cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞ አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ https://t.me/+a3-5g5CslOkwNjBk ተጠቀሙ

Больше
Рекламные посты
2 921
Подписчики
+224 часа
+217 дней
+3930 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

#የአፎምያ_አጽናኝ     ከቀደመው መንገድ ከላይ በተሰጠን ዕድሳት በማያውቅ በማይሻርው ዘመን በድንቅ ምስክሮች ብርሃን በሆኑን እንድንጓዝ ሁሌም የአፎምያ አጽናኝ ጠላት ቀስቱን ሰብቆ ሊያጠፋን ሲመጣ እንደ ቋጥኝ ከቦን የዚህ አለም ጣጣ በከንቱ ስንሮጥ ኋላ እንዳንቀጣ አማልደን መላኩ የነፍሳችን ዕጣ የሁሉንም ጸሎት ከአምላክ የምታደርስ ፍቅር እና ርህራሄ በሰው የምታለብስ ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ፈጥነህ ድረስ በአንደበትህ ፍሬ ውስጣችን ይታደስ የዳንኤል አጽናኝ የአፎምያ ረዳት በህይወት የቀየርክ የባህራንን ጽሕፈት በለአምን የታደክ ከእርግማን መቅጸፍት እኛንም ጠብቀን ከምናየው መአት የምጽአት ዋዜማ ለመሆኑ ምስክር በመጽሐፍ ያለው ቃሉ ሲተገበር መተማመን ጠፍቶ ሲቀዘቅዝ ፍቅር በወንጌሉ አንድምታ ልባችን ይታጠር ይቅርታ ምህርቱ ይምጣልን የእግዚአብሔር እረኛ እንደሌለው ሲጨነቅ ትውልዱ ተመሳስሎ ቆሞ ሲያስት በመንገዱ ግራ በመጋት ስንቶቹ ተጎዱ በየዋህነታቸው አብረው ተሰደዱ ዘንዶ አፉን ከፍቶ ነፍሳት እንዳይወጥ የተዋህዶን መዝገብ እውነቱን ለመግለጥ የቆመውን ሁሉ በአውደ ምህረቱ ያበረታን አምላክ እሰከ ምጽአቱ።            እንኳን ለሊቀመላአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ክብር በዓል በሰላም አደርሳቹ አደረሰን የመላአኩ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን አሜን!
Показать все...
6
#ከዲያብሎስ_መንጋጋ_ቅድስት_አፎሚያን_ያስጣለበት ።     #ቅድስት_አፎሚያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው ባለቤቷ አስተራኒቆስ ይባላል የኪልቅያ መስፍን ነበረ  ታሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ አፎምያ ከሀብቷ ከንብረቷ ለነዳያን እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስ ትኖር ነበር ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን ሴት መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ደጅ ሆኖ አስጠራት ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካአል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ አለቻቸው ። መነኩሴውም እኛማ በነግህ ጸልየናል እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርግልሻል ? በዚያም ላይ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም እነአብርሃም እነዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን ስለዚህ ቤት ሠሪ ጎመን ዘሪ ጧሪ ቀባሪ ልጅ ያስፈልግሻል ባል አግብተሽ ብትኖሪ ይሻልሻል አላት ። ❝ #ቆብህ_መልካም_ነበር_ንግግርህ_ግን_ክፉ_ነው ❞ አትጹሚ አትጸልይ ያልከኝ ጌታችን ❝ #ከመሥዋዕት_ይልቅ_ምጽዋትን_እመርጣለሁ ❞ ብሎ የለምን ፤ ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንቱን በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ብሎ ቢኖር ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን ? ብላ ባሏ ታሞ ሳለ ያሠራላትን ሥዕለ #ቅዱስ_ሚካኤል አውጥታ ብታሳየው ሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን መጥቼ ከተመካሽበት ከዚህ ግብሱስ ሥዕል ጋር አጠፋሻለሁ ብሎ ዝቶባት እንደ ትቢያ በኖ ጠፍቷል :: #ሰኔ_12 ቀን በነግህ ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጥቶ ጾም ጸሎትሽ ፣ ስግደት ምጽዋትሽ ዐርጎልሻል ያ ስሁት አጠፋሻለሁ እንዳለሽ አውቄ ላድንሽ መጥቻለሁና አላት አንተ ማነህ ? አለችው ሊቀ መላእክት ሚካኤል ነኝ አላት የንጉሥ መልእከተኛ ያለማኅተም ይሄዳልን ? በትረ መስቀልህ ወዴት አለ ? አለችው ። መስቀል አሲዞ መሣል ልማድ ነው እንጂ እኛስ አንይዝም አላት ቆየኝ ሥዕሉን ላምጣልህ ብላ ዘወር ስትል አርአያውን ለውጦ ደብረ ጽልመት መስሎ አንገቷን አነቃት #ቅዱስ_ሚካኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ደርሶ ቀጥቶ አስምሎ ገዝቶ እመቀ እመቅ ጥሎታል ። እሷንም ብፅዕት ሆይ ጾም ጸሎትሽ ስጊድ ምጽዋትሽ ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶልሻል ፤ ዕረፍትሽ ዛሬ ነው ብሏት ዐርጓል ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ ሥጋውን ደሙን ተቀብላ ጳጳሱንና ካህናቱን ወደ ቤት ጠርታ አብልታ አጠጥታ ወርቋን ብሯን ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ለድሆች ምጽዋት ያደርገው ዘንድ ለጳጳሱ አደራ ሰጥታ ዐርፋለች ። #የቅዱስ_ሚካኤል ሥዕሉም ከእቅፏ ወጥቶ በርሮ ማንም ሳይሰቅለው ከቤተ መቅደስ በር ላይ ተሰቅሎ ተገኝቷል ኋላም አብቦ አፍርቶ በአበባው በፍሬው ሕሙማንን የሚፈውስ ሆኗል ይህ የእግዚአብሔር ተአምር ነው ፤ ዛሬም ስለማይመዘገብ ነው እንጂ እግዚአብሔር በመላእክቱ ላይ እያደረ ዘወትር ተአምር ያደርጋል ። በዚህ መሠረት መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል በተአምራቱ ዘወትር እንደሚጠብቀን ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር  ❝ የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል የቀን እረኛ የሌሊት ጠባቂ ክንፎቹ የእሳት የኾነ #ቅዱስ_ሚካኤል ዘወትር የሚጠብቅ የእውነት ድንኳን ከተማ ነው ። ❞ በማለት ተናግሯል ። ድንኳን ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር እንደሚከለሉበት ሁሉ #ቅዱስ_ሚካኤልም በቃል ኪዳኑም የሚታመኑትን ሁሉ ከምሕረት አልባ ከዲያብሎስ ደባ ፤ አጋንንት ድብደባ ፣ ከዚህ ዓለም ፈተና ያድናቸዋልና
Показать все...
👍 2
#የባሕራንን_የሞቱን_ጦማር_ቀዶ_ሠርግ_ያደረገ_መልአክ      በእስክንድርያ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ፣ ቅዱስ ሚካኤልንም የሚወዱና ወርኃዊ በዓሉን የሚያከብሩ ደጋጎች ባልና ሚስት ነበሩ ። እነዚህ ባልና ሚስት በየወሩ #በቅዱስ_ሚካኤል በዓል በቅዱስ ሚካኤል ስም ድግስ እየደገሱ ለተራቡ ድሆችና ለጦም አዳሪዎች ሁሉ ያበሉ ይመጸውቱ ነበር ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የቤቱ አባወራ ጥቂት ታሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ባልዮው በሞተ ጊዜ ባለቤቱ ፀንሳ ነበር ( እርጉዝ ነበረች ) ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለቤቱ ለመውለድ ደርሳ ምጥ ያዛት ምጡም በጸናባት ጊዜ ከእግዚአብሔር እንዲያማልዳትና ከጭንቋ እንዲያድናት ወደ ቅዱስ ሚካኤል ትለምንና ትማፀን ጀመር በዚያኑ ጊዜ ያለችበት ቤት በድንገት በብርሃን ተሞላ እሷም ከጭንቀቷ ዳነች መልኩ ያማረ ወንድ ልጅ ወለደች ። ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ባረከው  በጐረቤታቸው አንድ ጨካኝ ምሕረት የሌለው ክፉ ባለጸጋ ሰው ነበር ታዲያ ያ የተወለደው ሕፃን የዚያን ባለጸጋ ሀብትና ንብረት እርሻውንም ሁሉ እንደሚወርስ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነገራት ይህንም ነገር በቤቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ሰምተው ስለነበር ወሬው ተዛምቶ ባለጸጋው ጆሮ ደረሰ ባለጸጋውም ይህንን ወሬ በሰማ ጊዜ ሕፃኑን ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ጀመር የልጁም ዕድሜ አሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ፣ እናቱ ገንዘቧ ሁሉ በማለቁ ከችግር ላይ ወደቀች ያም ርኅራኄ የሌለው ባለጸጋ ይህን ባወቀ ጊዜ ልጅሽ እንዲላላከኝ ስጭኝ በምቾትና በድሎት አኖረዋለሁ ! ትምህርትም አስተምረዋለሁ በአጠቃላይ እንደ ልጄ አድርጌ አሳድገዋለሁ ላንቺም በቂ ገንዘብ ( አንድ ወቄት ወርቅ ) እሰጥሻለሁ ›› አላት ። ሴትየዋም ይህን በሰማች ጊዜ ስለ ችግሯ ደስ ብሏት ልጇን ሰጠችው ። ያም ባለጸጋ ልጁን የወሰደው ለማሳደግ ሳይሆን እንዳይወርሰው ለመግደል ነበር ለእርሷ ኻያ ወቄት ወርቅ ሰጥቶ ሕፃኑን ላሳድገው ብሎ ወሰደው ወስዶም በሳጥን ከቶ ከባሕር ጣለው ማዕበል እየገፋ ወስዶ ከወደቡ አደረሰው አንድ በግ ጠባቂ አግኝቶ ወርቅ መስሎት ከቤቱ ወስዶ ቢከፍተው መልከ መልካም ብላቴና ሆኖ አገኘው ። ልጅ ይሻ ነበርና ደስ አለው ከበላው እያበላ ከጠጣው እያጠጣ አሳደገው  ከብዙ ዓመት በኋላ ያ ባለጸጋ ለንግድ ሲሄድ መሽቶበት ከእነዚህ ቤት አደረ ባሕራን ባሕራን እያለ ሲጠራው ሰምቶ #ባሕራን ማለት ምን ማለት ነው ? አለው ፤ ከባሕር የተገኘ ማለት ነው ብሎ አለው ለምን እንደዚህ አልከው ? አለው ከባሕር ስላገኘሁት ነው አለው መቼ አገኘኸው ?አለው ወሩን አስታውሶ ቀኑን ጠቅሶ ሲነግረው እሱ ከጣለበት ጊዜ አንድ ሆኖ ቢያገኘው ለካ አልሞተም ብሎ ሲነጋ እባክህ ወዳጄ አንድ ነገር ላስቸግርህ ከቤት የረሳሁት ዕቃ ነበር የድካሙን ዋጋ ለአንተ እሰጣለሁ ልጅህን ልላከው ፍቀድልኝ አለው እሺ አለው ። ደብዳቤ ጽፎ ❝ ይህ ልጅ እንደ ደረሰ ግደሉት ❞ ብሎ አትሞ ምልክቱን ነግሮ ስንቁን አሲዞ እንደ ይሁዳ በሽንገላ ስሞ ሰደደው ባሕራንም ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው ቅዱስ ሚካኤል በአምሳለ ሊቀ ሐራ በፈረስ ተቀምጦ መላእክትን እንደ ሠራዊት አስከትሎ ከመንገድ ተገናኘው አንተ ልጅ ወዴት ትሄዳለህ አለው እንዲህ ካለ ቦታ መልእክት ላደርስ እየሄድኩ ነው አለው ። እስኪ መልእክቱን አሳየኝ አለው ፤ ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል አለው ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ አለው ደብዳቤው እንደታጠፈ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትእዛዝ ጽፎበታል ያንጊዜ ይዞ ሄደ ፤ ለቤቱ ሹም ሰጠው ገልጦ ቢያነበው "ልጄን ዳሩለት ሀብት ንብረቴን አውርሱት ባሮቼ ይገዙለት ይህ ቃል የእኔ ለመሆነ ምልክቱ እንዲህ ነው ❞ የሚል አነበበ በጌታውም ማኅተም ታትሟልና ሁሉም ነገር ተደረገለት ባለጸጋው ከንግድ ሲመለስ የዘፈን የጨዋታ ድምፅ ሰምቶ አሽከሩን አግኝቶ ይህ ሁሉ ዘፈን ጨዋታ ምን ተገኝቶ ነው ? ብሎ ጠየቀ የላከው ሰው ልጅህን አግብቶ ሀብትህን ወርሶ ይኸው አርባ ቀን ሙሉ ይዘፈናል አለው ደንግጦ ከፈረሱ ወድቆ ሞተ ። ባሕራንም ይህ ሁሉ #በቅዱስ_ሚካኤል ተራዳኢነት የተደረገለት መሆኑን አምኖ ማዕርገ ቅስና ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ዕድሜውን በሙሉ በቅን ልቡና በትሑት ሰብእና ሲያገለግል ኖሯል ።         #ከገናናው_መልአክ_ከቅዱስ_ሚካኤል_አምላከ_ቅዱሳን_ረድኤት_በረከትን_ይስጠን
Показать все...
