cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM

በደ/ነ/ቅ/ዮሐንስ እና መ/ጎ/ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ ዌብሳይታችን www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg ለሀሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!! @FikureEgzi04

Больше
Рекламные посты
7 373
Подписчики
+824 часа
+407 дней
+19430 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
👨‍🏫 ኑ በጋራ አንባቢ ትውልድ እንፍጠር 👨‍🏫 መጻሕፍትን የማሰባሰቢያ መርሐ ግብር 📚📖 የአቡቀለምሲስ ቤተ መጻሕፍት የመጻሕፍት ክምችት ለማሳደግ 📚( አምስት መቶ) 500 📚 ከሕጻናት የተረት መጻሕፍት እስከ ትልልቆቹ መጻሕፍት ድረስ ይለግሱ 📚 እኔ ትውልድን በምግባር እና በሃይማኖት ለምትቀርጽ ሰንበት ት/ቤት አንድ መጻሕፍት እለግሳለሁ። 📗📇
Показать все...
👍 6 3👏 2😢 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር አስበዋል! 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖       የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት የክረምት  ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት   አዘጋጅቶ ይጠብቆታል። 👉 ትምህርቱ የሚሰጥበት   🗓 ሰኞ እስከ ዓርብ 🕰 ከምሽት12: 00 እስከ 2:00 ሰዓት ድረስ 👉 📅  ትምህርቱ የሚጀምረው ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም 📝 ምዝገባው: -  በሰንበት ት/ቤቱ ቤተ መጽሐፍት እና በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 9:00 እስከ ምሽቱ  2:00 ሰዓት ቅዳሜና እሁድ ከጠዋቱ 3: 00 እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ወይም  🌍  ከስር ያለውን የዌብሳይታችንን  ሊንክ በመጫን ባሉበት ቦታ ሆነው  መመዝገብ ይችላሉ። https://fikureegzi.com/Free_Registration          ትምህርቱ የሚሰጠው በነጻ ነው!! "አንተ ግን በተማርክበት እና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር" 2ጢሞ 3÷14
Показать все...
👍 7🥰 3👏 1
27👏 8
የደብራችን ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ በአሁኑ ሰዓት እያስገነባቸው የሚገኙት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተ መቅደስ እና የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት የመማሪያ አዳራሽ ሥራ ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? 1 የእመቤታችን ሕንጻ ቤተ መቅደስ ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ፦ የሁለተኛዉ(የላይኛዉን ዶም )ኮንክሪት ለመሙላት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን አጠቃላይ የስትራክቸር ሥራዉ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ እንዲያልቅ ከሕንጻ ተቋራጩ ጋር ስምምነት ላይ ተደረሶ ቀሪ ሥራዎቹ በመፋጠን ላይ ይገኛሉ። የቤተ መቅዱስን ሥራ ለማጠናቀቅ የሚቀሩ ዐበይት ሥራዎች፦ + ሙሉ የፊኒሺንግ የማጠናቀቂያ ግንባታዎች (የኤሌክትሪክ፣የሳኒተሪ ....) + የበር፣የመስኮትና የወለል ማንጠፍ ስራዎች + የሳይት ወርክ ሥራዎች + የቤተ መቅደስ ውስጥ የቅዱሳት ሥዕላት ዝግጅት  + የሊፍት እና የላይኛው መቅደስ ወለል ሥራዎች እና ሌሎችም ናቸው 2 የሰ/ት/ቤት የመማሪያ አዳራሽ ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ፦ ሰ/ት/ቤቱ ካለበት የቦታ ችግር አንጻር የሚገነባው አዳራሽ ባይጠናቀቅም የስትራክቸር ሥራው ተጠናቆ በከፊል አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል በአሁን ሰዓትም የብሎኬት ግንባታ ሥራዉ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የጂብሰም ሥራው 80% ተጠናቋል የዉጪው የኮንክሪትና የመስኮት ፍሬም ሙሊት ሥራ ደግሞ እየተከናወነ ይገኛል። የሰ/ት/ቤቱን አዳራሽ ለማጠናቀቅ የሚቀሩ ዐበይት ሥራዎች፦ +  ሙሉ የፊኒሺንግ የማጠናቀቂያ ግንባታዎች       (የኤሌክትሪክ፣የሳኒተሪ ወዘተ...) + የበርና መስኮት ሥራዎች + የኮርኒስ ሥራ እና የወለል ማጠናቀቂያ ሥራዎች + የመድረከ (ስቴጅ) ሥራ + የሳይት ወርክ ሥራዎች እና ሌሎችም ናቸው የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤቱ እነዚህ ሁለት የግንባታ ፕሮጀክቶች ተሠርተው እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻዎችን በማድረግና የመዝሙር ካሴት አዘጋጅቶ ሙሉ ገቢው ለሕንጻ ግንባታዎቹ እንዲሆን በመለገስ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል ። ይህን ድጋፍ ለወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን  56 ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችንን ምክንያት በማደረግ የሰ/ት/ቤቱ አባላት እና ምእመናን ድጋፋችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ ለማቅረብ እንወዳለን :: የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴው የባንክ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000241089707
Показать все...
