cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

አርማጌዶን

መረጃ አቅራቢ ድርጅት . ታሪክ እና ወጎች . የ መፅሀፍት ጥቆማ እና ቅንጭብጭብ

Больше
Рекламные посты
3 527
Подписчики
-424 часа
-207 дней
-5530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአውሮፓ ህብረት ሹማን ሽልማትን አሸነፉ جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) ኮሚሽነር ዳንኤል ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው ተገልጿል
Показать все...
“አገር የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ኹኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ አይቻልም” ሲል እናት ፓርቲ አስታወቀ Addis Maleda (RSS) በዚህ ሁኔታ “በምክክሩ ለመሳተፍ እቸገራለሁ” ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የምክክር መድረክ አስመልክቶ “አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ኹኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የሚቻል አይደለም” ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ። ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ “ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ኹኔታ የሚደረግ ምክክርም ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም” ማለቱን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታስረው ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ዜጎች ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ ባሉበት እንዲሁም አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት መደረጉ አግባብ አለመሆኑን እናት ፓርቲ አጽዖት ሰጥቷል። እንዲሁም በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና ሌሎች ምክንያቶች ባሉበት አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ ፓርቲው በምክክሩ ለመሳተፍ የሚቸገር መሆኑን አስታውቋል። ፓርቲው ከዚህ ቀደም የአገራችን ክፍሎች የተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ባልተፈታበት ትርጉም ያለው ምክክር ማድረግ እንደማይቻል መግለጹን አስታውሷል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍
👎
📨Пост отправки!
Фото недоступноПоказать в Telegram
ለዩክሬን የላኩት የጦር መሳሪያ የሩሲያን ግዛት እንዲመታ የፈቀዱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው? جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) ፑቲን በበኩላቸው ምዕራባውያን “በእሳት ከመጫወት” እንዲቆጠቡ አሳስበዋል
Показать все...
ጌታቸው ረዳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ያሳልፈው ውሳኔ “ትክክለኛ” እርምጃ ነው አሉ Addis Maleda (RSS) ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ ጌታቸው ረዳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዛሬው ውሳኔ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ የተደረገ አንድ እርምጃ ነው አሉ። አዲስ ማለዳ ከጌታቸው ረዳ ይፋዊ የኤክስ ገጽ እንደተመለከተችው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ይፋ የተደረገበትን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ በማያያዝ “የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው” በማለት ገልጸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህ.ወ.ሓ.ት በድጋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ በሕጋዊነት እንዲንቀሳቀስ የሚፈቅድለትን ‘የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ’ እንዲሻሻል ረቂቁን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስተላለፉን አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር። የሚኒስትሮች ምክር ቤትም የቀደመው አዋጅ ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የማያስችል በመሆኑ ይህን ለመቀየር ማሻሻያው እንዳስፈለገ ገልጿል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህ.ወ.ሓ.ት. በአሸባሪነት እንዲፈረጅ በሚያዚያ መጨረሻ 2013 ላይ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ሲሆን መጋቢት 15 ቀን 2015 ላይ ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲሰረዝ ፓርላማው መወሰኑ አይዘነጋም።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
የኮምፒውተር ቫይረሶችን በመጠቀም 6 ቢሊዮን ዶላር የመዘበረው ሰው جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) ግለሰቡ ላደረሰው ጉዳት የ60 ዓመት እስር እንደሚጠብቀው ተገልጿል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሁለት ጠባብ ክፍሎች ያሏት የአለማችን ትንሿ እስርቤት جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) በሳርክ ደሴት የምትገኘው እስርቤት በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍራለች
Показать все...
ህ.ወ.ሓ.ት በድጋሚ የፖለቲካ ፓርቲ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበት አዋጅ እንዲጸድቅ ለፓርላማ ተላለፈ Addis Maleda (RSS) ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ሕዝባዊ ነጻነት ግንባር ት.ሕ.ነ.ግ/ህ.ወ.ሓ.ት በድጋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ እንዲሾም ሊፈቅድለት የሚችል ረቂቅ አዋጅ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ‘የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ’ እንዲሻሻል ወስኖ ለፓርላማው አስተላልፏል። አዲስ ማለዳ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባገኘችው መረጃ እንደተገለጸው የቀደመው አዋጅ እንደ ህ.ወ.ሓ.ት ያሉ ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የማያስችል በመሆኑ አሁን “መልሶ” ሕጋዊ መሆን የሚችሉበት ስርዓት በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ተካቷል። የዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ማሻሻል በተጨማሪ፤ የንብረት ማስመለስ አዋጅ፣ በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ስለማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የቀረበ አዋጅን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፈዋል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
“ትሸታላችሁ”ተብለው ከአውሮፕላን በረራ ላይ እንዲወርዱ የተደረጉ መንገደኞች ክስ መሰረቱ جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) ክስ የተመሰረተበት የአሜሪካን አየር መንገድ ጉዳዩን እንደሚመረምር አስታውቋል
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እስራኤል ጋዛን ከግብጽ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን አስታወቀች جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS) እስራኤል ሃማስ በዋሻዎች የጦር መሳሪያ አስርጎ ያስገባበታል ያለችውን መተላለፊያ የተቆጣጠረችው በራፋህ የጀመረችው ዘመቻ ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው ተብሏል
Показать все...
👍
👎
📨Пост отправки!