cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Больше
Эфиопия1 261Амхарский1 038Книги1 490
Рекламные посты
16 218
Подписчики
Нет данных24 часа
+287 дней
+21430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

....እንጨምር ... "ተባረኪ ችግሩ አላዛር ከታሪክ ዉጭ ሆኖ ነው የሚያየኝ ። እኔ ደግሞ ታሪክ ልስራ እየለፋሁ ነው ። ጊዜዬን ለጭቁን ህዝቦች ነፃ መውጣት መስጠት ነበረብኝ ። ለምወደው ድርጅቴ መስጠት ነበረብኝ “ አዳም ፣ 242 ) :: በመሆኑም አላዛር ለተባረኪ የማይደፍር “ ፈሪ” ወይም የማይገባው “ ደደብ “ ወይም “ ከግል ስሜቱ መውጣት የከበደው ራስ ወዳድ ነው”( መረቅ ፣ 240 ) “ አማን በአዕምሮዬ መጣ :: አላዛር የሆነ ሴታ ሴት መሰለኝ። የሆነ ያልወለደኝ እማማ :: ጡት ባያጠባኝም የሆነ የወለደኝ ምንትስ። የምወደውን ልጅ ስሮጥና ስሸሽ አስታውሼው ፣ ስረጋጋ ፣ በዝምታ በልቤ እንዲህ አልኩት ፣ ማዘሬ ነህ ምንድነህ ?” (መረቅ ፣ 248) ። በላካናውያን እሳቤ ተፈጥሯዊው እውነት ትራውማ ነው እንጂ በትዕምርታዊ እርከን ዉስጥ ያለ ነገር አይደለም :: ለዚህም ነው ፋንታሲ ይህንን ትራውማ ለማከም ለሚደረገውን ጥረት መድረክ ሆኖ ብቅ የሚለው( fantasy is a setup ):: ይህ የእሷ እጣ ፈንታ ብቻ አይደለም ፤ በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ጣጣ ነው፤ ይህም ወጣቶቹ የወል ልቦናን ገንብተው የወል እርካታን ለመገንባትና ለማግኘት የሚዳክሩት ፣ በዢዤክ እሳቤ (Collective jouissance) ዉስጥ የሚታይ ነው :: ስሎቬኒያዊው ስሎቮን ዢዤክ እንዲህ ይላል፦ Nationalism thus becomes ‘the privileged domain of the eruption of enjoyment into the social field.’ The ‘national Cause’ is then cleverly related to Lacan’s concept of ‘the Thing’, which is closely linked with the concept of jouissance; it is itself a materialization of jouissance. እንደውም ብሔርተኝት ፣ ፋሺዝም ፣ ናዚዝምና ሌሎችም በዚህ በ Collective jouissance ውስጥ የሚታዩ ናቸዉ ይላል :: ይህም በረቀቀ መንገድ የሌሎችን ወሲባዊ እርካታን ቀንብበው ለዓላማቸው የሚያውሉ ደስታ ስራቂዎች (ብልጦች) አሉ ይለናል :- "What is at stake in ethnic tensions is always the possession of the national Thing: the ‘other’ wants to steal our enjoyment (by ruining our ‘way of life’) and/or it has access to some secret, perverse enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. In short, what gets on our nerves, what really bothers us about the ‘other,’ is the peculiar way he organizes his enjoyment. ( Slavoj Žižek ፥ 22 ) " ይህንን ሃሳብ በሜሎስ ነቅናቂ እሳቤ እናጠናክረው : “ ወሲብ ትልቅ ጉልበት ነው የወሲብን ስልጣን ወጣቶች ልብ ውስጥ እንይወጣ አድርገህ አምቀህ ለጫጫታ ትጠቀምበታለህ ። በየአቅጣጫው ታፍነውና አንድ የፖለቲካ መውጫ ብቻ ቀዳዳ ካበጀህለት ባሪያ አገኘህ ማለት ነው “ (መረቅ፥162) እዚህ ጋር በተለይ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ መረቅና የስንብት ቀለማት ረቂቅ በሆኑ የስነ ልቦና ፤ የታሪክ፣ የፖለቲካ ፣ የማህበረሰብ እሳቤዎችና እጅግ በላቀ እና በተዋጣለት ኪነጥበባዊ አለም ውስጥ የተሰሩ ናቸው :: በመሆኑ እነዚህ ብሉይ (Classic ) ስራዎች በላካንያን እሳቤ በዋነኛነት በ " fantasy Structure ፣ desire እና Collective Jouissance " ውስጥ ለመተንተን ሁነኛ ማዕቀፎች መሆን ይችላሉ። ይህም አዳም ረቂቅ ፈላስፋና አሳቢ፣ ጥልቅ አንባቢና የተዋጣለት ደራሲ መሆኑን ከስራዎቹ መረዳት ይቻላል :: *** ይህ ፅሁፍ ይድነቃቸው ሰለሞን (Ph.D) ለኢትዮጲስ ጋዜጣ ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በወጣው ፅሁፍ ገፋፊነት ምክንያት የተፃፈ ነው ። በዚህም የእሱ ፅሁፍ የተሳሳታቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለማረም ያለመ ነው። ለዚህም ሲባል የእሱን ቴክስቶች (ከመረቅ የወሰዳቸውን ተጠቅሜያለሁ) ለንፅፅር እዲመች :: ለተጨማሪ ንባብ ምክንያት ስለሆንከኝ ምስጋና ይድረስህ :: © Teshale Kebede Bedriya
Показать все...