👍 6 4
ከተቃጠለ 156 ዓመታት ያስቆጠረው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱ ከበረ ። በጉራጌ ሀገረ ስብከት  በምሁርና አክሊል ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘውን ጥንታዊ የመንቆረር ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሀሰን እንጃሞ በተባለ ወራሪ አማካኝነት ከተቃጠለ ከ156 ዓመታት በኋላ አቶ ቶማስ ለተባሉ አባት ስለ ቦታው በተገለጠላቸው ራዕይ መሠረት  ህንጻ ቤተክርስቲያኑን እንደ አዲስ  በመሥራት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ተባርኮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ  ምዕመናን በተገኙበት ህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ተመርቆ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።  በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ ይህን ህንጻ ቤተመቅደስ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው  በበዓሉ ላይ ለተገኙት ምዕመናን ይህን  “መልካም ነገር ተማሩበት፣ እውነትን እወቁበት የሰማይን አምላክ ተመልከቱበት” በማለት አባታዊ ምክራቸውን ሰጥተዋል።
Показать все...
15👍 5👏 2
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ‹‹ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።"(ማቴ 10:28)››   እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ አስቀድሞ ጌታችን በክርስቶስ  ክርስቲያን  ለተባልን ስለ ሃይማኖታችን የምንቀበል ንዑድ ክቡር  እንደሚያስብል ሲነግረን "ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።"(ማቴ 5:11፤) ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ስለ ክርስቲያኖች  መከራ ሲናገር ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለው። ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ለማውጣት የሁሉም ድረሻ አላቸው  በዚቺ ርትዕት ሃይማኖት ውስጥ ያለ የሃይማኖቱ ተከታይ ቤተክርስቲያን  በየጊዜ ከሚገጥሟት ችግር  መከራ ዳር ሆኖ ከመመልከት በየዘርፉ መንፈሳዊ ኃላፊነቱን ግዴታውን መወጣት አለበት ። ከእነዚህም መካከል ምዕመናን  አንዱ ናቸው   ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ለማውጣት የምእመናን ድርሻ ምንድን ነው? 1. እውነተኛ የክርስትና ሕይወት መኖር:- ከቤተ ክርስቲያን ጥላ ስር ሳይርቁ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅነትን ክብር በጥምቀት  ከውኃና ከመንፈስ በመወለድ ያገኘን ልጅነታችንን የሚያረጋግጥ መንፈሳዊ ሕይወትን መኖር ይጠበቅብናል:: የእውነተኛ ክርስትና መገለጫው ሥነ ምግባር ነው:: ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ “ምግባር የሌለው ሃይማኖት በራሱ የሞተ ነው::” (ያዕ2፣ 17) እንዳለ። ዕለት ዕለት በጸሎት የምንተጋበት፣ ለንስሐ የምንፈጥንበት፣ በአገልግሎት የምንበረታበት፣ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ታንጸን የምንኖርበት ሕይወት ሊኖረን ያስፈልጋል:: 2. በተሰጠን መክሊት ማገልገል:-  ቅዱስ ጳውሎስ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ “እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን… አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ::” (ሮሜ 12: 7) ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እግዚአብሔር በሰጠን ልዩ ልዩ ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን በትጋት ማገልገል ያስፈልጋል። በሰበካ ጉባኤ ባለን የሞያ ዘርፍ  ጠቃሚ ዕውቀት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት : አ: በምህንድስና፣ በህክምና፣ ፣ በሕግ ፣...ቤተክርስቲያንን እንጠቅምበታለን እኛም በረአት እናገኝበታለን ። 3.ቤተ ክርስቲያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ:-ቤተ ክርስቲያንን ዘወትር ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ፈተና ይደርስባታል።የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የካህናት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ምዕመናን  በሕብረት  ሆነው የሚያገለግሉት አገልግሎት ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያን ከተሓድሶ አቀንቃኞች መናፍቃን አጥማቂ ነን እያሉ ሥርዐተ ቤ/ክ ከሚያፈርሱ የቤ/ክ ገንዘብ ከሚዘርፉ  መጠበቅ ከእያንዳንዱ ምእመን ከሚጠበቁ የሥራ ድርሻዎች አንዱ ነው:: ቤ/ክ መጥቶ ከመማር ከማስቀደስ ከመቁረብ ጉን ለጎን ቤተክርስቲያን   ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ያርፈልጋል። በመጨረሻም አሁን ያለችው ቤተክርስቲያን  ቀጣይ ተረካቢ እንዳጣ ሁላችንም በሥጋ የወለድናቸውን ልጆቻችንን  በሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ዕውቀት እንዲያገኙ በቅድስት ቤ/ክ እንዲጸኑ ለነገዋ ቤተክርስቲያን  ተተኪ ለማድረግ ማስተማር  ምስጢራቱ እንዲካፈሉ በማድረግ ክርስቶስ በደሙ የመሰረታትን ሐዋርያት በዓመም ዙረው ያስተማሩላት ሰማዕታት የመሰከሩላት ቅዱሳን ጻድቃን የተጋደሉላትርትዕት ሃይማኖት  ቅድስት ቤተክርስቲያን ከመጣባት መከራ እንድንታደግ ልዑል እግዚአብሔር  ይርዳን።
Показать все...
