cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

💠አይዋሽም መስቀሉ💠

በቅድሚያ እንኳን ደህና መጡ።ይህ ኦርቶዶክሳዊ የግል የቴሌግራም ቻናል ነው።በውስጡም ሃይማኖታዊና አስተማሪ ነገሮች ብቻ ይለቀቁበታል። ❖ እግዚአብሔርን መስማት ያሳርፋል አለማችን እግዚአብሔርን ባለመስማት በመመላለሷ ረፍትን አጥታለች። እኛም እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ አለምን እየሰማን መቅበዝበዝን ጨምረናል፡፡ እግዚአብሔርን መስማት ግን ከሁሉ የሚልቅ ይጠቅማል።ወዳጄ ሆይ እርሱን ስማ።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
780
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለምን ? አባ እንጦንስ ስለ እግዚአብሔር ጥልቅ ፍርድ ሲያስብ ፡- “ጌታ ሆይ አንዳንዶች ገና ወጣት ሳሉ የሚሞቱት ሌሎች ደግሞ ከወጣትነት እስከ ሽበት ብዙ ዘመን የሚኖሩት ለምንድነው ? ጌታ ሆይ አንዳንዶች ምንም የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ድሆች ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ተርፏቸው የሚደፉ ባለጠጎች ለምን ይሆናሉ ? ደግሞስ ኃጢአተኞች በስኬት ሲኖሩ ቅኖች ግን ለምን ይቸገራሉ ?” ብሎ ጠየቀ ፡፡ አንድ ድምፅ እንዲህ ብሎ ሲመልስለት ሰማ ፡- “እንጦንስ ሆይ ትኩረትህን ራስህ ላይ አድርግ ፤ እነዚህ ነገሮች ለምን እንዲህ እንደሆኑ በእግዚአብሔር እውቀት ውስጥ ያለ ነገር ነው ፡፡ ስለ እነዚህ ነገሮች ማወቅ ላንተ ምንም ጥቅም የለውም ፡፡” በዘመናት ሁሉ የነበሩ ከነቢይ እስከ ፈላስፋ ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የጠየቁት ጥያቄ ቢኖር “ለምን ?” የሚለውን ጥያቄ ነው ፡፡ ብዙዎችም እንደ ገደል ማሚቱ የተናገሩትን ድምፅ መልሰው ከመስማት በቀር ማረፍ አልቻሉም ፡፡ ፍልስፍና በሰው ተጀምሮ በሰው የሚጠናቀቅ በመሆኑ መጨረሻው ጥርጣሬና ክህደት ነው ፡፡ እምነት ግን በእግዚአብሔር ተጀምሮ በእግዚአብሔር የሚልቅ በመሆኑ ዕረፍት አለው ፡፡ ፍልስፍና ከጥያቄ ወደ ጥያቄ ሲሄድ እምነት ግን ከጥያቄ ወደ መልስ ይሄዳል ፡፡ በእምነት ዓለም እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገሮች መልስ አይሰጥም ፣ ራሱ ግን መልስ ነው ፡፡ መልስ ቢሰጥ ሊቅ ነው እንለዋለን ፤ እርሱ ግን ራሱ ጥበብ ነው ፡፡ መልስ ቢሰጥ መምህር ብቻ እንለዋለን ፤ እርሱ ግን ህልውናው ዕረፍት ነው ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ በክፉዎች የሚቀኑ አያሌ ናቸው ፡፡ “እኔ እግዚአብሔር ፣ እግዚአብሔር እላለሁ ፤ የተመቻቸው ግን ከሃዲዎቹ ናቸው” የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ ፡፡ ደግሞም በፍትሐዊ አእምሮ ሆነው ክፉዎች እየገነኑ ደጎች እያነሡ ለምን ይሄዳሉ ? የሚሉ አያሌ ናቸው ፡፡ ነቢዩ ዕንባቆም ይህን ጥያቄ አንሥቷል ፡፡ ስለ ፍርድ መጓደል ፣ ማለቂያ ስለሌለው የድሆች መገፋት እግዚአብሔርን ሞግቷል ፡፡ “የእኔ ክፉ ዓይኖች ማየት ያልቻሉትን ግፍ የደጉ ጌታ ዓይኖች እንዴት ችለው አዩ ?” በማለት የጠየቁ ብዙ ናቸው ፡፡ ስድስት ሚሊየን አይሁድ በናዚዎች ሲፈጁ እግዚአብሔር እንዴት ዝም አለ ? በማለት ፍትሕ ፈላጊ አእምሮአቸው መልስ አጥቶ እግዚአብሔር የለም ያሉ አያሌ ናቸው ፡፡ ነገር ግን ግፍና ፍትሕ ሳይኖር ከዓለም አስቀድሞ እግዚአብሔር ነበረ ፡፡ የእግዚአብሔርን እጅ ስንፈልግ እኛስ የድርሻንን ተወጥተናል ወይ ? በዓለም ላይ ያለው ችግርስ እኛ የፈጠርነው ነው ወይስ እግዚአብሔር የላከው ነው ? ከሞቱት ሰዎች ይልቅ እኛ ለምን ኖርን ? ብለን ጠይቀን እናውቃለን ? አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ድካም ያዩና ከክርስትና ውጭ ያሉ ሰዎችን ብርታትና የመዳን ናፍቆት በማየት እኔ ከእነርሱ በምን ተለይቼ ነው ክርስቲያን የሆንኩት ? የተሻሉ እያሉ የወደቅሁ እኔ እንዴት በእምነት ዓለም ተገኘሁ ? ይላሉ ፡፡ ይህ አመለካከታቸውም ቅድመ ውሳኔ ቢኖር ነው ፣ አስቀድሞ የሚጸድቀውና የሚኰነነው ቢወሰን ነው እንዲሉ አድርጓቸዋል ፡፡ ነገር ግን ሌሎች ለምን ጠፉ ሳይሆን እኔ ለምን ዳንሁ ? ማለት ወደ መንፈሳዊነት ይመራል ፡፡ ጌታችን በሌሎች መሞት ወይም በሌሎች ላይ በደረሰው አደጋ ተገርመው ፣ ምን ቢበድሉ ነው ? ለማለት ዜናውን ይዘው ለመጡት፡- “ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ” በማለት ተናግሯል /ሉቃ. 13፡3/፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አሁንም ያሉት በኃጢአታቸውና በእነርሱ መካከል የእግዚአብሔር ምሕረት ጣልቃ ስለ ገባ መሆኑን ስለ ሌሎች መጥፋት ሲያስቡ እነርሱም ካልተመለሱ ከምድራቸው እንደሚነቀሉ ማለትም በ70 ዓ.ም ስለሚመጣው ፍርድ ነግሯቸዋል ፡፡ አዎ እግዚአብሔር አሰጣጡ ለየራስ ነው ፡፡ ለአንዱ የመብላት አምሮትን ለሌላው ደግሞ ምግብን ፣ ለአንዱ ጫማ ለሌላው ደግሞ እግር፤ ለአንዱ እንቅልፍ ለሌላው ደግሞ አልጋ ፤ ለአንዱ መታከሚያ ገንዘብ ለሌላው ደግሞ ጤና ፤ ለአንዱ ቪላ ቤት ለሌላው ደግሞ ሰላም ይሰጠዋል ፡፡ ብቻ ይህ ሁሉ ለምን እንደ ተደረገ ማብራሪያ አልተሰጠንም ፡፡ ምክንያቱም የታዘዝነውን መፈጸም እንጂ ሌላው ስለማይመለከተን ነው ፡፡ አዎ ሌሎች እየራባቸው ነው እኛስ እየመጸወትን ነው ? ሌሎች በወጣትነታቸው እየሞቱ ነው እኛስ ንስሐ እየገነባን ነው ? አዎ ቅኖች እየተገፉ ነው እኛስ እያስጠጋናቸው ነው ? አንዳንዴ የአፍ ወዳጅ እንጂ የተግባር ወዳጅ አይደለንም ፡፡ የራሳችንን ድርሻ ላለመወጣት እግዚአብሔርን ተጠያቂ ማድረግ እንወዳለን ፡፡ በርግጥ እንደ ቅዱስ እንጦንስ እንደ ነቢዩ ዕንባቆም በቅን ልብ ፡- “ለምን” ልንል እንችላለን፡ እግዚአብሔር ግን የሚሰጠን ምላሽ፡- - ትኩረታችንን ራሳችን ላይ እንድናደርግ / በእኛ ላይ የበዛውን ትዕግሥቱን በማሰብ ንስሐ እንድንገባ/ - ሁሉም ነገር ከእግዚአብሔር እውቀት ውጭ አይደለም ብለን በእርሱ እውቀት እንድናርፍ - የታዘዝነውን ማድረግ እንጂ ለምን እንደዚህ ሆነ ? የሚለው ጥያቄ ምንም እንደማይጠቅመን እንድንገነዘብ ነው ፡፡ ሠናይ ምሴት @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm
