cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የሀበሻ ጀብዱ ና ባህላችን🇪🇹

ኑ ባህላችን ጥበባዊና የአባቶች ቱፊታዊ ....ብዙ ቁም ነገሮች ይነሳል

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
243
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

እምየ አጤ ምኒልክ፣ ~~~~~~~~ እምዬ ብዙ ነገራቸው ያስደንቀኛል። ከነዚያ ነገራቸው አንዱ በባለቤታቸው በአራት ዓመታት መበለጣቸው ነው። አሁን ላይ እንኳን ሚስት በዕድሜ በልጣ ይቅርና አንሳ እንኳን ከሰውነቷ ትንሽ ገዘፍ ካለች ' እናቱን እኮ ነው ያገባው ' የሚል ማህበረሰብ ውስጥ ሆኖ ፣ ለዚያውም ከዛሬ 100 ዓመት በፊት፣ ንጉሠ ነገሥት ሆነው እምዬ ይህንን ጋብቻ መፈጸማቸው አጃኢብ ያሰኛል። ለማንኛውም እምዬ ከተወለዱ ዛሬ 178 ዓመት ሞላቸው። (፲፪ነሐሴ ፲፰፻፴፮ ዓ/ም ተወለዱ) እቴጌ 182 ዓመት። እንደአለመታደል ሆኖ ሊሰጣቸው የሚገባ ክብር ለሁለቱም አልሰጠናቸውም። እኛ እንኳን ስስት እምብዛም አያውቀንም ነበር፤ ምስጋና እና መደናነቅ ላይ ለምን እንደሚያቅረን ፈጣሪ ይወቅ። የምኒልክን ስም ምን ያህል እየታወሰ ነው? ዕድሜ ለንግሥት ዘውዲቱ እንጂ ሐውልታቸውም ላይኖረን ይችል ነበር። አራዳ ላይ ያለውን የእተጌን ሆቴል ሄዳችሁ እዩት፤ ፍርዱንም ስጡ። ድግስ ለመደገሥ ብዙ ሚሊዮን ብር በሚዘራበት አገር እንደዚህ ዓይነቱን ታሪክ ጠብቆ ለመቆየት ግን ባጀት የለንም። በዚህ አጋጣሚ የአጤ ቴዎድሮስንም ሐውልት እዩት። " በቅርብ ጊዜ ተሠርቶ በብታው ይውላል " ተባለና መድፉን አስቀምጠው ሸወዱን/ራሳቸውን ሸወዱት። በእምየ ሚኒልክ የልደት ቀን ብዙ አዘባዘባችሁኝ። እንኳን አደረሳችሁ! ትንሽ ስለእምዬ፣ አጼ ቴዎድሮስ የጀመሩትን ኢትዮጵያን ወደ አንድነት የማምጣት ዓላማ አጼ ዮሐንስም ሳይፈጽሙት መተማ ላይ በመሃዲስቶች እጅ ወደቁ። ኢትዮጵያን ከዘመነ መሣፍንት በፊት እንደ ነበረች አድርጎ የማዋሃድ እና የንጉሠ ነገሥቱን የማይገሠሥ ሥልጣን የማስከበሩን ጅምር ዓላማ እዳር የማድረሱን ተግባርም በዳግማዊ አጼ ሚንሊክ ጫንቃ ላይ ወደቀ። አጼ ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሥራ በአመዛኙ ኦሮሞዎች ከነበሩ አበጋዞቻቸው ጋር የካሮት እና ዱላ /carrot and stick/ ስልት በመጠቀም ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። መጀመሪያ ነፃነታቸውን ላስከበሩ ክልሎች ባላባቶቾ ዕውቅና ሰጥተውና በመካከላቸው ጦርነቴ እንዳይነሳ እንዲተባበሩ አሳስበው መልዕክት ይልኩላቸዋል። የንጉሠ ነገሥቱን የበላይነት ተቀብለው ግብር ለመገበር የሚስማሙትን ባላባቶች ግዛታቸውን ያጸድቁላቸውና በውስጥ አስተዳደራቸው ጣልቃ እንደማይገቡባቸው ቃል ይገቡላቸዋል። ይህን ማድረግ ያልፈለጉ ደግሞ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ሲሸነፉ የአጼ ሚንሊክ ሠራዊት በክልሉ ይገባና ይሰፍራል። በጦርነት ገብተው የተሸነፉትን መሳፍንት አጼ ምኒልክ ምህረት እየሰጧቸውና መልሰው ወደ ሥልጣን ያመጧቸዋል። በውስጥ አስተዳደራቸውም ጣልቃ አይገቡም ነበር። Decentralization ማለት ይህም አይደል? ስለአጼ ምኒልክ መሐሪነት እና አርቆ አስተዋይነት ብዙ ማለት ይቻላል። የራሳቸውን ሰው አይደለም ባህር አቆርጦ የመጣን የኢጣሊያ ወራሪ ሃይልን ሠራዊት ምርኮኛ እንኳ በአግባቡ ይዘው እና አሳክመው ይንከባከቡ የነበሩ ሩህሩህ ሰው እንደነበሩ እውነተኛ ታሪካቸው ይናገራል። እኒህን ሰው ነው ' ጡት ቆረጡ' የምንለው። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶልሳ ጂግሳ የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ያሉትን ልበል እና እኔም አረፍ ልበል። ለአጼ ምኒሊክ ፣ " በጦርነት ላይ የሴት ልጅ ጡት መቁረጥ ፍጹም ከባሕሪያቸው ውጪ ነው " ሁላችንም እውነታው ተገልጾልን እና ከስህተታችን ታርመን " አንድ ህዝብ " እንድንሆን ምኞቴ ነው። እንኳን አደረሰን። ሰናይ ቀን!
Показать все...
አለመታከት ናፈቀኝ ፠፠፠፠፠ ስለተፈጠረለት የጥበብ አምድ ሲል ተኮማትሮ ፣ ተጨብጦ ፣ የቃሉን ሃይል እውነት እና ስነ - ውበት አምጦ ለኛ ሲል ኖሮ ሲያበቃ ምንድን ነው እንዲህ ማለት ቆይ? ‘’ሁላችን ሽማግሌዎች በእድሜያችን መዝጊያ ትልቅ ጋቢ እንፈትላለን። ግን ሳንቋጨው እንሞታለን። አዎን እኔም እንደ አባቶቼ ያልቋጨሁት ነገር ይቆጨኛል’’ ብሏል ብላቴን ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን። ከዚያ ሁሉ መሰጠት በኋላ ያልሰራሁት ነገር አለ ብሎ እንደማሰብ ምን መታደል አለ? ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለመስራት ፣ ለትጋት መኖር ፣ ለአላማ መኖር እንዲህ ያለው አይበገሬነት እና አይረኬነት ይመስለኛል። ሁሌም ከሰራው ስራ ይልቅ ያልሰራው የቀረው ነገር ብቻ እንደሚያሳስበው የበለጠ ማስረጃ ገብርዬን በምናቡ ሲያናግረው እንዲህ ይለዋል፦ ‘’ ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ’’ የሰው ልጅ አፈጣጠሩ ይሄው ነው እኮ አላማው። ጥረህ ግረህ በላብህ ወዝ ብላ የመባሉ የዘፍጥረቱ ሕግጋት ይህንኑ ነው የሚደነግገው። እስከ እድሜው እንጥፍጣፊ ድረስ አለመርካቱ ጸጋዬ ይህንን የተፈጥሮ ሕግጋትን መኖሩ ይመስለኛል። በእውቀቱ ስዩም የስልጣኔ መዝሙር በምትሰኝ ግጥሙ ይህንኑ ተፈጥሯዊ ሕግ ሲያጸናልን እንዲህ ይለናል፦ የሥልጣኔ መዝሙር ^^^^^^ ማንጋጠጥ እንድችል <<ደመናው የ'ኔ ነው!