cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ መረጃና ትምህርት ⛪

ስለ ተዋህዶ ወቅተዊ ጉዳዮች ጠቃሚ የሆኑ መረጃወች አስተማሪ ነገሮች ይለቀቁበታል። @

Больше
Рекламные посты
258
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
-530 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የቁስቋም ክብር በኢትዮጵያ ቀደምት ሊቃውንት:- ✍በመጋቤ ሐዲስ ዶከተር ሮዳስ ታደሰ ከ3 ዓመት የስደት ውጣ ውረድ በኋላ የአምላክ እናት ልጇ አምላካችን ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ከመዐዲ ወደ ላዕላይ ግብጽ በጀልባ ደግሞ ከካይሮ በስተደቡብ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በላዕላይ ግብጽ በምትገኘው ወደ ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም 6 ወር ከ10 ቀናት ዐርፈዋልና ኅዳር 6 በደመቀ መልኩ በዓሏ ይከበራል፡፡ ✔በደብረ ቁስቋም ሳሉ ጨካኙ ሄሮድስ እንደሞተ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘኽ ወደ እስራኤል አገር ኺድ" ብሎታል (ማቴ 2፡19-20)። ✔ ይኽቺን ጌታ ከእናቱ ጋር ያረፈባትን የተቀደሰች ቦታን ጌታችን ባርኳት ወደ ናዝሬት ተመልሰዋል። ጌታችን ካረገ ከብዙ ዘመን በኋላ በኅዳር ስድስት ቀን “አስተጋብኦሙ እግዚእነ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ውስተ ዝንቱ ደብረ ቊስቋም ወቀደሰ ታቦተ ወቤተ ክርስቲያን ወሠርዐ ቊርባነ ወመጠዎሙ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ” ይላል (በዚኽ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል)  ይላል፡፡ ✔ በዚኽ ምክንያት ደብረ ቁስቋምን የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በግብጽ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ይሏታል፤ የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን በእጅጉ የሚወዷት የቁስቋም ገዳም ስትኾን በ1993 ዓ.ም. ላይ እመቤታችን በገዳሙ ተገልጣ እንደነበር ይናገራሉ፤ በዚኽችም ገዳም 100 መነኮሳት ይገኙበታል፤ ከቦታዋ ክብር የተነሣ "ዳግሚት ቤተልሔም" ይሏታል፤ በገዳሙም በቅዱሳት መጻሕፍት የተመላ ታላቅ ቤተ መጻሕፍት አለ፨ ✔ በጌታ በተባረከችው ይኽቺ ቦታ ላይ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቅዱስ ጳኩሚስ ገዳምን የገደመ ሲኾን፤ የእስክንድርያ 23ኛ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በታናሿ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምትክ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ባሰበ ጊዜ እመቤታችን ተገልጻለት የልጇ የክርስቶስ ትሕትናው በገዳሙ እንዲታሰብበት ባለበት እንዲኾን ነግራዋለች። ✔ ከኢትዮጵያ መሪዎች ውስጥ ቁስቋምን በእጅጉ ያስቡት የነበሩት ከ1723-1748 ዓ.