cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ከ ብእር ጠብታ

እነሆ ለስነ ፅሁፍ አፍቃሪዎች የተከፈተ ምርጥ ቻናል; እዚህ ቻናል ውስጥ በእኛ እና በሌሎች ምርጥ ምርጥ ፀሐፍያን የተፃፉ ልዩ ልዩ ልብወለዶችን ፣ ግጥሞች፣የተለያዩ ሃሳቦችን እና አሪፍ የምንላቸውን የፅሁፍ አለማትንም እናጋራለን :: እነዚህ ሁላ በአንድ ላይ ማግኘት ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ Join በማለት ለሌሎችም ያጋሩ:: በጋራ የጥበብ ባህርን በብዕር እንቅዘፍ ✊️✊️✊️

Больше
Рекламные посты
239
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የጂኒየስነት ሚስጢር💡💡💡💡💡💡💡 ክፍል 4 💡 ዛሬ ምነግራችሁ Maths እና Physics እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ተከተሉኝ ፦ 📚 በመጀመሪያ Maths ፣Physicsን ለማጥናት ራሳችንን በስነልቦና ማዘጋጀት አለብን ፣ማለትም ከባድ አለመሆናቸውን ራሳችንን ማሳመን አለብን ፡፤በመቀጠልም ትምህርቶቹን ስናጠና እነዚህን ማረግ አለብን ፦ ለPhysics ❓ 📚 concept መያዝ ያስፈልጋል ፡፡ እንዲሁም formula በመሸምደድ ፋንታ proof ማድረግ በጣም ጠቃሚ ናቸው ፡፡ እንዲሁም ዋና ዋና የሚታወቁ የ physics ህጎችን ለምሳሌ ፦ ፡-Newtons law of motion. ፦ Pascal principle ፦ Archemedian principle ወዘተ...ህጎችን መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለMaths ❓ 📚 ስናጠና ደግሞ የtopicኡን ህግ እንዲሁም ጥያቄዎቹ የሚሠሩበትን መንገድ step by step በደንብ ለመረዳት መሞከር እንዲሁም ያልገባን ጥያቄ ካለ የተለያዩ አጋዥ መፅሀፍችን( ከላይብረሪ ብትጠቀሙ ብዬ እመክራለሁ ) እና ት/ቱን የሚያስተምረውን አስተማሪ መጠየቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙዎች የሚሳሳቱት ነገር ❓ 📚 ደግሞ Maths ፣Physics ማጥናት ያለብን ፈተና ሲደርስ ብቻ አይደለም፡፡ሁልጊዜ ቢያንስ በዚያን ቀን የተማርነውን topic መከለስ አለብን እንዲሁም ቢያንስ በዚያን ቀን ከተማርነው topic 5 ጥያቄ ብንሠራ በጣም ይጠቅመናል ፤ ምክንያቱም እነዚህ ት/ቶች እንደሌሎች የሽምደዳ ት/ቶች ለፈተና concept እንዲሁም formula ሸምድደን በመግባት ብቻ የምንሰራቸው ከመሰለን በጣም ተሳስተናል፣ ይልቁንስ topicኡን በመረዳት እና የተለያዩ ጥያቄዎችን በመለማመድ የምንሠራቸው የት/ት አይነቶች ናቸው፡፡ አሁን ተግባባን አይደል ❓ 💬 ከእነዚህ ት/ቶች ደስ የሚለው ነገር ደግሞ topicኡን አንዴ በደንብ ከተረዳነው ከጭንቅላታችን አይጠፉም ስለዚህም ፈተና ሲደርስ በመጨናነቅ ፈንታ ራሳችንን በተለያዩ ጥያቄዎች challenge የማድረግ እድሉን እናገኛለን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ካለኝ ልምድ በመነሳት ይህንን ፃፍኩላችሁ ፡፡ በሉ ተነሱና ፍለጡት ❓ በተረፈ መልካም የፍሬሽነት ዘመን ይሁንላችሁ ፡፡ ስም :-ፀጋ ማቴዎስ ት/ቤት ፡- ሳውዝ ዌስት አካዳሚ የEntrance ውጤት:- 531 Join @Senior_exam_preparation
Показать все...
Welcome To entrance exam preparation group (@Senior_exam_preparation ) On this group You Will Get : 👉Entrance exam related News 👉study tips 👉resources and materials including worksheets, hand outs and reference books 👉interviews with straight A students So join the group and increase your academic result ( @Senior_exam_preparation )
Показать все...
የራሴንም የሌሎችንም ፅሁፋዊ ኪነ ጥበቦችን በማቅረብ አመታትን ቆይቻለሁ . ግን ከዚህ ቡሃላ ይሄንን channel manage ለማድረግ ጊዜ ስለማይበቃኝ ይሄንን channel ልሸጠው ወስኛለው . ማንኛውም ይሄን channel መግዛት ሚፈልግ ሰው @Lidsh19 በዚ account አናግሩኝ.
Показать все...
ብዙዎቻችን የሆነ ነገር ልናደርግ እንል እና ወደ ሁላ የሚጎትተን, እንደ እውነት አምነን መቀበል ያቃተንማ ፍርሃት አለ . ምንድን ነው ምትፈሩት? አይጥ ,እንስሳትን , መብረቅን, መቃብር ቦታን , ውድቀትን , መክሰርን , ሕዝብ ፊት ቆሞ ማውራትን , ያለፈ ታሪካችሁን .... ምንድን ነው አስሮ የያዛችሁ ልክ ልትለወጡ ስትሉ አንተ እኮ አትችልም የሚላችሁ .የለም ብትሉኝ አላምናቹም ምክንያቱም አሁን ካላችሁበት እንዳትንቀሳቀሱ ያደረጋቹህ ፍርሃትማ አለ . ግን ዋናው ጥያቄዬ ፍርሃታቹን ለማሸነፍ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ?አሁንም ደግሞ ይሰራችሁ ወይስ ትጋፈጡታላችሁ . እውነት ለመናገር እንደ'ኔ ፈሪ ሰው አልነበረም ምን ትፈርያለሽ እያላችሁ ነው መቼስ, public speech😂 ይገርማላ?ሰው ፊት ማውራት አሁን ምን ይከብዳል ትሉ ይሆናል ግን ለኔ ከባድ ነበር . Presentation ባለኝ ጊዜ ሁሉ even መምህር ክፍል ውስጥ ሲጠይቀኝ ማወራው ግራ ግብት ይለኛል እጆቼ በላብ ይዘፈቃሉ እንተባተባለው real pepresentation ያለኝ ጊዜማ panic attack ሁላ ያጋጥመኝ ነበር እንዴት ፍርሃትሽን አጠፋሽው ትሉ ይሆናል እውነት ለመናገር ፊት ለፊት ተጋፈጥኩት . እያንዳንዷ public speech ታለማምደኛለች ያልኩትን እድል ሁላ እጠቀም ጀመር ውስጤ አችይውም እያለኝ እንኩአን present ማድረግ ሚፈልግ ሲባል እጇን ምታወጣ ልጅ ሆንኩ . በአንዴ ሳይሆን ቀስ በ ቀስ ለመድኩት. ከ ጊዜ ቡሃላ እኔን የሚያስፈራውን ፍርሃቴን አስፈራው ጀመር ስሜ ሲጠራ እንኩአን በድንጋጤ ሮጦ የሚጠፋው ይመስለኛል ሁላ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ፍርሃታቹን ተጋፈጡት አለበለዚያ ዘላለም አስሮአቹ ይኖራል እናም በራሳችሁ መቼም ተስፋ አትቁረጡ . መልካም ምሽት ✍ሊዱ
Показать все...