🕊 1
#የባሕራንን_የሞቱን_ጦማር_ቀዶ_ሠርግ_ያደረገ_መልአክ በእስክንድርያ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ፣ ቅዱስ ሚካኤልንም የሚወዱና ወርኃዊ በዓሉን የሚያከብሩ ደጋጎች ባልና ሚስት ነበሩ ። እነዚህ ባልና ሚስት በየወሩ #በቅዱስ_ሚካኤል በዓል በቅዱስ ሚካኤል ስም ድግስ እየደገሱ ለተራቡ ድሆችና ለጦም አዳሪዎች ሁሉ ያበሉ ይመጸውቱ ነበር ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የቤቱ አባወራ ጥቂት ታሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ባልዮው በሞተ ጊዜ ባለቤቱ ፀንሳ ነበር ( እርጉዝ ነበረች ) ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባለቤቱ ለመውለድ ደርሳ ምጥ ያዛት ምጡም በጸናባት ጊዜ ከእግዚአብሔር እንዲያማልዳትና ከጭንቋ እንዲያድናት ወደ ቅዱስ ሚካኤል ትለምንና ትማፀን ጀመር በዚያኑ ጊዜ ያለችበት ቤት በድንገት በብርሃን ተሞላ እሷም ከጭንቀቷ ዳነች መልኩ ያማረ ወንድ ልጅ ወለደች ። ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ባረከው  በጐረቤታቸው አንድ ጨካኝ ምሕረት የሌለው ክፉ ባለጸጋ ሰው ነበር ታዲያ ያ የተወለደው ሕፃን የዚያን ባለጸጋ ሀብትና ንብረት እርሻውንም ሁሉ እንደሚወርስ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነገራት ይህንም ነገር በቤቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ሰምተው ስለነበር ወሬው ተዛምቶ ባለጸጋው ጆሮ ደረሰ ባለጸጋውም ይህንን ወሬ በሰማ ጊዜ ሕፃኑን ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ጀመር የልጁም ዕድሜ አሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ፣ እናቱ ገንዘቧ ሁሉ በማለቁ ከችግር ላይ ወደቀች ያም ርኅራኄ የሌለው ባለጸጋ ይህን ባወቀ ጊዜ ልጅሽ እንዲላላከኝ ስጭኝ በምቾትና በድሎት አኖረዋለሁ ! ትምህርትም አስተምረዋለሁ በአጠቃላይ እንደ ልጄ አድርጌ አሳድገዋለሁ ላንቺም በቂ ገንዘብ ( አንድ ወቄት ወርቅ ) እሰጥሻለሁ ›› አላት ። ሴትየዋም ይህን በሰማች ጊዜ ስለ ችግሯ ደስ ብሏት ልጇን ሰጠችው ። ያም ባለጸጋ ልጁን የወሰደው ለማሳደግ ሳይሆን እንዳይወርሰው ለመግደል ነበር ለእርሷ ኻያ ወቄት ወርቅ ሰጥቶ ሕፃኑን ላሳድገው ብሎ ወሰደው ወስዶም በሳጥን ከቶ ከባሕር ጣለው ማዕበል እየገፋ ወስዶ ከወደቡ አደረሰው አንድ በግ ጠባቂ አግኝቶ ወርቅ መስሎት ከቤቱ ወስዶ ቢከፍተው መልከ መልካም ብላቴና ሆኖ አገኘው ። ልጅ ይሻ ነበርና ደስ አለው ከበላው እያበላ ከጠጣው እያጠጣ አሳደገው  ከብዙ ዓመት በኋላ ያ ባለጸጋ ለንግድ ሲሄድ መሽቶበት ከእነዚህ ቤት አደረ ባሕራን ባሕራን እያለ ሲጠራው ሰምቶ #ባሕራን ማለት ምን ማለት ነው ? አለው ፤ ከባሕር የተገኘ ማለት ነው ብሎ አለው ለምን እንደዚህ አልከው ? አለው ከባሕር ስላገኘሁት ነው አለው መቼ አገኘኸው ?አለው ወሩን አስታውሶ ቀኑን ጠቅሶ ሲነግረው እሱ ከጣለበት ጊዜ አንድ ሆኖ ቢያገኘው ለካ አልሞተም ብሎ ሲነጋ እባክህ ወዳጄ አንድ ነገር ላስቸግርህ ከቤት የረሳሁት ዕቃ ነበር የድካሙን ዋጋ ለአንተ እሰጣለሁ ልጅህን ልላከው ፍቀድልኝ አለው እሺ አለው ። ደብዳቤ ጽፎ ❝ ይህ ልጅ እንደ ደረሰ ግደሉት ❞ ብሎ አትሞ ምልክቱን ነግሮ ስንቁን አሲዞ እንደ ይሁዳ በሽንገላ ስሞ ሰደደው ባሕራንም ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው ቅዱስ ሚካኤል በአምሳለ ሊቀ ሐራ በፈረስ ተቀምጦ መላእክትን እንደ ሠራዊት አስከትሎ ከመንገድ ተገናኘው አንተ ልጅ ወዴት ትሄዳለህ አለው እንዲህ ካለ ቦታ መልእክት ላደርስ እየሄድኩ ነው አለው ። እስኪ መልእክቱን አሳየኝ አለው ፤ ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል አለው ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ አለው ደብዳቤው እንደታጠፈ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትእዛዝ ጽፎበታል ያንጊዜ ይዞ ሄደ ፤ ለቤቱ ሹም ሰጠው ገልጦ ቢያነበው "ልጄን ዳሩለት ሀብት ንብረቴን አውርሱት ባሮቼ ይገዙለት ይህ ቃል የእኔ ለመሆነ ምልክቱ እንዲህ ነው ❞ የሚል አነበበ በጌታውም ማኅተም ታትሟልና ሁሉም ነገር ተደረገለት ባለጸጋው ከንግድ ሲመለስ የዘፈን የጨዋታ ድምፅ ሰምቶ አሽከሩን አግኝቶ ይህ ሁሉ ዘፈን ጨዋታ ምን ተገኝቶ ነው ? ብሎ ጠየቀ የላከው ሰው ልጅህን አግብቶ ሀብትህን ወርሶ ይኸው አርባ ቀን ሙሉ ይዘፈናል አለው ደንግጦ ከፈረሱ ወድቆ ሞተ ። ባሕራንም ይህ ሁሉ #በቅዱስ_ሚካኤል ተራዳኢነት የተደረገለት መሆኑን አምኖ ማዕርገ ቅስና ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ዕድሜውን በሙሉ በቅን ልቡና በትሑት ሰብእና ሲያገለግል ኖሯል ።         #ከገናናው_መልአክ_ከቅዱስ_ሚካኤል_አምላከ_ቅዱሳን_ረድኤት_በረከትን_ይስጠን
Показать все...
አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

🔔🔔🔔 አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ🔔🔔🔔 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች ፣ወቅታዊ መረጃ፣ሥርዓተ ማኅሌት ፣ዝማሬ፣የቅዱሳንን ታሪክ የምታገኙበት ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት @SDS12317212729 @Dn_amu_ki_17

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል አደረሳችሁ!! +  መልአኩ ነው +        ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ወንድማችን ብቻ ነበር፡፡ ድንገት ግን የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳና ሁላችንም ጨዋታችንን አቋረጥን፡፡ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ? ሠራተኛችን ሮጣ ሔደች:: ወዲያው ግን በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡ "በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡ እስዋ ግን በእርግጠኝነት ተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎ አላመነም፡፡ ባይሆን የመንግሥት ወታደሮች የቀረነውን ሊወስዱን ይሆን? ማን ሊሆን ይችላል? ብሎ ተብሰለሰለ:: በመጨረሻም የሁሉም ግምት አንድ ነገር ላይ አረፈ:: ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ አንድ ቃል ተናገረ "መልአኩ ነው!"   መልአኩ የሰው ስም አይደለም:: ቤተሰቡ የተስማማው "ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› ብሎ ነበር፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡ በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!       ይህ ገጠመኝ በአሁን ዘመን የተፈጸመ ነው ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል? እውነት በሌሊት የቤታችን በር ሲንኳኳ  መልአክ ነው ብለን እንገምታለን? ይህ ቤተሰብ ምን ዓይነት ቤተሰብ ነው? በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱ እየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚል ነው፡፡       በሐዋርያት ዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች በዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷን ተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን መልአኩ ነው፡፡›› አሉ፡፡ ይደንቃል የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)       ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስ እያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛም የመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባት ምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት በምድር የሚሆነውን ያውቃሉ:: (2 ሳሙ 14:20) በበደላችን ስንጸጸት "ኃጢአትህ ተሠረየችልህ" ይላሉ (ኢሳ 6:7) በክፋታችን ጸንተን ከቀጠልን ደግሞ "ይቅር አይሉም" (ዘጸ 23:20) ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው "የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?" ብለው ያማልዳሉ:: (ዘካ 1:12) ባለንበት ዘመን በዓለም ሁሉ በበሽታ የሚሠቃየው ብዙ ነው::  በሕመም ለሚሠቃየው ሁሉ "መልአክ ቢገኝለት እየራራለት [ለእግዚአብሔር] ፡— ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ 33:23-25 (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
Показать все...
