cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የደራሲው ማስታወሻ

አላማችን አንባቢ እና ምክንያታዊ የትዉልድ መፍጠር ነዉ ! @ye_deraswu_mastawesha

Больше
Эфиопия10 820Амхарский8 919Категория не указана
Рекламные посты
193
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

00:16
Видео недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
የካፊቾ የዘመን መለወጫ በዓል «ማሽቃሮ» **** የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል "ማሽቃሮ" በመባልም ይታወቃል። የካፊቾ የዘመን ለውጥ የክረምት ወቅትን ተከትሎ ይታደሳል። የማሽቃሮ በዓል ታሪካዊ አመጣጥ ልክ እንደብዙዎቹ የአዲስ ዓመታት ብያኔዎች የወቅቶች ፍርርቅና እምነትን ተከትሎ የመጣ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። በክረምቱ ወቅት በካፋ ምድር የሚገኙ ወንዞች አንደ ጎደፎ (ጎጀብ)፣ ጉማ፣ ጉሚ፣ ሻርማ፣ ወሺ፣ በቆ፣ እና ባሮ ሞልተው ይታያሉ፤ ምንጮችም በየቦታው ይፈልቃሉ። የካፋ ህዝብ የማሽቃሮ አዲስ ዓመት ከገበሬው የእርሻ ስራ ጋር የተያያዘ ሲሆን መለያውም ከመዝራት፣ ከእድገት እና ከመኸር ዑደት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል። የማሽቃሮ በዓል በኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ተብለው ከሚታወቁት ሀገራዊ ቅርሶች መካከል በየዓመቱ በመስቀልና አዲስ ዓመት በሚከበሩበት ሰሞን የሚከበር ታላቅ ባህላዊ ውርስ ነው።። በካፋ ተወላጆች ዘንድ ማሽቃሮ ተናፋቂ የሚያደርገው በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች በዕለቱ ከያሉበት ተሰብስበው ቤተሰብን የሚጎበኙበት በልዩ ልዩ ማህበራዊ ክንዋኔዎች፣ ስነ-ስርዓቶችና ፌስቲቫሎች በድምቀት መከበሩ ነው። በማሽቃሮ ህዝቡ በህብረት ይዘፍናል፤ ይጨፍራል፤ ግጥም ይገጥማል፤ ይሸልላል፡፡ ባህላዊ መሪዎችም ትርኢት ያሳያሉ። በማሽቃሮ በዓል በህዝቡ ዘንድ ፈጣሪውን በመፍራት እና በማክበር የሚተሳሰብበት፣ የፍቅርና የወዳጅነት መንፈስ የሚጎለበትበት ጊዜ ነው። በማሽቃሮ የተለያዩ የቤተሰብ አባላት ይገናኛሉ፤ ዘመድ ዘመዱን ይጎበኛል፤ በጋብቻ የተዛመዱ ቤተሰቦችም ይጠያየቃሉ። ማሽቃሮ በካፋ ህዝብ ዘንድ ህዝባዊ የሆኑ ታሪኮች የሚወሱበት፣ ባህል የሚከበርበት የአዲስ ዓመት መለያ ብቻ ሳይሆን የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር፣ የልማት፣ የአብሮነት፣ የተስፋ፣ የጽናት፣ አርበኝነት እና እምነት መግለጫ ነው። የካፋ ንጉስ መቀመጫ በሆነውና በየዓመቱ በዓሉ በሚከበርበት "ቦንጌ ሻንቤቶ" በሚባለው ስፈራ በዓሉ ሲከበር በዞኑ የሚኖሩ ብሔረሰቦችን ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያሳይ ስነ ስርዓት ያካሂዳሉ፡፡ https://t.me/ye_deraswu_mastawesha
Показать все...
