cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

tez bez😂😂😂

JOIN US 😘😘 @OLLIFEN 💞💞 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓💓 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
145
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🌿ወጣትነት ማለት...✍ ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! ✍ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም! ✍ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም... ✍ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው። ✍ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...። ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 ┄┉┉✽‌»‌✨🌹✿🌹✨»‌✽‌┉┉┄               #ያለው_ፍሰሀ ነኝ  ╔═══❖•✨🌺✨•❖═══╗ #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ            ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️
Показать все...
አንዴት ብሎ አንደሚነገርሽ ቃላት ጠፋው አፌ ሚልሽ ባጠበቂም ምላሽ ከኔ ታውቂዋለሽ ፍቅሬን ካይኔ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показать все...
2.69 KB
​​​​​​ ┈┈••◉❖◉●••┈ ካንቺ ጋራ ስሆን🌺 ❣ :¨·....................:¨: ❣ የኔ አለም አዳምጪኝ 🌺 ካንቺ ጋራ ስሆን..... ፍቅርሽን ሳጣጥም ፣ አይኖቼ በፍቅር ፡ ከአይኖችሽ ሲገጥም ፤ ካንቺ ጋራ ስሆን .... ♥ ንፋሳት ሁልጊዜ ፡ በፍቅር ያዜማሉ ፣ አይገርምም የኔ ዉድ ፡ እኔና አንቺ ሊያዩ ፣ ዥረቶች ለአፍታ ፡ ጉዞ ያቆማሉ ፣ ክዋክብት, ጨረቃ ፡ በኛ ይቀናሉ ፡፡ 'ካንቺ ጋራ ስሆን' ..... ♥ ምሽቱ ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣ አስቀያሚው ያምራል ፣ ጨለማው ያበራል ፡፡ ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣ ህይወቴ በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች ካንቺ ጋራ ስሆን ♥ አለም ለኔ እንዲህ ነች፡፡
Показать все...
ዉዴ ልዮ🥰 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показать все...
4.99 KB
ስወድህ ስወድህ😢😢😢🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Показать все...
4_5895771456272336648.ogg1.76 KB
'' ፃፈዉ ስምሽን'' ሚኪያስ ቸርነት
Показать все...
ሚኪያስ ቸርነት - ፃፈው ስምሽን 16k.m4a6.18 KB
'' ልጁን ያያችሁ '' ኤልሳቤት ተሾመ ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ​​​​​​ ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​@Napolo
Показать все...
ልጁን ያያችሁ - ኤልሳቤት ተሾመ.m4a1.68 MB
'' የታል ልጁ '' ነፃነት መለሰ @OLLIFENNN
Показать все...
የታል ልጁ - ነፃነት መለሰ.m4a1.25 MB
'' ሱሴ '' ፀዲ
Показать все...
Tsedi - Suse.. 16k.m4a5.17 KB
Famm♥️ . 🥰🥰💞💞💕💕💞💞💕💕💞💞💓
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.