አበው ይናገሩ እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡ እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡ ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡ ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡ ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡ ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት? ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት? ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት? እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡ ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡ እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡ የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው? በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው? ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው? ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው? ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት? አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ? ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡ የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡ የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡ እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ? የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ? መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡ ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው? ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና? በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ? የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው? ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡ ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን ልሳነ ጤዛ መናፍቅን ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡ በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡ ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡ የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡ ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡ ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡ እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡ እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡ ምንጭ፡- መለከት 1ኛ ዓመት ቁጥር 6 @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim #Join_and_share
Показать все...
👏 10
ቅዱስ ያሬድ ከዚያ በኋላ ወደ አከሱም ተመልሶ በመደባይ ታብር በተባለ ቦታ ቅዳሴያትን በዜማ አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቦታ ከአከሱም 15 ኪ.ሜ ርቆ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ አክሱምን ተሰናብቶ ለመሄድ ወደ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገባና «ቅድስት ወብጽዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት አንቀጸ ብርሃን ማዕርገ ሕይወት» እያለ አንቀጸ ብርሃን የተባለውን ድርሰቱን ሰተት አድርጎ አዘጋጀው፡፡ ይህንን ድርሰት ሲያዜም አንድ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ብሎ ይታይ ነበር ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በሰሜንና ወገራ፣ አገውና በጌምድር እየተዘዋወረ አስተምሮ ከሰሜን ተራራዎች ውስጥ እየጾመና እየጸለየ በብሕትውና ለብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ባለው በጸለምት ዋሻ ውስጥ በ571 ዓ.ም ግንቦት 11 ቀን ተሠውሯል፡፡ ይህ ቦታ በተለምዶ የሰሜን ተራሮች በሚባለው ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛና ብርዳማ ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማን ከማበርከቱም ሌላ በትምህርት ሂደትም አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ የድጓን፣ የጾመ ድጓን የዝማሬ መዋሥዕትንና የቅዳሴን ትምህርት ከማስተማሩም በላይ ለቅኔ ትምህርትም መሠረት ጥሏል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዓለም የመጀመርው የዜማ ኖታ/ ምልክት/ ባለቤት ነው። በእውነት የቅዱስ ያሬድን ጸጋ ያብዛልን ረድኤቱ ፣ በረከቱ ፣ ቃል ኪዳኑን ያብዛልን አሜን አሜን።
