cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Abidulmajed Melese

Information is more than anything. ድብቅ ሴራዎች ይጋለጣሉ ። አዝናኝ እና ቁም ነገር አዘል ቀልዶች ይለቀቃሉ። ሰበዐዊነት ይዘከራል ፣ይዳሰሳል ። አላማየ በዲኔ ላይ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ነዉ ። ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦ 1) ከቁርኣን፣ 2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ] 3) ከታማኝ ዑለማዎችና 4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል። @Salifya

Больше
Рекламные посты
332
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ደና እደር አትበሉኝ ደና ደር አትበሉኝ እንቅልፍ እፈራለዉ ተኝቶ አልሞ ያልነቃም አቃለዉ ደና ደር ስትል ወደሞት ሚገፋኝ የሞት አበጋዝ ድንገት ቢመጣብኝ በስስት ለሚኖ ነገን ለሚመኝ ሠላም ያንቃህ እንጂ ደና ደር አትበሉኝ 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹
Показать все...
ደና እደር አትበለኝ ደና ደር አትበሉኝ እንቅልፍ እፈራለዉ ተኝቶ አልሞ ያልነቃም አቃለዉ ደና ደር ስትል ወደሞት ሚገፋኝ የሞት አበጋዝ ድንገት ቢመጣብኝ በስስት ለሚኖ ነገን ለሚመኝ ሠላም ያንቃህ እንጂ ደና ደር አትበለኝ 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
ምዕራባዉያን እሱን ካዩ ሺንታቸዉ ይመጣል ፣ ይርበጠበጣሉ በአለም ላይ ካሉ ዉስን ጀግና መሪዎች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል ፣ ከአንደበቱ የሚሰማዉ የቁርዐን ድምፅ ነዉ ፣ ለሙስሊሞች እና ለኢስላም ትልቅ ቦታ እንዳለዉ የሚነገርለት የበሀረ ሰላጤዉን አለም ከጨለማ ለማዉጣት እየታገለ ያለ የአለማች የወቅቱ ምርጡ መሪ ፣ ሎሚ ከመሸጥ ኑሮዉን የጀመረዉ የቀድሞ የስታንቡል ከተማ ከንቲባ የአሁኑ የቱርክ ፕሬዝዳጋት ባባ ኤርዱዋን ምርጫዉን አሸንፏል ። እኔም ከምስረሰቅ አፍሪካ በትግራይ ምድር አዉሮፖ ህብረትን እና አሜሪካን ስንዋጋ ሀገሬን ለመጠበቅ ዱሮዉን ለላከልኝ ባባ ኤርዱጋን እንኳን ደስ አለክ ማለትን ወደድኩ ከሱጋ ያለን ዲናዊ አመለካከት ቢለያይም ከምዕራባዉያን ጭቆና የተላቀቀች ሀገር በመመስረት ሂደት አላህ እንዲያግዘዉ ዱዐየ ነዉ ። ምዕራባዉያንን ከማድነቅ 100 ሺህ ግዜ ከኤርዱጋን በኩል መሆን በላጭ ነዉ ። Congratulations 👏 ባባ ኤርዱጋን ። 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
ኣሮምያ ዉስጥ ያሉ አክቲቪስቶች ይህ ሁሉ ነገር እየተካሄደ ዝም ማለታቸዉ ግራ ያጋባል! ። የሆነ ነገርማ አለ! ። ለኣሮምያ አክቲቪስት ወንድሞቻችን ይህ ቀን አልፎ ያስተዛዝበናል ትናት ለዘር ስትጮሁ የነበረዉን ያክል ምነዉ? ዛሬ መስጂዳችን እየፈረሰ ዝም አላችሁ? ! ዘሩን ከእምነቱ ያስቀደመ ጃሂል ነጃ አይወጣም! ።
Показать все...
