cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

LAST TIME 🔔🕛🌍

🔛LAST TIMES "፤ ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። " (የማቴዎስ ወንጌል 24: 42) ☄ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶችና ትንቢቶች በጥልቀት እንመለከታለን። ☄እንዲሁም አሁን እየተፈፀሙ ያሉትን ትንቢቶች እናያለን። ⏰† ኢየሱስ ይመጣል!⏰ 🌟&🌟 😆#daily_Hope❤

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
218
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

አንድ ነገር እንዲቆጣጠርን ከፈለግን በዛ ነገር መቆየት አለባችሁ።ያ ነገር ካልተቆጣጠራቹ ደግም አይለውጣቹም። መጠጥ መጀመሪያ ጊዜ ስንጠጣው ይመረናል ወይም ያስጥላናል ነገር ግን እየቆየ ሲመጣ እየጣፈጠ ይመጣል።የመጠጥ ሱስ ያለባቸው ሰዎች የመጠጡ ሰአት ሲደርስ ያንቀጠቅጣቸዋል፤ ለዛ ቆሎ ብለው ያስለመዱትን ያን መጠጥ ይጠጣሉ። እኛ ክርስቲያኖች እንዲሁ በእግዚአብሔር ቃል ስር መሆን አለብን። ሳይንስ አንድ ነገር ልምድ እዲሆነን ከፈለግን ለሀያ አንድ ቀን ሳታቋርጥ አድርገው ከዛን ልምድ መሆኑ አይቀሬ ነው ይለናል፤ ስለዚህ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችን እዲያድግ የእግዚአብሔርን ቃል ሳናቋርጥ መመገብ ያስፈልጋል። የእግዚአብሄር ቃል በራሳችን መማር መልመድ አለብን።በትናንቱ በበላነው ምግብ ዛሬን መኖር እንደማንችል ሁሉ ፤ ለዛሬ ዛሬ መብላት እንዳለብን ሁሉ ፤ ከእግዚአብሔር ጋርም ያለንን ነገርም እዲሁ ማሳደግ አለብን እላለሁኝ። ጌታ እንደዚ አይነቱን ልምድ ያብዛልን፤ ፊቱን ማየት ይሁንልን ፤ ከሱ ጋር ማውራት ከሱ ጋር ግንኙነታች ቀን በቀን እያደገ ይሂድልን እግዚአብሔር ይርዳን አሜን። Quote:binisoft
Показать все...
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል የዛሬዋ የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ “ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡ የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡ ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡ “ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau “የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts “ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” - Unknown Source መልካም አዲስ አመት ለመላው ኢትዮጲያውያን ተከታታዮቼ!!! 🌟🌻🌻🌼🌼 @lasttimes 🌼🌼🌻🌻🌟
Показать все...
ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል የዛሬዋ የአመቱ የመጀመሪያ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡ ቀጥለው ያንብቡ
Показать все...
🌼🌻🌼 HAPPY NEW YEAR 2012🌼🌻🌼 🌻🌻🌻🌼🌼2012🌼🌼🌻🌻🌻 May this New Year is not a repetition of old habits May you reinvent yourself and embark upon a journey full of excitement and adventure.
Показать все...
ከላይ የቀጠለ በዚህም ሕይወት ሆነ በሚመጣው ዓለም እግዚአብሔርን እንደማወቅና ወደርሱም ተጠግቶ በፍቅሩ ሥር እንደመኖር አስደናቂ፣ አስደሳች፣ አርኪና፣ ዘላቂ ነገር የለም። በአዲሱ ዓመት ካወጣናቸው እቅዶችና ውሳኔዎች ሁሉ ዋነኛው እግዚአብሔርን ማወቅ፣ በበለጠ ወደርሱ መጠጋት እና እግዚአብሔርም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለኛ የገለጠውን ፍቅር መለማመድ፣ እሱን መታዘዝና በረከቱንም ለመቀበል መዘጋጀት ዋነኛዎቹ ካልሆኑ ሌሎቹ ምርጫዎቻችን ትክክለኛውን ቅደም ተከተል አልያዙም። የምናገኘውን ነገር ሁሉ አንድ ቀን ጥለነው እንሄዳለን። እግዚአብሔርን ችላ ብለን የምንሰበስበው ሁሉ የግድ አንድ ቀን ይበተናል። የምርጫችን ሁሉ ቁንጮ፣ የጥማታችንና የመሻታችን ሁሉ ዋነኛው ትኩረት ጌታ እግዚአብሔር ከሆነ ግን በዚህች አጭር ሕይወትም ሆነ በሚመጣው ዘለዓለም እጅግ የተደሰትን፣ ሙሉ ሰላም ያለንና የተባረክን ሰዎች እንሆናለን። እውነተኛው የሕይወት እንጀራ፣ የሚያረካው የሕይወት ውኃ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንን እንጀራ መብላትና፣ ከዚህም ውኃ መጠጣት ከአዲሱ ዓመት ውሳኔዎቻችን ሁሉ ዋነኛው ቢሆን ለዘላለም አትራፊ እንጂ የከሰርን አንሆንም። ይህ ጌታ ደግሞ እኛ ከምንፈልገው ይልቅ ፈልጎን እኛ አለንበት ድረስ መጥቷል ዛሬም ይመጣል። ባለንበት የእድሜ፣ የእውቀት፣ የኢኮኖሚ፣ የጉልበት፣ የጤና ሁኔታና ደረጃ ሊያገኘን ይናፍቃል። ይህች ቀን በምድር ላይ የቀረን እድሜአችን የመጀመሪያይቱ ቀን ናት። ታዲያ በዚህች ቀን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል እንዲህ ሲል ይጠራናል፤ “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ፣ ብሉም፥ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፣ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፣ በረከትንም ብሉ ሰውነታችሁ በጮማ ደስ ይበለው። ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፣ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፣ የታመነችውንም የዳዊትን ምሕረት፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ። ” ኢሳይያስ 54፤1፥3 ክርስቲያንም ብንሆን ገና ያላመንንን ሰዎች ጌታ እግዚአብሔር በሱ በኩል ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ወዳዘጋጀው የዘላለም ሕይወት ድግስ በክርስቶስ ይጠራናል። በዛሬይቷም ቀን ሆነ በነዚህ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ቀናት ምርጫችን ወደሱ መቅረብ ከሆነ ሌላው ነገር ሁሉ ሳይወድ በግድ ቦታውን ይይዛል። የያዘ ባይመስለንም ደግሞ በክርስቶስ ሆነን የዘላለሙን ሕይወታችንን ከያዝን ሌላውን ነገር ሁሉ በላቀና በከበረ መንገድ ሳንፍጨረጨር ለዘለዓለም እናገኘዋለን። ስለዚህ የዚህ የአዲሱ ዓመት ዋነኛው ውሳኔያችን በልተነው እንደገና የማንራበውን የሕይወትን እንጀራ ለመብላት እና ጠጥተነው እንደገና የማንጠማውን የሕይወትን ውኃ ለመጠጣት ይሁን። ይህ የሕይወት እንጀራና የሕይወት ውኃ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፥ በእኔ የሚያምንም ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም።” የዮሐንስ ወንጌል 6፥35 “መንፈሱና ሙሽራይቱም፤ ና ይላሉ። የሚሰማም፤ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፣ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው (በነጻ፣ በጸጋ) ይውሰድ።” የዮሐንስ ራዕይ ምዕ 22 ቁ 17 አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር በፈቃዱ አድማሱ
Показать все...
ከሁሉም የላቀ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ውሳኔ ከምዕራቡ ዓለም የአዲስ ዓመት አከባበር ወጎችና ልማዶች አንዱ እያንዳንዱ ሰው በአዲሱ ዓመት ይህን ወይም ያንን ማድረግ አለብኝ ወይም ማድረግ እፈልጋለሁ ማለትና ጥቂት ነገሮች በመምረጥ ከራሱ ጋር ቃል መግባት ነው። አንዳንዱ ሰው ጤናውን ለማሻሻል የአካል እንቅስቃሴን መጀመር ሲሻ፣ ሌላው ኑሮውን ለማሸነፍ የተሻለ ሥራን ለመያዝ ያቅዳል፣ አንዱ የተሻለ ትምህርትን ለመጀመር ሲያስብ፣ ሌላው ደግሞ ትዳር ለመመስረት ይነሳል። ልጅ የሌላቸው ልጅ ለመውለድ ሲዘጋጁ፣ ልጆች ያሏቸው ደግሞ ልጆቻቸውን በተሻለ መንገድ ለማሳደግ ቃል ይገባሉ። ሌሎች ደግሞ ሌሎች እቅዶችን ያቅዳሉ፣ ይፈልጋሉ ውሳኔንም ያደርጋሉ። እቅድ መልካም፣ ውሳኔም ጥሩ ነው። ታዲያ የሚፈልጉትን ሁሉ ማድረግ አስቸጋሪ ወይም ከባድ ነውና፣ ውሳኔዎችን ቅደም ተከተል በማስያዝ አንዱ ወይም ሁለቱ ላይ ማተኮር እጅግ ይጠቅማል። ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ የሚበልጥ ውሳኔ፣ ከምርጫዎችም በላይ የሚበልጥ ምርጫ ደግሞ አለ። በመጀመሪያ እረኛ የነበረና የወንድሞቹ ሁሉ ታናሽ ወንድም ቢሆንም የኋላ ኋላ የእስራኤል ንጉስና የእግዚአብሔር የልብ ሰው የተባለለት ዳዊት ገና በልጅነቱ ነበር ከምርጫዎች ሁሉ በላይ የሆነውን ምርጫ የመረጠው። ሌሎች ፍላጎቶቹንም ለዚህ ለዋነኛው ምርጫው የበታች አድርጎ አስቀመጣቸው። ያንን ታላቁን ምርጫውን እንዲህ ሲል ነው ዳዊት የገለጠው፤ “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።” መዝሙር 27፥4 ዳዊት አምላኩን ለማወቅ፥ ወደሱም ተጠግቶና እሱን ደስ እያሰኘ ለመኖር የነበረው መሻትና ውሳኔ እጅግ ጠንካራ ስለነበር ይህ ፍላጎቱን በረሃብና በጥማት መልክ ይገልጠው ነበር። በመዝሙር ምዕራፍ 42 ላይ ለምሳሌ እንዲህ ይላል፤ “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፣ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” መዝሙር 42፤1ና2 ይቀጥላል... 🔴 @lasttimes
Показать все...