👍 3
የላካኒያን ሳይኮአናሊሲስ እና መረቅ *** በእርግጥ "መረቅ " በኪነ ጥበብ ምትሃት ፣ በእሳቤ ጥራትና በፍልስፍናው ጥልቀት በከባዱ የሚያነቃንቅ ብሉይ ስራ ነው። እውቁ ፈረንሳዊው የሳይኮአናሊሲስ ጠበብት ዣክ ላካን፣ ሳይኮአናሊሲስ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ፈላስፋ ነው። ፍሩድን በጥልቀት ያጠናና በስራዎቹም ሥነ - ፅሁፍን ፣ ፊልም ፣ ፖለቲካና በማህበረሰብ ጥናት ላይ ተጽዕኖውን ማሳረፍ የቻለ አሳቢ ነው። እንደ ላካን እሳቤ "ሰው '' በዋናነት የህይውት ዘይቤው የተበጀውና መንገዱን የተቀየሰለት ቋንቋን መጠቀም ከጀመረበት ቅፅበት ጀምሮ በሚገነባው ኢ-ንቁ የአዕምሮው ክፍል ነው :: ይህም “Unconscious mind is structured like a language” ይላል። የላካንያን ኢንቁ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ትዕምርቶችና መዋቅሮች ማከናወኛ (ሚዲየም፣ ስቴጅ ) ጭምር ነው። በዋናነት አንድ ህፃናን ከተወለደ በኋላ ራሱን የሚያውቀው በእናቱ ጡት አማካይነት ነው። በዚህ ጊዜ ጨቅላው እራሱን መለየት አይችልም፤ ይልቁን ፍፁም እርሱነቱንና አካባቢውን ማገናዘብ ባልቻለበትና እራሱን በእናቱ የመስለባቸውን ደረጃዎች ያልፋል :: ጨቅላው ከእናቱ ጡት እንደተነጠል ( ከ6 እስከ 18 ወራት ያለውን ጊዜ ይሸፍናል) የእኔነት ምስሉን መቅረጽ ይጀምራል። የእናቱ አንድ አካል እንዳልሆነም ይረዳል። ይህን ego form የሚያደርግበት እርከን ላካን Imaginary order ሲል ሰይሞታል። ይህን imaginary order በማለፍ በትዕምርትና በቋንቋ ወደተዋቀረው ስርዓት ውስጥ የሚገባው ጨቅላው እናቱም ብትሆን ከሙሉ እሱነቱ የተነጠለች (M)Other እንደሆነች ይረዳል። ሕጻኑም የደስታና የእርካታ ምንጩን ትቶ በማህበረሰቡ አስቀድሞ ወደተሰሩት ፍላጎቶች ፊቱን ያዞራል። (unreplaceable lack ) በሌላ አገላለጽ ህፃኑ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱ ፋንታሲ ወደ ፋንታሲ ሽግግር ያደርጋል :: በዚህም ህጻኑ ከተፈጥሯዊ እሱነቱ ወጥቶ በቋንቋና በትምዕርት ወደ ተዋቀረው ስርዓት ውስጥ ይገባል። ይህንን የቋንቋ ስርዓት በአርስቶትል አባባል ... “Automation:-Signifiers of the signifiers) ነው። ይህም ተፈጥሮኣዊ እሱነቱና እርካታውን ሙሉ በሙሉ የሚያጣበትና የሌሎች ፍላጎት (desires of the Other) ለተፈጥሯዊው ፍላጎቱ አማራጭ ሆኖ የሚመጣበት ነው ። ስለዚህ የላካንያን ሳይኮአናሊሲስ መሰረት የሆኑት ሶስቱ እርከኖች ማለትም Imaginary፣ Symbolic እና Real order፣ ለትዕምርታዊ ዓለም ተገዢ ይሆናሉ፡፡ በዚህም ተፈጥራዊ እውነት (real ) ሙሉ በሙሉ በቋንቋ ስለ ማይወከል ከቋንቋ ውጪ ይሆናሉ ፤ ይህንን ለካን ( Symbolic castration) ይለዋላል :: በዚህ በቋንቋ የሚመራው ግለሰብ እነዚህን ጉዳዮች በሌላ ማህበሰባዊ እውነታ (social reality) ይተካሉ :: ስለዚህም ተፈጥራዊው እውነት እና እርካታው (enjoyment) ፣ ስነ-ልቦናዊ ምስቅልቅሎሽ ( trauma) በመሆን ወደሌላ ምናባዊ አለም ወይም ፋንታሲ ሽግግር (transference) ያደርጋሉ። በዚህም ተፈጥራዊ እውነታ እና እርካታ ፋንታሲ ውስጥ ይገባሉ :: በዚህም መሰረት መረቅን በላካን ለማንበብ የተደረገውን ጥረት እንይ ፦ "ከሁሉ ለመሸሽ የምችል ዓይነት ወደ አማን ደረት ተጣበቅሁ ። አማን ጓደኛዬ ነው ፣ ጓደኛዬ ነበር፣ እና ምን አለበት? አይኖቼን ገርበብ አድርጌ አላዛርን አስባለሁ። አላዛር አ አይኖቹን ጨፍኖ እየተልቆሰቆሰ ሲያቅፈኝ። በፀሃያማ ቀን በቀስታ ታኮኝ ሲቆም ። በሃሳቤ እዛና እዛ ስቀባዥር