Показать все...
"Three persons stood on the Mount of Transfiguration, each gloriously illumined. Each had excelled in fasting; each had fasted forty days and forty nights. They were Christ the Lord, glory be to Him, Moses and Elijah. Does this glorious scene conceal behind it an important notion- that in subduing the body through fasting, the spirit transfigures, and the body transfigures? Did Christ the Lord choose two of those who fasted to appear with Him on the Mount of Transfiguration, to show us that the nature which will be transfigured in eternity will be that which, through fasting, subdued the body?" + Pope Shenouda + [Taken from 'Sanctify a Fast'] @Hesychasm @Hesychasm
Показать все...
የኒቂያ የሃይማኖት መግለጫ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደህንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብና ከወልድ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተነገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተስረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንን ትንሣኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን Πιστεύομεν εἰς ἕνα Θεὸν Πατέρα παντοκράτορα ποιητὴν οὐρανοῦ καὶ γῆς ὁρατῶν τε πάντων καὶ ἀοράτων· καὶ εἰς ἕνα Κύριον Ἰησοῦν Χριστὸν τὸν υἱὸν τοῦ Θεοῦ τὸν Μονογενῆ, τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων, Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ, γεννηθέντα οὐ ποιηθέντα, ὁμοούσιον τῷ Πατρί, δι' οὗ τὰ πάντα ἐγένετο· τὸν δι' ἡμᾶς τοὺς ἀνθρώπους καὶ διὰ τὴν ἡμετέραν σωτηρίαν κατελθόντα ἐκ τῶν οὐρανῶν, καὶ σαρκωθέντα ἐκ Πνεύματος Ἁγίου καὶ Μαρίας τῆς παρθένου, καὶ ἐνανθρωπήσαντα, σταυρωθέντα τε ὑπὲρ ἡμῶν ἐπὶ Ποντίου