሆነ፡፡ ደግሞም የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ እየበረረች እንደቀድሞ ‹‹ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም›› እያለች በመጮህ ዘለፈቻቸው፡፡ በሌሊትም እየመጣች ትዘልፋቸው ነበር፡፡ የዮሐንስም ራስ እስከ 15 ዓመት ድረስ እየበረረች ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዓረቢያ ምድር ዐርፋ በዚያው ተቀበረች፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ መጥምቁ ለሁለት ክርስቲያኖች ተገልጦላቸው የከበረች ራሱ ያለችበትን ነግሯቸው ከተቀበረችበት እንዲያወጡ ነገራቸው፡፡ ይኸውም ከተቀበረችበት ቦታ የተገኘችው በየካቲት 30 ቀን ነው፡፡
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ዮሐንስን_እንወቅ ክፍል ፭: የዮሐንስ ራስ
Показать все...
#ዮሐንስን_እንወቅ ንጉሡ ርጉም ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊጶስን ሚስት ሄሮድያዳን በማግባቱ መምህር ወመገሥጽ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ሄዶ ንጉሡን ‹‹የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም›› ብሎ ገሠጸው፡፡ ስለሌላውም ክፉ ሥራው ሁሉ ይዘልፈው ስለነበር ንጉሡ ቅዱስ ዮሐንስን አሠረው፡፡ በንጉሡም የልደት በዓል ቀን ትልቅ ድግስ አዘጋጅቶ የገሊላን መኳንንት፣ ሹማምንቱን፣ መሣፍንቱን ሁሉ ጠራቸው፡፡ የሄሮድያዳም ልጅ ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች፡፡ የሄሮድያዳ ልጅ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገ፡፡ እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በጽኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ ‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?›› እያለ በመሐላ በጠየቃት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ የንጉሡም ወታደሮች የዮሐንስ ራሱን ቆርጠው በወጭት አድርገው ለዚያች ዘፋኝ ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጧት፡፡ እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠቻት፣ እናቷም በዮሐንስ ራስ ላይ ክፉ ልታደርግ ወዳ ነበር፣ "ንጉሡን እና እመቤቲቱን በአደባባይ ታዋርጂ የነበርሽ ምላስ፣ ይህ ንጉስን እና እመቤትን የሚደፍር ምላስሽ፣ ትዕቢትሽ እና አለብላቢነትሽ ዛሬ ወዴት አለ?" እያለች በሰፌድ መስፊያዋ ምላሱን ልትወጋ ስትል የዮሐንስ ራስ ዕለቱን ክንፍ አውጥታ ከሄሮድያዳ እጅ ላይ ተነሥታ ወደ አየር ስለበረረች ታላቅ ድንጋጤ ሆነ፡፡ ደግሞም የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ እየበረረች እንደቀድሞ ‹‹ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም›› እያለች በመጮህ ዘለፈቻቸው፡፡ በሌሊትም እየመጣች ትዘልፋቸው ነበር፡፡ የዮሐንስም ራስ እስከ 15 ዓመት ድረስ እየበረረች ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዓረቢያ ምድር ዐርፋ በዚያው ተቀበረች፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ መጥምቁ ለሁለት ክርስቲያኖች ተገልጦላቸው የከበረች ራሱ ያለችበትን ነግሯቸው ከተቀበረችበት እንዲያወጡ ነገራቸው፡፡ ይኸውም ከተቀበረችበት ቦታ የተገኘችው በየካቲት 30 ቀን ነው፡፡
Показать все...
💥💥💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💥💥 የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች ምዘና መርሐግብር!!! የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት አንድነት በዘንድሮው 2016 ዓ.ም በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ  በሀገረ ስብከት ደረጃ ትምህርታቸውን #ከ120 በላይ በሚሆኑ አጥቢያዎች ሲከታተሉ የነበሩ #የ4ኛ#የ6ኛ እና #የ10ኛ  ክፍል ተማሪዎች ብዛታቸው #ከ12000 (ከአስራ ሁለት ሺህ) በላይ የሆኑ ተማሪዎችን በሀገረ ስብከት ደረጃ ምዘና ይሰጣል። በዚሁ መሠረት👇 👉  ሰኔ 23/2016 የናሙና (ሞዴል) ምዘና ፤ 👉  ሐምሌ 21/2016 የማጠቃለያ ምዘና የሚሰጥ ሲሆን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎቻችሁን ስታስተምሩ የነበራችሁ ሰንበት ት/ቤቶች በሙሉ ለዚሁ ምዘና ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ የአንድነቱ ትምህርት ክፍል ያሳስባል። #የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት 💥💥💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💫💫💫💫💫💫💥💥💥💥💥💥💥
Показать все...
👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው!!! ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 የሰንበት ትምህርት ቤት መማሪያ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው። በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በመሉ ትግበራ ላይ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 መጻሕፍትን የያዙ በ4 ጥራዝ የተዘጋጁ መጻሕፍትን ሕትመት ተጠናቆ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ የየመምሪያውና የድርጅት ኃላፊዎች፣ ከየሀገረ ስብከቱ የሚወከሉ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች እና የአዲስ አበባ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት አመራር አባላት በታላቅ ድምቀት ሰኔ 16 2016ዓ.ም በበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰንበት ት/ቤቶች ቀን ያስመርቃል። 13ኛው ዓለም አቀፍ ሰንበ ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ከሰኔ 15 እስከ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል። 👉 የመማሪያ መጻሕፍቱ #የ4ቱም ጥቅል ዋጋ #ብር_2000 ሲሆን ሰንበት ት/ቤቶች መግዛት የምትችሉትን የመጻሕፍት ብዛት ቀድማችሁ በደብዳቤ ለአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል እንድታሳውቁ እናሳስባለን።
Показать все...
👍 1
እንኳን #ለ13ኛው ዓለም አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!!! "በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።" {ሐዋ 9፡31} በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ 13ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነው ዓመታዊው የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የፊታችን #ሰኔ_15_እና_ሰኔ_16_2016_ዓ_ም በበዓለ ጰራቅሊጦስ ቀን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ይከበራል። #በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኙ የሁሉም አጥቢያዎች የሰንበት ት/ቤት ሥራ አመራር እንዲሁም የየክፍለ ከተማው አንድነት የሥራ አመራሮች በሙሉ በሁለቱም ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንድትገኙ ፤ #ከየሰንበት ት/ቤቱ የምትወከሉ አባላት ልብሰ ስብሐታችሁን በመልበስ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በመዝጊያው መርሐ ግብር ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል። ሰኔ 16/2016 በዚሁ ዕለት በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በሙሉ ትግበራ ላይ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ6 የትምህርት ዓይነት የተዘጋጁ 23 መጻሕፍትን የያዙ በ4 ጥራዝ የተዘጋጁ መጻሕፍት ሕትመት ተጠናቆ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የመንበረ ፓትርያርክ የየመምሪያውና ኃላፊዎች፣ ከየሀገረ ስብከቱ የሚወከሉ የሰንበት ት/ቤት አንድነት አመራሮች እና የአዲስ አበባ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት ሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚህች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት ፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና ቅዱስ ባሕራንን የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን። በረከቱም ትድረሰን ፤ የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
Показать все...
5
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.