cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Halaba Sportt

💚💛❤️ #ሀላባ_ከነማ 💚💛❤️ 🌐ስለ ክለባችን #ሀላባ በስፋት ይዳሰስበታል❗️❗️ 👉የስታዲየም ድባቦች 👉የጨዋታ ቀጥታ ስርጭት 👉የጨዋታ ፕሮግራም ማሳወቅ 👉የተጨዋቾች ዝውውር መረጃ እንዲደርስዎ ከታች ያለውን halaba sport በመጫን ይቀላቀሉ 💛 @halabasportt 💛 ❤️ @halabasportt ❤️ያላችሁን ሀሳብ @halabasportbot ያድርሱን

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
278
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ እና ሐ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ይደረጋሉ 👍ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።   ⤵⤵👇⤵⤵👇⤵️⤵️👇⤵️⤵️    💚 @halabasportt 💚 💛 @halabasportt 💛 ❤️ @halabasportt ❤️  👉 ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ ።
Показать все...
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አስረኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ የተደረጉ ሲሆን በምድብ ለ ሀላባ ከተማ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ኢኮሥኮ፤ በምድብሐ ኮልፌ ቀራኒዮ ሙሉ ሦስት ነጥብ አሳክተዋል፡፡ 4፡00 ሲል ሀምበሪቾ ዱራሜን ከ ሀላባ ከተማ አገናኝቷል፡፡ ተጠባቂ በነበረው እና ብርቱ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ የሀምበሪቾዎች ፈጣን እንቅስቃሴ የታየበት የነበረ ቢሆንም ሀላባዎች ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታ ቅርፅ በመግባት ተመጣጣኝ እንቅስቃሴን ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ በአምስተኛው ደቂቃ ላይ የሀምበሪቾው የመስመር ተጫዋች አምረላ ደልታታ እጅጉን ለግብ የቀረ አጋጣሚን አግኝቶ መጠቀም ሳይችል የቀረበት ቀዳሚዋ የጨዋታው ሙከራ ነበረች፡፡ በእንቅሴቃሴ ሳቢ የነበረ ነገር ግን የጠሩ አጋጣሚዎችን ደቂቃዎች በገፉ ቁጥር መመልከት ያልቻልን ሲሆን ሀላባ ከተማዎች ወደ መልበሻ ክፍል ሊያመሩ ጥቂት ደቂቃ ሲቀር በእዩኤል ሳሙኤል አማካኝነት ያልተሳካ ሙከራን ማድረግ ችለዋል፡፡ ውጥረቶች ነግሰው በታዩበት በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ኳስን በመቆጣጠር ሁለቱም ተመሳሳይ የአጨዋወት መንገድን መከተል ቢችሉም ሀላባ ከተማዎች የፈጠሩት ፈጣን የሽግግር እንቅስቃሴ ጎል እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡ 65ኛው ደቂቃ ላይ ሰይድ ግርማ ከቀኝ የሀምበሪቾ የግብ ክልል ውስጥ እየገፋ ገብቶ የተከላካዮችን ስህተት በመጠቀም ጎል አስቆጥሮ ሀላባን መሪ አድርጓል፡፡ ከጎሉ መቆጠር በኃላ ኃይላቸውን ወደ ማጥቃት ሽግግሩ በይበልጥ በማድረግ ጥቃት ለመሰንዘር የሞከሩት ሀምበሪቾዎች በተደጋጋሚ ወደ ሀላባ ግብ ክልል ቀይረው ባስገቧቸው ተጫዋቾች አማካኝነት ሲደርሱ ተስተውሏል፡፡ 81ኛው ደቂቃ ላይ ከሀላባ የግብ ክልል ፊት ለፊት ዳግም በቀለ አክርሮ መቶ ግብ ጠባቂው ሲተፋው ከቀኝ በኩል ሾልኮ በመግባት ተቀይሮ የገባው ብሩክ ኤልያስ ኳስን እና መረብን ቢያገናኝም በረዳት ዳኛው ከጨዋታ ውጪ ተብላ ተሽራለች፡፡ በስታዲየሙ የታደሙትንም ሆነ የሀምበሪቾን የቡድን አባላት ያበሳጨችው ከጨዋታ ውጪ ውሳኔን በመቃወም በረዳት ዳኛው ላይ ክስ አስይዘዋል፡፡ ጨዋታው በዚህ ምክንያት አምስት ደቂቃ ዘግይቶ በድጋሚ ጀምሯል፡፡ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በአምረላ ደልታታ አማካኝነት ሀምበሪቾዎች አቻ ለመሆን መቃረብ ቢችሉም መሳካት ሳይችል ጨዋታው 1 ለ 0 በሀላባ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ የሀምበሪቾው አጥቂ ዳግም በቀለ ጨዋታው የሀላባን ተጫዋች ሆን ብለህ ተማተሀል በሚል ቀይ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ሀምበሪቾዎችም ከዳኛው የሪፖርት ክስ በተጨማሪ ክሳቸውን በፅሁፍ አስገብተዋል፡፡ 👍ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።   ⤵⤵👇⤵⤵👇⤵️⤵️👇⤵️⤵️    💚 @halabasportt 💚 💛 @halabasportt 💛 ❤️ @halabasportt ❤️  👉 ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ ።
Показать все...
በዛሬው እለት በአርባምንጭ ከተማ እና ሀላባ ከነማ በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ሀላባ ከነማ ቤስቱንና ቤንቹን ለመለየት በ2 ቡድን ተከፍሎ ጨዋታው የተደረገ ሲሆን በመጀመሪያ የተሰለፈው ቡድን 120 ደቂቃዎችን ተጫውቶ ያለምንም ጎል ጨዋታው የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህ ጨዋታ ተከላካይ # ልመነህ በቀይ የወጣበት አጋጣሚ ክለቡን ረብሿል። ሁለተኛው ቲም በተመሳሳይ የተጫወተ ሲሆን ዳኛው አማተር በመሆኑ መሰጠት የማይገባውን ፔናላቲ በመስጠት አርባምንጭ ከተማዎች ወደ ጎልነት ቀይረው መሪ መሆን ችለዋል። ሀላባ ከነማ የጫወታ የበላይነት የያዚ ቢሆንም ግብ ማስቆጠር አልቻለም። በ50ኛው እና በ55ኛ ደቂቃ በተቆጠሩ ተጨማሪ ሁለት ግቦች በድምር ውጤት 3:0 አርባምንጭ ከተማዎች ማሸነፍ ችለዋል። እንደ ክለብ ይህ የወዳጅነት/የአቋም መለኪያ ጨዋታ በመሆኑ የታዮ ጎድለቶችንና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በቀጣይ ለዋናው ውድድር ዝግጅት ይፈልጋል። 👍ሊንኩን ተጭነው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።   ⤵⤵👇⤵⤵👇⤵️⤵️👇⤵️⤵️    💚 @halabasportt 💚 💛 @halabasportt 💛 ❤️ @halabasportt ❤️  👉 ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ ።
Показать все...
ተጀመረ አርባ ምንጭ Vs ሀላባ ከነማ (የወዳጅነት)
Показать все...
# አርባ_ምንጭ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 11የሀላባ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከአርባምንጭ ከነማ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጫወታ ትላንት ማምሻውን አርባምንጭ ገብቶ ውበቴ ሆቴል አድሯል። ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጨዋታውንም ያደርጋል። ተጫዋቾችም ቀለል ያለ ቁርስ ተመግበው ወደ ስቴድየም አቅንተዋል።
Показать все...