አማን አናቴን ሲስመኝ ሰማሁት :: አላዛርን ማለም አቆምኩ :: ግራ በመጋባት ምልክት ቀና ብዬ አየሁት :: ቀና ብዬ እያየሁት ሳለሁ ሳልጠብቀው አፌ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳመኝ ። በፍጥነት ከእቅፉ ተላቀቅሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቆም ብዬ ጃኬቴንና ሱሪዬ አስተካከልኩ። “ የት ነው? “አለኝ “ቤት ለመሄድ ነበር “ተራዬ እንዳልሆነ አውቃለሁ ” መኪና የለም ::ትንሽ ረጋ በይ :: ተራሽ ገና ነው” የምመልሰው አልነበረኝም ..... ይህ ሁነት በመጋቢት 1969 ተባረኪ የወጣቶች ሊግ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ሌሊት ነው። በመጀመሪያ ተባረኪ ሰላማዊ ሰልፉን ለመሳተፍ ፈርታ ስታመነታ ነበር ። ሆኖም ፍራቻዋን ለትግል አጋሯ አማን (የእሷም ፣ የአላዘርም አብሮ አደግ) በቁንጽል ወይም በዝርዝር አትነግረውም፡፡ “ ፈሪው ወዳጄ አላዛር በልቤ ጥርጣሬ አስገብቶ ሳይሆን ይቀራል ፤ ለአማን ልነግረው አልደፈርኩም ። ግን ደግሞ የጠላቴን አይን እያየሁ ግንባሩ ላይ መጮህ እፈልጋለሁ ...” (መረቅ ፥ 246።) ከትዕምርታዊ ስርዓት ይልቅ ፣ ነገሩን በቀጥታ ለማየት ከፈለግን ተፈጥሯዊው ፍላጎት እንደሆነ እንረዳለን ። ነገር ግን ይህ ተፈጥሯዊ ፍላጎት ለማግኘት ለአማን የሚቻል አይደለም ፤ ይህም የአማን ፍላጎት ወደ ፋንታሲ ውስጥ ተሻጋሪ ይሆናል ። በመሆኑም አማን ተባረኪ የዓላዛር ፍቅረኛ መሆኗ እያወቀ እሷን ከመመኘት አላገደውም፤ ይህም ተፈጥሯዊ ፍላጐቱ ለማርካት የነበረውን ማንኛውም አጋጣሚ ከመሞከር ወደኋላ አላለም ፤ ይህም ተባረኪ በአማን አዕምሮ ውስጥ የምትንሳፈፍ ለተፈጥሮኣዊ ፍላጎቱ መልስ ሰጪ ናትና ። እዚህ ጋር የስሎቮን ዢዤክን ሀሳብ ላምጣ ፦ "For a Man ,the relationship with a women is possible only in as much as she fits his formula " ይላል :: ለዚህም አካላዊ ባይሆንም በፖለቲካው መድረክ የነበራቸው ግንኙነት ለዚህ ወሲባዊ ፍላጎት ልዋጭ ሆኖ መቅረቡን እናያለን። እንዲህ ትላለች ቴቤ ፦ " ....አማንን ሩካቤ ስጋ እምቢ ብላውም ባማረ መልክ በፖለቲካ ተራክበናል። እኔ እንደማልረሳው እሱም አይረሳኝም " ትላለች (መረቅ፥293 )። ..ሌላ እንጥቀስ ... ” የስላማዊ ሰልፉ ማግስት በመሽሽ ላይ እያለሁ ፣ ትዝ ያለኝ ብቸኛ እናቴና አላዛር ነበሩ። ለብቻዬ በኮሮኮንች ላይ እየተወለካከፍኩ ስሮጥ የከበበኝ ጨለማ ማሃል የታወሱኝ እማማና አላዛር ነበሩ። ፍቅር ከዋናው አላማዬ በላይ የሚንሳፈፍ ጉድ የለዉም (መረቅ ፥ 246)” እዚህ ጋር ተባረኪ ፣ እናቷና ዓላዛር ተያይዘው የመጡት ሁለቱም ለተፈጥሯዊ ፍላጎቷ መገኛ ቢሆኑም የነበረችው በትርክት ውስጥ ስለሆነ አታገኛቸውም ። ምክንያቱም ትዕምርታዊ አለም ተፈጥሮኣዊ እዉነት (real ) እርካታ ( jouissance) በቋንቋ አይወከሉም ፤ ይህም እንዴት ወደ ፋንታሲ ሽግግር እንደሚደርግ ከላይ አይተናል ። ይህንን ክፍተት በፋንታሲ ከተያዘ በኋላ ለሌሎች ፍላጐት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ፤ በዘመኑ የነበረው ፋንታሲ ውስጥ መጫወት የሚችል ርዕዮት ዓለም ደግሞ ማርክሲዝምና ሌኒንዝም ነው፡ ፡ በመሆኑም የማርክስ ርዕዮት ዓለም የእናቷና የዓላዛር ተቀናቃኝ ሆኖ ይመጣል ። ዢዤክ እንደሚለው (fantasy is narative) ፋንታሲ ትርክት በመሆኑ በወቅቱ የነበረው የማርክሲስም ርዕዮተ አለም አዕምሮዋን መቆጣጠር መቻሉና አዕምሮዋ ውስጥ ያለዉ የፋንታሲ መዋቅር ወዲህ በእናቷና ዓላዛር እሳቤ ወዲያ በርዕዮተ ዓለሙ ለሁለት ተከፍሎ እናያለን።
Показать все...