የደራሲው ማስታወሻ

አላማችን አንባቢ እና ምክንያታዊ የትዉልድ መፍጠር ነዉ ! @ye_deraswu_mastawesha

#የንግሥቲቱየቀብርሥነሥርዓትእናየመጨረሻስንብት የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ አስክሬን ዛሬ ግብአተ መሬቱ ይፈጸማል። የዓለም ርዕሳነ ብሔራት ሥነ ሥርዓቱን ለመታደም ለንደን ገብተዋል። የዛሬው የቀብር ሥነ ሥርዓት ታላቁ ዊንስተን ቸርችል ከ60 ዓመት በፊት ሲሸኙ ከታየው ሥርዓት ወዲህ በታላቅ ሐዘን የሚከናወን የመጀመሪያው የቀብር ሥነ ሥርዓት ይሆናል። ንግሥቲቱ በግል በሥነ ሥርዓቱ እንዲካተቱላቸው የጠየቋቸው የኑዛዜ ኩነቶችም ይኖራሉ። የዛሬ ሰኞ የዳግማዊት ኤልዛቤጥ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዝርዝር መርሐ ግብር እነሆ፦ የጊዜ ሰሌዳው በለንደን ሰዓት አቆጣጠር መሆኑን ልብ ይሏል። የንግሥቲቱ አስክሬን በለንደን እምብርት በሚገኘው ዌስትሚኒቴር ታላቁ አዳራሽ ማረፉ ይታወቃል፤ ይህም እስከ ዛሬ ማለዳ ብቻ ይሆናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላለፉት ቀናት ወደዚህ አዳራሽ ተሰልፈው እየገቡ የንግሥቲቱን አስክሬን ሲሰናበቱ እንደነበር አይዘነጋም። እንግዶችን ለመቀበል የዌስትሚኒቴር አቤይ በሮች ይከፈታሉ። የበርካታ አገራት ርዕሳነ ብሔራት በዚህ ሥነ ሥርዓት ለመገኘት የንጉሣዊ ቤተሰቡን ለማጽናናት፣ የንግሥቲቱን ሥራ እና ሕይወትን ለመዘከር ወደዚህ መትመመቻቸው ይታወቃል። የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ታላላቅ ፖለቲከኞች እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮችም በዚሁ ሥፍራ ይገኛሉ። ከንግሥቲቱ ጋር በደም የሚዛመዱና በልዩ ልዩ የአውሮፓ አገራት ነዋሪነታቸውን ያደረጉ ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ። የቤልጂየሙ ንጉሥ ፍሊፔ እና ንግሥት ማቲልዴ፣ የስፔኑ ንጉሥ ፌሊፕ እና ንግሥት ሌቲዚያ የተዘጋጀላቸውን የክብር ቦታ ይይዛሉ። የዕለቱ ሥነ ሥርዓት በይፋ ይጀመራል። የንግሥቲቱ የአስከሬን ሳጥን ከተሸፈነበት ያጌጠ የክብር ማረፊያ ተነስቶ ወደ ዌስትሚኒቴር አቤይ ይወሰድና ለቀብር ሥነ ሥርዓት ዝግጁ ይደረጋል። አስክሬኑ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በዚህ የዌስትሚኒቴር አቤይ የክብር አዳራሽ ለሕዝብ ሽኝት መቀመጡ ይታወሳል። አስክሬኑ በባሕር ኃይል የክብር ሰረገላ ታጅቦ ወደዚያው ያቀናል። 