Πιλάτου, καὶ παθόντα, καὶ ταφέντα, καὶ ἀναστάντα τῇ τρίτῃ ἡμέρᾳ κατὰ τὰς γραφὰς, καὶ ἀνελθόντα εἰς τοὺς οὐρανοὺς, καὶ καθεζόμενον ἐν δεξιᾷ τοῦ Πατρὸς, καὶ πάλιν ἐρχόμενον μετὰ δόξης κρῖναι ζῶντας καὶ νεκρούς, οὗ τῆς βασιλείας οὐκ ἔσται τέλος· καὶ εἰς τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον, τὸ Κύριον καὶ Ζωοποιόν, τὸ ἐκ τοῦ Πατρὸς ἐκπορευόμενον, τὸ σὺν Πατρὶ καὶ Υἱῷ συμπροσκυνούμενον καὶ συνδοξαζόμενον, τὸ λαλῆσαν διὰ τῶν προφητῶν· εἰς μίαν ἁγίαν καθολικὴν καὶ ἀποστολικὴν ἐκκλησίαν· ὁμολογοῦμεν ἓν βάπτισμα εἰς ἄφεσιν ἁμαρτιῶν· προσδοκῶμεν ἀνάστασιν νεκρῶν, καὶ ζωὴν τοῦ μέλλοντος αἰῶνος. ἀμήν. 🙄ቻናሉን ተቀላቀሉ @Hesychasm @Hesychasm
Показать все...
የዐቢይ ጾም የእለታት ስያሜዎች የዕለታቱን ስያሜዎች የሰየመው ቅዱስ ያሬድ ነው ። ቤተክርስቲያናችን በየሳምንቱ አባታችን ያሬድ በሰየመው ስያሜ ከስያሜው ጋር የተያያዘ ነገር ትሰብካለች። የዕለታቱ ስያሜዎችም ፦ ፩ ዘወረደ ፪ ቅድስት ፫ ምኩራብ ፬ መጻጒዕ ፭ ደብረ ዘይት ፮ ገብርኄር ፯ ኒቆዲሞስ ፰ ሆሳዕና ናቸው ። አልያዝ ላላችሁ ማለትም ኦርደሩ የሚምታታባችሁ በምህጻረ ቃል ያዙት ፦ ዘቅምመደገኒሆ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ሼርም ያድርጉ 👇👇👇👇 @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm
Показать все...
ወዳጄ ሆይ "በዚህ ዓለም ላይ ብዙ የጦርነት ዘመን አልፏል ብዙ የእልቂት ዘመኖችም ተፈራርቀዋል። አይነቱን የሚለውጥ ችግር እንጂ ችግር ሲጠፋ በዓለም ላይ አላየንም ሥልጣኔ የምንለው ነገር ስናስበው ችግርን የሚያርቅ ሆኖ ነው የምናገኘው። በዘመናችን ከችግሮች አንዱ ምንድነው ስንል እውነትን በሐሰት የመተካት ሂደት የዘመናችን ትልቁ ችግር ነው። የጠሩ እውነቶች እየጠፉ የጠሩ ቅብ እውነቶች እየበዙ ነው። ባለንበት ዘመን ላይ ሰዎች ሰይፍ መዘው ጦር ወርውረው አይዋጉ ይሆናል በአንጻሩ የምላስ ጦርነቶች እየበዙ ነው። ሰዎች ሁሉ ይሣሣቃሉ ሰላም የለም ሰላም ነው ይባባላሉ። ብዙ ችግር አለ ችግር የለም ይላሉ። ስለዚህ በዘመናችን ካሉ ተግዳሮቶች አንዱ ምንድን ነው ስንል ሽንገላ ነው። @Hesychasm @Hesychasm @Hesychasm
Показать все...
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰቦቻችን፡፡ በዚህ ቻናል የምንለቃቸው ነገሮች የማይመቹ ከሆነ ማሻሻል ያለብንን እንድናሻሽል @Bekirstoss የሚለውን በመጫን አስተያየት እንድትሰጡን በጌታ ስም እንጠይቃለን፡፡
Показать все...
Показать все...
ስለ ማርያም

