cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

فَذَكِّرْ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٌۭ

የአላህ  መልዕክተኛ (ﷺ)  እንዲህ  ብለዋል፦ (ከሰዎች መካከል የመልካም በር ከፋች የሆኑና የመጥፎ በር ዘጊዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ከሰዎች መካከል የሸር  በር ከፋች የሆኑና የመልካም በር ዘጊ የሆኑ አሉ። አላህ የመልካም በር መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ላደረገለት ‘ጡባ’ አለለት ፤  አላህ  የመጥፎ  በር መክፈቻ  ቁልፍ  በእጁ  ላደረገለት  ‘ወይል’ አለለት።) [ኢብኑ ማጃህ (237) ዘግበውታል። 

Больше
Рекламные посты
417
Подписчики
Нет данных24 часа
-57 дней
-130 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ወንጀልን ለማሰረዝ፣ ደረጃን ከፍ ለማድረግ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “ላመላክታችሁን? አላህ ኃጢአቶችን የሚያብስበትንና ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር። ሲሉ ሰሓቦች አዎ ይንገሩን የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አሉ። ረሱልም (ﷺ)፡‐ በብርድና በመሳሰሉት እየከበደ ውዱእ አሟልቶ ማድረግ፣ ወደ መስጊዶች እርምጃዎችን ማብዛት፣ ከአንዱ ሶላት በኋላ ሌላውን ሶላት መጠባበቅ ነው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 251
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
#አንዳንድ ጊዜ የሆነ የተስፋ ብርሃን ይታየኛል ። አንዳንዴ ደግሞ ፊትለፊቴ ሁሉ ይጨልምብኛል። ~ በብርሃን ተስፋው ላይ ሙጭጭ እላለሁ እንጂ እንዲሁ እጅ አልሰጥም ። ብርሃን ማየቴን አልተውም።
Показать все...
👍 3
አረ እንዲች ነችና ለካ አልተዋወቅንም ማንነቴን አላወክም አትበል አትፎክር ማንነትህን አላህ ካልሰተረልህ ብዙ አሳፋሪ ነገሮች በጀርባህ አሉ። ማንኛውንም ነገር ስትሰራ በአላህ እገዛ እንጅ በችሎታህ እንዳልሆነ አስብ ማንኛውንም ነገር ስትሰራ አላህ እንዲወድልህ ምናልባት ወንጀልህን ይቅር እንዲልህ ጀነትን እንዲናጎናፅፍህ እንጅ ማንነትህን ማሳያ አታድርገው ተጣጥረህ የሆነ ነገር በማሳየትህ ሰዎች በዛ የሚያስቡህ ማንነት አይደለም ያንተ ማንነት ያንተ ማንነት አንተ የረሳሀውንም ጨምሮ የሚያውቀው አላህ ብቻ የሚያውቀው ማንነት ነው። ሁሉም ሠው ወደ አላህ ከጃይ እንጅ በራሱ ምንም የማድረግ አቅም ያለው አይደለም። ۞ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ ❝ እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ ❞ [ ሱረቱ አል-ፈጢር - 15 ]
Показать все...
👍 2
ሴት ልጅ ዲን ካላት ሁሉ ነገር አላት። ዲን ከሌላት ግን ሁሉ ነገር እንደሌላት ነው። ዲን + ሐያእ + አኽላቅ → ፉንጋዋን ከቆንጆዎች በላይ ያደርጋታል። የነዚህ አለመኖር ደግሞ ቆንጆ የምትባለዋን ከፉንጋ በታች ያደርጋታል። اللهم أصلح نساء المسلمين، زيِّنهم بالعفاف والحِجاب والحشمة، احفظهن من أن يَفْتنَّ أو يُفتنَّ يا رب العالمين🤲✍🏽አብ ፈውዛን ከሷሊሆች ከሰለፊዮች አሏህ ከሚወዳቸው ያርገን እህቶቼ ወንድሞቼ ከአሏህ መውደድ በላይ ምን አለ 
Показать все...
"እስልምና" የማይረታው እምነት!!✍✍✍✍✍✍✍✍