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሐነ ትንሳዔው አደረሳችሁ። በዓሉ የሠለም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆን ከመጻሕፍት ዓለም - Book Shelf ይመኛል።
Показать все...
👍 5
ትዝ ይላቹሀል? Phsyics እና Maths ላይ የነበሩ solve አርጉ ምንባላቸው problems? እና ደሞ እነዛ የMaths ረዣዥም equations? The value of 'x' ፍለጋ ብዙ ወረቀት እኮ ነው የጨረስነው። አንድ መስመር ጥያቄ ተሰጥቶን 2 ባዶ ወረቀት ለመልስ ሲያስከትሉልን የነበረው ጭንቀት አረሳውም። ከelementary እስከ ዩኒቨርሲቲ maths በጣም ከባድ ትምህርት ነው። ብዙ ለፍተን . .አጥንተን ነው የምንሰራው። ነገ Maths ነው ፈተናው ሲባል ሌሊቱ ይለያል. .እንቅልፍ አይታሰብም ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ያን ሁሉ ትግል ሳስብ ቆጨኝ። ያን ሁሉ አቅሜን ያዋልኩበት ልፋት አሁን ላይ ትምህርት ጨርሼ ህይወትን ለብቻዬ ስጋፈጣት ምንም ጥቅሙ አልታይ አለኝ። ዛሬ ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትፈትናለች። The value of 'X'ን ስለመፈለግ ያን ሁሉ ከምንማር አሁን ለሚገጥሙን ፈተናዎች መፍትሄ ፍለጋ ብንማር ምን ነበረበት? እንዲሁ በምኞት ሀሳብ ስሞላ እነዛን በስንት ጥረት የሸመደድኳቸውን equations ተጠቅሜ የአሁን ውጣውረዴን መፍታት ያምረኛል። በነዛ word problems ውስጥ ዛሬ የሚገጥመኝ የህይወት እንቅፋት ተተንትኖ ከነ አሰራሩ ተፅፎበት በነበር ብዬ እጓጓለሁ። አሁን የሚገጥመን የሴትነት ፈተና ፣ የትዳር ችግር ፣ ድብርት ፣ ብቸኝነት ፣ አምኖ መካድ ፣ የልብ ስብራት ፣ ስራ ማጣት ፣ ራስን መጥላት በየትኛው equation ነው solve ሚደረገው? እኚህን ቻሌንጆች በየትኛው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው የተማርነው? አልተማርንም! ዛሬ ብዙ የህይወት ገፃችንን ቢወስድም ለትምህርት የሰጠነውን ያህል ቦታ ተሰጥቶት ግን አላወቅነውም። ትምህርት አያስፈልግም አልልም። ነገር ግን ያን ያህል ሁሉን ረስተን አቅማችንን invest ልናደርግበት አይገባም። አሁን ባለንበት ሁኔታ የተማርነው እውቀት አብዛኛው የሚጠፋ ነው። የሚቀረውን ደሞ ለሆነ ድርጅት ግብዐት ሆነን በመስራት ብንጠቀመው ነው (እሱም ከተገኘ)። ከስራ ውጪ ግን ብዙውን የህይወት መንገዳችንን ሚይዝ ከተለያዩ ሰዎች ጋ መኖር ፣ ትዳር ፣ እናትነት ፣ አባትነት አለ። ቀላል አይደሉም....እስክንኖርባቸው አዲስ ናቸው። ማወቅ ፣ መዘጋጀት ፣ መጠንከር አለብን። ሁሌ ደሞ አልጋ በአልጋ አይሆኑም ማጣት ፣ መውደቅ ፣ መሰበር ይኖራቸዋል. .ለዚህስ ከማደጋችን ጋ ሚመጣ እውቀት መኖር የለበትም? ስንት ልጅ ነው ደህና ወላጅ ኖሮት እንዲህ አይነት ስለ ህይወት ትምህርት የሚያገኘው? . .አላውቅም! ግን በቃ ትምህርት የሰጠነው እድሜ አይገባውም። እሱ ላይ ብቻ መደገፍ የለብንም. .አላማችን ሊሆን አይገባም። ከልጅነት ጀምሮ ከትምህርት ጎን ለጎን ራሳችንን ምንሰራበት ህይወት ሊኖረን ይገባል። ውስጣችን ያለውን አቅም ፣ የተፈጠርንለትን አላማ ነው ማጠንከር ያለብን። እንጂማ ትምህርት ብቸኛ መንገዳችን ከሆነ 12 ላይ ወይም ዩኒቨርሲቲ ላይ ሲያልቅ ራሳችንን በማጣት እንጎዳለን። ወዴት እንደምንሄድ ሲጠፋን...ህይወታችንን በምን ማስቀጠል እንደምንችል ግራ ሲገባን አጉል አወዳደቅ እንወድቃለን። ማንፈልገውን ትምህርት በብዙ ፈተና ተምረን. .የሚገባን ቀርቶ የሚያኖረንን ስራ እንኳን ስናጣ አናሳዝንም? ለመኖር ፣ ላለመወቀስ ፣ ላለመውደቅ ብለን እንደገና ማንፈልገው ፣ ሰው ያሰመረልን መንገድ ላይ መሄድ ደሞ ይታክታል። ስለ ነገኣቹ . .ስለ ህይወታቹ አስቡ. .አላማችሁን ለዩና እሱን ዋና መንገዳቹ አድርጉት. .ራሳቹ ላይ ስሩ! ስኬት በትምህርት ብቻ አይደለም! © Nejat Hussen
Показать все...