ይቅር አልልሽም """"""" """"''''''''''''''' ገፍተሽ ሄደሻል..........የፍቅርን ጉልበት ፣ ተረማምደሽዋል......የናፍቆትን ቁርበት ፣ ንቀሽ አልፈሽዋል .......የልመናዬን ቃል ፣ በይ........እስቲ ንገሪኝ ላኖርሽብኝ ሀዘን....ስንት እንባ ይበቃል ፣ ስንት ድንኳን ልጣል ስንት ቦይ ልገድብ ፣ ገለሽኛል ብዬ...........ተዝካሬን ልቀልብ ። ይቅር በለኝ ብለሽ.........እንዳትማፀኚ ፣ ይቅር አልልሽም..........ይህንን እመኚ ፣ ያንቺን በደል ጥፋት ስቆጥር አልገኝም ፣ ላንቺ የምሰጥሽ.........ይቅርታ የለኝም ። ተከፋሁኝ ብዬ ተበደልኩኝ ብዬ.....ቅንጣት ባንቺ አላዝን ፣ ደግሞም አውቃለሁኝ የፍቅር መስፈርቱ ፅድቅ እንደማይመዝን ፣ ልክ ነሽ እኮ.....አንቺም አንዳንዴም ቅመም ነው.....ለፍቅር ጥላቻ ፣ ሳይበዛ በስሱ............ፍቅርን ማጣፈጫ ። ግን የልብሽን በራፍ.............ጨክነሽ አትዝጊ ፣ ይቅር አይለኝም ወይ ? ብለሽ እንዳትሰጊ ፣ እንኳን ሰው እና ሰው  በመንገድ ይጋጫል........እግርም ከእግር ፣ ለሌለኝ ቅያሜ ላልቆጠርኩት በደል.......አልልሽም ይቅር ፣ ከጥፋት በላይ ነው ከስህተት በላይ ነው..ቂም አይዝም ፍቅር ። ግን......ይቅር አልልሽም ለምን አልተቀየምኩሽም #በረከት_ዘውዱ
Показать все...
ሰው_መሆን !!! ረቂቅ ነው ቃሉ፣ ክቡድ እና ሙሉ፣ ገነትን ቀድሞ የረገጠ፣ መላዕክትን በፍርሃት ያንቀጠቀጠ፣ ሰውነት ክቡር ነው መለኮትን ያስቀመጠ። ሰው ማለት! ሰው ማለት ሰባተኛ፣ የጥበብ ልጅ ጥበበኛ፣ ክቡር ፍጡር እውነተኛ። ሰው ክቡድ ነው ታምረኛ። ሰው መሆን ሰውነት የታረዘን ማልበስ፣ ማዘን ማስተዛዘን ለራስ ለሰው ማልቀስ፣ የሰው እንባን ማበስ፣ ሰው መሆን ክቡር ነው! ምስለ መንፈስቅዱስ። ታዲያ.... ታዲያ የኛ ግብር ሰው ያስብላል፣? የሰውነት ትርጉም በኛ ተንፀባርቋል፣? እርኩሰት ወይንስ ቅድስና ክብር ወይንስ ውርደት፣ ማፍቀር ወይንስ መጥላት መግደል ወይንስ ማንሳት፣ ማልበስ ወይንስ መግፈፍ ማመፅ ወይንስ መርዳት፣ የትኛው ነው ሕይወታችን፣? የትኛው ነው ተግባራችን፣? ጉድ ነው ሰውነታችን ቆሽሿል ተበክሏል በድፍ፣ ሰው መሆን ተረስቷል ሰው አንሷል ከጉድፍ። ሰው መሆን ክቡር ነበር፣ ከራስ አልፎ መኖር፣ በሰውነት ሰውን ማክበር፣ ምስለ ማርያም ምስለ እግዚአብሔር። እዚያ ማዶ በምትታየው ዓለም፣ ከጥቂቶች በቀር ነብሴን ያለ የለም፣ ህዝቡ ያድራል ቅዠት ሲያልም፣ በስጋ ፍላጎት እንዲሁ ሲስለመለም። የተማረ ፤ የተመራመረ የሰውነት ክብርን ያወቀ፣ ደግሞም ከንቱ ነኝ ሚል እራሱን ያላመፃደቀ፣ ጥቂት ነው በዝች ዓለም ሰውነቱን የጠበቀ፣ ሰው ሆኖ የሚኖር ከፈጣሪው የታረቀ። ግድ የለህም የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰውነትን መልበስ ያስከብርሀል በሰማይ፣ ደግሞም ከፍ ትላለህ ከፍጡራን በላይ፣ ሰውነት ወልድ ነው የአዳም ሲሳይ። ሰውነት ማለት የታረዘን ማልበስ የተራበን ማጠጣት፣ የታሰረን መጠየቅ የተጠማን ማጠጣት፣ እራስን ማሳነስ የወደቀን ማንሳት፣ ሰውነት ይሄ ነው ለሰው ክብር መስጠት። #ገጣሚ_ሄኖክ_ፀጋዬ #ብሶተኛው_ጢም_አልባው_ገጣሚ   
Показать все...
