cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ተግሳጽ

በዚህ channel ለህይወት አስፈላጊ የሚባሉ ተግሳጾች ይለቀቃሉ ከኛ የሚጠበቀው መማር ብቻ ነዉ ። ጥር ፪፯ ፪1፫ ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇 @uraman4u13

Больше
Рекламные посты
999
Подписчики
Нет данных24 часа
-57 дней
-2730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

†  🕊  ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት  🕊  †  † ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች:: በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ [መሪ] ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል:: በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት:: አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት [ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል] ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው:: ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው:: በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ:: በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው [አዛርያን] መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል:: ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል:: † ቅዱስ ሩፋኤል ¤ መስተፍስሒ [ ልቡናን ደስ የሚያሰኝ ] ¤ አቃቤ ሥራይ [ ባለ መድኃኒት ፈዋሽ ] ¤ መዝገበ ጸሎት [ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው ] ¤ ሊቀ መናብርት [ በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ ] ¤ ፈታሔ ማኅጸን [ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ ] ¤ መወልድ [ አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል ] ይባላል:: "ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል::
Показать все...
2
እንዴት ንስሐ እንግባ? ንስሐ ለመግባት ለሁሉም ክርስቲያኖች ሊያገለግሉ የሚችሉ ጠቅለል ያሉ መመሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህ መመሪያዎች በተለይ ንስሐ ለመግባት ለሚያመነቱና ዛሬ ነገ እያሉ ቀጠሮ ለሚያበዙ ሰዎች ያገለግላሉ:: 1. ዘወትር ከልብህ ጋር ሁን፤ ቁረጥና ኃጢአትን ጠልተህ ንስሐ ግባ 2. ለኃጢአትህ ማካካሻ ለመስጠት አትሞክር፣ በመዘመርህ፣ በማስቀደስህ፣ በመመጽወትህ፣ እኔ ንስሐ መግባት አይገባኝም አትበል። ሁሉም ሰው ንስሐ መግባት አለበት። በኃጠአቴ መቀጣት አለብኝ ብለህ ራስህን ለቅኖና አዘጋጅ። 3. ሁልጊዜ ትኩረትህ በንስሐ ላይ ይሁን። እግዚአብሔር አንተን እንጂ ያንተ ያልሆነውን አይፈልግምና ንስሐ ገብተህ እውነተኛ ልጅ መሆንህን ግለጽ። 4. ዘወትር የእግዚአብሔር ልጅነትህንና ለአንተ ያለውን ፍቅር አስብ፤ 5. ወደ ኃጢአት የሚወስዱህን መንገዶች ሁሉ ዝጋ፣ ጓደኞችህና የምትውልበት ሥፍራ የተመረጠ ይሁን። «ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ» ዕብ.4÷7
Показать все...
👍 1
ከመጀመሪያው አዳም ያለመገናኘት ሴት /ሔዋን እንተፈጠረች ክርስቶስም ያለግንኙነት ከእመቤታችን ተወለደ፡፡ የጌታችን ነፍስ ከድንግል ማርያም አይደለችም ለማለት ከደፈርህ የማርያም ነፍስም ከአዳምና ከሔዋን አይደለም : ማለት : ነዋ! ወይስ የሕፃናት ነፍስ ከእናትና ከአባታቸው አይደለችም ማለት ይቻልሃልን? ሰነፍ ሰው ሆይ ጌታችን ነፍሱን የነሳው ከድንግል ማርያም አይደለም ማለት እንደማይቻልህ ስማ፤ በእርግጥም የእመቤታችን ማርያም ነፍስ ከአዳምና ከሔዋን ነው፣ ሥጋዋም ከሥጋቸው ነው፡፡ እንደዚሁም ለክርስ ቶስም ከድንግል ማርያም ነው። ለሕፃን ነፍሱም ሥጋውም' ሕሊና ውም ከእናትና ከአባቱ ነውና፤ የወንድ ዘር በማሕፀን አንድ ከሆነ በኋላ ደም ይሆናልና፡፡ እርሱም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነፍስና ሥጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህም አዳም የዓለም ሁሉ አባት ይባላል፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ የእርሱ ልጅ ነውና፡፡
Показать все...