ጥያቄ: መልቲ-ቫይታሚን (multivitamin / prenatal) አልወሰድኩም፣  ልጄ ሲወለድ ችግር ይኖረው ይሆን? መልስ: ከፎሊክ አሲድ በስተቀር ሌሎች ቫይታሚኖችን እና ሚኒራሎችን ከምግብ ማግኘት ይቻላል። ሆኖም ግን በየቀኑ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ በጣም ግድ ይላል። ሁሌም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ስለሚያስቸግር ነው  መልቲ-ቫይታሚኖችንም (multivitamin) እንድንወስድ የሚመከረው ፣ የአስፈላጊ ቪታሚን እጥረት ተከስቶ ልጅሽ ላይ ቋሚ ጉዳት እንዳይደርስ። የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ ክብደቱ ከተለመደው በታች የሆነ ህጻን ከመውለድ ባሻገር የእናትየዋን የአጥንት እና የደም ጤንነት ሊያውክ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ፎሊክ አሲድ(folic acid) እና  ቪታሚኖች እንድንወስድ የሚመከረው። 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
የእማየ ፀሎት ከፊት ፈተናችን ከተራራ ገዝፎ። አዕምሮየ ሲያልም በሀሳብ ተጠልፎ። መጥፎ ነገር መጥቶ ሲፈልግ ሊያጠቃን። ገለል ያደርገዋል የእማየ ምርቃን። ስኬት እየሳበ እላይ ላይ ሲያወጣን። የድል ጽዋ ሞልቶ ፈልጎ ሲያጠጣን። ልቤ ያስብ ጀመር የራስ ልፋት መስሎት። ለካስ ስኬታችን በ እናታችን ፀሎት። ቆማ ተቀምጣ እጆቿን ወደሱ ወደ ላይ አንስታ። ለምናው ነበረ ያን ታላቁን ጌታ። ሁሉን አረገላት የእናትነት እዝነት ልመናዋን አይቶ። ካሰበችው በላይ ሰጣት ያለ ተመን ሳያጎድል ሞልቶ። ትንፋሽሽ ምርቃን ልባዊም ፍለጋ። ገና በልጅነት በእድሜ እያለሁ ለጋ። ሸምግየ ለምኖረው ገና ለወደፊቴ የምትጨነቂ። የመቶ አመት ችግር በፈጣሪ ፈቃድ በፀሎትሽ ብርታት የምታላቅቂ። አንች ነሽ እናቴ ያንችው ፀሎት ነው በብዙ የካሰኝ። አውቃለሁ ዱዓሽ ነው አንድ ፈጣሪን ይዞ እዚህ ያደረሰኝ።! 🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
" አይ ዘመን"   ብረት በገለባ  ወገቡ ሲሰበር፣ ሰነፍ እያቅራራ  ጀግና ሰው ሲቀበር፣ ምነው ይሄን ታ'ምር  ባላየነው ነበር፣ ቅል ድንጋይን ሰብሮ  በታየበት ዘመን፣ ግድየለም እስከዚያው  እንኑር በጎመን፣ ጊዜ የጣለውን   ጊዜ እሰከሚያነሳው፣ ጅብ እየገነነ  ይሞታል አንበሳው፣ እስከተፈቀደ   እንደዚህ ቢኖርም ፣ ሁሉም ወደ ቦታው  መመለሱ አይቀርም። መስጂዴን አታፍርሱብኝ! !።                      🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