👍 3 2
ያለፈውን ታሪክ፣ የማህበረሰቡን ዕሴትና ዕውቀት በጭፍን ማጥላላትና መናቅ የመሰልጠን መንገድ አድርገን እየሄድንበት ያለው መንገድ ቆም ብለን ለመረዳት እንኳ ጊዜ ያለን አይመስልም፡፡ የማጥላላት ዘመቻውም የሚያጋፍረው መድረኩን የያዘው ዘመንኩ ወይም ተማርኩ ባዩ ነው፡፡ ፈላስፋው Valentin Mudimbe ከላይ በጠቀስኩት መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ ቢያንስ ነጭ ቅኝገዥዎች የአፍሪካን መሬት ለቀው ቢወጡም በእነሱ ቦታ "ጥቁር ቅኝገዥዎች" ወይም ልሂቃን ተተክቷል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የቅኝግዛታዊ ዲስኮርስና ዕውቀት ተኮትኩተው ያደጉት አፍሪካውያን ቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ሲከውኑት የነበረውን ነገር በአንድም ሆነ በሌላ አቅጣጫ ቀጠለ እንጂ አልተቋረጠም፡፡ ነጭ ቅኝ ገዥዎች የተኩት አፍሪካውያን የፖለቲካ ልሂቃን ከምዕራቡ ዓለም ሥርዓት ወይም ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት የጌታና የሎሌ ወይም የጥገኝነት እንዲሆን ያደረገውም ይኸው የቅኝአገዛዝ ሌጋሲ ነው፤" …colonialism should have produced a body of knowledge on the means of exploting dependencies." በሃገራችን ኢትዮጵያም የሆነውና እየሆነ ያለው ይኸው የቅኝ አገዛዝ ማዕከላዊ እሳቤ ከትምህርት ስርዓታችን አንስቶ እስከ ፖለቲካዊ መድረኮች ተሞልቷል፡፡ እውቀት ከሌሎች ሃገራት ተፈልጎ የሚመጣ እንጂ ከራሳችን አንጥረን ማውጣት እንደምንችል ሊገለጥልን እንዳልቻለ የምዕተ-ዓመት ጉዟችን ምስክር ነው፡፡ አዳምም ይህንን በደመነፍስ የሚደረግ ጉዞ አጥብቆ ይተቻል፡፡ "የኢትዮጵያ ምሁራን ሲሰለጥኑና ዘሮቻቸውን ሊያሰለጥኑ ሲፈልጉ መጽሃፎች ይጽፋሉ፡፡ በነዚህ መጽሃፎች ውስጥ የሚጠይቁት አንድ ዋነኛ ጥያቄ እኔ ምን አለኝ? ሳይሆን እነሱ ምን አላቸው? ነው አሉ፡፡ …ካላመናችሁ ጃፓን እንደምን ሰለጠነችን አንብቡ፡፡" (785) ፕ/ር ማዕምር መናሰማይ "A Critical Dialogue between Fifteen and Twenty first Century Ethiopia"በተሰኘው ጥናታቸው ያለፉትን ሶስት የመንግስት ስርዓቶችን (አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ደርግና ኢህአዴግ)ኢትዮጵያን ለማዘመን የሄዱበት መንገድና ዘይቤ "ፍዝዝመና" (passive modernization) ሲሉ ሰይመውታል፡፡ ይህም ማለት በልማት ስም ምዕራባዊ ለመምሰል መሞከር፣ በምዕራቡ ዕውቀትና ሥነ-ዘዴ ላይ በመመስረት ልማት ለማምጣት ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ነው ፍዝ ዝመና ብለው የጠሩት።፡ ይህ ፍዝ ዝመና ሃገር በቀል ዕውቀቶችን፣ እሴቶችን፣ እይታዎችንና ባህሎችንና ተቋማትን አፈራርሶ በምዕራቡ እሳቤ የመተካት ሙከራ ነው ይላሉ። የዚህ ውጤትም በሃገሪቱ ውስጥ መልከ-ብዙ ቀውስና ምስቅልቅሎሾችን አስከትሏል፡፡ "…the failure of modernization in Ethiopia is also the failure of knowledge: of Ethiopia and of modernization." አዳም ረታ በ'እቴሜቴ ሎሚ ሽታ' በሰዓሊና በሃያሲ መስኮት ገረሱ በኩል የዘመኑን ሁኔታ እንዲተነትን፣ እንዲተችና እንዲተረጉም አጭቶታል፡፡ መስኮት በተለይ ፈረንጅ ያልነካው ወይም 'ያልባረከው' ነገር ፋይዳ ቢስ ለሚያደርጉና የፈረንጅ እውቀት የሁሉም ነገር መመዘኛ አድርገው ለተቀበሉ የዘመኑ ወጣቶችን በየጋዜጣው ይተቻል፡፡ ሃገር በቀል እሴቶቻችንም ወደ መድረኩ ይመልሳቸዋል፣ ይተነትናቸዋል፣ አንዳች እውነት ፈልቅቆ ለማውጣት ይተጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መስኮት አስቀድሞ ይከተለው የነበረው የ"አብስትራክት ኤክስፕረሺንንዝም" የአሳሳል ዘይቤ በመተው፣ የሃገር በቀል ዕውቀትና experience መሰረት ያደረገ "ተነካናኪ" ወይም "ቅርባዊነት" የተሰኘ የአሳሳል ዘይቤ ፈጥሯል፡፡ ክፍለ ዘመን የተሸገረው የተቃወሰው ጉዟችን ዳግም መታደስ የሚችለው፤ ከራሳችን ጋር እርቅ አውርደን ነጋችንን ለማሳመር የመስኮት ገረሱን ፈለግ ከመከተል የተሻለ ሌላ ምን ምርጫ ሊኖረን ይችላል?! © Teshale Kebede Bedriya
Показать все...