>> እንድል ተራሮችን እንድነድል ከጥልቅ ሸለቆዎች ጥግ የምንጭን ዱካ እንድፈልግ ከሀኖስ እስከ ውቅያኖስ መንገዴን እንድዘረጋት ልቤን እርካታ የለሽ፣ ሕይወቴንም ጥም አድርጋት። ይሄ አንድ እራሱን የቻለ ጸሎት ነው። እውነትም በርእሱ እንደሚናገረው የስልጣኔ መዝሙር ነው። መሰልጠን ማደግ ሰው መሆን ካሻን በየጥቃቅኑ ስራ እርካታ ተጠምደን መቆም እና ማረፍ የለብንም። የኛው ፈላስፋ ዘረያቆብም ይህንኑ ነው አምላኩን የጠየቀው ጥበብን ግለጽልኝ ፣ አንተ የምታውቀውን እንዳውቅ እርዳኝ ነው ያለው። ታዲያን የእግዚአብሔር ጥበብ ሰፊውን አለም መጠየቅ ፣ ማወቅ ፣ መመርመር ፣ ስለሰው ልጆችም መጨነቅ ፣ ለፍቅር ሲሉ ሕያው በሆነ የፍቅር ጥበቡ መኖር አይመስላችሁም? እኔ ይመስለኛል እረ ምን መምሰል ብቻ ነውም እንጂ። እንደ ጸጋዬ ያሉቱ ግን ይህንን ነው የሰሩት። በስራቸው ውስጥ በድፍረት የምናገረው ሃቅ አለማዊ የመሰለ ስራቸው ውስጥ ሁሉ ቅንጣት ተራ ሃሳብ ፣ ከሀገር ፈቀቅ ያለ ሃሳብ ፣ ሰውን ከማክበር የሰነፈ ሃሳብ አልተነሳም። ይህ ደግሞ ፈጣሪም የሚፈልገውን ስራ እንደመስራት ያለ በጎ ፈቃድ ነው። ጸጋዬ በጴጥሮስ መንፈስ እንዲህ ይላል ፦ ‘’,,,,,,ባክሽ እመብርሃን ፣ ባክሽ ምስለ ፍቅር ወልዳ ጸናት ስጭኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያ ፍዳ’’ ‘ ‘ ማናችን ነን የሀገርን ፍዳ ለመሸከም መለመን ቀርቶ የተሸከሙትን እንኳ የምናወድስ? ከመውቀስ ከመተቸት ውጭ ፣ በስራችን ፣ በሃሳባችን እንኳን ሰውን አስተምረናል? ማስተማሩ ይቅር በተግባርስ ምሳሌ ሆነናል? ምሳሌ መሆኑም ይቅር ለመሆኑ በውስጣችን ስንቶቻችን ነን ስለሀገር ፣ ስለትውልድ ፣ ስለፍቅር የምናስብ የምናውጠነጥን? ይህንን ማሰብ የሆነ የቅንጦት አስተሳሰብ ይመስል ስለነገሩ እንኳን ሲነሳ ‘’ዎኦ አንተ ደልቶሃል ወንድሜ’’ ብለን አይደል እንዴ የምንሄደው? በጅምላም ባይሆን ከጥቂት ሰዎች በስተቀር። ሎሬቱ ግና እንዲህ ብሎ የሰውነቱን ልክ ነገረን፦ ‘’ጥበብ ይናፍቀኛል ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ ያስቀናኛል ድንቁርና ያስፈራኛል ጦርነት ያስጠላኛል። ‘’ እናም እንዲህ እንዳለ የሚናፍቀውን ጥበብ ኖሮ ያውም ባለመርካት ያልቋጨሁት አለ እስከሚል ድረስ ኖሮት አልፏል። ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ ያስቀናኛል እንዳለ እንደቀና ፣ ይህንን የዋተተለትን ፣ የደከመለትን ፣ የታሰረ የታገተበትን ምኞት መቻቻል ይሉት ስልጣኔ ሳያይ እንደናፈቀው አለፈ። ድንቁርናም ያስፈራኛል እንዳለ የድንቁርናችንን ልክ ሃሳቦቹን መግፋት ፣ ሰውዬውን በማንጓጠጥ እና ስራዎቹን ሳንሱር በማድረግ አሳይተነዋል። ምንም እንኳን አንዳንድ ግለሰቦች የቀድሞ ስድባቸውን ሽረው ይቅርታ ጸጋዬ እያሉ በድጋሜ ከስሩ የከደሙ ቢኖሩም በቁሙ ሳለ ባለማድነቅ እና ስራዎቹን ባለመዘከር ድንቁርናችንን በሚገባ አሳይተነዋል። ‘ ‘ ‘ ‘ ጦርነትም ያስጠላኛል ያለው ወዶ አይደለም ጸጋዬ ፡ የተወለደበት ዘመን ጣልያን የገባበት ወቅት ነው ፣ ከዚያም በኋላ የ53ቱ የ66ቱ የ83 የ91ዱ እያልን ይሄው አሁን ድረስ በጦርነት እርስ በርስ መፈሳፈስ ይዘናል። ጦርነት እንደ እባብ ወገባችን ላይ ተጠምጥሞ አልለቅ ያለን ጉዶች ነን። ‘’ልጆቻችንን በላን’’ ይላል በእናት አለም ጠኑ ቲያትሩ። መክሊታችንን አውቀን ሀገራችንን ለማገልገል ያብቃን እናም እንደ ጸጋዬ ሰርተን ሰርተን ስናበቃ ያልቋጨሁት ነገር አለ ላለማለት ከወዲሁ እድሜና ዘመናችንን እንገልገልበት። ‘ ‘ ‘ ‘ ‘’ሁላችን ሽማግሌዎች በእድሜያችን መዝጊያ ትልቅ ጋቢ እንፈትላለን። ግን ሳንቋጨው እንሞታለን። አዎን እኔም እንደ አባቶቼ ያልቋጨሁት ነገር ይቆጨኛል’’ ይሄ የጸጋዬ ንግግር እና ‘’አንገትሽ እራስሽን ችሎ ልየውና ማግስቱን ይውሰኝ አስር ሞት ይምጣና’’ የሚለው የጋሽ ጥላሁን ሙዚቃ የሃሳብ ተመሳስሎነቱ ይደንቀኛል። ሁሉም ስለሃገራቸው ማየት እንደፈለጉ ፣ ያልቋጩትን ተቋጭቶ ማየት እንደሻቱ አለፉ። ግን ግን ቢሆንም ፦ የቃለ እሳት ነበልባሉ አልባከነምና ውሉ የዘር-ንድፉ የፊደሉ ቢሞት እንኳ ሞተ አትበሉ። ነውና ነገሩ በአካለ ስጋ ቢለዩንም እንቁዎቻችን ለዘለአለም በውስጣችን አሉ ይኖራሉም። My eternity is in the grateful memory me men እንዲል ፕሌቶ። እነሆ ጸጋዬም ሰሞነ ልደቱ ነው በልባችን ሰርክ ኣንዳዲስ ይወለዳል ፣ በሃሳቡ በፍልስፍናው ይርመሰመሳል።
Показать все...
💢Birthday flayers 💢Logo 💢Business card 💢 Banner 💢Invitation card 💢T-shirt design እና ሌሎችንም በጥራት እንሰራለን። ማሰራት የምትፈልጉ 📥📥📥📥📥📥📥📥📥📥 👾👾👾👾👾👾👾👾👾👾 t.me/vectordesign7
Показать все...
Vector design

አሪፍ አሪፍ designs እዚህ ያገኛሉ። #Logo #Business card #Birthday flayer #T-shirt design ማሰራት ለምትፈልጉ Contact us on Our bot 👇👇👇 @Oasisdesigns_bot ወይም በ @Oasisgamer SHARE 乂 ●́‿ ●̀乂 乂 ●́‿ ●̀乂 乂 ●́‿ ●̀乂

Показать все...
Bela chaw🎸🎸🎸
Показать все...