cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኪራኮስ ማማከር፣ ማኔጅመንት እና ንግድ

stress less, Live more.

Больше
Рекламные посты
277
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
-330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የጫት_ላኪነት_ንግድ_ስራ_ፍቃድ_ቅድመ_ፈቃድ_መስፈርትን_ስለማሳወቅ_231109_180724.pdf5.62 KB
ንግድ ሚንስቴር ሕገ ወጥ የጫት ነጋዴዎችን ከግብይት ሥርዓቱ ለማስወጣት አዲስ አሠራር ተግባራዊ አደረገ ንግድ ሚንስቴር፣ የጫት የወጪ ንግድ ገቢን ለማሻሻል አዲስ የጫት ላኪነት ንግድ ሥራ የቅድመ ፍቃድ መስፈርት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል። አዲሱ አሠራር ሕገ ወጥ ነጋዴዎችን ከግብይት ሥርዓቱ ለማስወጣትና አገሪቱ ከወጪ ንግዱ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንደኾነ ተገልጧል። ካኹን ቀደም የተመዘገቡትና አዲስ ከጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 15 ድረስ በዳግም ምዝገባው እንዲመዘገቡና አዲሱን ፍቃድ እንዲወስዱ ሚንስትር አሳስቧል። ሚንስቴሩ፣ በተጠቀሰው ጉባኤ ውስጥ ፍቃድ ያልወሰዱ ጫት ላኪዎችን ፍቃድ እንደሚሰርዝ ሚንስቴሩ አስጠንቅቋል። Source: Seleda @Ethiopianbusinessdaily
Показать все...
#Ethiopia " ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በገንዘብ መድን ፈንድ ዋስትና ያገኛል " በኢትዮጵያ በባንኮች ገንዘብ ከሚያስቀምጡት አብዛኛዎቹ ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በባንክ ያለው የገንዘብ መጠን ከ100,000 ብር በታች መሆኑ ተገለፀ። ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ወደ ሥራ መግባቱን በተነገረበት ጊዜ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። በተለያዩ ገንዘብ ተቋማት ላለ ተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና የሚሰጥ የገንዘብ መድን ፈንድ ተቋቁሞ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡ ይህ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው ተብሏል። ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በዚሁ ፈንድ ዋስትና ያገኛል የተባለ ሲሆን ጥበቃው የሚመለከተው 100,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነን ብቻ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መርጋ ዋቆያ ተናግረዋል። ይህም በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከተፈፀሙ ለውጦች አንዱ ነው ተብሏል። ፈንዱ አደረጃጀቱ ምን ይመስላል የሚለውን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። የፈንዱ ስልጣንና ተግባር በክፍያ ካዝናነት የተገደበ ነው ተብሏል። አላማው ህዝባዊ ነው የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ በመንግስት እንደሚተዳደር ተገልጿል። ምክትል ገዢው አንድ የፋይናንስ ተቋም የሚወድቅ ከሆነ ኮሽታ ሳያሰማ ህዝቡን ሳይረብሽ ኢኮኖሚውንም ሳይረብሸው እንዲወጣ ፈንዱ ይሰራል ብለዋል። ይህ በሚሆን ጊዜም በመድን የተሸፈነውን ገንዘብ ለአስቀማጩ ከ 7 ቀን እስከ 90 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ አስረድተዋል። 147 ሀገራት የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተቋም አላቸው የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ 148ተኛ ሀገር ሆናለች። የዚህ መረጃ ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው። ፎቶ፦ ኢዜአ @tikvahethiopia
Показать все...
መንግስት የውጭ ላኪ ኩባንያዎች ኪሳራቸውን ለማካካስ ሌሎች ሸቀጦችን ከውጭ እንዲያስቡ ሊፈቅድ ነው መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ በላኪነት የተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን ገቢ ሌሎች ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንዲያውሉት ለመፍቀድ ጥናት መጀመሩን ሪፖርተር ዘግቧል። ጥናቱን እያደረገ ያለው፣ ከንግድ ሚንስቴርና ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተውጣጣ ግብረ ኃይል እንደኾነና የጥናቱ ውጤት ለፖሊሲ አውጪዎች እንደሚቀርብ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጥናቱን የጀመረው፣ በርካታ ላኪ የውጭ ኩባንያዎች ኪሳራቸውን ለማካካስ ሌሎች ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት እንዲፈቀድላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። አኹን በሥራ ላይ ያለው ሕግ፣ በላኪነት የተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነት ዘርፍ እንዳይሳተፉ ይከለክላል። Source: Seleda @Ethiopianbusinessdaily
Показать все...
ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎችና እና ኪሳራዎች   የሚከተሉት ወጪዎች በተቀናሽነት አይያዙም፡- *  የካፒታልነት ባህሪ ያላቸው ወጪዎች፤    *የኩባኒያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሰረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ፤    *ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15% (አስራ አምስት በመቶኛ) በላይ በፈቃደኝነት የሚደረግ ጡረታ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ፤    *የአክሲዮን ድርሻ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል፤    *በመድን፣ በካሳ ወይም በዋስትና ውል መሰረት የተመለሰ ወይም ሊመለስ የሚችል ወጪ ወይም ኪሳራ፤    *ማንኛዉንም ህግ ወይም ዉል በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ካሳ፤    *ግብር ከፋዩ በሂሳብ መዝገቡ የሚይዘው በወቅቱ ወጪ ያልተደረገ ነገር ግን ለወደፊት በግብር ዓመቱ ለሚከሰቱ ወጪዎች ወይም ኪሳራዎች መጠባበቂያ ይሆን ዘንድ የሚያዝ ገንዘብ ወይም የመጠባበቂያ ሂሳብ፤    *በገቢ ግብር አዋጅ ወይም በዉጪ ሀገር የታክስ ህግ መሰረት የተከፈለ የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤    *10 በመቶ በላይ ለግብር ከፋዩ ሠራተኛ የሚከፈል የኃላፊነት አበል ወይም የዉክልና አበል፤
Показать все...
የሒሳብ_መዝገብ_አያያዝ_መመሪያ_ቁጥር_176_2014.pdf6.67 MB
2023_የትራንዚት ፈቃድ በተመለከተ (2).pdf4.45 KB