142 የባሕር ኃይል መኰንኖች ያጅቡታል። ይህ የክብር ሰረገላ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው እንደነርሱ አቆጣጠር በ1979 ለልዑል ፍሊፕ አጎት ሎርድ ሞንትባተን ጊዜ ነበር። አገልግሎት ላይ የዋለው ደግሞ የንግሥቲቱ አባት ጆርጅ አራተኛ በሞቱ ጊዜ ነው፤ ይህም እአአ በ1952 ነበር። የባሕር ኃይል መኮንኖች ጋር አዲሱ ንጉሥ ቻርለስ ሣልሳዊ እና ልዑላኑ ዊሊያምና ሔሪ ይኖራሉ። የንግሥቲቱ ይፋ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ 2000 እንግዶች ይገኛሉ። ይህም በዌስትሚኒቴር አቤይ ይከናወናል። ሥነ ሥርዓቱ ብሔራዊ ደረጃ የሚከናወን ነው። ይህም ለነገሥታት የሚደረግ ጥብቅ መመሪያና ፕሮቶኮል የሚከተል ይሆናል። ይህ የጸሎተ ፍትሐት ሽኝት ሥነ ሥርዓት በአቤ አዳራሽ የሚከናወን ነው የሚሆነው። አቤይ የብሪታኒያ ነገሥታት ዘውድ ሲጭኑ ሥርዓቱ የሚፈጸምበት ቦታ ነው። ንግሥቲቱ በ1953 ዘውድ የጫኑትም እዚሁ ሥፍራ ነበር። ከዘውዱ በፊትም ልዕልት ኤልዛቤጥና ልዑል ፊሊፕን በ1947 (እአአ) ጋብቻ የፈጸሙበት እጅግ የተከበረ ሥፍራ ነው። በዚህ ሥፍራ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመ ንጉሥ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የለም። ይሁንና የንግሥቲቱ እናት ሲሞቱ በዚሁ ሥፍራ ሥነ ሥርዓቱ ተደርጎላቸዋል። ይህም በ2002 ነበር። ይህ የፍትሐት ሥነ ሥርዓት በካንተንበሪው ሊቀ ጳጳስ ጀስቲን ዌልቢ ቡራኬ ይመራል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ሌሎች ሥነ ሥርዓቶችን ይመራሉ። ሥነ ሥርዓቱ ማብቂያን ለማወጅ ሁለት ጊዜ ጡሩንባ ይነፋል። ይህን ተከትሎ የሁለት ደቂቃ አርምሞ ይደረጋል። የብሔራዊ መዝሙር ይዘመራል። የሥነ ሥርዓቱ ማብቂያም ይታወጃል። ይህን የፍትሐት ሥነ ሥርዓት ተከትሎ፣ የንግሥቲቱ አስክሬን በእግር ጉዞ ከዌስትሚኒቴር አቤይ ወደ ዊሊንግተን አርክ ይወሰዳል። ይህም ሃይድ ፓርክ ኮርነር የሚገኝ ነው። የእግር ጉዞ ሽኝቱ በወታደርና በፖሊስ ሠራዊት የሚታጀብ ነው። ግዙፉ የለንደን የሰዓት ማወጂያ ማማው፣ ቢግ ቤን በየአንድ ደቂቃው ደውል ያሰማል። ከሃይድ ፓርክ የክብር መድፍም ይተኮሳል። ነዋሪዎች ካሉበት ቦታ ሆነው የአስክሬን ሽኝቱን ሥነ ሥርዓቱን መመልከት ይችላሉ። ንጉሥ ቻርለስ ሣልሳዊ ከተቀሩት የንግሣዊያን ቤተሰቦችና ልዑላን ጋር በመሆን የእግር ጉዞ ሽኝቱን አስክሬኑን ከያዘው ሰረገላ ጎን በመሆን ይመራሉ። ካሚሊያ፣ የዌልሷ ልዕልት የሰሴክስ ሶፋኒት እና የተቀሩት ሉዑላን በተዘጋጀላቸው መኪና ይከተላሉ። አስክሬኑ ወደ ዊንድሶር ካስል ጉዞውን በሌላ የቤተ መንግሥት አስክሬን