Показать все...
👍 2
​​እንኳን ለቅዱስ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ። #ቅዱስ_ያሬድ_ማነው? የቅዳስ ያሬድ አባቱ አብድዩ / ይስሐቅ/ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ / ይባላሉ። በሌላም በኩል አባቱ እንበረም እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ፡፡ የትውልድ ሥፍራው አክሱም ነው፡፡ የተወለደው በ505 ዓ.ም/ ሚያዝያ 5 ቀን ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡ ከአባ ጌዴዎንም ዘንድ እየተማረ ለ25 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለሆነ በጣም ያዝን ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከትምህርት ድክመቱ የተነሣ አጎቱ በጨንገር ቢገርፈው በዚህ ተበሳጭቶ ትምህርቱን ትቶ ሄደ፡፡ በመንገድም ሲጓዝ ውሎ በቀትር ደክሞት ከዛፍ ሥር ዐረፈ፡፡ በዚያ ጊዜ አንድ ትል ከዛፉ ላይ ያለውን ፍሬ ለመብላት ስድስት ጊዜ በመውደቅና በመነሣት ዛፉ ላይ ለመውጣት ሞክሮ በሰባተኛው ሰተት ብሎ ወጥቶ ሲበላ ተመለከተ፡፡ እርሱም በፈጸመው የብስጭት ተግባር በመጸጸት ተመልሶና አጎቱን ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ አጎቱም ተደስቶ ዓይነ ልቡናውን ያበራለት ዘንድ እያለቀሰ ፈጣሪውን ለመነለት፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለቅዱስ ያሬድ ዕውቀትን ገልጾለት መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ዐወቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ መምህሩ ተመልሶ ትምህርቱን ቀጠለና ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ አጠና፡፡ ሢመተ ዲቁናን ቀጥሎም ሢመተ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝልና አራራይን ከሦስት ወፎች/መላእክት በወፎች ተመስለው/ መማሩን ሊቃውንት ይገልጣሉ፡፡ እነዚህ በወፍ የተመሰሉ መላእክት እየመሩት ወደ አርአያም አርጎ የ24ቱን ካህናተ ሰማይ ዜማ ከተማረ በኋላ ጠዋት በ3 ሰዓት በአክሱም ቤተ ክርስቲያን «ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሣረረ ወበዳግመ አረአዮ ለሙሴ ዘከመ ይግበር ግብራ ለደብተራ» ብሎ አዜመ፡፡ ይህን ዜማ የደረሰበት ወሩ ታኅሳስ ቀኑም ዕለተ ሰኞ ነው ይባላል፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው «አርያም» በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘ መሆኑን ለማጠየቅ የተሰጠው ስም ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ይህንን ዜማ በተመስጦ ሲያዜም ንጉሡ ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ መኳንንቱና ካህናቱ ወደ አኩስም ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው መጥተው በአድናቆት ያዳምጡት ነበር፡፡ ምክንያቱም ገድለ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገልጥልን ከዚያ በፊት በውርድ ንባብ ከሚደረግ ጸሎትና መንፈሳዊ አገልገሎት በቀር ይህን የመሰለ ዜማ አልነበረምና፡፡ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ብሉይን ከሐዲስ ያስማማ ፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ የያዘ ፣ እንዲሁም ለልዑል እግዚአብሔር ፣ ለእመቤታችን ፣ ለቅዱሳን መላእክት ፣  ለሰማዕታት ተገቢ የሆነውን ምስጋና የያዘ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለአራቱ የዓመቱ ወቅቶች እንዲስማማ አድርጎ ለበጋ፣ ለክረምት ፣ ለመጸውና ለጸደይ እንደሚሆን አድርጎ ከፋፍሏቸዋል፡፡ ለየበዓላቱም ተስማሚ ድርሰት መድቦላቸዋል፡፡ ይህንን ድርሰቱን በግእዝ ፣ በእዝልና በአራራይ ዜማ ያዘጋጀው ሲሆን ለነዚህም ስምንት የዜማ ምልክቶች ሠርቶላቸዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድ ዜማ አንዴት ሁሉንም ይመስጥና ወደ አርያም በመንፈስ ይወስድ እንደ ነበር ለማስረዳት በገድሉም በሌሎችም መጻሕፍት የተመዘገቡ ታሪኮች አሉ፡፡ አንድ ቀን ንጉሥ ገብረመስቀል ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ሲያዜም ንጉሡ በመመሰጡ የተነሣ በመሰቀል ተሰላጢኑ ጫፍ የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው፡፡ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ መዝሙሩን ሲፈጽም ንጉሡ መስቀል ተሰላጢኑን ቢያነሳው የቅዱስ ያሬድ ደሙ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡ በዚህ ደንግጦ ለዚህ ካሣ ይሆን ዘንድ የፈለግከውን ጠይቀኝ እሰጥሃለሁ ብሎ ቃል ገባለት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግን ከዚህ ዓለም ተለይቶ በምናኔ መኖርና መዝሙሩንም በሚገባ ማዘጋጀት እንደሚፈልግ ገለጠ፡፡ ምንም እንኳን አክሱምን ለቅቆ መውጣቱ ንጉሡን ቅር ቢያሰኘውም ቃሉን አንድ ጊዜ በመስጠቱ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡ ቅዱስ ያሬድም ከዚህ በኋላ አኩስምን ለቅቆ ወደ ስሜን ተራራ ጸለምት መጓዙ ይነገራል፡፡ በጐንደር ፎገራ በሚባል ሥፍራ ቅዱስ ያሬድ ጣዕም ያለው ዜማውን ሲዘምር ተጠምደው የሚያርሱ በሬዎች ድምፁን እየሰሙ ገበሬውን ሥራ ስለ አስፈቱት በዚህ ተናዶ ቅዱስ ያሬድን በጅራፍ እንደ ገረፈው ይነገራል፡፡ ቦታውም « ወርቀ ደም እየተባለ እስከ ዛሬ ይጠራል፡፡ ወርቃማና ንጹሕ ደሙ የፈሰሰበት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀበት ዘመን ከ540-560 ዓ.