ም. የነገሡት የዐጼ በካፋ ሚስት እቴጌ ምንትዋብ ሲኾኑ የእመቤታችን የስደቷና ቁስቋም የመቀመጧን ነገር ኹሌ የሚያስቡ ንግሥት ነበሩ፤ እመቤቴ ልጇን ይዛ ከሀገሯ ወጣ ብላ ቁስቋም እንደቆየች እኔም ከከተማው ወጣ ብዬ መቀመጥ እሻለሁ ብለው 5ት ኪሎ ሜትር ከጎንደር  ከተማ ርቀው በአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ የግንባታ ጠበብት የእመቤታችን የቁስቋም ቤተ ክርስቲያንን ሲያሠሩ 500ው ቆመው ስሕተቶችን በመንገር ያስገነቡ ነበር። ✔ ንግሥት ምንትዋብ የእመቤታችንን ስደት በማሰብ ዕንባቸውን ያፈሱ የነበሩ ንግሥት ሲኾኑ የእመቤታችን ስደቷን አስበው የፈቃድ ጾም የኾነውን ጾመ ጽጌን ለመጀመሪያ ጊዜ መጾም የጀመሩ ንግሥት ርሳቸው እንደነበሩ ሊቁ ዶክተር ሥርግው ይገልጻሉ። ✔ በርካቶች የኢትዮጵያ ሊቃውንት እመቤታችን ከልጇ ጋር ወደ ቊስቋም የመግባቷን ነገር የጻፉ ሲኾን ለምሳሌም አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ በስፋት ሲዘረዝረው፡- “በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ ምስለ ዮሴፍ አረጋይ ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ሐዘን በብካይ” ✍️የሰማዩ አውሬ ሄሮድስ ሕፃናትን መብላት ባሰበ ጊዜ፤ ከሐዘንና ከልቅሶ የምታረጋጋ ማርያም ከአረጋዊዉ ዮሴፍ ጋራ ወደ ቊስቋም ኼደች (ተሰደደች)። “አሥረጸት ማርያም አክናፈ ረድኤት አምሳለ ዖፍ ለዐሪገ ቊስቋም ህየ ከመ ትትዐቀብ ዘመነ ወአዝማነ ወመንፈቀ ዘመን በከመ ይቤ መጽሐፍ” ✍️ማርያም ወደ ቊስቋም ተራራ ለመውጣት እንደ ዎፍ የረድኤት ክንፎችን አበቀለች በመጽሐፍ እንደተናገረ በዚያ በዘመንና በዘመናት በዘመን እኩሌታም ትጠበቅ ዘንድ። “ብጽዐን ለኪ ኦ ደብረ ቊስቋም እምኲሎን አድያም እምናዝሬት እስከ ቤተልሔም ዘተጸወነ ላዕሌኪ መድኀኔ ኲሉ ዓለም” ✍️ከናዝሬት እስከ ቤተ ልሔም ካሉ አውራጆች ኹሉ የዓለም ኹሉ መድኀኒት ወደ አንቺ የተጠጋ የቊስቋም ተራራ ሆይ ክብር ይገባሻል) “በቃለ ውዳሴ ጥዑም ይደሉ ሰላም ለዕበይኪ ፍጹም አድባረ ቊስቋም ማኅደረ ልዑል ዘአርያም” ✍️በአርያም ያለ የልዑል ማደሪያው የኾንሽ የቊስቋም ተራራ ሆይ ፍጹም ለሚኾን ክብርሽ በሚጣፍጥ የምስጋና ቃል ሰላምታ ማቅረብ ይገባል)  በማለት ዘርዝሮ ጽፎላታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ በስደቷ ወቅት በደብረ ቊስቋም ስለማረፏ በድጓው ላይ ሲጽፍ፡- “መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም ወልደ ቅድስት ማርያም ኀሠሠ ምእራፈ ከመ ድኩም ንጉሥ ዘለዓለም ግሩም እምግሩማን ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም ኀደረ ደብረ ቊስቋም” ✍️ቅድመ ዓለም የነበረች ጌትነቱ ምልእት ስፍሕት የኾነች የቅድስት ድንግል ማርያም የባሕርይ ልጅ የዘለዓለም ንጉሥ ሲኾን እንደ ደካማ ማረፊያን ፈለገ፤ ከግሩማን ይልቅ ግሩም፤ የማይጨልም የሕይወት ብርሃን ርሱ በደብረ ቊስቋም ዐደረ። “መንክር ወመድምም ዘተገብረ በደብረ ቊስቋም መንክር ወመድምም ዘይሴባሕ በአርያም አምላክ ፍጹም ኀደረ ውስቴቱ መድኀኔ ዓለም ዘሀሎ እምቅድም ኀደረ ውስቴቱ ለዝንቱ ደብር ዘአብ ቃል ምስለ እሙ ድንግል ደመና ቀሊል” ✍️በደብረ ቊስቋም የተደረገው የሚያስደንቅ እና የሚያስገርም ነው፤ በአርያም የሚመሰገን ፍጹም የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም በውስጡ ዐደረ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ የአብ አካላዊ ቃል ፈጣን ደመና ከተባለች ከድንግል እናቱ ጋር በዚኽ ደብር በውስጡ ዐድሯል) በማለት መስክሮላታል፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦ “ተአምረ ግፍእኪ ለአርእዮ እምገጸ ሄሮድስ መስቴማ አመ ጐየይኪ ማርያም በሐዊረ ፍኖት እለ ደክማ ምስለ እግረ ጽጌኪ ልምሉም ኀበ አእጋርኪ ቆማ ለምድረ ገዳምኪ ቅድስት ቊስቋም ስማ እምፈተውኩ በጺሕየ በሰጊድ እሰዓማ” ✍️ማርያም የግፍሽን ተአምር ለመግለጥ ከጠላት ሄሮድስ ፊት በሸሸሽ ጊዜ ከለመለመች ከልጅሽ እግር ጋር መንገድን በመኼድ የደከሙ እግሮችሽ የቆሙባት ስሟ ቊስቋም የተባለ የተቀደሰች ገዳምሽን እኔም ደርሼ ብሳለማት እመኛለሁ እወዳለሁ) በማለት የጸለያት ጸሎት ነበር፡፡
Показать все...
🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🌷🥀🥀🥀🥀🥀 ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "በዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" "፮ኛ ሳምንት" "#ተፈጸመ" ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። 🌺@ermiasyeabolje🌺 መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። 🌹@ermiasyeabolje🌷 ዚቅ ሃሌ ሉያ፤ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት፤ ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤ እግዚአ ለሰንበት፤ አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ፤ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ። 🌼@ermiasyeabolje🌻 ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ። 🌸@ermiasyeabolje🌺 ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/ ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/ ☘@ermiasyeabolje🍀 ዚቅ እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤ ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ። ማኅሌተ ጽጌ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። ወረብ እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/ ዚቅ ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ንባብኪ አዳም፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት፤ አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ፤ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ። ዓዲ (ወይም) ዚቅ ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኲሎሙ መላእክት፤ ከመ ታዕርጊ ጸሎተነ ጊዜ መንፈቀ ሌሊት። ማኅሌተ ጽጌ ሰዊተ ሥርናዩ ለታዴዎስ ወለበርተሎሜዎስ ወይኑ፤ እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተከልኪ እደ የማኑ፤ ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ሰበኑ፤ ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ። ወረብ ማርያም ለጴጥሮስ "ጽላሎቱ"/፪/ ወለጳውሎስ ሰበኑ/፪/ ወሐዋርያት "መላእክተ"/፪/ በሰማይ ኮነኑ/፪/ ዚቅ ኦ መድኃኒት ለነገሥት፤ ማኅበረ ቅዱሳን የዓውዱኪ፤ ነቢያት የዓኲቱኪ፤ ወሐዋርያት ይሴብሑኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ፤ መላእክት ይኬልሉኪ፤ ጻድቃን ይባርኩኪ፤ አበው ይገንዩ ለኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ። ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ። ወረብ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቊ ባሕርይ/፪/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግስቱ ለጊዮርጊስ መንግስቱ ለሕዝበ ክርስቲያን/፪/ ዚቅ ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል። ማኅሌተ ጽጌ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኮስኮስ ዘብሩር፤ ተአምርኪ ንፁሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር። 🌷@ermiasyeabolje🌹 ወረብ 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 🌟ናሁ "ተፈጸመ"/፪/ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/ "አስምኪ ቦቱ"/፪/ ንግሥተ ሰማያት /፪/🌟 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ ጥቀ አዳም መላትኅኪ ከመ ማዕነቅ፤ ይግበሩ ለኪ ኮስኮሰ ወርቅ። ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ሀገረኪ ናዝሬተ፤ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤ በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ። ወረብ "ተመየጢ"/፪/ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/ ወኢትጎንድዪ "በግብጽ"/፪/ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/ ዚቅ ሃሌ ሉያ፤ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ፤ ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤ እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ፤ ከመ መድብለ ማኅበር ሑረታቲሀ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። መዝሙር በ፮: ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤ ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤ አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ። ዓራራይ በሰንበት እውራነ መርሐ፤ በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤ እለ ለምጽ አንጽሐ፤ ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት። ዕዝል መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤ መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ። ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ። 🌹መልካም በ
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት  1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል። የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
Показать все...
በትግራይ ጦርነት ወቅት የተሰዉ የክልሉ ተዋጊዎች በትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰማዕትነት ክብር እንዲሰጣቸው መንበረ ሰላማ ውሳኔ አስተላለፈ❗❗ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል ለሁለት አመታት በዘለቀው ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት የተሰው የክልሉ ተዋጊዎች የክብር ሰማዕትነት ተሰጥቷቸው፣ “የእግዚአብሔር ሀገር ቅድትስ ትግራይ ሰማዕታት” ተብለው እንዲጠሩ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ላዕለዋይ ቤተክህነት ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ። ።።።።።የሚገርም ነዉ።።።።
Показать все...
