cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ዝክረ ቅዱሳን ዘናዝሬት

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ ጥያቄ እና አስተያየት ካላቹ https://t.me/+Jmm8mYFhFpFkNTM0

Больше
Рекламные посты
515
Подписчики
Нет данных24 часа
+27 дней
+1530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ግንቦት 29 .mp34.48 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+ =>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን ነው:: +"+ አባ አፍፄ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና በሕጻንነታቸው ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው:: +ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል:: ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር:: ❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:- 1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት አገልግለዋል:: 2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል:: 3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል:: 4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል:: ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ (አፈ-ዐፄ)" ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም "ንግግር አዋቂ" ማለት ነው:: +ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል:: እግዚአብሔርም በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: +"+ አባ ጉባ +"+ =>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው ቴዎዶክስያ ደጐች ነበሩ:: +አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል:: +በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን መጥተዋል:: በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር:: +ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል: መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት የእርሳቸው ናት ይባላል:: +ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም አንስተዋል:: እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል:: +በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው:: (በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ- ልሳን" ማለት ነው) ❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት ያድለን:: በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን:: ❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን) 3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81 ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ) 4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ 2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል 3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ 5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ 6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ 7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ 8፡ ጉባኤ ሰማዕታት ++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdus
Показать все...
ዝክረ ቅዱሳን ዘናዝሬት

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ ጥያቄ እና አስተያየት ካላቹ

https://t.me/+Jmm8mYFhFpFkNTM0

ግንቦት 28 ..mp34.39 MB
✝✞✝ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ገዳማዊት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝ +*" ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ "*+ =>ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት:: +አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች:: +አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ : አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች:: +በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም : የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር:: +ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች:: +ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::" +ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን : ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት : ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች:: +በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች : ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች : ማንንም ሰው ሳታይ : በፍጹም ተጋድሎ ለ38 ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር : የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት:: +ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ:- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው:: +ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ38 ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም:: +እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም:: +አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት 28) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ:: +አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች:: =>አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን:: =>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት) 2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት) 3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ 4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት) 5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት) 6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት =>ወርኀዊ በዓላት 1.አማኑኤል ቸር አምላካችን 2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም : ይስሐቅና ያዕቆብ) 3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት) =>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdus
Показать все...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ግንቦት 27.mp32.84 MB
✝✞✝ በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ ✝✞✝ "" ግንቦት 27 "" +"+ ቅዱስ አልዓዛር +"+ =>ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: +በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ:: +ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው:: +ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ.11:1) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: "አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ:: +ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው) +ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል:: =>የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን:: =>ግንቦት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ 2.ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ 3.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት 7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት =>+"+ ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና" ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት" አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdus
Показать все...
ዝክረ ቅዱሳን ዘናዝሬት

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ ጥያቄ እና አስተያየት ካላቹ

https://t.me/+Jmm8mYFhFpFkNTM0

👍 1
ግንቦት 26 .mp37.14 MB