👍 7
አዳም ረታ እንደ postcolonial ፈላስፋ **** "…ቅኝ አልተገዛንም ብለው ጉራ እየነፉ በየቀኑ ግን የተገዥነት አገልግሎት ይሰጣሉ" (የስንብት ቀለማት፣24) አዳም ረታ በተለይ ኋላ ላይ ባሳተማቸው 'እቴሜቴ የሎሚ ሽታ' እና 'የስንብት ቀለማት' ውስጥ የ-postcolonialism ፍልስፍናዊ እሳቤዎችን ጎልቶ ይንጸባረቅባቸዋል፡፡ አድዋ ላይ ቅኝ ገዥዎችን ድል አድርገን መልሰናል የሚለው ኩራታችን አፋዊ እንጂ ከልብ የመነጨ እንዳልሆነ በላቀ ኪናዊ ውበትና ጥልቅ መረዳቱን ገልጦ አስነብቦናል፡፡ ነጻነታችንን እና የስልጣኔ አሻራዎቻችን እንደልቃቂት አውጥተን ጥለን ፈረንጅ ለመምሰል የተጋጋጥንባቸው የሕማም ዓመታት እንደገና እንድናጤናቸው በድርሰቶቹ ብዙ ገስጾናል፡፡ እኛ ግን ከራሳችን ጋር መታረቅ ተስኖን እዚያው'ጋ ነን… እንደመነሻ፣ ከድህረ-አድዋ በኋላ እንደወረደ ተቀብለን ከተጋትናቸው ጉዳዮች መካከል እውቅት፣ ስልጣኔ፣ የተቋማት ግንባታ፣ ቁሳዊ ልማት፣ ርዕዮታዊ መረዳት…ከውጭ ሃገር እንደሸቀጥ አምጥቶ በየቦታው የሚከፋፈል አድርጎ የመረዳት ሥሁት ግንዛቤ አንዱ ነው፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ እውቀት በተውሶ ለማምጣት ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላ ሀገር ስንዞር አንድ አንድ ክፍለዘመን ተሻገርን፡፡ በሃገር ውስጥ በፈረንጅ አፍ እያወራን በስልጣኔ ብርሃን ለመጥለቅለቅ በሚል የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ከፈትን፡፡ "የአውሮፓ የስልጣኔ መንገድ" በመከተል ካለንበት 'ጨለማ ወጥተን' ልክ እንደ'ሰለጠኑት' ሃገራት በ'ብርሃን' መንገድ ለመጓዝ በሚል እዚህም እዚያም ባጀን፡፡ ኋላ ላይ የመጡት መንግስታትና የፖለቲካ ልሂቃንም አንዴ ሶሻሊዝም ሌላ ጊዜ የልማታዊ መንግስት ሞዴል አምጥተው ለመተግበር ሞከሩ፡፡ ሙከራው ግን ከቀውስ ወደ ቀውስ ከመሸጋገር ያለፈ አንድ ስንዝር እንኳ ፈቅ እንድንል አላገዘንም፡፡ለምን?... አዳም ይህንን የህማም ጉዟችንን እንደ ከያኒ ሥነውበታዊ ፍኖቱን ሳይለቅ፤ እንደ አሳቢ ደግሞ ከሥነዕውቀታዊ ከፍታው ሳይወርድ ገልጦ ያሳየናል፡፡ ታመን እንዳልታመምን በማስመሰል የመጣንበትን ሥሁት መንገድ ዳግም እንድናጤነው ይወተውተናል፡፡ ከህማማችን የምንፈወስበት መውጫ መንገዱን ጭምር ይጠቁመናል፡፡ እዚህ'ጋ ለማስታወስ ያህል postcolonialism የቁም ፍቺው እንደሚያመለክተው ከ-colonialism ቀጥሎ የሚመጣ ሥርዓት ሳይሆን፣ የኮሎኒያሊዝም ሌጋሲዎችን በተዘዋዋሪ መንገድ በድህረ ቅኝ ግዛት የቀጠሉ መሆኑንና ይህም በሃገሬው ነባር ባህል፣ ዕውቀት፣ እሴት፣ ማህበራዊ መስተጋብር…ላይ ከፍተኛ ተቃርኖ እንደፈጠረ የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ አፍሪካዊው ፈላስፋ Valentin Mudimbe 'The Invention of Africa' በተሰኘው መጽሃፉ እንዳሰፈረው፣Colonialism ማለት ቅኝገዥዎች የቅኝ ተገዥውን ሃገርና ማህበረሰብ በሃይል በመቆጣጠር አንድም የተፈጥሮ ሃብቱን አሟጦ ወደ ምዕራቡ ዓለም የመላክ ሲሆን፣ ይህንን ብዝበዛ ቀጣይነት እንዲኖረው ደግሞ የቅኝተገዥው ማህበረሰብ ማንነታዊ መሰረት እንደገና የማዋቀርና የመቅረጽ ስራ ይሰራል፡፡ በሌላ በኩል ማንነትን እንደገና የመበየንና የመቅረጽ ሂደት የስልጣን ተዋረዱ ሳይዛነፍ እንዲቀጥል፣ ቅኝ ተገዥዎች በዚህ የሃይል ተዋረድ ቦታቸው የተገዥነትና ጥገኝነት መሆኑን በሥነዕውቀታዊ፣ በተረክና በሌሎችም ይስሙላ ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው ላይ እውነታነት እንዳለው የሚያትት