👍 6🙏 1
ምን እንጠይቅልዎ ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ለማውጣት የምእመናን ድርሻ ምንድን ነው? የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው ትምህርት በቆረሰው ቅዱስ ሥጋው፣ ባፈሰሰው ክቡር ደሙ የተመሠረተች ጸንታ የምትኖር ናት።ይህች ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ስብከት የተስፋፋች፣ በሰማዕታት ደም የጸናች፣ በቅዱሳን ተጋድሎ ትሩፋት ያጌጠች፣ በምእመናን ጥብዓት የጠነከረች ሰማያዊት ስትሆን በምድርም ያለች ሰማይ ሥርዓት የሚከናወንባት የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት። ቤተክርስቲያን በዘመነ ነቢያት ጀምሮ አሁን አስካለንባት ዘመን ድረስ መከራ ስደት ሰማዕትነት ቤ/ክ መቃጠል.. ከውስጣዊ ና ከውጪም በሆነ አካት አስደናግዳለች ታስተናግዳለች። በዚህ መከራ ተጠቂ የሚሆኑት አገልጋዩ ካህናት አባቶችና ማኅበረ ምእመናን (አማኞቹ ናቸው።
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ወደብድረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጋብቻህን  የፈጸምከው የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ አቶ ኤፍሬም ዘነበ (ተክለ አብ ) ከ እህታችን ከማህሌት አላዩ (ወለተ ፃድቅ ) የፈጸምከው ጋብቻ የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ዮሐንስ ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ " ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "                           መጽሐፈ ዲድስቅልያ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ/አዲስ አበባ) ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዌብሳይታችን   www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ የቴሌግራም ገጻችንን https://telegram.me/Fikureegzi4 √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/fikure_egzi?r=nametag √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@fikure_egzi_media
Показать все...
12👍 8
"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጋብቻችሁን  የፈጸምችሁት የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋዮች ①  ዲ/ን በሱፍቃድ ወንድሙ ከ ወ/ሪት ሜላት ዳሩንጋ ጋር ②   ወ/ሪት ፅጌሬዳ አለሙ  ከአቶ አድማሱ አቅሰማ  ጋር የፈጸማችሁት ጋብቻ የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ዮሐንስ ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ " ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "                           መጽሐፈ ዲድስቅልያ ግንቦት 25  ቀን 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ/አዲስ አበባ) ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዌብሳይታችን   www.fikureegzi.com √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/Fikureegzi4 √ የቴሌግራም ገጻችንን https://telegram.me/Fikureegzi4 √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/fikure_egzi?r=nametag √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@fikure_egzi_media
Показать все...
👍 19 6🥰 4👏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ መሪ ዕቅዱ እንዲተገበር ውሳኔ አስተላለፈ። ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ( ፍ.እ.ሚ./አዲስአበባ ) የግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለበርካታ ዓመታት የተጠናው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲደረግ በዛሬው እለት ባደረገው ጉባኤ ውሳኔ አስተላለፈ። ከዚህ በተጨማሪ በብፁዓን አባቶች የቀረበውን የአህጉረ ስብከት የዝውውርና የሽግሽ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ውይይት ካደረገ በኋላ ለጉዳዩ የተሰየመው ኮሚቴ አጥንቶ ባቀረበው መሰረት ዝውውርና ሽግሽጉን አጽቋል። በዚህም መሰረት፦ 1ኛ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ ምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት፤ 2ኛ.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ከምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ ኢትዮ ሱማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት፥ 3ኛ.ብፁዕ ጨቡነ ዳንኤል ከምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ አፋር ሀገረ ስብከት፤ 4ኛ.ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ከኢትዮ ሶማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ወደ ምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ተዛውረ አህጉረ ስብከቱን በአባትነት እንዲመሩ ተወስኗል። 5ኛ.ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመድበዋል። 6ኛ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ አሁን በያዙት የዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ላይ ከንባታ፣ሀላባና ጠንባሮ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ተወስኗል። 7ኛ.ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል አሁን የያዙትን አህጉረ ስብከት እንደያዙ የምሥራቅ ወለጋ፣የምዕራብ ወለጋ፣የሆሮ ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ተወስኗል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጉባኤውን በመቀጠል በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ከሰኞ ጀምሮ ተወያይቶ ልዩልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
Показать все...
👍 12