cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

❤የፍቅር ልቦች❣

💞ለምን ወደድኩህ/ሽ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 💞እንዴት ማረከኝ/ክሺኝ? እንጃ🤷‍♀️🤷‍♂️ 👉ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💞ማለት፤ ➽ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤ ➽በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤ 💁‍♂️💁‍ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💞 ሀሳብ ለመስጠት @Aschuuuuu

Больше
Рекламные посты
192
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ወዳጄ አንዳንዴ በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ሁሉ ይጨልማሉ፣ የምታደርገው ይጠፋሀል፤ የት አባቴ ሄጄ ከዚህ ስሜት ልውጣ የምትይበት ጊዜ ይመጣል....ያኔ አንድ ነገር አድርጊ....እጅሽ ላይ ያለውን ሁሉ  እያሰብሽ አመስግኚ፤ ለፍተን ካጣነው በነፃ ያገኘነው ይበልጣል እኮ...ለዛሬ ያልደረሱ ስንት አሉ...ቢያንስ እየተነፈስክ ነው አየር የሚከፈልበት ቢሆን ምን ይውጠን ነበር? ልጅ ካለሽ በልጅሽ ተፅናኚ! ወንድም እህት ካለህ እነሱን አስበህ ተፅናና! አባት ወይ እናት ካለሽ በነሱ ተደሰች! ታማኝ ፍቅረኛ ወይ ጓደኛ ካለን እነሱን ማሰብ በቂ ነው! ከሁሉም በላይ ግን ከመቃብር በላይ ትንፋሽ ሰጥቶ ለዛሬ ባደረሰን ፈጣሪ ተስፋ እናደርጋለን! ተስፋ የሞላበት ሰናይ ዕለተ ሰንበትን ተመኘሁላችሁ  Join and share @Yefikerleboche
Показать все...
#ልባም❤️_ወንድ 🎯#ልባም_ወንድ የትላንት ታሪክ እስረኛ አይደለም የዛሬዋን ቀን በጥበብ የሚጠቀምባትና የነገውንም ቀን በተስፋ የሚጠባበቃት እንጂ። 🎯#ልባም_ወንድ መነሻው የሆነችው እናቱን ፍቅርን ያለ ስስት ለግሳ ያሳደገችውን እህቱን በማሰብ ለሴት ዘር በሙሉ ከእነርሱ ለእነርሱ የሆነውን የሚገባቸውን ክብር ይለግሳቸዋል 🎯#ልባም_ወንድ አጠገቡ ላለችው እናቱ እህቱ እንዲሁም የህይወቱ ማገር ለሆነችው የፍቅር አጋሩ መከታ ጋሻና አለኝታ ይሆናል 🎯#ልባም_ወንድ አይቸኩልም በሁኔታም ተስፋ አይቆርጥም። የነገውን መልካም ቀን እያየ በተስፋ የሚራመድ ልበ ሙሉ እንጂ። 🎯#ልባም_ወንድ እንደ አካሎቹ ጠንካራ ነው። ለ አላማውም ጨካኝ ነው ለ እ/ርም ታዛዥ፣ታማኝ ነው። 🎯#ልባም_ወንድ ስጋውን፣ስሜቱን፣ፍቃዱን ለ አለም የሰቀለ ነው። ማስቀደም ያለበትን ያውቃል የሚያስፈልገውንም እንዲሁ በራሱ ሀሳብ ውስጥ ሳይሆን በእ/ር ሀሳብ ውስጥ ለመኖር የሚጥር ልበ ቀና ነው። 🎯#ልባም_ወንድ ታማኝ ነው ቃላባይ አይደለም አያስመስልም ያልሆነውንም ነኝ ለማለት አይፍጨረጨርም። ለሰው ሁሉ ክብር እንጂ ንቀት የለውም። 🎯#ልባም_ወንድ ቅድስና መታወቂያው ነው። ጉብዝናውንና ችሎታውን አቅሙን ሁሉ ለ እ/ር የሰዋ ነው። መልካምነትን ሀብቱ ያደረገ ትህትናን የተጎናፀፈ የዝሙት ጠላት የሆነ በአሉባልታ የማይመራ እራሱን የሆነ ጀግና ነው። 🎯ታድያ አንተ እራስህን ማን ብለህ ትጠራዋለህ? ወንድ ወይስ ልባም ወንድ? Join and share @Yefikerleboche ✍ Aschu
Показать все...
