cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

የአርሴምዬ ልጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሚን ውድ ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ደህና መጣቹ በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የሚደግፍ ቻናል እና የተለያዩ መዝሙራትን ፣ ስዕላትን ፣ ና ኦርቶዶክስ መረጃን በፍጥነት ሚያገኙበት ቻናል ነው። ቻናሉ ላይ ሚስተካከል ነገር ካለ ወይም ሀሳብና አስተያየት ካለ @andu24ykidya @andu24ykidya አናግሩ

Больше
Рекламные посты
251
Подписчики
+124 часа
+17 дней
-130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🕊 [ † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † 🕊 † ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን †  🕊 † ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ፪፻፲፭ [215] ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ ፹ [80] ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ ፵ [40] ዓመቱ ነበር:: ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ፵ [40] ቀን የታሠበላቸውን መንገድ ፵ [40] ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ [ጥላ] እንዲሆን ነው:: ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ፵ [40] ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል [አገልግሎታል]:: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው ፹ [80] እየሆነ ነበር:: † እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን [አስተዳዳሪ] እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ: ¤ ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ ¤ ሕዝቡን አሻግሮ ¤ የኢያሪኮን ቅጥር ፯ [ 7 ] ጊዜ ዙሮ ¤ በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ ¤ የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ:: የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ፲፪ [12] ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም [በኤሎም ሸለቆ] አቆመ:: ሰባት አሕጉራተ ምስካይ [የመማጸኛ ከተሞችን] ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ፵ [40] ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው :- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: [ኢያ.፳፬] (24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ ፫ [3] ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ:: ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ ፫ [3] ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ፫ [3] ወገን [በነፍስ: በሥጋ: በልቡና] ድንግል ናት:: አንድም በ፫ [3] ወገን [ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት] ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" [የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ] ሲል ያመሰገናት:: ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ፹ [80] ዓመት: በተወለደ በ፻፳ [120] ዓመቱ [ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ፻፲ [110] ዓመቱ ይላል] በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ፴ [30] ቀናት አለቀሱለት:: † በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕዛብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን:: 🕊 [ †  ሰኔ ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን ፪. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ቅዳሴ ቤቱ] [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ ፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ ፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን ፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን † " አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" † [ኢያሱ.፳፬፥፲፬] (24:14) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показать все...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፳፮ - ] .mp32.32 MB
01:08
Видео недоступноПоказать в Telegram
                         †                         ሰው ራሱን አገኘ የሚባለው መቼ ነው ?          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
Показать все...
7.92 MB
[ + እውነተኛ ፍቅር + ] .mp36.53 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " ከቅጣት የሚያወጣን እውነተኛ ፍቅር !  " [    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ፥ አቤቱ ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ❞ [  መዝ . ፵፪ ፥ ፩  ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Показать все...
[ + ውለታህ ከበደኝ + ] .mp34.73 MB
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
                       †                          [     🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊     ] [  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] †                       †                       † [        በሌላ ላይ አለ መፍረድ !        ] 🕊 " በታቦቱ አጠገብ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ .. " ........ ጠቢብ የሆነ አንድ አረጋዊ ነበር፡፡ የአገሩ ሰዎች ወደ ኤጴስ ቆጶሱ ሄዱና ፦ “ይህ ካህን እያሳዘነን ስለሆነ ይባረርልን” ሲሉ ጠየቁት። ኤጲስ ቆጶሱም ፦ "ያሳዘናችሁ በምን ምክንያት ነው?" አላቸው። እነሱም ፦ "ቅዳሴ በሦስት ሰዓት የሚገባበት ጊዜ አለ ፣ በስድስት ሰዓትም የሚቀድስበት ጊዜ አለ ፣ ሰንበታትን አይጠብቅም ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያፈርሳል" አሉት፡፡ ኤጲስ ቆጶሱም ብቻውን ወሰደውና ፦ "ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትስ ለምን ታፈርሳለህ?" አለው፡፡ አረጋዊውም ፦ "አባቴ ሆይ ፣ ይቅርታ አድርግልኝ ፣ የማደርገውን አላውቅምና፡፡ በእሁድ ጠዋት አገልግሎት ከመፈጸም በኋላ መንፈስ ቅዱስ በመስዋዕቱ ላይ እስኪታይ ድረስ በታቦቱ አጠገብ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ ፣ ያን ጊዜ በፍርሃትና በረዓድ ሆኜ ቅዳሴውን አከናውናለሁ" አለው:: ኤጲስ ቆጶሱም ይህን ሲሰማ እጅግ አደነቀ ፣ ሕዝቡንም "በሰላም ሂዱ" ብሎ አሰናበታቸው:: ለዚሁ ቅዱስ አረጋዊ ሌላ ግሑስ አረጋዊ ሦስት የእሳት ፍሞችን በጨርቅ ቋጥሮ ላከለት ፣ ከዚህ አረጋዊ ካህን ዘንድም እሳቱም ሳይጠፋ ፣ ጨርቁም ሳይቃጠል ደረሰ፡፡ እርሱም ውኃ በጨርቅ አስሮ ላከለት ፣ በመካከላቸው ያለው ርቀት ሃያ አምስት ምዕራፍ ያህል ነበር። ቢሆንም ውኃው ሳይፈስ ደረሰ ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡ የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.