አንዳንድ ስሜቶች . . በልባችን ያሉ አንዳንድ ስሜቶች፤ ትዕዛዝን የጣሱ የፈረሱ ህጎች፤ ባሸዋ ላይ ያሉ የቋጥኝ ካቦች፤ ድነው የማይድኑ የዘወትር ህመሞች። በጊዜ አቅማራት የሚፈራረቁ፤ በነፋስ ሽዉታ ታይተዉ የሚጠልቁ፤ ህመምን አፅንተዉ የሚያስጨንቁ፤ ቅርብ እየመሰሉ እጅግ የሚርቁ። በሰቀቀን ገመድ አስረዉ የሚያኖሩ፤ በፀፀት አለንጋ ገርፈው የሚሰብሩ፤ በጥላቻ ሀሳብ ቅጥር የታጠሩ፤ ጥዑም መስለዉ ከሬት የመረሩ። በልባችን ያሉ አንዳንድ ስሜቶች፤ በጥላቻ ከስለዉ የጠቆሩ ፊቶች፤ ስቀዉ የማይስቁ የፈገጉ ጥርሶች፤ ድነዉ የማይድኑ የዘዉትር ህመሞች። 🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
የተከፈለበት ቡና በአንድ ወዳጄ ቤት ቁምነገር በቀልድ እየተወዛ ስንጨዋወት አንድ ወንድማችን ስለ 'pending coffee ' አንስቶ በ' ስካንዲኔቪያ ሀገራት ' እና በጣልያን ሃገር ውስጥ የተለመደ የበጎ ተግባር መሆኑን አብራርቶ አጫወተን፤ ነገሩ ቀልቤን ስለሳበው እና ጥሩ ልማድም ስለሆነ ለዚህ ጦማር ቤተሰቦች ላካፍል ወደድኩ እና እነሆኝ፦ አንድ የካፌ ደንበኛ ካፌ ገብቶ አንድ ቡና ያዝዝ እና የሁለት ወይም የሦስት ቡና ዋጋን ከፍሎ ይወጣል ሌሎችም እንደሚፈልጉት የሚየሻቸውን ተጠቅመው ግን አብዝተው ከፍለው ይወጣሉ፤ ይህን የሚያደርገቡት ምክንያትም አቅም የሌላቸው እና አረጋውያን በእነዚያ ካፌዎች ሄደው ቡና አለ ወይ? የሚበላ አለ ወይ ብለው ሲጠይቁ ቀድሞ ሂሳብ የተከፈለባቸውን የምግብ እና የመጠጥ አይናቶች ያቀርቡላቸው እና በነፃ ተመግበው ይሄዳሉ ። ቁምነገሩ ያለው እዚህ ውስጥ ነው። ሰዎች በማያውቃቸው ሰዎች ይደገፋሉ ሌሎችም የማያውቋቸውን በሚችሉት መንገድ ይረዳሉ። ወዳጄ ሰው በሚችለው መንገድ እና አቅም አንድ ሰው ለመርዳት ምክንያት መሆን ከቻለ ምን ያህል በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ መመልከት እንችላለን። በጎ እንሁን ለመመስገን እና ለመደነቅ ሳይሆን የሰው ችግር ተካፋይ ለመሆን እንኑር። አላህ ከመልካም ባሮቹ ያርገን! መልካምነት ይለምልም!! 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
00:43
Видео недоступноПоказать в Telegram
ብቻ እኔ የለሁበትም ገለቴ ¿¿ 👉ኣረ ተዉ ግን ተዉ ¿¿ ። 🪡 እኔኳን የሚመጡና የሚያድኗችሁ አይመስለኝም! ግን እንዲህ ስታለቅሱ ሰዉ አይደለሁ አዘንኩ ¿ በድሮ በሬ ማረስ የለም በሀገራችን ባንድራ ስር ተደብቃችሁ ስሰሩ የነበራችሁ ሙድረ ገልቱ በጎንደር ፣ በአስቴ፣ በሞጣ በወንድሞቻችን ላይ ያደረጋችሀት እያንዳንዷ ድርጊታች ዋጋ ታስከፍላችሁ አለች ። 🪡🪡 በፆም አንጀታቸዉ የተሰዉትን ወንድሞቻችንን ስናስብ እኛም እንባችንን መገደብ ነዉ የሚቃተን! ። 🪡🪡 Abidulmajed Melese 🇪🇹 👇👇👇 @YMAH9 @YMAH9
Показать все...
02e6216e01dbb160bc632f2709e12656.mp42.82 MB
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.