ትጠብቀኛለህ? ከሚሰድቡኝ አስበለጥኸኝ ከሚሸነግሉኝ ሸሸግኸኝ ከቀኑብኝ አልቀኸኝ "እንዳልታበይ ትንሽ ትንሽ ጣልኸኝ።" ያንተን ጥበብ አላውቀውም። ግን ምርጥ ሐኪም ነህ። አንተን ያህል አምላክ አላውቅም። ጌታዬ የሚጠሉኝ በአቅም ይበልጡኝ ነበር እኮ ተሸነፍኩ ያልኩትን ትግል ሳሸንፍ አሳየኸኝ። እንደለመድኩት ልኮንንህ ቃል አበጅቼ ተነሳሁብህ አሁንም ተሳሳልኛለህ በሰውነቴ አመጽኩብህ እንደአባት ገላዬን ልታጥበኝ ትጠብቀኛለህ ስንቴ በስምህ እንደዋሸሁ አንተ ረስተሀል እኔ አውቃለሁ ጸሎቴ መሐል ቅጥ ያለው ቃል ሰምተህ አታውቅም ግን ታደርግልኛለህ የማይታመን አምኜ ፈራሁ አንተን ማመን እጅህ ላይ ራሴን መልቀቅ አሰጋኝ ዓለምና ውሸቷ ውሸቷና ትዕቢቷ በለጡብኝ። ደጅ ደጁን ታያለህ ይመጣል ብለህ ትጠብቀኛለህ? ኤልያስ ሽታኹን💜🔥
Показать все...
በሕይወቴ እጅግ የማከብራቸው 2 ቀናት አሉ:: የመጀመሪያው የተወለድኩበት ቀን ሲሆን ሌላው ደግሞ ለምን እንደተወለድኩ የገባኝ ቀን ነው:: ዛሬ ወደዚች ዓለም ከመጣው 16 አመታትን ቆይቻለው :: እና ምን ተማርሽ ብትሉኝ ዘርዝሬ አልጨርስም; ካገኘውት ወይም ካጣውት, ከጠላኝ ወይም ከወደደኝ, ካስለቀሰኝ ወይም ካሳቀኝ,ከ ሕያዋን ወይም ከሙታን ውስጥ የሚመደብ በሕይወቴ ውስጥ ያለፈ እያንዳንዱ ሰው ትልቅ ትምሕርት አስተምሮኛል::ግን ከሁሉም በላይ የሌለንን ነገር እያሰቡ መብሰልሰል ምን ያህል እንደሚጎዳ እና ባለን ነገር ተደስተን ተመስገን ማለት እና ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረብ ያለኝን ይበልጥ እንደሚያበዛልን እና እንደሚባርክልን በዚች ጥቂት አመታት ውስጥ ተረድቻለው:: ቀናቹን በምስጋና ጀምሩ እና ፍቅርን እስትንፋሳቹ አድርጉ እላለው የናንተው ሊዲያ ነኝ ሰናይ ቅዳሜ ይሁንላችሁ😉
Показать все...
🔮🏮የ እናቴ ልጀ🏮🔮 🔦ክፍል አስራ አምስት🔦 🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈 አንዳንዴ ሰፈር ውስጥ እንዲ መፈራቴን ሳስበው ይገርመኛል ፡ ሴቱም ወንዱም ከፊለፊት ሲያየኝ ከመንገዴ ዞር ብለው ነበር የሚሄዱት ፡ እነሱ ድንገት የሚነሳብኝ ነው የሚመስላቸው ኪኪኪ ፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ማንንም ሳይነካኝ አልነካም ፡ አለመነካት ስል አንዳንድ ሰው አለመነካት የሚመስለው ፡እራሱን ብቻ ነው ፡ እንደዛ ግን አይደለም ሌሎች ሰወችን የሚያስጨንቁ ፡ አቅማቸውን ተማምነው ችግር የሚፈጥሩ ፡ ስንቶች አሉ በየሰፈሩ እኔ ከነሱ ጋር ስደባደብ ትክክለኛ ነገር ያደረኩ ነው የሚመስለኝ ፡ ለዚ ሁለታዬ እንደውም ሊያመሰግኑኝ ይገባል ፡በወቅቱ የስንቷን ሞባይል ስልክ ነው ያስመለስኩት ፡ ፖሊስ ይወጣው የሚለኝ ካለ ያስቀኛል ፡ ........