ዕሳቤ ነው፡፡ ህንዳዊቷ ፕ/ር Ania Loomba ታዲያ 'Colonialism/ Postcolonialism' በተሰኘው መጽሃፏ ይህንን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስና ተረክ ከስር መሰረቱ መረዳትና ይኸ ተረክ በድህረ-ቅኝግዛት ዘመንም እንዴት እንደቀጠለ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው ትላለች፡፡ ቅኝአገዛዝ በታሪክ ሁለትዮሻዊ ተቃርኖ (binary opposition) በመፍጠር አደገኛና ውስብስብ ተረኮችን ፈጥሯል፡፡ አውሮፓን ወይም ምእራቡ ዓለም "እኛ" በሚለው ጎራ ውስጥ በማስገባት "ከምዕራቡ ዓለም ውጪ ያለውን ማህበረሰብ ደግሞ "ሌሎች" (others) በሚለው ጎራ መድቧቸዋል፡፡ ይህን የሁለትዮሻዊ ዓለም (west-east) ተረክ አውሮፓውያን ለራሳቸው ያላቸውን ምስልና ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሕዝቦች መካከል አለ የሚሉትን የልዩነት መስመር ለማስመር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ለአብነትም አውሮፓውያን "የሰለጠኑ"፣ በ"አመክንዮ ታግዘው ማሰብ የሚችሉ"ና ዕውቀታቸው ለሌሎችም "አርዓያ መሆን የሚችል" አድርገው ሲቀርጹት፤ በአንጻሩ ከአውሮፓ ውጪ ያለው ማህበረሰብ ደግሞ "ያልሰለጠነ"፣ ስሜቱን "መግራት ያልቻለ" አድርገው ፈርጀውታል፡፡ እንዲሁም ነባር ባህሉንና እሴቱን እድገትና ለውጥ ለማምጣት የ"ማያስችል" አድርገው በይስሙላ ሳይንሳዊ ጥናቶቻቸው ጭምር አስደግፈው ለማሳመን ችሏል፡፡ ታዲያ ከ19ኛው ክ/ዘ አንስቶ እየኖርንባት ያለችው ይህች ዓለም በዚህ ቅኝት ነው የተበጃጀችው፡፡ ቅኝአገዛዝ "አበቃ" ቢባልም መልኩን በመቀየር ከአውሮፓ ውጭ ባሉ ሃገራት የትምህርት ስርዓት፣ የመንግስት አወቃቀር፣ የባህል ዘርፍ…ውስጥ ሰርጾ በመግባት ህልውናውን ማስቀጠል ችሏል፡፡ የ-postcolonial አሳብያንና ስራዎቻቸውም ከትናንት የተሻገሩ የቅኝገዥዎች ሌጋሲዎቻቸውን በዛሬው አስተሳሰባችን፣ የህይወት ዘይቤያችንና ተቋሞቻችን ውስጥ እንዴት ተተግባሪ እንደሚሆኑ ያሳዩናል፡፡ አዳም ልክ እንደ postcolonial ፈላስፎች፣ ቅኝ ገዥዎች ሃገራችንን በሃይል ወርረው በመያዝ ለዓመታት ባይቆዩም፣ ቅኝግዛታዊ አስተሳሰባቸውን፣ የህይወት ዘይቤያቸውን፣ የአገዛዝ ስልታቸውንና ዕቅዳቸውን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ተቀብለን እየተገበርነውና እየኖርነው እንዳለ ከመጣንበት የትናንትናው መንገድ ሰበዞችን እየመዘዘ ይወቅሰናል፡፡ "ባዴ [ፈረንጅ] የተለየ ብሩህ አይደለም ብለው የነዘነዙኝ በባዴ ቅኝ ገዥዎች ራሳቸውን እንዲጠሉ ጥልቅ ትምህርት የወሰዱና ዛሬም ከእነሱ እግር ስር የማይጠፉ ወገናቸውን ባዴ በቀደደላቸው መንገድ የሚቀረቅቡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡" (ስ.ቀ፣ 23)-ይህን የተባሉት ራሱን የ"ወርቃማው ትውልድ" ወይም የ"ያ ትውልድ" አባላት ነው ለሚሉት አብዮተኞች የተሰነዘረች ትችት ነች፡፡ ትልቁ አሳቢና ሳይካትሪስት ፍራንዝ ፋኖን 'Black Skin White Mask' በተሰኘው መጽሃፉ የጥቁሮች የበታችነት ሥሜት (Inferiority complex) ምንጩ የ" Colonial discourse" ነው ይላል፤ "…colonialism not only exploits but dehumanize and objectifies the colonized subject." ፋኖን የቅኝ ግዛታዊ ዲስኮርስ በቅኝ ገዢው ግለሰብ ሥነ-ልቦና ውስጥ እንዲሰርጽ ያደረገበት መንገድ ደግሞ ግለሰቡ የወጣበትን ማህበረሰብ ታሪኩን፣ ማህበራዊ እሴቱን ዋጋ በማሳጣትና