ማጓጓዣ ተሽከርካሪ እንዲዛወር ተደርጎ ወደዚያው ይወሰዳል። ዊንድሶር ጥንታዊ ቤተ መንግሥት ለንግሥቲቱ ልዩ ሥፍራ የነበረው ነው። ለንጉሣዊያን ቤተሰቡም ላለፉት አንድ ሺህ ዓመታት ተፈራርቀው ኖረውበታል። በተለይ ንግሥቲቱ ወጣት ሳለች ለንደን የቦምብ አደጋ ስጋት ላይ በነበረችበት ጊዜም ወደዚሁ ቤተ መንግሥት ተወስደው ነበር። ኮከሮናቫይረ ወረርሽኝ በተቀሰቀሰ ጊዜም ንግሥቲቱ በዚሁ ጥንታዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ እራሳቸውን አግልለው ነበር የከረሙት። የአስክሬን መኪናው 5 ኪሎ ሜትሮችን ያህል በአጀብ ይጓዛል። ይህም ወደ ዊንድሶር ካስል የሚደረግ ጉዞ ነው። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ንግሥቲቱን በጎዳናዎች ወጥቶ ካለበት ቦታ ሆኖ እንዲመለከት ይሆናል። ንጉሡና ልዑላን ኳድራንግል አካባቢ በድጋሚ ብቅ ይላሉ። አስክሬኑ ግብአተ መሬቱ የሚፈጸምበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይገባል። ሴይን ጆርጅ ቻፕል ቤተ ክርስቲያን ወትሮም በንጉሣዊ ቤተሰቡ ለጋብቻም፣ ለክርስትናም ለቀብርም የሚመረጥ ነው። የሰሴክስ መስፍን እና ሶፋኒት፣ ልዑል ሐሪ እና ሜጋን በ2018 የተጋቡት እዚህ ነበር። የንግሥቲቱ ባል ግብአተ መሬትም የተፈጸመው በዚህ ሥፍራ ነበር። በዚህ ሥፍራ የሚኖረው ሥነ ሥርዓት 800 ሰዎች ብቻ የሚታደሙበት ይሆናል። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በካንተቤሪ ሊቀ ጳጳስ ጀስቲን ዌልቢ ቡራኬ ይመራል። በዚህ ሥነ ሥርዓት የንግሥቲቱን መጨረሻ የሚያመላክቱ ሥነ ሥርዓቶች የሚንጸባረቁበት ይሆናል ለምሳሌ የንግሥቲቱ ዘውድ፣ አምባር እና የንግሥናቸው በትር በቤተ መንግሥቱ የጌጣጌጥ ባለሙያ ከአስክሬኑ ላይ በክብር ይነሳሉ።  ይህም ንግሥቲቱ ለመጨረሻ ጊዜ 70 ዓመታትን ከዘለቀ ንግሥናቸው መለያየታቸውን ያውጃል። ከዚህ በኋላ “እግዚአብሔር ንጉሡን ይጠብቅ” (God Save the King) የሚለው ዝማሬ ይሰማል። ይህ ዝማሬ እንዲዘመር ንግሥቲቱ በኑዛዜ ያስቀመጡት ነው ተብሏል። የንጉሣዊያን ቤተሰብ በሙሉ የጸሎት ቤቱን ለቀው ይወጣሉ። በዚያው ምሽት፣ ለቤተሰብ ብቻ በሚደረግ ሽኝት ንግሥቲቱ ግብአተ መሬታቸው ይፈጸማል። አስክሬናቸው የሚያርፈውም የኤደንበራው መስፍን ከነበሩት ባለቤታቸው ጎን፣ በንጉሥ ጆርጅ አራተኛ መታሰቢያ መቅደስ ውስጥ ነው። በመጨረሻም በመቃብሩ እምነ በረድ ላይ ዳግማዊት ኤልዛቤጥ (ከ1926-2022) የሚል ጽሑፍ ይታተማል።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Показать все...