ሰላም ላንቺ ይሁን!" እህት ዓለሜ ! እንድት አድረሻል ? አረ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን ይባላል 🙈 ብቻ አንቺና የአንቺ የሆኑት ሁሉ ደህና እንድትሆኑ የኔ በምግባር ታናሽ የሆንኩት የወንድምሽ የየአብ-ስራ ምኞት ነው 🙏 -ወደ እለቱ መልዕክቴ ልግባ አብረሽኝ ቆይ👇👇👇 ☞ሔዋኔ አምላክሽን ማመን ብቻ በቂ አይደለም::ከልብሽ  ማፍቀርም ጀምሪ:: - ☞እርሱ የፈጣራቸው ብዙ ውብ🥰 ፍጥረታት አሉ::እንደ አንቺ  አስውቦ 😍 የሰራው  ግን የለም🙅‍♂ አየሽ አይደል አንቺ ለዚህ ዓለም🌍 መተኪያ አምሳያ የሌለሽ ማንም ሊመስልሽም ሊያህልሽም የማይቻለው ለፍጥረታት በሙሉ በተለይ ለእኛ ወንዶች የተቸርሽን ገፀበረከት ነሽ👸 :: - ☞ውብ ያደረገሽ ውብ በሆነው መንፈሱ ነው::ይህም ንፁሁ ያልተቀየጠ ፍቅር ነው::አዎ አንቺ ንፁሁ ፍቅር💖 ነሽ:: - ☞ካንቺ በህይወት መገኘት አብልጦ  የአምላክን ፍቅር💝 ምን ሊገልፀው ይችላል? - ☞ያንቺ አሰራር እና ፀጋ ከሁሉም ፍጥረት የሚልቅ የአምላክ ጥበብን ያዘለ ነው::ይህም ፍጥረትን ሁሉ የሚያድን የአምላክ ንፁህ ፍቅር ነው:: - ☞እርሱ ፍቅር❤️ አድርጎ ሰርቶሻል::አንቺ ግን እርሱን አፍቅረሻል? ልብሽን ለልቡ አስገዝተሻል? መልሱን ለአንቺው ተውኩት - ☞ፍጥረት ሁሉ የአምላክን  ፍቅር ባንቺ ውስጥ ለማየት እየናፈቀ ነው::ነፍስ ሁሉ ሰላምን ተጠምቶ ካንቺ ልብ ለመጠጣት እየጠበቀ ነው:: - ☞ገንዘብ💵 እንጂ አምላክ ባልተፈቀረበት አለም አንዲት አምላክን በልቧ ያነገሰች ልባም ሴት ሁኚ :: 🌍አለምን መስማት ትተሽ ጆሮሽን ወደ አምላክ አዘንብይ🛐 :: እርሱን የቀንም  የሌሊትም ጌጥሽ 👸አድርጊው::እስቲ ....እውነተኛ  የልብሽን ሜክአፕ በፈጣሪሽ ፍቅር በሆነ መዓዛ ተቀቢው:: - ☞በጊዚያዊ እርካታ የጠፋው አለም በዘለዓለማዊ የአምላክ ፍቅር ባንቺ በኩል ይዳን:: - የደግነት እና የመልካምነት ብርሃንሽ በሰዎች መካከል ይብራ::ትልቁ የአምላክ መንፈስ ባንቺ ውስጥ ይስራ:: - አሜን‼️ Join and share @YefikerlebocheAschu
Показать все...
ወዳጄ ሴት እናት ናት፤ ሴት ልጅ እህትም፣ ሚስትም ናት ። 👸ሴት ልጅ ርህራሄዋ ከሰው ልጅ አእምሮ አድማስ ሺሕ ዕጥፍ ይልቃል ። 👧ሴት ልጅ የቤት ካስማ የአገር ማገር ናት። ሴት የሌለበት ቤት ባዶ ነው ። 😍የሴት ልጅ ሩህሩህ ማንነት በእናትነት👵 ይገለጻል 🇪🇹በአገራችንም ዓውድ ሴት ልጅ የደግነት እና የአዛኝነት🥺 ተምሳሌት ነች ። 👉ሴት፣ ልጅ ከወለደች ለልጇ መኖር ግዴታዋ እስኪመስል ድረስ ማንኛውንም ዋጋ ስትከፍል ይስተዋላል ። ባሏ አጠገቧ ኖረም አልኖረም ፣ የእናትንም ፣ የአባትንም ቦታ ሸፍና ልጇን ታሳድጋለች። የአእምሮ ሕመም ያለባቸው እናቶች እንኳን ፣ በየመንገዱ ሲንከራተቱ፣ ልጃቸውን በፍጹም ከጎናቸው አይነጥሉትም። ሴት ልጅ በምድር ስትኖር ኃላፊነቷን፣ የምትችለውን ብቻ ሳይሆን ፣ ከምትችለው በላይ ስለምትወጣ ዘላለማዊ ክብር ይገባታል። ክብር ለሴቶቻችን👸 ክብር ለእንስቶቻችን👩‍🦰 ክብር ለእናቶቻችን 👵 ክብር ለሔዋን👩‍🦳 ዘር በሙሉ ይሁን                                       በፍቅር 🥰 የምታምሩበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበረቁበት ሰናይ 😁 ምሽት  ይሁንላችሁ Join and share @Yefikerleboche
Показать все...