✍ሥነ-ማርያም ጥናት”Mariology” በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ 1. የማርያም እናትነት”parturition” 2. የማርያም ንፅህና”Infallibility” 3. የማርያም ድንግልና”Virginity” 4. የማርያም አማላጅነት”Intercession” 5. የማርያም እርገት”Assumption” የሚያጠና ነው፡፡ ዛሬ የመጡ ተሐድሶ ፕሮቴስታንቶች ከሉተር ምንኛ እንደራቁ ተመልከቱ፡፡ ሉተር እንዲህ አለ፡፡ ፧ <<<“አንድ ሰው ማርያምን ሲያከብራት እርሷ በወደደችው እና በምስጋናዋም ላይ በጠቀሰችው መንገድ ሊሆን ይገባል፡፡ እርሷ እግዚአብሔርን ላደረገው ነገር አመስግናዋለች፡፡ እርሷን ታዲያ እንዴት እናመስግናት? የቅድስት ማርያም አክብሮት ማለት የእግዚአብሔር አክብሮት ማለት ነው – ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ምስጋና ነው፡፡ ማርያም በራሷ ምንም አይደለችም፤ በክርስቶስ እንጂ! ማርያምም ወደ እሷ እንድንሄድ…

Показать все...
ስለ ማርያም

✍ሥነ-ማርያም ጥናት”Mariology” በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ 1. የማርያም እናትነት”parturition” 2. የማርያም ንፅህና”Infallibility” 3. የማርያም ድንግልና”Virginity” 4. የማርያም አማላጅነት”Intercession” 5. የማርያም እርገት”Assumption” የሚያጠና ነው፡፡ ዛሬ የመጡ ተሐድሶ ፕሮቴስታንቶች ከሉተር ምንኛ እንደራቁ ተመልከቱ፡፡ ሉተር እንዲህ አለ፡፡ ፧ <<<“አንድ ሰው ማርያምን ሲያከብራት እርሷ በወደደችው እና በምስጋናዋም ላይ በጠቀሰችው መንገድ ሊሆን ይገባል፡፡ እርሷ እግዚአብሔርን ላደረገው ነገር አመስግናዋለች፡፡ እርሷን ታዲያ እንዴት እናመስግናት? የቅድስት ማርያም አክብሮት ማለት የእግዚአብሔር አክብሮት ማለት ነው – ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ምስጋና ነው፡፡ ማርያም በራሷ ምንም አይደለችም፤ በክርስቶስ እንጂ! ማርያምም ወደ እሷ እንድንሄድ…

Показать все...
ሴት ሆይ

✍የትዳር ምርጫሽን ስትመርጭ ብር ያለው ፣ቆንጆ የሆነ ተክለ ስውነቱ ያማረ፣ወይም ሀብታም ፣የተማረ ድልቅቅ አርጎ የሚያኖርሽ ትፈልጊ ይሆናል አትሳሳች..... ፧ ✍ትዳር በሀብት ብዛት የማትወሰን በመልክ ማማር የማትመካ ድንቅ የህይወት መንገድ ናት....ነገር ግን ሰነፍና ሱሰኛ ወንድ አትምረጭ፡፡ ፡ እህቴ ሆይ: መልኩ ሳይሆን ቆንጆ ልብ ቆንጆ የሆነውን፣ልብሱ ሳይሆን ንፁህ ልቡ ንፁህ የሆነውን የህይወት አጋርሽን ከፈለግሽ የምትወጅውን ወንድ ከማንም ጋር አታወዳድሪው፡፡ ከወደድሽው አግቢው፡፡ እወድሻለሁ ስላለ ብቻ ግን ልብሽን አትስጭ የወደደሽ በምን ምክንያት እንደሆነ አስቢው፡፡ ፡ እህቴ እንደ አምኖን ከወደደሽ ይልቅ የጠላሽ እንዳይብስ በስሜት ለሚነጉድ ሞትኩልሽ ሄድኩልሽ ለሚል ወንድ ክብርሽን አትጣይ፡፡ ሀይማኖቱን አክብሪና ፈጣሪውን የሚፈራ ባል እንዲሰጥሽ አምላክን በንጽህና ለምኝው፡፡ በትዳርሽ ደስታ…

Показать все...
የኃጢአተኞች ኪዳነ ምህረት

================== ✍እስኪ እንተያይ፦ ፕሮቴስታንቶቹም ኦርቶዶክሶች በጣም ከሚገርመኝ ነገር ስለ ኪዳነ ምህረት ያላቸው አመለካከት (Attitude) ነው፡፡ ኪዳነ ምህረት (Covenant of Mercy) የፍጥረቱ መዳኛ እንዲሆን እግዚአብሔር የምህረት ኪዳን (Covenant of Mercy) ለህዝቡ ሰጠ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ሰውን የሚያፈቅርበት የፍቅር ጥግ እንጂ የክርስቶስን የመስቀል ስራ የሚጋርድ አይደለም፡፡  ፧ እግዚአብሔርን ምህረት ማን ይጠራጠራል? እንኳን የጌታዬ እናት ድንግል ማርያም እኔም ኃጢአትን ይቅር የማለት ስልጣን አለኝ፡፡ "ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም" ተብያለሁ፡፡ (ማቴ 6:15) ፧ እግዚአብሔር ስለ እንደ ልቤ ስላለው ስለ ዳዊት ከተማዋን ጠብቋል፡፡ " ስለ እኔም፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ"…

Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.