ፖሊስ እኔ የማውቀውን ጉራንጉር የት ያውቀውና እንዲሁም አንድ ጊዜ ላፕቶፕ ከአንድ ጎረምሳልጅ ተዘርፎ ፡ ፖሊሱ እራሱ እንድረዳው ጠይቆኛል ፡ በጣም ውስብስብ ያለበትን ነገር ፈትቼለታለው ፡ ምክንያቱም ሰፈር ውስጥ ብቻ ሳይሆን አካባቢያችን ላይ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቄ ነበር የማውቀው ፡ ያኔ ማለቴ ነው ።እንግዲ በሁለት አመቴ ስመለስ የተቀየረ ነገር ካለ እናያለን ,,,,,,,,,,,,,,, 👉አቤልን ይዘውልኝ የገቡት ጎረምሶች ግቢውስጥ ሲደርሱ የት እናርገው አሉኝ ፡ ፊታቸው ላይ ፍርሃት ያየው መሰለኝ ፡ ከዚ በፊት አይቻቸው አላውቅም "አምጡት ወደዚያ ክፍል "አልኳቸው ጊቢው ወስጥ በመደዳ ከተሰራው ሰርቢስ ቤት አንዱን እያሳየዋቸው በዚመሃል አክስቴ ደግነሽ ወጥታ እሪታዋን አቀለጠችው ፡በፍጥነት ሄጄ አፏን ጥርቅም አድርጌ ይዤ"ዝም በይ እናቴ እንዳትረበሽ "አልኳት ወዲያው ዝም አለች እና "አቤል ምን ሆኖ ነው ?ማጅራት መቺ መታው ? አይይይ እንደው ምን ይሻላል ?ተርፏል ወይስ እንዴት ነው ?ለምን አኪም ጋር አንወስደውም ? ለምንድነው ከዚያ ክፍል የምትከቱት ?"እያለች የማያባራ ጥያቄዋን እያከታተለች ተከታተለችን "ብዙ ጥያቄዎች አሉሽ መልሱን በዋላ እሺ አክስቴ "አልኳት ፡የሰርፒስ ቤቷን ከፈትኳት በውስጡ ምንም ነገር አልያዘም አንድ ጥግ ላይ ብቻ የቆየ ምንጣፍ አለ እሱን ዘርግቼ እሰዚ ላይ ተውት አልኳቸው ፡እርስ በእርስ ተያዩና እንዳልኳቸው አደረጉና ፡ ቆሙ "በቃ አመሰግናለው መሄድ ትችላላቹ "አልኳቸው "እሺ ናቲ ስትፈልገን አለን ስልክ መለዋወጥ እንችላለን አለኝ ጠቆር ያለው ልጅ እሺ ብዬ ስልኬን ሰጠውት ፡ "ዘኪ እባላለው እሲ ደሞ ቶማስ ፡ " "እሺ አመሰግናለው ትንሽ ስላስቸገረ ልቀጣው ፈልጌ ነው ፡ እሺ ያን ያክል አልጎዳውም ፡ ይሄ ስለ እናቴ ነው "አልኳቸው "ያለምክንያት ምንም እንደማታረግ እናውቃለን "አለኝ ቶማስ የተባለው "የት ሰፈር ናቹ " "የታች ሰፈር ልጆች ነን " "እሺ በቃ ሂዱ እንገናኛለን " "አብሽር ጣጣ የለውም "ብለውኝ ተከታትለው ወጡ ፡አቤል መጠጡ ነው መሰል ዝግት አድርጎታል ጎንበስ ብዬ ሳየው ጭንቅላቱን ብቻ ይወዘውዛል ፡ተናደድኩበት ፡ሆነብሎ ዝም እንዳለ ገብቶኛል ፡እሱ በዝምታ ነው ሰውን የሚጎዳው ፡ "ስማ ማንነቴን አውቀሃል ሆነ ብለህ የተጎዳህ አታስመስል ቀና ብለህ እየኝ "ብዬ ደነፋውበት "ተወኝ"ብሎ መሬቱላይ ጥቅልል ብሎ ተኛ "አልተውህም ለምን እንደማልተውህ ታውቃለህ ፡ ስለ እናቴ ነው! ስለእኔማ በደል አልተናገርኩህም ነበር ቤቱንም ጥዬልህ ወጥቼ ነበር ፡ አንተ ግን አላረፍክም አብዝታ የምትወድህን እናቴንም ጎዳሃት ፡ ማንም