𝚃𝚑𝚎 𝙱𝚞𝚖𝚋𝚕𝚎𝚋𝚎𝚎 𝙿𝚊𝚛𝚊𝚍𝚘𝚡 ንቦችን ስንመለከት በመጀመሪያ ዕይታችን በእነዚህ ትናንሽ ነፍሳት ላይ ለየት ያለ አስደናቂ ነገር ሊኖር እንደሚችል አናስተውልም። ነገር ግን አንድ ምዕተ-ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ለቆየ የሒሳብ ጥያቄ (የሒሳብ ውዝግብ ልንለውም እንችላለን) ምንጭ ሆነው ቆይተዋል። በ 1930ዎቹ ጀርመን ውስጥ በሚገኘው አንጋፋው ጎቲንገን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተሠሩት የሒሳብ ቀመሮች ፤ ንቦች መደበኛዎቹን የኤሮዳይናሚክስ ህግጋት ተጠቅመው በአየር ላይ መብረር እንደማይችሉ ያመላከቱ ነበሩ። ይሁን እንጂ ንቦች የሒሳብ ሊቃውንቱን ቀመር ከቁብ ሳይቆጥሩት አየር ላይ እንደልባቸው ሲበሩ እናያለን። ይህ 𝐭𝐡𝐞 𝐛𝐮𝐦𝐛𝐥𝐞𝐛𝐞𝐞 𝐩𝐚𝐫𝐚𝐝𝐨𝐱 ተብሎ የሚጠራው ውዝግብ ከሳይንሱ ዓለም አልፎ በተራው ሕዝብ ምናብ ውስጥ ሁሉ ገብቷል። ሮበርት ኮርሚየር የተባለ ታዋቂ የልጆች መጽሐፍ ደራሲ እንደውም "The Bumblebee Flies Anyway" በሚል ርዕስ መጽሐፍ ሁሉ አሳትሟል። ከጎቲንገኑ የሒሳብ ቀመር በኋላ በ1996 የኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-እንስሳት ትምህርት ክፍል ተመራማሪዎች በተለያዩ ነፍሳት ክንፎች ዙሪያ ያለውን የአየር ፍሰት በጥልቀት ለማጥናት ሲሉ በመጠን ከፍ ያሉ የነፍሳት ቅርጽ ያላቸውን ሮቦቲክ ሞዴሎች መገንባት ጀመሩ። በእንስሳት ሜካኒክስ ባለሙያዎች የሚመራው ይህ ቡድን መጀመሪያ ላይ ውዝግቡን የሚፈታ የሚመስል ውጤት ማግኘት ችሎ ነበር። ንቦችን ሊያንሳፍፉ የሚችሉ ተጨማሪ የኤሮዳይናሚክስ ሊፍት ኃይሎች የሚገኙት ንቦች ክንፋቸውን ወደ ታች በሚቀዝፉበት ወቅት በክንፋቸው ዙሪያ እና ጠርዝ ላይ በፍጥነት በሚጓዝ የአየር አዙሪት (vortex) ምክንያት መሆኑን ይደርሱበታል። ሆኖም ፣ የንቧ ምስጢር በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አልነበርም። በቅርቡ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተመራማሪዎች የኬምብሪጆቹ አጥኚዎች ከሠሯቸው ግዙፍ የነፍሳት ሞዴሎች ጋር የሚመሳሰሉ ሮቦቶችን ሠርተው ለየት ያለ ውጤት እንዳገኙ 'ኔቸር' በተሰኘው መጽሔት ላይ ጠቁመዋል። ጥናታቸውን ለማድረግም አየርን የሚቀዝፉትን ትናንሽ ንቦች በእኩል መልኩ ሊገልፁ የሚችሉ ግዙፍ ሜካኒካል የንብ ሮቦቶችን ሠርተው ወፍራም የሆነ ዘይት ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ አደረጓቸው። ይህ ሁኔታ በጣም ቀጭን በሆነው አየር ውስጥ የምትወዛወዘውን የትንሽዬዋን ንብ አሠራር እንዴት በእኩል መልኩ ሊገልጽ ይችላል? የሚል ጥያቄ ከተነሳ ከዚህ በፊት ስለ ተፈጥሮ ህጎች ከመጠን ጋር መቀያየር የጻፍኩትን ማስታወስ ይኖርብናል። የትንሽዬዋ ንብ እንደ አየር ባለ ቀጭን ሚዲየም ውስጥ መንቀሳቀስ እና እንደ ሮቦቲክ ሞዴሎቹ ያሉ ግዙፍ አካላት የዘይት ዓይነት ወፍራም ሚዲየም ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ተመሳሳይ ፊዚክስ ስላለው ነው። ከዚህ በፊት 'The Biophysics of Motility' በሚለው ጽሁፌ ስለ Reynold's number ያነሳሁትን ማስታወስ በቂ ነው። በእነዚህ ሙከራዎች መሰረት እንግዲህ የኬምብሪጁ መላምት ያብራራውን ፤ ማለትም "ወደ ታች በመቅዘፍ ጊዜ በሚፈጠር vortex ምክንያት ነው ንቦች እና ሌሎች እንደ ሃሚንግበርድ ያሉ ትናንሽ የወፍ ዝርያዎች አየር ላይ የሚንሳፈፉት" የሚለው ሳይንሳዊ መላምት ትክክለኛውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ሊያብራራ እንደማይችል ተደርሶበታል። ታዲያ ንብ እንዴት ይሆን የምትበረው? ትክክለኛው ሜካኒክስ እስኪታወቅ ድረስ መልሱ "ገና አይታወቅም" የሚል ይሆናል። But, the Bumblebee flies anyway. ይሄን ማጥናት ግን ለምን አስፈለገ? የሚል ሰው ካለ ያኔ ድሮ ላይ ሊዮናርዶ ዳቬንቺ የአውሮፕላንን ንድፍ ከመሥራቱ በፊት ለምን እርግቦችን ማጥናት አስፈለገው? የሚለውን ተመሳሳይ ጥያቄ በመመለስ ማስረዳት ይቻላል። የንቦችን የበረራ ሁኔታ በዚህ ልክ በጥልቀት ማጥናት highly efficient የሆኑ ፋኖችን ፣ ተርባይኖችን እና ለብዙ ጥቅም የሚውሉ ትናንሽ በራሪ ሮቦቶችን ሁሉ ለመሥራት ያስችላል። አብዛኞቻችን እንደ ተራ ነገር የምንወስዳቸው በዙሪያችን ያሉት የተፈጥሮ ክስተቶች በዚህ መልክ በጥልቀት ሲጠኑ ኋላ ላይ ምን ዓይነት ጥቅም ይዘውልን እንደሚመጡ አናውቅም። Curiosity is what drives human civilization! https://t.me/ye_deraswu_mastawesha
Показать все...
የደራሲው ማስታወሻ

አላማችን አንባቢ እና ምክንያታዊ የትዉልድ መፍጠር ነዉ ! @ye_deraswu_mastawesha

Фото недоступноПоказать в Telegram
ጦርነቱም ያበቃል፡፡መሪዎችም በይቅርታና በስምምነት እጅ ለእጅ ይጨባበጣሉ፡፡ በዕድሜ የገፋች እናት በጦርነቱ የተሰዋ ልጇን ይመጣል እያለች መጠበቋን ትቀጥላለች፡፡ልጃገረዲቱም ተወዳጅ ፍቅረኛዋን በናፍቆትና በጉጉት ትጠባበቃለች፡፡ህጻናት ልጆችም ጀግና አባታቸው አንድ ቀን ይመጣል ሲሉም ይናፍቃሉ፡፡ሀገራችንን ማን እንደሸጣት አላውቅም ፤ ነገር ግን ዋጋውን ማን እንደከፈለ ተመልክቻለሁ፡፡ ፣፣፣ ማሃመድ ዳርዊሽ ፍልስጤማዊ ገጣሚ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ምዕራብ እና ምስራቅ ብሎ ከፋፍሎ ከሚያስበላህ የፖለቲካ ደላላ እራሳችሁ አግልሉ። ወርቅ ሆነህ መዳብ ካልሆንክ ብለህ እራሳችሁ የምታሳንሱ ወንድም እህቶቼ እንደ ጅቡ ከፋፍሎ ሊውጣችሁ ከተዘጋጀው ወጥመድ ቶሎ አምልጡ።ወጥመዱ እጅግ በጣም አደገኛ እና ከተያዝክ እዛው የመሰልቀጥ እጣ ፈንታ ነው የሚጠብቅህ። መወጣጠር ሳይሆን ተቀራርቦ በጋራ ችግሮች መፍታት ይበጅሀል።
Показать все...