እኔ እንደማውቀው ከሆነ እውነተኛ ጓደኛ የፈጣሪ ትልቅ ስጦታ🎁 ነው ። 👉ይሄን ስላቹ ምን ማለት ፈልጌ መሰላቹ እውነተኛ ጓደኛ ማለት ስታጠፋ የሚመክርህ ሲከፋህ የሆድህን አጫውተሀው የሚረዳህ ነው ። 🤔ግን ምን ያደርጋል አንዳንዶች ጓደኝነትን ይመሰርቱትና ስትደሰት  አብረውህ ይሆናሉ ሲከፋህ ትተውህ ይነጉዳሉ እና ታዲያ ይሄ ጓደኝነት ነው, የምር ጓደኝነት ማለት እኮ ቃል 🗣 ብቻ አይደለም  ስትጨነቅ አብሮ የሚጨነቅ ሲከፋህ መከፋትህ አሳስቦት የሚጠይቅህ ነው ። 👉እኔ ግን አንድ የምላቹ ነገር ቢኖር በህይወታቹ በጭራሽ ማንንም አትጥሉ መልካም ሰዎች ደስታን ይሰጡሀል ክፋ ሰዎች ደግሞ ትምህርት ይሆኑሀል። በመልካም ስራ የምናምርበት በፍቅር 🥰 የምንተሳሰርበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበርቅበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንልን Join and share @Yefikerleboche
Показать все...
ካንቺ ጋራ ስሆን❤️ የኔ አለም አዳምጪኝ 😊 ካንቺ ጋራ ስሆን..... ፍቅርሽን ሳጣጥም ፣ አይኖቼ በፍቅር ፡ ከአይኖችሽ ሲገጥም 🤗 ካንቺ ጋራ ስሆን .... 🔥 ንፋሳት ሁልጊዜ ፡ በፍቅር ያዜማሉ ፣ አይገርምም የኔ ዉድ ፡ እኔና አንቺ #ሊያዩ😻 ዥረቶች ለአፍታ ፡ ጉዞ ያቆማሉ ፣ ክዋክብት, ጨረቃ ፡ በኛ #ይቀናሉ 🤦‍♂ 'ካንቺ ጋራ ስሆን' ..... ❤️ ምሽቱ #ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣ አስቀያሚው ያምራል ፣😊 ጨለማው #ያበራል ፡፡ ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣ ህይወቴ #በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች🥰 ካንቺ ጋራ ስሆን አለም ለኔ እንዲህ ነች🤗    @Yefikerleboche
Показать все...
"ሰው ራሱን ሊያሸነፍ አይችልም፤ነገር ግን በራሱ ውስጥ ያለውን ነገር ማሸነፍ ይችላል" በማለቴ ከብዙ ሞቲቬተሮች "ምን ማለትህ ነው የሚል ጥያቄ ሲጎርፍልኝ ነበር ። እኔ እንደሚመሰለኝ ራስን ለማሸነፍ የሚደረገው ትንቅንቅ ከራስ ጋር መታገልና ራስን መጨመደድ ይመስለኛል፤ምናልባት ራስን መጨምደድ የሚለው ቃል እንዴት እንደሚገለፅ ባላውቅም ሲመስለኝ ሲመስለኝ ግን  " ራስን ከማስጨነቅ" ጋር የተያዘዘ ነው ብዬ አስባለሁ። በቀላሉ ራስን ማሸነፍ የሚባል ነገር የለም ነው እያልኩ ያለሁት፤እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ "ሰው እንዴት ራሱን በራሱ ያሸንፋል? ውስብስብ ያለ ነገር እኮ ነው። ምናልባት ሰው በራሱ ውስጥ ያለውን ነገር ማሸነፍ ይችላል አይደል መሆን ያለበት።ምንድን ነው በራሱ ውስጥ ያለው ነገር የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ ጭንቀት፣ፍርሃት፣ህመም፣ፈተና ወዘተ ሌላም ሌላም ብዬ እመልሳለሁ።እነዚህን በራሳችን ውስጥ ሆነው የሚያስጨንቁንን፣ የሚያስፈሩንን፣የሚያሳምሙንና የሚፈትኑንን በተጨማሪም ኮንፊደንሳችንን ለማሳጣት የሚሞክሩ ነገሮችን ማሸነፍ እንችላለን ነው አባባሌ!  @Yefikerleboche
Показать все...