በማጥፋት በማጥፋት ከትውስታው ማህደር እንዲፋቅ በማድረግ በምትኩ የነጭ የበላይነት ተፈጥሮኣዊ አድርጎ የሚቀበልና እሱን ለመምሰል የሚሞክር ግለሰብ ሆኗል ይለናል፡፡ "…የአገራችንን መልካም ታሪክ እንጥቀስ ስንል ዐይኖቻቸው ቀልተው 'the past is a foreign country' (ያለፈው ዘመን ባዕድ አገር ነው) ይሉናል፡፡…የነጭና የጥቁር ተራቾች ግን ታሪክ አስፈላጊ አይደለም……ያውም ደብተራ የዘባረቀው ብለው ለምን የታሪክ ምሁር እንደሆኑ ግን አይነግሩንም፡፡…የባዕድ ደብተራ የጻፈውን ግን ያምኑታል፡፡"(ስ.ቀ፣ 23)
Показать все...
👍 4
በአማዞን ቤት ፡ እያንዳንዱ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደወል ነበር ። 🔔 ጄፍ ቤዞስ ፡ እ.ኤ.አ. በ 1995 ላይ በትንሽ ጋራጅ ውስጥ አማዞንን የመሰረተ ጊዜ ፡ የሚጠቀሙበት ሰርቨር ብዙ የኤሌትሪክ ሀይል ስለሚፈልግ ፡ በስራ ሰአት ሚስቱ የፀጉር ማድረቂያ መጠቀም ፡ ወይም በቫኪዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት አትችልም ነበር ። .... ከዛም ይህን ድርጅት ከመሰረቱ ከቀናት በኋላ ቢዝነሱን ሰፋ አድርገው ሀያ የሚሆኑ ሰራተኖችን ቀጥረው ፡ በዌብሳይታቸው ገብቶ መፅሀፍ የሚገዛ ሰው መጠበቅ ጀመሩ ። እና በዛን ወቅት ወደ አማዞን ዌብሳይት የሆነ ሰው ገብቶ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ በአማዞን ቤት ደስታ ይሆናል ። አስገራሚው ነገር አማዞን ሽያጭ በጀመረባቸው በነዚህ ሳምንታት ፡ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ ደወል ይደወላል 🔔 ይሄኔ የአማዞን ሰራተኞች የሆነ ሰው በኦንላይን መፅሀፍ እንደገዛቸው ያውቃሉ ፡ እና ፡ ይህን ከአማዞን መፅሀፍ ያዘዘው ሰው ስም ለማየት ኮምፒውተሩን ይከባሉ ። ...... ማለትም በቀን ውስጥ አስር ጊዜ ሽያጭ ከፈፀሙ ፡ አስር ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። ሆኖም አማዞን ብዙም ሳይቆይ ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ትእዛዞች መቀበል በመጀመሩ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል መደወል ያቆመው በሳምንታት ውስጥ ነው ። .... ዛሬስ. ..... ያ. .. አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደውል የነበረው አማዞን በአንድ ቀን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል ። እንደድሮው ቢሆን በቀን ውስጥ ስድስት ሚሊየን ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። .... እያንዳንዱን ስኬቱን ደወል በመደወል ያበስር የነበረው አማዞን ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ በደስታ ያጨበጭብ የነበረው አማዞን ፡ ዛሬ ላይ ከ1,525,000 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ። እንደምንም በቆጠባት አስር ሺህ ዶላር ቢዝነስ የጀመረው ጄፍ ቤዞፍ አሁን 197 ቢሊየን ዶላር ሀብት በስሙ አስመዝግቧል ። ...... ነገ በተሻለ ጉልበት ለመንቀሳቀስ ሀይል ይሆነን ዘንድ በያንዳንዱ ትናንሽ ስኬት ፡ እንደጄፍ ቤዞስ በደስታ ደወላችንን እናንሳ 🔔 ........ ፎቶ ፡ የአሁኑ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞፍ አማዞንን በመሰረተበት ወቅት © Wasihune Tesfaye
Показать все...
👍 6 1