“ከሁሉም የላቀ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ውሳኔ” ምንድነው? ዛሬ ማታ ይጠብቁን
Показать все...
👍 2
👎
//ትልቁ ፈተና መሞት አይደለም አለመኖር እንጂ! ,// ትልቁ ፈተና መፀለይ አይደለም አለማመን እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ማፍቀር አይደለም አለመፅናት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና መደመር አይደለም አለማካፈል እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ማጣት አይደለም ተስፋ መቁረጥ እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ማግባት አይደለም አለመግባባት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና መደሰት አይደለም ደስታን አለመቆጣጠር እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ማሰብ አይደለም የሚያንስብንን አለማጤን እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ችግር አይደለም ትግስት ማጣት እንጂ .! //ትልቁ ፈተና ማዘን አይደለም አለማማረር እንጂ !! //ትልቁ ፈተና ሀይማኖታዊ መሆን አይደለም መንፈሳዊ መሆን እንጂ .! //ትልቁ ፈተና ስልጣን አይደለም አጠቃቀም አለማወቅ እንጂ ! //ትልቁ ፈተና እዉቀት አይደለም እያወቁ መሳሳት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ስደት አይደለም የተሰደዱበትን አላማ መርሳት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ወደ ራስ ማየት አይደለም ዘረኝነት እንጂ.! //ትልቁ ፈተና ስኬታማ መሆን አይደለም ራእይ መርሳት እንጂ .! //ትልቁ ፈተና የፀለይቱን ማግኘት አይደለም ያገኙትን ማማረር እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ዝምተኛ መሆን አይደለም በዝምታ ዉስጥ መረጋጋት ማጣት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ቤተክርስቲያን ወይም መስጂድ መሄድ አይደለም የሄዱበትን መዛባት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም በገንዘብ የምናረገዉን ያለማስተዋል እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ልጅ መዉለድ አይደለም ልጅን አለመቅረፅ እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ዜግነትን መቀየር አይደለም ማንነትን መርሳት እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ማጣላት አይደለም ለበቀን ማቀድ እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ይቅርታ መቀበል አይደለም ይቅርታን አለማመን እንጂ ! //ትልቁ ፈተና መለያየት አይደለም እንደሚገናኙ አለማሰብ እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ፈጣሪን ማሰብ አይደለም ፈጣሪን አለማመን እንጂ ! //ትልቁ ፈተና መምታት አይደለም ክፉ ቃል መናገር እንጂ ! //ትልቁ ፈተና ተሰሚነት መጨመር አይደለም ለሰሚው መልካም አርአያ መሆን እንጂ ! //ትልቁ ፈተና አብሮ ስራ መስራት አይደለም አብሮ ስራዉን መፈፀም እንጂ ! //ትልቁ ፈተና አለማቀድ አይደለም ለማቀድ አለመሻት እንጂ !
Показать все...
እግዚአብሔር እረኛ ከሆነ ምን ሊጎድል ይችላል? የሰው እረኛ ለመንጋው መብል ተፈጥሮን አልያም መኖ አቅራቢዎችን ይታመናል፤ በሰው መሬት ላይም ይመራል፤ ለሰውም (ለራስ ወይ ለሌላ) ይንከባከባል እንጂ ለመንጋው ጥቅም አይደለም። እግዚአብሔር ግን ሙሉ ሆኖ ነው የሚጀምረው፤ እቅድና አቅም ይዞ። ሁሉ የእርሱ ነው፤ መሬቱ፣ መኖው፣ የሚያስፈልገው ሁሉ! እርሱ አንዳች አጥቶም አያውቅም። አጥቂም ከመጣ ለመከላከል ከማንም በላይ ብርቱ ነው። ስለዚህም፣ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ አንዳች አይጐድልብኝም” (መዝ 23፥1) የሚለው መዝሙር ያስተጋባ። ናሁሰናይ አፈወርቅ Psalm 23:1 The LORD is my shepherd, I lack nothing. What can we possibly lack if God is our shepherd? Human shepherds rely on nature or fodder provision; they also tend their flocks on lands that don’t belong to them. In all this, everything they do is for people, either for themselves or others – not for the flock. God on the other hand starts full, with a complete plan and power. All is His: the land, the fodder, whatever is needed! He never runs out of resources. He is also powerful to shield us from possible attacks. So, let’s echo the psalm: “The LORD is my shepherd, I lack nothing” (Ps 23:1). Nahusenay Afework @DailyInjera
Показать все...
ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ ቅዱሳን! ለረጅም ጊዜ ስላጠፋው ይቅርታ እጠይቃለሁ
Показать все...
👍 5
👎
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.