👍 3
እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!! ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር የሚፈልገው ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም መማር ማወቅ የሚፈልገው እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ ከሲዖል የሚጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል እንዳያመልጥዎ
Показать все...
ቤተሰብ እንዴት ናችሁ
Показать все...
1  አቤቱ አምላኬ ፥ ባንተ ታመንኹ፤ ከሚያሳድዱኝ ዅሉ አድነኝና አውጣኝ ፥ 2  ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሯት ፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር። 3   አቤቱ አምላኬ ፥ እንዲህስ ካደረግኹ ፥ ዐመፃም በእጄ ቢኖር ፥ 4   ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብኾን ፥ ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ብኾን ፥ 5   ጠላት ነፍሴን ያሳዳት ያግኛትም ፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት ፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳ ት። 6   አቤቱ ፥ በመዓትኽ ተነሥ ፥ በጠላቶቼ ላይ በቍጣ ተነሣባቸው፤ አቤቱ አምላኬ ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ። 7  የአሕዛብም ጉባኤ ይከቭኻል ፥ በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ። 8   እግዚአብሔር በአሕዛብ ይፈርዳል፤ አቤቱ ፥ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ ፥ እንደ የዋህነቴም ይኹንልኝ። 9   የኃጥኣን ክፋት ይጥፋ ፥ ጻድቁን ግን አቅና፤ እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል። 10  እግዚአብሔር የጽድቅ ጋሻዬ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው። 11 እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው ፥ ኀይለኛም ታጋሽም ነው ፥ ዅልጊዜም አይቈጣም። 12 ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይስላል ፥ ቀስቱን ገተረ አዘጋጀም፤
Показать все...
ተግሳፅ
የእመቤታችን አንድምታ ውዳሴ ቅዳሴ
እዌድሰኪ ኦ ድንግል
ንዒ ማርያም
ለእንጀባራ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የማይክራፎን ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በተናጠልም ሆነ በግሩፕ አናገሩኝ
Показать все...
1  ሳምንት * ሳምንት “ሰመነ ስምንት/8/ አደረገ ከሚለው ከግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። * በሕገ ዑደት መሠረት ዕለት ከተነሣበት ማለትም ከእሑድ እስከ እሑድ ያለው ጊዜ ሳምንት ተብሎ ይጠራል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉት ቀናት እያንዳንዳቸው 24 ሰዓት ያላቸው ናቸው። 2  የዕለታት ስያሜ 1 እሑድ ፡ አሐደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረግ * የመጀመረያ ሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ስለጀመሩ እሑድ ተብሏል፡፡ 2. ሠኑይ ያሰኞ/፡ ሠነየ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሁለት አደረገ ማለት ነው፡፡ ለሥነ-ፍጥረት ሁለተኛ ስለሆነ ሰኑይ/ ሰኞ/ ተብሏል። 3. ሠሉስ ማክሰኞ ፡ ሠለሰ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ሦስት አደረገ ማለት ነው፡፡ ማክሰኞ የሚለው የሰኞ ማግስት ማለት ነው፡፡ 4. ረቡዕ ፡ ረብዐ /አራት አደረገ/ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን ማለትነው፡፡ 5. ሐሙስ፣ ሐመሰ ኣምስት አደረገ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን ማለት ነው። 6. ዓርብ ፡ ዓረበ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው። ፍጥረታት እሑድ መፈጠር ጀምረው አርብ ስለተካተቱ ተፈጥረው ስለተፈፀሙ አርብ ተብሏል። 7 ቅዳሜ፡ ቀዳሚት ማለት ሲሆን ሰንበተ ክርስቲያን ከሆነችው ከዕለተ እሑድ ቀድማ ስለምትገኝ ቀዳሚት ሰንበት ቅዳሜ ተብላለች፡፡
Показать все...
ተግሳፅ
የእመቤታችን አንድምታ ውዳሴ ቅዳሴ
እዌድሰኪ ኦ ድንግል
ንዒ ማርያም
የእግዚአብሔር ቃል 👉ከቅርንጫፎቹ ሁሉ የተባረከ ፍሬ የሚያቀርብልን የሕይወት ዛፍ ነው። 👉እርሱ በምድረ በዳ እንደ ተቃጠለ፥ ከእርሱም ሁሉ መንፈሳዊ መጠጥ እንደ ተሠጠ ድንጋይ ነው። 👉እንግዲህ ስለ ተጨንቃችሁ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ አሸንፎአችኋልና አትዘኑ። 👉የተጠማ ሰው ሲጠጣ ይደሰታል, እና አይጨነቅም, ምክንያቱም ጸደይ ማለቂያ የለውም. 👉 ፀደይን ሳያሟሉ ጥማትዎን ማርካት ይችላሉ; 👉ከዚያም እንደገና በተጠማችሁ ጊዜ እንደገና አንድ ጊዜ ልትጠጡት ትችላላችሁ። -- ኤፍሬም ሶርያዊ ❤
Показать все...
ተግሳፅ
የእመቤታችን አንድምታ ውዳሴ ቅዳሴ
እዌድሰኪ ኦ ድንግል
ንዒ ማርያም
#ዕጣንና_ጽንሃ_በቤተክርስቲያን #ዕጣን ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለአለም ድህነት የሚለምኑበት ነዉ፡፡ በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት ፡ በነገህ ጊዜ በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናዉን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል ፡፡ ስለ እጣን የመፅሀፍ ቅዱስ ማስረጃ ዘጸ 30፥1 የዕጣን መሰዊያዉን ስራ ከግራር እንጨት አድርገው። ዘጸ 30፥35 በቀማሚ ብለሀት እንደተሰራ፥ በጨዉም የተቀመመ ንጹህና ቅዱስ እጣን አድርገው፡፡ ዘጸ 30፥34 እግዚአብሄርም ሙሴን አለዉ፦ ጣፋጭ ሽቱ ዉሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ በዛጎል ዉስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ዉሰድ የሁሉም መጠን ትክክል ይሁን፡፡ ዘፀ 40፥5 ለዕጣንም የሚሆነዉን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ታኖራለህ፥ በማደሪያዉም ደጃፍ ፊት መጋረጃዉን ትጋርዳለህ፡፡ ዘጸ 40፥27 የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን አጠነበት፡፡ ዘሌ 10፥1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብድዩድ በየራሳቸዉ ጥናዉን ወስደዉ እሳት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት በእግዚአብሔር ፊት እሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ፡፡ ዘሌ 16፥12 በእግዚአብሔር ፊት ካለዉ መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናዉን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ እጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም ዉስጥ ያመጣዋል፡፡ ዘኁ 16፥7 ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ እጅግ አብዝታችኀል ብሎ ተናገራቸው፡፡ ዘዳ 33፥10 ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ህግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሰዊያህም የሚቃጠል መስዕዋት ይሠዋሉ፡፡ መዝ 140፥2 ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ ፥ እጅ መንሳቴም እንደሰርክ መስዕዋት ትሁን፡፡ ማቴ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ህጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር እዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸዉንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት፡፡ ሉቃ 1፥10 በዕጣንም ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በዉጭ ቆመውዉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ራእ 5፥8 መጽሀፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንሰሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳዳቸም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ፡፡ ራእ 8፥3 ሌላም መለአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለዉ በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ እጣን ተሰጠዉ #ጽንሃ ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው። ሦስት ሰንሰለቶች አሉት። ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው። በሰንሰለቶቹ ላይ ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል። ‘’ሻኩራ’’ ማለት ሶስቱ ሰንሰለቶች ላይ ያሉት ክብ ነገሮች ናቸው። የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው። ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ። ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን: መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል። ፍሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያሳያል።
Показать все...
ተግሳፅ
የእመቤታችን አንድምታ ውዳሴ ቅዳሴ
እዌድሰኪ  ኦ  ድንግል
ንዒ ማርያም
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.