የስልጤ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአንድ እምነት ቁጥጥር ስር የወደቀ በመሆኑ ራሳችንን ከተቋሙ አግልለናል!! መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከስልጤ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባልነት ሙሉ በሙሉ ራሷን ያገለለችው በተደጋጋሚ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በዝምታ መታለፉ ሳያንስ ለአንድ እምነት ያደላ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውና ተቋሙ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአንድ እምነት ቁጥጥር ስር የወደቀ በመሆኑ ከተቋሙ ጋር መቀጠል ተገቢ እንዳልሆነ ስለታመነበት እንደሆነ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከተሚማ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ግጭቶችን መንግሥትን በማገዝና ሰላምን በመፍጠር የመቻቻል እሴቶችን ማስቀጠል ዓላማ ያደረገ ተቋም ቢሆንም በዞኑ የሚገኘው የሃይማኖት ተቋም ግን  ኦርቶዶክሳውያን አማኞች ለጉዳት እንዲዳረጉ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን የሚሸረሽሩ አክራሪዎችና ጽንፈኞችን  ሽፋን በመስጠት የተመሠረተበትን ዓላማ የሳተ አካሄድ በመከተሉ ቤተ ክርስቲያን ከተቋሙ ራሷን ማግለሏን በደብዳቤ እንዳሳወቀችም ገልጸዋል። በአሁን ሰአት በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሳለ በአንድ ሃይማኖት ቁጥጥር ስር የወደቀው የዞኑ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔም ሆነ የዞኑ የመንግስት አካላት ግን እስከ አሁን ድረስ የተፈናቀለውን ህዝብ የት እንዳለ እንኳ ለማየት እንዳልሞከሩና ጉዳዩ ግድ እንዳልሰጣቸውም የገለፁ ሲሆን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕግ ክፍል ጋር መረጃ በመለዋወጥና ጉዳዩን ወደ ፌደራል በመውሰድ አጥፊዎች በሕግ እንዲጠየቁ እየተሰራ እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል። #Ethiopia #Tewahedo_Media_Center #TMC_Addia_Ababa ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
Показать все...
* ማርያም * የእመቤታችን ስም ብዙ ትርጓሜ የያዘ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተወሰኑትን እንመለከታለን። #ማ - ማለት #ማህደረ_መለኮት (የመለኮት ማደሪያ ) ማለት ነው። #ር- ማለት #ርግብየ_ይቤላ የዋሂት የሰለሞን ርግብ ፣ በጥፉት ውሃ ጊዜ ለኖህ የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ የጥፉት ውሃ መጉደሉን ያበሰረች ለምህረት የመጣች ርግብ ማለት ነው። #ያ - ማለት #ያንቃዐዱ_ኀቤኪ ፣ በአንቺ አማላጅነት ያመኑ ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልን እያሉ ወዳንቺ ይለምናሉ ማለት ነው። #ም - #ምስአል_ወምስጋድ ወመስተስረዬ ኃጢአት፡ኃጢያትን ለማስተሰረይ ምህረትን ከፈጣሪ ዘንድ እያማለድሽ የምታሰጪ ማለት ነው። @eotcy #ማርያም ፦ ማለት #መርሕ_ለመንግስተ_ሰማያት ማለትነው። በዚህ ዓለም ያለ በስጋ አይነ ስውር የሆነ ሰው መሪ በትር እንደሚያስፈልገው ሁሉ ወደ ሰማያዊዉ ዓለም ለሚጓዙ ሁሉ መሪ የሆነችና በታመነው አማላጅነቷ መርታ ወደ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስርየተ ኃጢያትን በረከተ ስጋንና በረከተ ነፍስን ከልጇ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ እየለመነችና እያማለደች የምታሰጥ ማለት ነው ። #ማርያም ፦ ማለት #ፍፅምት ማለት ነው ። ለጊዜው መልክን ከደምግባት ጋር አስተባብራ ተገኝታለችና ፍፃሜው ግን ንፅሀ ስጋን ንፅሀ ልቡናን ንፅሀ ነፍስን አስተባብራ ተገኝታለችና። ፍፅምት ትባላለች። @eotcy #ማርያም ፦ ማለት #ፀጋ_ወሐብት ማለት ነው ። ለጊዜው ለእናቷ ለቅድስት ሀና ለአባቷ ለቅዱስ ኢያቄም ጸጋ ሐብት ሆና ማለት የስለት ልጅ ሆና ከፈጣሪዋ ተሰጥታለችና ። ፍፃሜው ግን በዕለተ አርብ ጌታችን መስቀል ላይ ሆኖ በወንጌላዊዉ ቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት በአለም ላለን ክርስቲያኖች ሁሉ እናት ሆና ተሰጥታለችና። @eotcy #ማርያም ፦ ማለት #ማሪ ማለት በዕብራይስጥ #እመቤት ማለት ነው ። #ሐም ፦ ማለት ደግሞ #ብዙሀን ማለት ነው ። በዕብራይስጥ #ማሪሐም ማለት #የብዙሀን_እመቤት ማለት ነው። የዓለም ሁሉ እመቤት የሆነች የእናት አማላጅ ናትና። የአባ ኤፍሬም ውዳሴ ፣ የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ፣ የያሬድ ውብ ዜማ የነብያት ትንቢት የሀዋሪያት ስብከት ፡ የመላዕክት እህት የሰማዕታት እናት የሆነችው ማርያም ከፊት ትምራቹ ከሁዋላ ትከተላቹ ከግራ ከቀኝ ትቁምላቹ ። በጨነቃችሁ ነገር ሁሉ አለው ትበላቹ ከፈጣሪ ዘንድ ታማልዳቹ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌼የተከበራቹ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ🌼 በሰላም አደረሳችሁ እያልን ባሳለፍነው ዓመታት የኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች በሚል ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ የሆኑትን ነገሮች እያቀረብንላቹ ቆይተናል፤ ነገር ግን በታቀደለት ልክ እያደገ አይደለም ፤ በአዲሱ ዓመትም ሰፋ ያሉ ትምህርቶችን አዘጋጅተን እንጠብቆታለን 👉 እርሶም የኦርቶዶክስ አስተምሮቶች ለሁሉም ይስፋፋ ዘንድ ቻናላችንን ይጋብዙልን ። ስለትብብሮ ከልብ እናመሰግናለን🙏           አብሮነቶ አይለየን 🌼፳፻፲፮ ዓ.ም የሠላም የፍቅር ያድርግልን🌼 ሀሳብ አስተያታችሁ ይጠቅመናልና https://t.me/eotcy_comment  ላይ ይቀላቀላሉ ቻናሉ https://t.me/eotcy         https://t.me/eotcy         https://t.me/eotcy ሼር❗         ሼር ❗        ሼር❗ ለወዳጆ ያጋሩልን ዘንድ በአምላከ ቅዱስን ስም እንጠይቃለን🙏🙏🙏 .......እነሆ የተወደደችው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው 🌼       1ኛ ቆሮ6÷2
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!!! "ከዚች ዓለም የፈተናና የመከራ ቂም በቀል ኑሮ በመላእክት አጃቢነት በክብር ለተለየችው ፀዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ቅዱሱ አባት ሆይ፤ የመርዓስ ዓቃቤ ሕግ ቶማስ የተባልክ አንተ ተክለ ሃይማኖት ነህና፤ በሕይወተ ሥጋ ሳሉ መታሰቢያህን ላደረጉ ሁሉ ጌታዬ ሆይ፤ ክብርና ሞገስን አጎናጽፋቸው፡፡" መልክዐ አቡነ ተክለሃይማኖት
Показать все...
" ቅዱስገብርኤል ሆይ አስቀድሞ ቂርቆስን እና እናቱን ኢየሉጣን እንዳዳንካቸው እኔንም የመከራ ቁስል እንዳይጠዘጥዘኝ ከ እሳት ነበልባል አድነኝ " - መልክዐ ገብርኤል https://t.me/DnwaseTefe
Показать все...
ኦርቶዶክሳዊ መረጃና ትምህርት ⛪

ስለ ተዋህዶ ወቅተዊ ጉዳዮች ጠቃሚ የሆኑ መረጃወች አስተማሪ ነገሮች ይለቀቁበታል። @

የገባን  እንዲገባቹ  .......የነካን  ይንካቹ  😍😍 ማርያምን  ለመውደድ   ጥቅስ  የምትፈልጉ   ማርያምን  ለማመስገን     የሚዳዳቹ    ማርያም  ሲባል  የሚነዝራቹ   እውነት    የገባን እንዲገባቹ  ...የነካን  የእናትነት  ፍቅሯ  ይንካቹ .. ማርያምን  ነው  የምላቹ   በቀን  ውስጥ  ስሟን  ሳልጠራ  አልውልም  የማዋያት  እናቴ  ሚስጢረኛዬ ሲከፋኝ  እደጇ  ሄጄ  የማለቅስባት አፌን የፈታውበታ  ገና በልጅነቴ  በልቤ ላይ  የታተመች   የፍቅር  መፅሀፍ    የማትጠገብ  የህይወት   ፅዋ  ናት  .....በቃ  እናቴ  እኔ  አንቺን  እወድሻለው ለምን  የሚለኝ  ካለ ቀርባቹ  እይዋት  .....ከምንጠቅሰው  ጥቅስ  በላይ  ማርያም ፍቅር   ደግሞም  ወንጌል  ናት  😍 ለምን  ወደድካት  አትበሉኝ   የገባኝ  እንዲገባቹ         ጠጋ ብላቹ  ህይወቷን  አንብቡ በነገራችን  ላይ  ሰው  ጤነኛ ሆኖ  ማርያምን  አይጠላም                        
Показать все...