❥ሁሌም ቢሆን ለዲንህ ትልቁን ቦታ ስጥ!! «ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ፡፡» Channelu ሚሰጣቸው አገልግሎቶች👇 ኢንሻአላህ አላማችን ተውሂድን ማስተማርና የዱንያን ጠፊነት የአኼራን ዘላለማዊነት ማስታወስ ነው።!!!😍 ኢስላማዊ አጀንዳዎች ,islamic qoutes & others

https://t.me/islamisthebasetrilgen

ሰው ስለ ብርድ ባወራ ቁጥር "አግባ/አግቢ"  ምትሉ ሰዎች i got a question for you guys.. ሰው ቢያገባ በብርድ ወቅት ሁለት የበረደው ሰው እንጂ ሌላ ምን ይሆናል? ወይስ ሌላ ሰው ሲበርደው ማየት ያፅናናችኃል ነው? እና ደሞ ያገባ ሰው ከቤት አይወጣም እናንተ ሰፈር? ያው ቤት ውስጥ ድሮም አይበርደንም ብዬ ነው .. እና ደሞ እንዳየነው ከሆነ ያገባም ይበርደዋል (አገባሁ ብሎ ሹራብ መልበስ ያቆመ ስለማናውቅ) .. any way መፍትሄ ስትሰጡ /ለሰው ስትመክሩ ሚሰራ ነገር ቢሆን ባይ ነኝ (Allah knows the best) 😌 © Semir
Показать все...
👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌺 ሰዎች ለጊዜው የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሰጥተው ጊዜያዊ ደስታን ሊያስደስቱን ይችላሉ" ...ነገር ግን ዘላቂ የሆነ ደስታ ሊሆንልን አይችልም ✅ እውነተኛና ዘላቂ የሆነ ደስታን የምናገኘው ከጌታችን አላህ እንጂ ከሰዎች አይደለም 🔘 ስለዚህ ከጌታችን ጋር ያለንን ግንኙነት እናሳምር። 📎https://t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/3837
Показать все...
👍 4
~አንዳንዴ…ሳቃቸው መለያቸው እስከሚሆን ድረስ የሚስቁ ግና ለብቻቸው ሲሆኑ ለምን እንደሚስቁ ግራ የሚገባቸው ሰዎች አሉ። የትኛውም የተስፋ ቃል ልባቸውን የማያረጋጋው አላህ ይሁናችሁ ከማለት በቀር ምንም ልናደርግላቸው የማይቻልን ሰዎች አሉ። ነገር ዓለሙ ግራ የገባው፣ ከመጪው ዓለም ፈተና የበለጠ በዱንያ መቆየት ያስፈራው፣ የያንገሸገሸው ሰው አለ። የውስጧን ህመም ውበቷ ሊከልለው ያልቻለ፣ በክብር የለበሰችውን ሒጃብ ሊያስወልቃት የሚደርስ በደል እየደረሰባት የምትገኝ እንስት ትኖራለች።ለሁሉም የሆነ ማንም ያልሆነው አለ። እንባ የደረቀበት፣ ናፍቆት ያለቀበት፣ ህይወት ጥፍጥናን ያጣበት፣ እግረ መንገዱን ዝም ብሎ የሚኖር ሰው አለ። ለአንዳንድ ሰዎች ከልባችሁ ወደ አላህ ዱዓ ልታደርጉላቸው ካልሆነ በቀር በቃላቶቻችሁ ምንም ልትፈይዱላቸው አትችሉም። የታመመ ሁሉም አይፅናናም። የተገኘ ሁሉም አይመከርም። አንዳንድ የሰዎችን ጉዳይ በዱዓ ብቻ ለመፍታት ሞክሩ። በቃ ተግታችሁ ዱዓ ብቻ አድርጉ! ብቻ አብሽሩ! አላህ ለልባችሁ ሰላም ይስጣችሁ!
Показать все...
3👍 1
ቀጥታ ስርጭት ተጀመረ የሷሊህ ሴት ባህርያት ልዩ ሳምንታዊ የነብያት ፋና መድረክ https://t.me/nhwdr?livestream=7f0c497cb90a778df1
Показать все...
የነብያት ፋና ብሮድካስቲንግ (አለም አቀፍ) መርከዝ እና የዳዕዋ ማዕከል

💫"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው። 🕌በደረጃ የሚለቀቁ 1:-ነህው 2:-ሶርፍ 3:-ተጅዊድ 4:-ተፍሲር 5:-ፍቅህ 6:-አቂዳ 7:-መንሀጅ 8:-ሀዲስ 9:-ሲራ 10:-ሙስጦለህ 11:-ቀዋኢደል ፍቅህ 12:-ኡስሉል ፊቅ 13:-አህላቅ ወል አዳብ 14፡-ስለሴቶቻችን 15:-ንፅፅር

ተጀምሯልኮ!
Показать все...
👍 2
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.