ም ባለው ጊዜ መሆኑ ይነገራል፡፡ ዜማውን ካዘጋጀ በኋላ 11 ዓመት አስተምሯል፡፡ በእርሱ ዘመን ተሰዓቱ ቅዱሳን በሃይማኖት ችግር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው መጥተው ስለ ነበር ቅዱስ ያሬድ ከአንዱ ከአባ ጰንጠሌዎን የውጭውን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ባሕልና ሥርዓት ይጠይቅ ነበር፡፡ በጆሮ የሰማውንም በዓይን ለማየት ሁለት ጊዜ ሮም የተባለችውን የቁስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን ጐበኘሁ ይላል፡፡ «ወሪድየ ብሔረ ሮሜ ለቤተ ክርስቲያን ርዒክዋ» እንዲል፡፡ የታሪክ ምሁሩ ሥርግው ሀብለ ሥላሴ ለቁስጥንጥንያ ዜማ መነሻው ቅዱስ ያሬድ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚያደርጉት የቁስጥንጥንያን ዜማ የደረሰው ሊቅ ዜማውን አገኘው የሚባለው የቅድስት ሶፍያን ቤተ ክርስቲያን ሲዞር ከሰማው ዜማ ነው፡፡ ይህ ዘመን ደግሞ ቅዱስ ያሬድ ከተነሣበትና ወደ ሮሜ ሄድኩ ካለበት ዘመን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም ምናልባት ያ ሰው ዜማውን የሰማው የቅድስት ሶፍያ ቤተ ክርስቲያንን እየዞረ ሲዘምር ከነበረው ከቅዱስ ያሬድ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ፡፡ Ancient and medival Ethiopian History/ ቅዱስ ያሬድ ማትያስና ዮሴፍ በተባሉ የአቡነ አረጋዊ ደቀ መዛሙርት መሪነት ወደ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጥቶ ከጻድቁ ጋር በመገናኘትና የቤተ ክርስቲያኑን ሥራ እያደነቀ ዙሪያውን ከዞረ በኋላ «ዖድክዋ ወርኢኩ ሥነ ሕንፃሃ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን» ሲል ዘመረ፡፡ በዚያም ለአንድ ሳምንት ሰንብቶ ሄዷል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከአቡነ አረጋዊ እና ከዐፄ ገብረ መስቀል ጋር በመሆን በወሎ፣ በጎንደር፣ በሸዋ እና እስከ ጋሞጎፋ ብርብር ማርያም ድረስ በመሄድ አስተምሯል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች የዐርባ ምንጭን ታሪክ ከቅዱስ ያሬድ፣ ከአቡነ አረጋዊ እና ከዐፄ ገብረ መስቀል ታሪክ ጋር ያያይዙታል፡፡ ሦስቱም ብርብር ማርያምን ለማየት ሄደው በነበረ ጊዜ በዛሬው ዐርባ ምንሥ አካባቢ ሠፍረው ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ለወታደሩ የሚበቃ የሚጠጣ ውኃ በመጥፋቱ አቡነ አረጋዊ ጸልየው መሬቱን በመስቀል ቢመቱት ዐርባ ውሃዎች ፈለቁ ይባላል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል የጣና ቂርቆስን ቤተ ክርስቲያንን በሚያሠራ ጊዜ በዚያ ቦታ ለሁለት ዓመት ተቀምጦ ድጓውን በማስተማሩ ምልክት የሌለው ድጓው እስከ ዛሬ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ቀጥሎም የዙር አባን ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ወደ ጋይንት በተጓዙ ጊዜም በዚያ ሁለት ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት የተባለ ድርሰቱን አስተምሯል፡፡ ይህ ቦታ እስከ ዛሬ የዚህ ትምህርት ማስመስከሪያ ነው፡፡
Показать все...
👍 3
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? 👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። 👉 ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ" (ዮሐ20:29) የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
Показать все...
👍 9 2
#ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት የዛሬው ዕለት #ቅዱሳት_አንስት ወይም #አንስት_አንከራ ተብሎ ይጠራል 👉"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ነገራ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ፤ ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውን ተናገሩ ማለት ነው ለጊዜው የጌታን ትንሣኤ ያበሠሩ ሴቶች መታሰቢያ ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለክርስቲያን ሴቶች ሁሉ መታሰቢያ ቀን ነው። ዛሬም ብሥራተ ትንሣኤውን በዝማሬ በምስጋና በማስቀደስ በመቁረብ በሚዲያ በቃል በተግባር በማብላት በማጠጣት በማስተናገድ በጸሎት....በልዩ ልዩ አገልግሎት የሚፋጠኑ የሚመሰክሩ ሴቶች "ቅዱሳት አንስት" ይባላሉ (የተለዩ የተመረጡ የጸኑ  ማለት ነው)። እግዚአብሔር እናቶችንና እህቶችን ይጠብቅልን!
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.