"የሰው ልጅ የመኖሩ መሰረት ባዶነቱ ነው" እንዴት?🤔🤔 እስቲ ቤትህን🏘 ተመልከት! ምንም እንኳን ጣራ ወለልና ግድግዳ ቢኖረውም የምትኖረው ግን ባዶ ቦታው ላይ ነው ። ውሃ መጠጫ ብርጭቆህን🫙 ተመልከት!ሲጠማህ ቀድተህ የምትጠጣው ባዶ ቦታው ላይ ነው ። 🫶ፈጣሪስ ሄዋንን የፈጠራት ለምን ይመስልሃል?🤔🤔 ለአዳም ሀዘንና😔 መከራ እንድትሆነ? አትሳሳት ባዶ ጎኑን እንድትሞላለት ነው። ይሄ ሁሉ ወንድ ሲደክም የምታየው ባዶ ጎኑን የምትሞላለት ሴት የሔዋን ዘር ፍለጋ  ነው ። ሴቷም እንደዛው። ህይወት ባዶ ባትሆን ኖሮ እነኚህ ሁሉ ሙላቶች ባልኖሩ ነበር። በባዶነትህ መጠቀም እንጂ መጎዳት የለብህም           ❤                             Join and share @Yefikerleboche
Показать все...
✝መስቀሉ #ሰላም 🕊 ✝መስቀሉ #ፍቅር 💝 ✝መስቀሉ #ይቅርታ 🙏 ✝መስቀሉ #የዋህነት 🤗 ✝መስቀሉ #ቅንነት 🥰 ✝መስቀሉ #ራስን_ዝቅ_ማድረግ ነው የሚያስተምረን ይሄ ምስጢር የገባችሁ የተዋህዶ ልጆች በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ላላችሁ ወንድም እህቶቼ በሙሉ 😍   እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። ✝መስቀሉ በፍቅር መንገድ እስከመጨረሻው ታግሎ ላመኑበት #መሞት እንጂ እንደ ጦሩ ቤት ህግ፤ በሃይል ታግሎ ላመኑበት ነገር #መግደልን ጥበብ ነው ብሎ አስተምሮ አያውቅም። 👉የተገኘው መስቀል ዛሬም በልባቸው ያልተገኘ፤ በሚዳሰስ ጨላማ የሚኖሩ ሰዎች መስቀሉ የማያውቀውን የማሸነፍ ትርጉም ይኧውም #መግደልን ያወራሉ። 👉ስለ ፍቅር 🥰 #መሸነፍን በተማርንበት በዛው መስቀል በኩል በጉልበትና ቀፀብ ማሸነፍን ሲያወሩ አልፎ አልፎ ይደመጣሉ። #መስቀልና #መግደል በታሪክ አንድ ግዜ ነው የተገናኙት። መስቀል የገደለው አንድን ነገር ብቻ ነው። እርሱም #ጥልን🖤 በመስቀሉ ገደለ። ሰላምን🕊 ከሰው ወደ ሰው፣ ሰላምን🕊 ከሰው ወደ አምላክ👆 መስቀል ሰበከ። መስቀል ከዚህ ውጪ ገድሎ የሚያውቀው ነገር የለም 🙅‍♂። 👇ዛሬም ብርሃነ መስቀሉ #ብርሃናዊነትን አስተምሮን #ጥልን ብቻ ገድሎ ይለፍ እላለሁ! በመስቀሉ ብርሃን 👺 ክፉ ጠላት ድያብሎስንና አስተናጋጆቹን ድል የምንመታበት፥ 🥱የተራቡ በልተው የሚጠግቡበት ፥ 🤤 የተጠሙ ጠጥተው የሚረኩበት፥ 🤕 በደዌ ዳኛ ባልጋ ቁራኛ ተይዘው በህመም የሚሰቃዩ ከበሺታቸው የሚፈወሱበት፥ ⛓በግፍ የታሰሩ የሚፈቱበት፥ 🕊ሰላም ያጡ ሰላም የሚያገኙበት፥ 🚶  የተሰደዱ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት፥ 😏የተጣሉ የሚታረቁበት፥ 👎በውሸት የተለያዩ በእውነት አንድ የሚሆኑበት፥ ☹️ጨካኞች የሚራሩበት፥ ⚖ፍትሕ የሚሰፍንበት፥ ይሁንልን በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!                                                                           በፍቅር 🥰 የምታምሩበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበረቁበት ሰናይ 😁 በዓል ይሁንላችሁ Join and share @Yefikerleboche
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.