የላትም ብለህ አላማህ ምንም ይሁን ምን አይመለከተኝም ነገርግን እናቴ እንዲ ለመሆኗ ምክንያት አንተ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ ፡ምን አድርገሃት ነው ፡ ተናገር "አልኩትና እጁን እስኪያመው ጨምቄ ያዝኩት ፡ያን ያክል አሞት ሳይሆን ሆነብሎ ጮኽ ፡ስለተናደድኩ በቦክስ ነረትኩት ባሰበት ፡ አክስቴ አነስተኛ ፍራሽና ብርድልብስ ይዛ እየተጠደፈች መጥታ ገባችና"ተው ናቲ ይሞትብሃል ምን አድርጎ ነው ፡ ተው ልጄ እንዲ አትጨክን "አለችኝ አቤልን እየከለለች "አይ ማውራት አለበት እናቴ በምን ምክንያት ነው እንዲ የሆነችው ይናገር አለበለዚያ ያውቀኛል እንደማላቆም "አልኩት "እኔ ምን አውቅልሃለው የትም ከርመህ መጥተህ ይህን ጥያቄ ስትጠይቅ አታፍርም ፡ምን እንዳሳለፍን ተውቃለህ "ብሎ ጮኽ አክስቴ ደግነሽ ዞር እንድትል ነገርኳት እምቢ አለች "አንተ የትም ከርመህ የምትለው እኔን ነው አፍ አለህ በማን ምክንያት ነው የሄድኩት እንዲ ስትል አታፍርም መቼ ነው የምትታረመው"ብዬ ጮውኩ "ናቲዬ ቆይማ እባክህ ነገ ታወራላቹ ትንሽም ሳይቀምስ አይቀርም በጤናው ይሻላል ፡በዛላይ እናትህ የሰማችው ድምፅ ስላለ በርበሩን በስጋት እያየች ነው "አለች አክስቴ ደግነሽ "እኮ ስለሷ ነው እኮ ጥያቄዬ ማነው እንዲ ያደረጋት በሩን ስትከፍት በወቅቱ ማነው ያናገራት ፡ ማወቅ አለብኝ ፡እሱ ደሞ እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነኝ ፡"አልኩአት ፡አቤል ለመነሳት ተፍጨረጨረ እናም "በኔ ምክንያት አይደለም ባንተ ምክንያት ነው እንዲ የሆነችው "ብሎ ጮኽ "ምን እንዴት እባክህ አስረዳኝ እስኪ አብረሃት ያለኽው አንተ "አልኩት ድርቀቱ እየገረመኝ "በሩን ስትከፍት አንዲት ሴት አገኘቻት ከዛ ,,,,,"ከዛ ብሎ ዝም አለ "ከዛ ምን?ማናት ያቺ ሴት ?"ባዩሽን ገለል አድርጌ አፋጥጬ ያዝኩት የፈራኝ መሰለ ተጨነቀ "እእኔ ቶሎ መድረስ ነበረብኝ ግን እኔ ከመድረሴ በፊት ስትዝትብኝ የነበረውን ነገር ነገረቻት !"ብሎ ማልቀስ ጀመረ "ግልፅ አድርገው እስኪ ምኑን ነው የነገረቻት ማናት እሷ"አልኩት ይበልጥ እየተጠጋውት "ሚጣ ናት የዕፃኗ እናት የተስማማንበትን ነገር አፍርሳ ፡ ለእናቴ መጥታ ነገረቻት ፡የዕፃኗ አባት አቤል ነው ፡ ያኛውን ልጅሽን ያለ አጢያቱ ነው የቀጣሽው ፡ አሁን የምፈልገው ልጄን እንድትሰጡኝ ነው አለቻት ፡ ይህን ስትላት ወደቀች እራሷን ስታ በቃ" ከማለቱ አክስቴ ጮኽች"ውይ ውይ የቤቴ ጉድ ዕፃኗ የአቤል ናት ፡ውይ ውይ ዘውድዬ ጉድሽ አላልቅ አለ ፡አዬ መከራሽ "እያለች ወደ እህቷ ፈጠነች ፡እኔና አቤል ተፋጠጥን,,,,,,,,,,,,, ደራሲ Unknown ይቀጥላል......    
Показать все...